የአብይወለማ ሌጋሲ ኦቨር ኮንፊደንስ እና ጦሱ ኦሮማራን ላይመለስ ምሶ ቀበረው።


እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ መጡልኝ።
የአብይወለማ ሌጋሲ
ኦቨር ኮንፊደንስ እና ጦሱ።

„የሰዎች መፈጠረ በበጎም በክፉም ነውና።“
 መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፭

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጨምቷ ሲዊዘርላንድ
29.06.2019

እንዴት ናችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ይህችን እርእሰ ጉዳይ „ኑልን አገር ግቡልን“ ሲባል ምን መሰናዶ ስላለ በሚል ቀደም ብዬ ጽፌበት ነበር። ውጭ ያለውን የዲያፖራ ፖለቲካ ከነፍሱ ስለማውቀው በኢህዴግ አቅም ይወጣዋል ብዬ ለማሰብ ስለቸገረኝ ነበር ያንን የጻፍኩት። አሁንም ልድገመው። ትንሽ የጹሑፉ የጭብጥ አያያዝ ከአሁኑ የኦዴፓ መንግሥት ካደራጀው ቀውስ ጋር አያይዤ። 

የአብይወለማ ሌጋሲ የችግሩ ምንጭ ኦቨር ኮንፌደንስ ይመስለኛል። በራስ መተማመን ሲያንስ የበታችነት ስሜትን፤ ሲበዛ ደግሞ የበላይነት ስሜትን ያስከትላል።

በሁለቱም መንገድ መመጣጠን ከሌለ ደግሞ ሁለቱም የአደጋ ጦር ነጋሪ ናቸው። አይደለም በመንግሥት ደረጃ በግል ህይወትም በራስ መተማመን ሳያንስም ሳይበዛም ተመጥኖ በልክ መራመድ ይኖርበታል።

በዛ የሰኔ 16 የህዝብ ድጋፍና ያን ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አብሶ በአማራ ክልል በነበረው የሚሊዮኖች ድጋፍ፤ የውጩ ያንን ያህል መጠኑን የዘለለ አክብሮት እና ተቀባይነት አቅም ሁሉንም አደርጋለሁ ከሚል ውሳኔ ደርሷል አቤቶ አብይወለማ የጥምር መንፈስ ንግሥና።

ለዚህም ነው ካለምንም የህሊና መሰናዶ፤ ካለምንም ተቋማዊ መሰናዶ ውጭ የነበሩ በግልም፤ በቡድንም፤ በድርጀትም ሲታገሉ የነበሩትን ቧ አድርጎ ከፍቶ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ያደረገው። ኤርትራም የራሷ ድርሻም አላት። ያ የወዘተረፈ ችግር እና የመፍትሄ አልቦሹ የመከራ ቅርጫ ሆኖ ቀጥሏል።

የተሻለ የሚባለው በአማራ ሥር የነበሩ መንፈሶች ወደ አገር ሲገቡ ከክልሉ መስተዳደር ጋር አብረው ለመስራት ባደረጉት ለስላሳ ጉዞ የአብይወለማን ፍላጎት ተሸክሞ በአንድ ትክሻ ለማስተናገድ አመት ከሁለት ወር ተዘለቀ። ምስጋና ክብር ዕውቅና አልባ። አሁን ይፋዊ ጭፈጫፋ ተካሄደበት። 

ጫናው፤ ተጽዕኖው፤ የቤት ሥራው ዕልቀት አልነበረውም በአማራ ክልል፤ ያው ግርባነት የለመደባቸው ስለሆኑ ብአዴኖች። የፌድራል መንግሥቱን ኃላፊንት የአማራ ክልል ብቻ እንዲወጣ ነበር የተደረገው። አታካች ጊዜ ነበር ከልቡ ለተከተታለው። ብአዴን የፖለቲካ ተግባር ሳይሆን የ የኢንተርቴይመንት ተግባር ነበር ሲከውን የባጀው። 

ለዛውም አማራ እንደገና ለመግዛት ተነሳብን ተብሎ በ ዓለም እንዲህ ውገዘ አርዮስ እንዲባል መሰሪ ሴራ ተደራጅቶ። ለነገሩ ግንቦት 7 የተጠጋው መንፈስ ሁሉ እንዲህ ነው። ወይ ራሱ አይድን ወይ ሌላውን አያድን። መናድ መፍረስ ወጥንቅጥ መከራ። ይህን እንኳን ራሱን አስችሎ መገምግም አልተቻለም። 

ብአዴኖች እኔ እንዲያውም አዴፓ ሲባሉ ስለምን ኢዴፓ አትባሉም ሁሉ ብዬ ጽፌ ነበር። ተቃዋሚ/ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተደማሪ የሚባሉትን ተሸከም የተባለውም ያ ክልል ብቻ ነበር። ተክሊል ድፋላቸውም፤ ማህሌት ቁምላቸው፤ ዘብ ሁንላቸው፤ ሥጋቻ አንጥፍላቸውም ነበረበት። ሠርግና መልሳቸውን በፌስታ ደንክርላቸውም ነበረበት።

እነሱ ደግሞ የዴሞግራፊ ተልዕኮ ለማሳካት፤ ትጥቁን ፈቶ የገባውን ኦነግን በሎጅስቲስ መልሶ በማደራጀት እና ተፎካካሪ ሆኖ እንዲወጣ በማገዝ፤ መንግሥታዊ መዋቅሩን በሙሉ ለመሙላት ካድሬዎቻቸውን በማሰልጠን እና በመመደብ፤ አክቲቢስቶቻችውን የመኖሬያ ሁኔታ በማሰናዳት፤ ኢትዮጵያዊነት የምትባል ዝግጀት በክልሉ እንዳይኖር በመዝጋት ይተጉ ነበር።

በአማራ ክልል ደግሞ የአብይወለማ መንግሥት ፍላጎት እና ጫና መብዛት ከክልሉ አቅም በላይ መሆኑ ላይበቃ፤ ችግሩን መቻሉ አልበቃው ብሎ ፌድራሉ ችግር አደራጅቶ በቀውስ እና በሰላም እጦት ደግሞ ቀልብንም መበተን የባጀበት የክልሉ መከራ ነበር።

በአራት ሚዲያ ነበር ወከባው በኤል ቲቢ፤ በአንድአፍታ፤  በኦኤምኤን፤ በህወኃትም „ትምክህት፤ ህገ መንግሥት ተጣሰ“ በማለት የኦዴፓ ሚዲያ ወከባ አካል ነበረች። ሊሂቃን የተባለውም በሙሉ አንድ ለነፍስ ሳይኖር በአማራ ድርጅት አብሶ በአብን ላይ የተደራጀ ዘመቻ ባጀ።

የአማራ ልጆችን በዬክልሉ፤ በየዩንቨርስቲው የማፈናቀል፤ በመንግሥት በተደገፈ መደበኛ ውጊያ ህዝብን ህልውናውን አደጋ ላይ በመጣል፤ ያም አልበቃም ብሎ በቀዬው ህዝብን በማፈናቀል በዛ ደግሞ እንዲጠመድ ብዙ ርቀት ተጉዟል የአብይወለማ ሲኦሉ አና ማተበቢሱ ሌጋሲ።

ከዚህ ጋር በተያየዘ ደግሞ ብአዴን አፍርሶ በራሱ አምሳል ለመቅረጽ ከመስከረሙ ጉባኤ ጀምሮም ሌላም የሸፍጥ ተግባር ተከውኗል።

በጥቅሉ ሲታይ የአብይወለማ የአገር ውስጥ ተግባር አትኩሮት  የአማራን መንፈሳዊ ጥምረት አቅም ወጥሮ፤ አስጨንቆ ሲቻል ወርሶ፤ ሳይቻል ለግንቦት 7 ሸልሞ ማንበርከክ ነበ። ውርሱን ራሱ ማስኬድ ካልተቻለው ደግሞ ተልእኮዬን ይፈጽማል ላለው ቀለበት ላሰረለት፤ በጫጉላ ማጫ ላይ በፌስታ ለባጀው ለግንቦት 7 ማስገበር ነበር።

ይህን ለማስፈጽም ጥረቴ፤ አቅሜ ያለው አብይወለማ ሌጋሲ በራሱ ላይ ያለው የተዛባ ግምት ነበርያም በአገር ውስጥና በውጭ ያገኘው ተቀባይነት እና የሽልማት ነዶ ሙሉ ለሙሉ በመተማመን ሊጎድልም፤ ሊቀነስም፤ ሊያልቅም ያሰበበት አይመስልም። አብሶ የግንቦት 7 እና የኢሳት አብሮ መሰለፍ የልብ ልብ ሰጠው። ይህም ከልኩ በላይ በሆነ ኦቨር ኮንፊደንስ ወጣጠረው።

ይህ በዚህ እንዳለ በሌላ በኩል ለኢትጵያ ሉዕላዊነት የሚያሰጉ ጉዳዮችን ደግሞ ህጋዊ ሽፋን፤ የሎጅስቲክስ ድጋፍ በመስጠት እና መዋቅሮችን አሟልቶ እና አሰናድቶ በማዋቀር ረገድ ደግሞ ከብርኃን የቀደመ የተቀናጀ ተግባር ፈጽሟል አቤቶ የአብይወለማ ሌጋሲ። ኦነግን ቄሮን ብቻ ሳይሆን ኤጄቶን፤ ቅማንትን ወዘተ … በማደራጀት እና ለቀወስ በማነሳሳት ... 

በዚህ ማህል ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል ሆነና እጅግ ለመስማት የሚዘገንኑ ጭፍጨፋዎችን አቅዶ በመከወን "ሽብር" ተፈጠረ ብሎ ውንጀላን አቅዶ እና አልሞ አደረጀ። 

ለዛ ሰለባ ደግሞ ያ ቀን ያወጣ፤ ክብሩን፤ ታሪኩን አሳልፎ የሰጠ  የአማራ ክልል ሆነ። የ አማራ የህለውና ተጋድሎን ትተን እንኳን ብአዴን ሙሉ ድምጹን ባይሰጥ አብይወለማ የዚህ ዕድል ባለቤት አይሆኑም ነበር። ለነገሩ ይህ ሲፈጠር ሰው ሆኖ ለተፈጠረ የሚሰራ ቀመር ነው። 

ስለሆነም ሰው የሆነ ሁሉ ይህን እንደ ሰው አስቦ ከራሱ ጋር ታርቆ  ከእውነት ጋር ይቆም ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁኝ ለቅኖቹ የብሎጌ ታዳሚዎች። ነግ ለእኔም ማለት ያስፈልጋልና። 

ትግራይ እንዲህ አልተደፈረም። ስለምን? ስለራሳቸው ራሳቸውን የሆኑ መሪዎች ስላሉት። እንጂ መጀመሪያ ኮማንዶ የተላከው ትግራይ ነበር። ለማፈን፤ ክልሉን ለማተራመስ። የባህርዳሩ ደም መፋስስ ቀድሞ የታቀደለት ክልል ትግራይ ነበር። ነገር ግን በመንፈስ ቀጥተው ወደ መጣበት መልሰውታል። ከዛ በኋላ ነው መልመጥመጥ የተያዘው። 

በዚህ እምቅ ፍላጎት ውስጥ ነው የጄ/ አሳማንው ጽጌ ተጋድሎና ህልፈት መታዬት የሚገባው። እንደ ድርጅት ልክ እንደ ህውኃት ራሱን፤ ክብሩን፤ መንፈሱን ጥበቃ ብአዴን ሊያደርገው የሚገባውን ተልዕኮ ማድረግ ባለመቻሉ ሰማዕትነት ለመቀበል የፈቀዱት ጄኒራሉ ክልሉ ባለቤት ያጣ ስለነበር እንጂ የራስን ችግር ራስ ለመፍታት የማንንም ፍላጎት ለማዳበል ለዛውም ውርሰ ኦነግን ምኞት ለመረከብ ባይሞከር ይህ ሁሉ አደጋ አይከሰትም። ወኔ ተረከዝ ላይ ተቀረቀረ። 

መቼም የጃዋር ሌሌ ከመሆን በላይ ድርብ ሞት የለም። ሰው ሁሉ ተቋማት ሁሉ ሬሳን አሽኮኮ አድርገው ነው እዬሄዱ ያሉት። "ለውጥ እንደግፍ" የሚሉት። የነጻነት ተጋድሏችን ለ አቶ ሌንጮ ሌታ የዘመናት የቅንድብ ጸጉር ትግል አሰረክበን አብጭበን ባዶ እጃችን ነው የተቀመጥነው። ባዶ መሆናችን ሲያውቁ ደግሞ ጦርነት አወጁ። ብዙ ነፍስ ነው የጠፋው። 

ለዚህ ነው ማህበራዊ ሚዲያው የታፈነው። ይህንም ጎሽ የሚሉ ሆዱ ዘመቼዎች እያዬን ነው። በዘመነ ህወኃት የነበረው መራራ ነገር ኦነግ ሲደግሞ ለ እነሱ የሠርግ ሽርሽር ነውና። ማፈሪያዎች!

በዚህ ላይ አንድ ነገር ማለት እችላለሁኝ ትግራይ ላይ ኮማንዶው በቁም እስር ቆይቶ ሲመለስ ማህል አገር ላይ አንድም የተጋሩ ነፍስ ድፍረም ጥቃትም አልገጠመው። አማራ ግን በገፍ ቀራንዮን እዬተቀበለ ይገኛል። „ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን“ ሆኖ ….ይህ አንድ ያላደረገው አማራን መቼውንም አማራ አንድ ሊሆን አይችልም። 

ሴቶችም ይህን ምነፈስ ታቅፎ ለሚተኛ ወንድ ፍቅርን መስጠታቸው እብንነት ይመሰለኛል። ቢያንስ በእጅ ያለውን መንፈስ ማሸፈት እንዴት ያቅታል? 

ይህም ብቻ ሳይሆን ተጋሩ በራቸውን ስለዘጉ እንዲህ መዛለያ እና የህዝባቸውን መከራ ቁጭ ብለው እንዲመለከቱ አልተገደዱም። ልባሞች ናቸውና። አቅማቸውን ተከላክለው አቅማቸውን እንደ ታቦት ከብክበው ተከብረው ይገኛሉ ከቁጥር ሳይጎድሉ። 

አጉል እወድድ ባይነት እና ከንቱ ውዳሴ መሻት ከዚህ አድርሷል ለብአዴን። ግንኙነት ልክም ደንበር አለው። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ጠ/ሚር ሄሮድስ አብይ አህመድ እኔ ነኝ የብአዴን ሰብሳቢ እስከማለት ያደረሳቸው ውስጡን ስለሚያውቁት ነበር። እሳቸው መቼም ወዘተረፈ ናቸው። ወዘተረፈው ጠ/ሚር ይባሉ ይሆን? ይባሉ እንጂ ምን ሲቀራቸው። 

ሚኒስተሮች ሆኑ የሥም ናቸው። እንጂ ሚ/ሩ እሳቸው ናቸው።
ኮሚሽነሮች የስም ናቸው እሳቸው ናቸው ኮሚሽነሩ፤ ምክትል ሚሩ እሱ ወይንም እሷ አይደለችም እሳቸው ናቸው። የቀበሌው ሊቀመንበርብ እሳቸው ናቸው እሳቸው ወዘተረፈ ናቸው። ባዛ ላይ መባተታቸው ደግሞ ይገርመኛል ኮሽ ባለ ቁጥር ይባንናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የ5 ዓመት ንድፍ ይነድፋሉ ... ኮሚሽ ይላሉ ጀርመኖች። 

የማይገቡበት፤ ዘው የማይሉበት፤ ጥልቅ የማይሉበት አንዳችም መስክ የለም። ስለምን? ፈሪ ስለሆኑ። ሀዩለት ጊዜም አማራ ክልል  የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርግ ከህሊናቸው ጋር አልነበሩም። ነጋ ጠባ እዛው ተወትፈው ውለው ያድራሉ። ለስልጣናቸው እና ለኦነጋዊ ወራሽነታቸው ስስታም ስለሆኑ። ዶር ብርኃነመስቀል አባባ እኮ ነግረውናል „አብይ የኦነግ ወራሽ ነው“ ብለው።

ነፍሳቸው ያለው ዕድሜውን ሙሉ ቅንጣት ኢትዮጵያዊ ጠርን አልባውን ኦነግን መንበረ አጤ ማድረግ ነው። ይህን የሚሞገት ነፍስ ሁሉ ይረፈረፋል፤ በካቴናም በመድፍም … 

ይህ ደወል ነው ቀጣዩ ኢትዮጵያ የመፈናቀል አንደኝነት ደረጃዋን አስጠብቆ ብቻ የሞት መንደር ትሆናለች። የዛን ጊዜ ዳግሚያ ሶርያ ይታያል … 

የኦሮሞ ፖለቲካ ሊሂቃን ፍልስፍና መነሻው የበታችነት ነው። የበታችነት ደግሞ የሥነ - ልቦናዊ በሽታ ነው። በሽታው ደግሞ ቂመኝነት ነው። ቂመኝነቱ ነው አሁን በቀሉን በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ደም እዬጠጣ መኖርን መግዛት ያለመው ነው። በፈለገ ሁኔታ እርካታ ኖሮት መረጋጋትን አያሰክነውም። ውስጡ ያለው ባዶነት በሽታ ስለሆነ። 

ሔርድስ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደ ኦዴፓ እኔ "የአዴፓ" ሰብሳቢ ነኝ ባሉት ልክ በዛ ሥልጣናቸው ነው አሁን ያሹት ለማድረግ የሞከሩት የሆነውም የሆነው። ጭካኔያቸው አርዮሳዊነትም ነው። ክህደቱ በዛ ልክ ነውና መለካት ያለበት። 

ንድፋቸው ከቁጥጥር ውጭ ሲሆን ሲበላሽባቸው ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሰመን „መፈንቅለ መንግሥት“ ተደረገብኝ ብሎው ለማሳመን ሞከሩ።

በተዘጋ መንፈስ የባጀችው ትግራይ ግን በዬትም ቦታ የሚኖሩ ልጆቿ ብዙም ወከባ ሳይደርስባቸው፤ ውርዴትም ስንቋ ሳይሆን ቀለል ባለ መስዋዕትነት እንዲያውም ተከብራ በአቅሟ ልክ አንዳችም ሊሂቃኗን ሳታጣ ተወዳዳሪና ተፎካካሪ ሆና በቀጣይ ትቀርባለች። ለነገሩ ኮንፈዴርሽኑን አላወጀችም እንጂ በዛ ልክ ነው ስትንቀሳቀስ የባጀቸው።

አማራ ግን እርኛ አልባ ሆኖ ብትንትኑ ወጣ። "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" ኢህአዴግን እንደ ምሰሶ ማዕከላዊ መንግሥቱን ያቆመው ብአዴን ነበር። አሁን የለም። የአማራ ክልል እንዲህ ብትንትኑ መውጣቱ የፌድራሉን ሁለመና ተሸክሞ የቆዬ ስለሆነ ለአገር ሉዕላዊነትም ትልቅ የስጋት ምንጭ ነው።

በዚህ ውስጥ ከእትጌ ኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት ምን መልክ እንዳለው አይታወቅም፤  ምክንያቱም ኦህዴድ ብቻ ነው የዚህ ሆድ ዕቃው። ከጎረቤት አረብ አገሮች ጋር ያለው ሁኔታም በዛው ልክ ነው። ይህም ከኦህዴድ ውጭ የሚያውቀው የለም። 

የውጭ ግንኙነቱ የተከረቸመ ነበር። ይህን ተሸክመህ ለውጡ እንዳይደናቀፍ ማለት ዕብደት ነው። አገርህ በራስህ ላይ መፍረሷ አልታይህ ካለ ነገ ራሱ ያሳይኃል በራሱ ጊዜ። በዚህ ውስጥ የቆሞስ ስመኛው በቀለን ሞት እሰቡት።

የውጭ ግንኙነቱ የባጀው የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦሮሞ/ ጠ/ሚሩ ኦሮሞ/ የጠ/ሚሩ ቢሮ ኃላፊ ኦሮሞ/ ፕሬስ ሰክሬታርያቱ ኦሮሞ በድፍን የባጀ መከራ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ውጭ ጉዳይ ከሆኑ እንኳን የቻይናውን እና የደቡብ ሱዳኑን ጉዞ ተመልክተናል። እንዴት በዝግ ሂደት እንዳለ … 

ኢትዮጵያን በጸርነት በጥርሱ የያዝ የኦነግ ወራሽነትን አዝለህ ኢትዮጵያ በሉዕላዊነቷ ክብር እንድትቀጥል ይተጋል ብሎ ኦዴፓን ማሰብ ጅልነትም ነው። እዬታሰሩ ያሉትም ኢትዮጵያ የሚሉት ናቸው።

ስለዚህ ተጋድሎው ኢትዮጵያዊነትን ሰብሮ ኦነጋዊነትን ማስከበር ነው። ይህ የማይገባው ካለ አለመኖርን የተቀበለ ሰብዕና መሆን አለበት። ጥንቱን ሊያመጡ ማለት ቋንቋው ኢትዮጵያነት ሊነግሥ ነው። ሌላ ፍቺ የለውም። ኢትዮጵያዊነት አቅም ለመሰብሰብ ተፈለገ አቅም ከተገኜ በኋላ ግን የተመሰጠረው ተተረጎመ። እባብ የተፈጠረበትን፤ ጃርት የተፈጠረበትን፤ እፉኝት የተፈጠረበትን ትዕይንት ነው እያዬን ያለነው። 

አገር ውስጥ የገቡት ተቃዋሚ/ ተፎከካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተዳማሪዎች ደግሞ ውጫቸውን እንጂ ውስጣቸው ምን እያሰበ እንዳለ አይታወቅም። ቀን አብረው ሲከቡ ሌሊት ደግሞ ሲያፍርሱ …

ተደማሪዎች ራሳቸው እንዲህ በራሱ ሸፍጥ፤ ሴራ እና ጸረ አማራ ተልዕኮ እርቃኑን አብይወለማ ሲሆን የውስጥ ፌስታቸው ነው። የተቃውሞውንም ታገድሎውን ውስጣቸው ይደግፈዋል። ስለምን? ጉዳያቸው ሥልጣን እንጂ የህዝብ መከራ አይደለም እኛ።

ከዚህ አመክንዮ ውስጠት ጋር መታረቅ ያልቻለው አብይወለማ መንፈስ ምን ያህል የአቅም ድህንት እንዳለበት በማስተዋል ማዬት ይቻላል። የኃይል አሰላለፉን እራሱ አሁን ላይ አያውቀውም። አብሮ ድንኳን ላይ መገኘቱ ብቻ ነው የሚያዬው።

ለዚህ ነው እውር ድንብሱን ያገኘውን ሁሉ እያሰረ እና እዬገደለ፤ የዜጎችን የመናገር ነፃነት ገድቦ በመታበይ እዬገሰገሰ የሚገኘው። በዚህ ማህል ደግሞ ኢኮኖሚው ይታሰብ። ከውጭ የሚለከው ገንዘብ ቢቆም ምን ሊሆን እንደሚችል እሰቡት?

የሆነ ሆኖ አሁን ባለው ግብረ ምላሽ የአብይወለማ ዝበት የዘፈነበት ጉዞ ለደጋፊው፤ ለተደማሪው፤ ለተፎካካሪው፤ ለተቀናቃኙ፤ ለተቃዋሚው ሳይቀር የልብ ልብ አቅም ይቸረዋል።

ስለምን ቢባል ያ ገድላዊ ድጋፍ የውስጥ ካንሰራቸው ነበርና። የታሰበም የታቀደም አልነበረም እንደዛ አብዝተን ከምነጸዬፈው ከኢህዴግ ሰው ወጥቶ እንደዛ ህዝብ ይቀበለዋል ተብሎ አይታሰብም ነበርና። የሆሊውድ ኪኖ ነበርና።  

ሌላው በመንፈስ ልዕልና ላይ ቁብ ያለው ነገረ ቄሮ እና የተሰጠው መጠኑን የሳተ ሥልጣን፤ የጉላሌው መንግሥት እና ሉዐላዊነትን የመዳፈር ህጋዊ ሽፋን እዬተሰጠው፤ በምርጥ የበላይነት የተቀመጠው የአቶ ዳውድ ኢብሳ መንፈስና ኮረቻው፤ ያደፈጡ አገር ውስጥ የነበሩ የተቃዋሚ/ ተፎካካሪ/ ተቀናቃኝ/ ተደማሪ ድርጅቶች ጉዳይ ሲታሰብ ከልክ በላይ በሌለው አቅም ላይ የተንጠራራው የአብይ- ወለማ ሌጋሲ ሲታሰብ እና ኢትዮጵያን አንድ የውጭ ኃይል ሊወር ቢነሳ ብሎ ሲታሰብ እርሾ አልባ የሆነች አገር ስለመሆኗ መገመት የፖለቲካ ተንታኝነት አያሻውም። ኢትዮጵያ ባለቤት የሌላት አገር ናት በአሁኑ ሰዓት።

የአብይወለማ ሹምሽረት የድምት የእርግዝናን ጊዜ የማያሟለ ባረጋ እና ባልሰከነ መንግሥት የሚታይ መንቀዥቀዥ ተብሎ መታዬት ይቻላል።

ስለሆነም የአብይወለማ ሌጋሲ ልኩን ቢያውቅ ጥሩ ነው። ልኩን ያወቀ አይመስለኝም። የውጭ መንግሥታት አቅም ወደ አለው የሚገለበጡት ሚዛኑን አይተው ነው። አንድ ነገር ቢፈጠር፤ ማለቴ ከዚህ የባሰ ጉዳይ ቢከሳት ሥልጣን ከጨበጠው ጋር ይሆናሉ። ሁሉም ከራሱ ጥቅም በላይ አይደለምና።

ጎንደሬዎች „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ። በቀጣይነት አብይወለማ አገር የመምራት ምኞቱ ብቻ ነው ያለው እንጂ የመንፈስ ኃይል የለውም። በምኞት እና በማስፈጸም አቅም ደግሞ ሰፊ ልዩነት አለው። አሁን ባለው ሁኔታ አብዝቼ ስቃወመው የነበረውን አሁን ግን ሊሆን ይገባል የምለው የህብረት መንግሥት የመመሥረት ሂደት መጀመር ይኖርበታል።

ጤናማ መንፈስ ያለው ሱማሌ ላይ ሲሆን እሱን ደግሞ ቀንተው ካልበተኑት፤ በዛ ልክ ታስቦ ከሰባዕዊነት ጋር መንፈሳቸው የተዋህደ ዜጎችን ማሰብ የሚገባ ይመስለኛል። ሶዴፓ ወደ አማራ ክልል መሄድ ያለመውን ቀጭቶ ወደ አንቦ ጉዞ እንዲያደረግ የታሰበው ሴራ ለዚህ ነበር ሱማሌ ክልል። በኦሮማራ የተገኘው አቅም እክል እንዳይገጥመው። 

ከሰሞናቱም ዓርማውን ሳዬው ኢትዮጵያዊነትን አክብሮ አግኝቸዋለሁኝ። ከብአዴንም የተሻለ ሆኖ ነው ያገኘሁት። የጠራ የነጠረ የውስጥነት መንፈስ እንዳለ ተረድቻለሁኝ። ራሱን አስችዬ እጽፈዋለሁኝ ስል የመከራው ድባብ ውጦኝ ሳልችል ቀረሁኝ።

እርግጥ ነው የአብይወለማ መንግሥት በግርዶሽ የያዘው ጸረ ኢትዮጵያ አቋሙና፤ አቅምን የመፍራት ሁኔታም በዛም መንደር ንደት እንዳይፈጠር ስጋቴ ብዙ ነው። ስለሆነም ክልሉ ራሱን መጠበቅ እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁኝ። ደግሞ ሌላ የተስፋ ማረፊያ እንዳናጣ። 

ሶዴፓ አዲሱን ዓርማ ይፋ አደረገ
June 20, 2019

ልኩን ያላወቀው የአብይወለማ መንግሥት በመሳሪያ ኃይልና አንድን ማህበረሰብ ለጥቃት ባገለጠ መልኩ የተያያያዘው ዘመቻ መጨረሻው ይናፍቀኛል። 

አብሶ እዬተጋፋ ታስታወሱ ከሆነ ለዬክልሎች የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድጋፍ ሲያደርግ የታዬው ግለት ይታወቃል፤ ይህም ሆኖ ገመናውን ሸፍኖ የኖረን ህዝብ እንደ መንግሥት ገልባጭ አድርጎ ቀርፆ ለዓለሙ ህብረተሰብ ማሳዬት መቼውንም የማይደን፤ የሚያመረቅዝ መከራ ያዘለ ተራራ ነው መሸከም ከቻለው የ ኦሮሞ ፓለቲካ። የ ኦሮሞ ፖለቲካ ማጣፊያው ሲያጠረው የሄደበት መንገድ ኢትዮጵያን ጥላሸት ቀብቷታል። ለነገሩ ስለ ኢትዮጵያ ምን ግዱ ሲሆን? 

ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ለዴሞግራፊ ስኬት ከቀዩ ነቅለህ አስፈረህ፤ የባቢሎን ግንብ ቀራጩን አቶ በቀለ ገርባን አንቀባረህ ይዘህ ለዛውም የትውልድ መምህር አድርገህ፤ አንዲት ሉዕላዊት አገርን ርእሰ መዲና አልባ አድርገህ እዬሰራህ የአማራን የቀጣይ የመግዛት ፍላጎት አከርካሪ ተሰበረ አስብሎ ማሳወጅ እውነት እውነት ሆና ስትወጣ በጦር ወንጀለኝነት መጠዬቅ ግድ ያደርገዋል።  

የአብይወለማ ተነጠራርቶ ንቀቱ ደግሞ ይገርመኛል። የተወጣጠረው ድፈረቱ ደግሞ ይደንቀኛል። አቅሙን አለማወቁ ደግሞ እንደ አገር ኢትዮጵያ ሰለመቀጠሉ ስጋቴን ከፍ አድርጎታል።

የሚገርመው አማራ ላይ ይህን ከውኖ ወለጋ ላይ ደግሞ ኦነግ እንዲወገዝ ሌላ የሰላማዊ ሰልፍ ድራማ ከውኗል። እውነት ብናገር ኦዴፓ ከእውነት ጋር ተገናኝቶ ለማዬት ጉጉቴን አፍልሶታል። ውሸታም መንግሥት ነው። ለምን ያን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳዘጋጀው „ባናርስ እናጣምዳለን“ ነው።

ሌላው የቲያትር ጨዋታው ሁለት ሦስቶችን ስለስገበረ ሁሉም የገበረለት ይመስለዋል፤ ድጋፍ ሰልፍ የገብያ ውሎ ነው። የገብያ ውሎ ደግሞ ገብያው ሲበተን ይበታናል። ያን ተማምኖ ነበር ለኦነግ አቅም ሰጥቶ የኦነግን መንፈስ ወርሶ ኢትዮጵያን ኦሮሙማ ለማድረግ እዬተጋ ያለው። ይህ ግን የጊዜ ጉዳይ ነው።

አቅም በራስ ውስጥ ያለ እንጂ የገብያ ውሎ አቅም፤ አቅም ነው ተብሎ ለሌላ ፍላጎት ያን ኢንቤስት እያደረጉ ጠማማ ፍላጎትን ማሳካት አይቻልም።

ከዘበጠ ድልድይ ላይ ሆኖ ኢትዮጵያን አይደለም ወደ ዴሞክራሲ ወደ ዴክታተርነት እንኳን ማሸጋገር አይቻልም። በወታደራዊ መንግሥት ሥር ለማድረግም ዘመኑ አይፈቅድም። እሺ የሚል ትውልድም የለም።  
ይልቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አህጉራዊ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ኢትዮጵያን ለቀው የሚወጡበት ሁኔታም ሊኖር ይችላል። 

ይህም የሚፈለግ ነው ለጸረ ኢትዮጵያ ተልኮ ለሚተጋ የጢስ ፖለቲካ፤ የፌስታል ፓለቲካ። አሁን እዬሆነ ያለውን እኮ አቶ አዲሱ አረጋ  የጃዋራዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን የልቤ የነገሩን ሳይውል ሳያድር ነው የተፈጸመው።

ያልነገሩን ቀውሱን እንዴት አደራጅተው እንደሚያስማሙት ብቻ ነበር። ለነገሩ ፍጥነታቸው የሚገርም ነው። በጣም ችኩሎች ናቸው።  በማግስት አማራ ተጨፈጨፈ፤ ታሰረ፤ ተሰደደ።

የአብይወለማ ሌጋሲ አለኝ የሚለው አቅም የህዝብ ድጋፍ ብቻ ነበር ለዛውም አማራ ላይ የነበረው ሁሉን የማድረግ እና የማስደረግ። ያ ደግሞ ስንጥቅጥቁ ወጥቷል።

ተጨባጩ እንደሚነግረን አማካሪዎቼ አጋሮቼ ብሎ በምርጥ ዜግነት ያቀረባቸው ኃይሎቹ ምን ያህል ወደ ገደል አፋፍ እንዳቀረቡት ራሱን ራሱ ያሳዬዋል ልብ ከፈጠረለት። „አንተ ማን መሆንህን ለማወቅ ጓደኛህን ንገረኝ“ እውን ሆኖ የታዬበት አጋጣሚ ነው። ይዘውት ላጥ ወደ አለ ገደል ካደረሱት በኋላ ወደ ላጥ ወዳለው ገደል ለቀውታል። መሰባባሩን እያስተዋሉም ለዋንጫችን ሆኗል። 

ሌላው ሰላሙን ለመንጠቅ፤ ነጻነቱን ለማወክ የሚባለውን ፊሽካም ተግ ማድረግ ያለበት ይመስለኛል ባለ ሥልጣኑ ኦነጋዊው ኦዴፓ። የሳሙና አረፋ እና ጤዛ የአፍታ ጉዳይ እንጂ የህልውና አሰቀጣይ ሊሆን ስለማይችል። የቆመበት መሬት እዬተናደ ነው። አቅም አይሸመት ነገር፤ አቅልም በገቢያ ህግም አይተዳደር።  

አቅመ ቢሱ የአብይወለማ ሌጋሲ እዬወደቀ ስለመሆኑ ድንኳኑን ጥሎ ልዝ ቢያዘጋጅ መልካም ነው። ልዕልና የመንፈስ እንጂ የባሩድ ስላልሆነ። ልዕልና የእውነት እንጅ የሸፍጥ ካብ ስላልሆነ፤ ልዕልና የጠራ ፍላጎት እንጂ የጎሸ የጢስ ቤተኛ ባለመሆኑ።

ለኦሮሞ የበላይነት እዬተጋህ ለዛውም ጸረ ኢትዮጵያ አቋም ያለውን መንፈስ አሽኮኮ አድርገህ ለኢትዮጵያ ነው ማለቱ በራሱ ሰባራ ገል ነው። ሰባራ ገል ደግሞ አገልግሎቱ እሳት ለመጫሪያ ወይንም ለእጣን ማጤሻ ብቻ ነው።

አቅምን ማውቅ ብቻ ነው የድል መባቻ። አቅምን አለማወቅ ደግሞ መሰናበቻ ይሆናል። መንፈሱ ራሱ ተሰናብቷል። የቀረው ጠበንጃ እና ፋቲክ ብቻ ነው።

ቀጣዩ ተገዳይ ታሳሪ በምግብ ብክለት ሟች ደግሞ ማን ስለመሆኑ የድንገቴው ቀዥቃዣ የአብይወለማ መስመር የሜጫ ሱናሜ ይጠበቃል
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል።

አይዟችሁ! ክብረቶቼ ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። 
ኑሩልኝ።
መሸቢያ ሰንበት።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።