አማራ መሆንህ የገባህ ዕለት የጉድጓዱን ጥልቀት ትረዳዋለህ።


እንኳን ደህና መጡልኝ።
ተስፋ ይመጣል።
ተስፋ ይሄዳል።
ተስፋ ይከሳል።
አማራ መሆንህ የገባህ
ዕለት የጉድጓዱን
ጥልቀት ትረዳዋለህ።

„ልጄ ሆይ! ኃጢያተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲“

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
26.06.2019

እኔ እምጽፈው ሰው ለሆኑ፤ ከህሊናቸው ጋር ላሉ፤ ሰው ለሚለውን ታላቅ ፍጥረት አክብሮት ላላቸው ወገኖች። የቤተ መንግሥት እርቦ እራፊ የቀፈት ከፈን ለማሳኛቸው ነው።  

ውዶቼ የኔታዎች ቅደም ተከተሎችን በፅሞና ማዬት ያስፈልጋል።
ህወሃትን ለማግለል አማራን መማጸን ነበረበት "በጣና ኬኛ" የአብይወለማ ሴራዊ ሌጋሲ።

አማራን ለመጨፍጨፍ ህውኃትን መማጸን ሌላው "አክሱም ኬኛ" ያልነፈሰበት አፍለኛ የአብይወለማ ብርንዶ የሴራ ቋት ነበር።

ቁምነገሩ ደግሞ አማራም ትግራይም በጸረ ስሜን ፖለቲካ አራማጅነት ጥይፉ ናቸው በኦነጋውያኑ ብቻ ሳይሆን በቀስተደመናው ድርጅት ወራሹ በግንቦት 7። ሰነዱ እጃችን ላይ ይገኛል። ዘመቻው ግን በቅደመ ተከተል ነው የተከወነው እንቅልፋም ሲገኝ ምን ይሆን።

አንዱን ለመስበር ሌላው አስፈላጊ ስለነበር የሥልጣን እርካቡን ለማግኘት አማራ ተፈለገ። አሁን ሁሉንም መዋቅር የተቆጣጠረ ሲመስለው አብይወለማ ፍርፋሪውን ለህወሃት ለማከፈል ህውሃት አስፈለገው። የኦነግን የበላይነት ተቀብሎ በሥር ለማደር ደግሞ ይሄኛው ተመራጭ መንገድ ነው። ለዚህ ነው አውስትራልያ አቢንባሲ እና ቢኦኤ ላይ በ አብይወለማ የመደመር ፍልስፍና እፍፍፍፍ ያሉት። 

ከባህርዳር በፊት እኮ ኮማንዶ የተላከው ትግራይ ላይ ነበር። ግን ትግራይ ከአባቶቹ በወረሰው ጀግንነት አሳፍሮ መለሰው የዛሬ ዓመት ሀምሌ ላይ። ተሳክቶ በቢሆን ግን ሁሉንም ተቆጣጥሮ መቀሌን መሳገበር ነበር። ከቅዳሜ ጀምሮ እዬፈሰሰ ያለው የደም አላባ መቀሌ መሬት ላይ ይሆን ነበር። 

ባህርዳር የፈሰሰው ደም እዛ ቀድሞ ይፈስ ነበር። አሁን ፍቅር በፍቅር የባጀው ገዱወደመቀወአንባቸው በሩን ከፍቶ ሊቀመናብርትነቱን ለጠ/ሚሩ አሰረክቦ የበቃውን ያህል ተጎርጉሮ ሁሉም መከነ በ አንድ ላይ እምሽክ። ጓዳ ጉድጓደው ክፍት ስለሆነ ዘረፋው በ አሸናፊነት ገዢ መሬቱን መቆጣጠር ተቻለ። በዚህ ማህል የኤርትራ ባለቀለቦች ደግሞ እናይ።

ምርጦቹ ሦስት ብቻ ናቸው። ቲፒዴኤም ኦንግ እና ግንቦት 7። ቲፒዴኤም ከቁጥር የማይገባ ታጣቂዎችን ወደ አገር አስገብቷል። ሰፊው ታጋይ ግን በሙሉ ትጥቅ እዛው ይገኛል። የጎረቤት አገር እርዳታ ሲፈለግ ይመጣል የተባለው የቲፒዴኤም ሠራዊት ናቸው። እነሱ ለግንቦት 7 የምዕራባውያን አሽኮከነት ቤተ - መንግሥት ሲጋባ የተዘጋጁ ልዩ ኃይሎች ነበሩ። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው …

አብን በሄልተን ሆቴል ላቀረበው ምክንያተዊ ጥያቄ "ለአንድ ሰፍር ተብሎ ህገ መንግሥት አይቀዬርም፤ መንግሥት የመሆን ተስፋህን አዝለኸው ዙር" ዓይነት በስላቅ እና በመታበይ ነበር ጠ/ሚሩ የተናገሩት፤ በሌላው ህዝባዊ ጉባኤ ደግሞ "የወግ" "እውነቱን ብነግረህ አብርሃም ደስታ ተወዳደረህ ካሸንፍከኝ አቅፌ ስልጣኑን አስረክብኃለሁኝ በማለት ደግሞ ሌላ ትውና ተጫወቱ። መነሻው ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ጦርነት ለመግጠም ነጋሪት የጎሰሙበት እና ያወጁበት ዕለት ነው። 

በሁለቱም አገላለጽ የህውኃትን ልብ ለማራራት የተከወነ ነው። እነ ተጋሩ ሰማይ እና መሬት ቢገናኝ ለደማቸው ያላቸው ክብርና ውህድነት የተደሞ ቅኔ ነው። "አቶ አብርኃም ደስታ አረና መሆኑ አይደለም ህወኃት የሚዬው አቅም ላለው ተጋሩ ሥልጣነ መንበሩን ለመስጠት የቤተ መንግሥቱን ዝግጁነት እንጂ። እኛ ይህ ሁሉ ሲሆን ተኝተናል።

ምርጦቹ ሁለት የኤርትራ ቅልበኞች አንዱን የ ኦነግን መንፈስ ለኦህዴድን በማስረከብ ሙሉ የሎጅስቲክስ ድጋፍ ቲፍ ካለ ዕውቅና ጋር፤ ሁለተኛውን ብአዴንን በማስረከብ ቲፍ ካለ ዕውቅና ጋር ውል ነበር። ለዚህ ነው የባህርዳሩ ግርግር በግንቦት 7 የተሰናዳው። የወሎ ግርግር በደሴ የተሰናዳው። የጠ/ሚሩ የደሴ ጉዞ ከዚህ ጋርም የሚታይ ነው። 

የባህርዳሩን በግንቦት 7 የታቀደውን የ ኦነግ መንፈስ ማራገፊያነት ያን ያከሸፉ ዜጎች ናቸው ሞት እና እስር ያሉት በባህርዳር። ውቧ ባህርዳርም የደም አለባ የሆነችው በታመቀ በቀል ነው። ታፍኖ ነው እንጂ ብጹ ንጹኃን አለፈዋል አሉ። አሉ ነው ያልኩት። አሳዛኝም አሰጨናቂም ሁኔታ ላይ ያለችው ባህርዳር በዛ የቂም ኩትኩት ምክንያት ነው። ጎጃም ቅኔው የበቀል ማወራረጃ ሆነ። "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ሆኖ" ነገ ደግሞ ኢዜማን ተሸከም ይባላል ... ዕድሉ ከተገኜ ግን የከፋ ሁኔታ እንዳለ ነው የሚደመጠው። 

ከባህርዳሩ እና ከደሴ ግርግር ከጠ/ሚር አብይ ፕሮጀክት ክሽፈተ በኋላ የተደረገው የግንቦት 7 አጀንዳ ብኤደን ሙሉ ለሙሉ እንዲሸከም ተደረገ።  ከዛ ብአዴን የግንቦት 7 አጀንዳ ይዞ በኢህዴግ ሥ/ አ/ ጉባኤ እንዲገባ ተደረገ። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ምንትሶ እና ቅብጥርሶ። ይህን ህወኃት አይገባውም። 

… ጠ/ሚር አብይ አህመድ በራሳቸው ድርጅት ኦነግን መንፈስ ለማስፈጸም ሲሹ የግንቦት 7 ተልዕኮ ደግሞ በአማራ ትክሻ ነው። የሁለቱም ጥምረት የስሜን ፖለቲካ ጥላቻ ነው። የብአዴን የኦነግ ጀሌዎች እና ህወሃት ያልገባው ተቀብሮ የተያዘው ሚስጢር ይህ ነው ጸረ ስሜን ፓለቲካ።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሁለት የፖለቲካ ተለጠፊ ድርጅቶችን ባራሳቸው አምሳል ቀርፀዋል። አንዱ ኢዜማ ሌላው ህብረት በሚል። ለሁለቱም ድርጅት ዕውቅና ሰጥቷል የአብይወለማ ሌጋሲ። ተፎካካሪዎች በሚል ተለጣፊዎችን አደራጅቶ መገልገያ ማድረግ የውጩን ማህበረሰብም ለማምታታት። መቼም ምድር እንዲህ ዓይነት የፖለቲካ ትዕይንት አይታ አታውቅም። 

መሰልጠን የነበረባቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሰላም እንዴት እንደሚገኝ ሳይሆን ቀውስ እንዴት አደራጅቶ በደም ዋንጫ ሥልጣነ መንበር እንዴት ማስከን እንደሚቻል። 

በዚህ ውስጥ ደግሞ ማገዶ የሆነ የቀደመ ድርጅት ደግሞ አለ። በማህል የአማራ ጥርኝ አለበት የሚባለው፤ የቅንጅት መፍረስ ጦስ ነው የሚባለው፤ የቀደመ አሰተሳሰብን ይዞ መከራን ተጋፍጦ የሁላችንም ውርጅብኝ፤ ግለት፤ ወጨፎ ተቋቁሞ የዘለቀው አዴፓ። ሥሙ ተፈልጓል። ዓላማው፤ ርዕዮቱ ፍልስፍናው ተውርሶ ድርጅቱ ግን እንዲፈርስ ተደርጓል። ይህም ያው ከስሜን ፖለቲካ የሚፈለገው የአስተሳሰቡን ልቅናዊ ጥገትነት እንጂ የሰብዕና ዕውንነት አይደለም።

የዚህ ሁሉ ተወኔት መነሻ መሰረቱ ግን የጠ/ሚር አብይ አህመድ እና የአቶ አንዳርጋቸው ዝግ ስብሰባ ውጤት ነው። አመዛኙ የቀወስ መነሻ ይኸው ነው። ብዙ ጥረዋል የአማራ ብሄርተኝነትን ሰብሮ የግንቦት 7 ተገዢ ለማድረግ ግን አልተሰካም። ያልተሳከው ልብን፤ ህሊናን፤ መንፈስ ማሸነፍ አይቻልምና። ግን እንደፈቀዱት የደም መሬት ሆኖላቸዋል። 

አሁን ደግሞ ወደ ውስጥ እንዝለቅ። ወደ ውስጥ ስንዘለቅ ሰሞናቱን ጠ/ሚር አብይ አህመድ መቀሌ ነበሩ አማራን ጨፍጭፈው፤ አማራን እረኛ አልባ አድርገው የመቀሌው መንግሥት ዋንጫ እንዲሸልማቸው ውል በዝግ የተከናወነበት ነው። ከዛ መልስ ደግሞ ወሎ በተወልጄነት እዛም ነበሩ። እሳቸው ብዙ ናቸው። ካድሬ፤ ተዋጊና አዋጊ፤ ሰባኪና ገዳይ፤ አደራደሪና ቀውስ አደራጅ፤ ሰብዐዊነት እና ጭካኔ፤ እርዳታ እና መቃብር ቆፋሪነት .... ወዘተ ... 

ሁለት ነገሮች ይነሱ ከዚህ ላይ የትግራይ ክልል መግለጫ እና የቢኦኤ ቃለ ምልልስ እኩል ነው የተሰተናገዱት። ከዛ በፊት ሌላ ጉዝጓዝ ነበር። የሰቆቃውም … ዲሲ ላይ ያለውን ጠንካራ የፖለቲካ አቋም ለመስበር ግንቦት 7 እና የጠሚር አብይ ቢሮ አብረው ነበር የተጓዙት።

አብረው ሲጓዙ ለፈርጀ ብዙ ተግባራት ነው። አናት የሆኑ ሰዎችን አግኝተው አማራ ወደ ሥልጣን ለለመምጣት የአብይን መንግሥት ሊገለብጥ ነውና ተባባሩን ለማለት ነው። ይህን ለማስደረግ ደግሞ ሚዲያውን መዳፍ ውስጥ ለማስገባት የኢሳት ጋዜጠኞች ማስወገድ ቀዳሚ ተግባር ነበር። ሞቱ ቀረ። ለጊዜው ጋዜጠኞች ተረፉ። ለእነሱ የተሰናደው ሁለተኛው የሞት ቀን ከሰኔ 15 የባህርዳር ጭፈጨፋ በፊት የተሰነዳው ዲሲ ላይ ነበር።

ውስጥ ለውስጥ ስንጓዝ ጎጃም ብቻውን የማሰቀረት መሰሪ ሴራም አለበት። የዓፄዎችን መንፈስ ለይቶ በስፖርት ሥም መንከባከብ። ይህ በዚህ እንዳለ ጠ/ሚሩ በቤተ መንግሥት፤ ሰክሬታርያታቸውም ዲሲ ላይ ሁለቱም የአሜሪካ ድምጽ ቃለ ምልልስም አድራጊዎች ነበሩ። ይህ ሁሉ ለሰሞናቱ የ አማራ ሊሂቃን ጭፍጨፋ መሰናዶ ነው። 

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ምን ያህል ዶር አንባቸው መኮነን አንሰፈው ሲገርፏቸው እንደባጁ ልብ ያለን ሰዎች እናውቃለን። የክፋታቸውን ዲካ መለካት ፈጽሞ አይቻልም። አቶ ገዱም ቢሆኑ ቦታውን አሟሙቀው እንዲቀዩ ነው እንጂ ቀጣይ ተፈላጊ አይደሉም። ሲን ሲከውኑ እሳቸውም በሆነ መልክ ይሸኛሉ። 

ምንድነው የተፈለገው? ዙፋኑ እስከ እልፍኝ አሰከልካዩ ከቢኦኤ አማርኛው ዝግጅት ጋር ጥድፊያ በግራ ቀኝ የያዘው።

Published on May 29, 2019

ድርጊቱ ሲፈጸም ሁለት የአማራ ከፍተኛ አካላት ውጭ ናቸው። ጉዳዩ ከእነሱ ጋር እንዲነካካ አልተፈለገም። አማራ ገዱወደመቀ በሚል አሁንም በእነሱ ለሚሰጠው አቅም ተንጠላጥሎ ደግሞ የኦሮሙማን ነፍስ ለማሰንበት።
ዛሬ ኢሳት የሻማ ቀን አክብሯል። የአማራ አርበኞች ተነጥለው። እንዲህ የለዬለት ነገር ሲከውን መልካም ነው። የቀረችው እንትፍጣፊ የሻማ ብርሃን ተንጠፍጥፋ ግብዕቷ ይፈጸማል። 

የሻባ ኢቤንቱን እያዬሁኝ ይህ መቼም ቃብቲያ ላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም አለን ተብሎ፤ አካባቢው በአውሮፕላን ተጨፍጭፎ የፖለቲካ ትርፍ ግንቦት 7 እንዲያገኝ ካደረገው ጥርት ተጨማሪ በደል ነው የተፈጸመው። በዚህ መንፈስ ውስጥ የአማራን አቅም ሰብሮ የኦነግ መንፈስ ገዢ ሆኖ ኦሮሙማን ማንገሥ ነው። የአማራ ልጆች መንፈስንም ለመክፈል ነው። የአማራ እናት ሁሎቹም ልጆቿ ናቸው። ሁሎችም ወንድሞቻችን ናቸው - ለእኛ።

ከዚህ ምን ይማራል አማራ? እኛ ሰለዬትኛውም ዜጋ ምስክርነት ስንሰጥ ስለዜጎቻችን ስንማገድ ኖርን። በዚህ ቀውጢ ቀን ግን አንድም ነፍስ  ከአማራ ጎን የተሰለፈ የለም። የግንቦት 7 የባህርዳር ውርዴትን ካሳ አብይ ባህርዳርን የደም ምድር በማድረግ ክሷል። እፉኝት እንዲህ ነው። ሲረገዝ አባቱን ሲወለድ እናቱን።

ለጊዜው ሰው አማኙ አማራ የውጩ ማህበረሰብ እንኳን ከገኑ ሊቆም እንዳይችል የተለመደው ተግባር እዬተከወን ነው። የፕ/ብርሃኑ ነጋ ትልም በውኑ ተሳክቷል። ተክሰዋልም። በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ አላቸው። ነገ ደግሞ ጋዜጠኛ እስክንድር አንድ ነገር ሲሆን ትንሳኤ ራዲዮ ያስከፍቱ እንደለመደባቸው። ትእግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል። 

ለነገሩ ግንቦት 7 ኤርትራ በርኃ ላይ አርበኞችን በጭንት መኪና ሲልክ እና የቀሩትንም ሲበትን ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ አለላችሁ ከዛ ይንከባከባችኋል ብሎ ነበር። አሁን "ለሟች ዘመድ" የለው ሆኖ ሚዲያው ነጥሎ ለሌሎቹ ዝክረ መታሰቢያ ፕሮግራም አሰናዳ ... እንዲህ ነው ለካህዲዎች ቀንም ሌትም ለእነሱ ሲያረግድ። 

ፕሮፌሰሩ ፈጽሞ የደከሙበት፤ የናወዙበት ጉዳይ ቢኖር አማራን ከህውኃት ጋር ተደርቦ እዬገዛ ስለመሆኑ ማሰመን ነበር ለውጭ ዜጎች። አሁን ተሳክቶላቸዋል። አንድ ሸማ አብይወለማ ሸለማቸው። አሁን በማዬው ሁኔታ በስውር ጊዜያዊ ወዳጅነት ከህውኃት ጋር በጠ/ሚር አብይ አደራዳሪነት መንፈሱ እዬተቀናጣ እያዬሁኝ ነው። ልማታዊ ካድሬዎችም ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ተመልከተናል። 

የሆነ ሆኖ የመረቀዘውን ክፍትተ ደፋኝ አስፈፃሚው አደራዳሪው ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ናቸው። ምስጥ! ነገ ግንቦት 7 እና አብይ ጠንክረው ሲወጡ ተጋሩ ልኩን ያገኛል በተራው። ምክንያቱም ጥቅል የተጋድሎው ዓይን የስሜን ፖለቲካን ድራሹን ማጥፋት ነውና። „ልብ ያለው ሸብ“ እንደ ጎንደሮች።

የሚገርመው የአሜሪካው ድምጽ የዶር አንባቸው መኮነን ሹፌር ጥዬቃ ጉዞ እና የትግራይ መንግሥት መግለጫ ሰው ምን ይለኛል አልተባልም በተመሳሳይ ወቅት፤ በተመሳሳይ መንፈስ ይዞ ከች ብሏል። ቀደም ብሎም የአውስትራልያ አንባሳደርም ቀዳሚውን ኢላማ ተኩሰዋል። በአማራ ታገድሎ ልባቸው ቁስል ያሉት አንባሳደሯ ... የትግራይ ክልል መግለጫም በ አኅትዮሽ አስኪዶታል። መደመርን ዓውጇል። የመደመር ነገር ተቀብሮ ሰንብቶ ኦክስጅን ተሰክቶለታል። 

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ለአገራችን የማይመጥን ነው።” – አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም
June 24, 2019
ሰበር | የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሀረ ጉዳይ መግለጫ ሰጠ Ethiopia Abiy Ahmed
Published on Jun 25, 2019
/ አምባቸው መኮንን ሹፌር :- “ኮለኔል አለበል አማረ ታግተው ተመልክቻለሁ” (በባለ ሥልጣኖች የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ እንደነበረና በመግለፅ ዐየሁ ያለውን ይናገራል)
June 26, 2019

ተጋሩ በአንድ ላይ ቢሆኑ ግን ይገባቸዋል። የሚፈልጉትን የበቀል ጽዋ ኦነግ ፈጽሞላቸዋል። ስለዚህ ይህን ጉዳይ በተለያዬ ሁኔታ ትዕይንት ውስጥ አስገብተው  የኢቤንት ሴሪሞኒ ማድረግ የውስጣቸው ብርኃን መሆኑ ሊደንቀን አይገባም። 

ያ አንድ ቀን ድህረ ገጹ ሆነ ሚዲያው ተጎብኝቶ የማያውቅ የ ኦህዴድ ድርጅት በሁለት እግሩ ያቆመ አማራ ከዚህ በላይም ሲቀጣ ማዬት ጽኑ ራዕይ ነው ለነተጋሩ። የ100 ዓመት ራዕይ ተጎሳቁሎና እንኩት ብሎ የቀረው እኮ የኦህዴድን ስብዕና ገንብቶ፤ አቅሙን አጎልምሶ እኩል የማድረጉ ድርሻ ተሸካሚው ብአዴን እና ሰፊው የአማራ ህዝብ ነበር። የዛሬን አያድርገውና ... ዓመቱን ሁሉ የፌድራሉን የቤት ሥራ ሲሰራ የባጀው የግርባው ብአዴን አመራር አሁን በሰኔልና በቹቻ ለዘር ሳይበቃ ተደመረ። 

ዛሬ ደግሞ ሊሂቃኑ በአደባባይ ተረሸኑ ... የባጀበትን ፋታ ነሽ ነገር ተመልክተናል። የጦር ወንጀሉን የምርመራ ውጤት እንዳይጋለጥ ታስቦ ... ሁሎችም አለቁ። በሌላ በኩል ዶር አንባቸው መኮነንም ከዚህም በላይ ባለ የሥልጣን የወደፊት ተፎካካሪነትም ስጋትም አለባቸው የልብ ጓደኛቸው ዶር አብይ አህመድ። ለዛ ነበር አንሳፈው የቀቷቸው። ሊዮቸው አይሹም። 

አንድ የቀረ ነገር ግን የቤተ መንግሥቱ አሸኛኛት ላይ ስለምን የአቶ ምግባሩ አስከሬን አሸኛኜት አብሮ እንዲሆን አለተፈለገም? ስለምን? ይህም ሌላ የእድምታ ቋት ነው። የጀዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ጉሮሮ ሌላም ነገ ያንቆረቁራል የደም አላባ ...  

አማራነትህ የገባህ ዕለት የጉድጓዱን ጥልቀት ይታይኃል።
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል፤ ፍቅር ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል።
የኔዎቹ ማለፊያ ጊዜ። ኑሩልኝ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።