ልዑል እግዚአብሔር ዞግ ስሌለው ፍትህን፤ ርትህን ከእዮር እንጠብቃለን በተጠንቀቅ!



እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ መጡልኝ።

ልዑል እግዚአብሔር ዞግ ስሌለው ፍትህን፤
ርትህን ከእዮር እንጠብቃለን በተጠንቀቅ!


„ከንቱነትን እና ሃሰትን የሚጠብቁ
ምሕረታቸውን ትተዋል።
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፱“

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02.07.2019
ከእም ዝምታ ሲዊዚና።


እንዴት አደራችሁ የኔታዎቼ? ደህና ናችሁ ወይ?  
አንድ መንግሥት ቶላርንስን መርሁ ካለደረገ ቶለሬት የሚያደርግ ህብረተሰብ ለመፍጠር ይሳነዋል። በዚህም ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወድቀዋል። ፈተናውን ለማለፍ አልተቻላቸውም። የሚገርመው እና የሚደንቀው ቶለራንስም ኢትዮጵያ ውስጥ በዞግ የተመደበ መሆኑ ነው። 

አሁን ፈጣሪም እንደዛ እንዲሆን እዬተፈለገ ነው። የአቤቱ ጌታ ሆይ! የአቶ ጃዋርን መንገድ ጠብቅልኝ አቤቱታም አለበት። የአቶ ጃዋር ሎሌዎችንም አባራክትልኝም የሱባኤው መባቻ ነው።

መልስ ግን አለኝ። አይሰቡት!!!!!!!!!!! ለሰከንድ የአቶ ጃዋር መንፈስን ያቀርብኩ ዕለት ሞቴን እመርጣለሁኝ። የኢትዮጵያ ጉድጓድ ስለሆነ። ከዛሬው የባሰ ነገ ደርቆ እዬመጣ ነው።

ይህን ማሰብ ለተሰናቸዋም አዝንላቸዋለሁኝ። ቅርፊቱ እንጂን የፖለቲካውን ግንድ ለማግኘት ማስተዋሉን ሰጥቶ ለሽ ካሉበት ቢያንስ እንዲነቁ እጸልያለሁኝ። ሁሉ ነገር ከመሼ ከሆነ ግን „አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ“ ይሆናል። እራሱን ችሎ በተነሳበት አዲስ ራዕይ ይጓዛል በሚል የሰጠነው አቅም ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈለን እያዬነው ነው።

በአገር ውስጥ መፈናቀል ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቀዳሚ ተጠቃሽ መሆኗ አልበቃ ብሎ በፖለቲካ ግጭት ሊሂቃን እንደ ቅጠል የረገፉበትን ትዕይንትም እያስተናገደች ነው። በዚህ ላይ ራህቡ፤ በዚህ ላይ ለ እርሻ ብቁ የሆነው ዜጋ በተለያዬ ሁኔታ ከማማረት ተግበሩ መስተጓጓሉ፤ በግፈኞች መከራም የዘንድሮ የዝንብ መጠን፤ የተዘራው የመብቀል ሁኔታም አሳሳቢው ጉዳይ ነው። 

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በግብርና ላይ ተስፋ የጣለ፤ የግብርናው ተስፋ ደግሞ በተፈጥሮ ላይ ጥገኛ ስለሆነ። 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ የባጀው የኦነግ የመተበይ ጉዞ እና የነበረውን የመንፈስ ሰቆቃ ሁላችንም የነበርንበት ሲሆን ለዛ ምቾት የሰጣቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ዛሬ ራሳቸው አደራጅተው፤ ራሳቸው በፈጠሩት ቀውስ ተጠያቂው እሳቸው መሆን ሲገባቸው ጠቅልለው ወደ ሌላው ለማሸገር እዬጣሩ ብቻ ሳይሆን የእርግማን ናዳም ለቀዋል። እርግማኑ እሳቸውን ተመልሶ ካልቀጣቸውስ? በመታምን ውስጥ ያለ ክህደት መጀመሪያ የሚያሰቃዬው እራስን ነውና። 

በሌላ በኩል እርግማኑ ተፈጻሚነቱ በሳቸው እጅ ስለማይሆን እንደ ፈረሰኛ የሙላት ውኃ፤ ወይንም እንደ ሳሙና አረፋ አይቶ ቢታለፈም እንደ አገር፤ እንደ መንግሥት ግን ቶለራንስን የሚገፋ፤ ጨርሶም ቶለራንስ በዞግ መከፈሉ አልበቃ ብሎ አትንኩኝ ስገድልም አጨብጭቡልኝ፤ ሳፍንም እጀቡኝ፤ ስሳደብም ወሩብልኝ፤ ስወርፍም አዚሙልኝ፤ ሳገልም ባንድ ከፍታችሁ ተወዛወዙልኝ ነው የሚሉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ዕብንነት!

እሳቸውና ወገኖቻቸው የተነፈሱበት ሁሉ ቅዱስ፤ እሳቸውን የሚሞግት ደግሞ ሰይጣን፤ አገራዊ ኃላፊነት እማይሰማው አድርገው ነው ያዩት። ከሳቸው በፊት ለነፃይቱ ኢትዮጵያ ዋጋ ከፍለናል - እኛ። እሳቸው ሳይነገሩን እንዲህ ንጉሥ ሆነው ሳይወጡ፤ ዓለምም እንዲህ ሳያውቃቸው ሥማቸው ጉግል ላይ 1000 ፈላጊ ባልነበረው ጊዜ ስለሳቸው አቅም፤ ክህሎት፤ ተስፋ የሞገትን ነፍሶች አብሶ እኔ ራሴን ነው ያዬሁበት፤ ራሴን ነው የታዘብኩት። የሠራኋቸው ነገሮች ሁሉ ለታሪክ መቀመጥ ስላለባቸው ተቀምጠዋል።

እንደ እኔም ከእሳቸው ጎን ሆኖ የሞገተም በግልም መከራም የተቀበለም የለምና። ይህም የሆነው መነሻዬ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ በነበራቸው ሰውኛ እና ተፈጥሯዊኛ ጠረን ነበር። ያን ሳስበው ምን ያህል ውስጤ ትልቅ ነገር እንዳጣ ይሰማው ይመስላችኋል? ግን እሳቸው ስንት ሰው ናቸው? አንድ? ሁለት? ሦስት? ወይንስ ወዘተረፈ …?

የሆነ ሆኖ በሰው ውስጥ ስንት የሰውነት ባህሪ እንዳለ ተምሬበታለሁኝ። አሁን ትክክለኛው ማንነታቸው ሲገለጥ በቀደመው አክብሮቴ ባልጸጸትም፤ እንደ አንድ የአገር መሪ አሁንም ባከብራቸውም 1% የቶለራንስ አቅም የሌላቸው መሆናቸውን ሳይ በተሳሰተ መንገድ ላይ እንደ ነበርኩ አሰተውያለሁኝ።

እኔም ሰው ነኝ እና ስህተቴን ለወደፊት የቅንነት ስህተቴን አርሜ ለማናቸውም የአገሬ ልጅ ወገኔ ብዬ ከምሰጠው ማናቸውም ሰብዕዊ ምስክርነት መቆጠብ እንዳለብኝ መማር ችያለሁኝ። የሚገርመው ሁለት ቦታ ነበር የተባለው „የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ“ አሁን ቤንሻጉል መጨመሩ ደግሞ ግርም ብሎኛል። ማጣፊያው አጠረና ሌላ ሦስተኛ አደናግሬ ነገር ደግሞ ተፈጠረ። አራተኛውን ቦታም እዬጠበቅን መሆኑን በስሌት ሰሌዳም ይመዝገብ ብለናል ለእነ አያልቅበት የድንጌተ ተውኔ የማማረቻ ካንፓኒ … 

በዚህ ቶለራንስ በተመለጠበት ወይንም በተላጨበት የአብይወለማ አስተዳደር ከውስጤ በማዘን ስለትውልዱ ጭንቅ ነው ያለኝ።

1.           ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ቶለራንስ በዞግ መሆኑ እጅግ አሳስቦኛል።
2.           ቶለራንስ የሌለው መንግሥት ለወደፊት ምን ዓይነት ትውልድ ሊፈጥር
           እንደሚችል ውስጤን ሰላም ነስቶታል። ቶለራንስ ለ እኩልነት እንጂ
            ለአግላይነት አልተፈጠረም እና።
3.           በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ኢትዮጵያ ከሉላዊው የቶለራንስ ማዕቀፍ
            ውጪ መሆኗም ስጋቴን ጨምሮታል።
4.           ሌላው የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ይዘዋት
            የነበሩትን ፍደኛ አላዛር ኢትዮጵያን እንኳን ለማግኘት መንገዱ የሳሳ
             ስለመሆኑ መከፋቴን ከፍ አድርጎታል።

የተወካዮች ምክር ቤት ጭብጨባ እና የፍትህ መከራም ሌላው የውስጥ ስቃዬን የጨመረው አምክንዮ ነበር። እኔ እንዲያውም ጭብጨባውን ሳይ ዘመነ ኪሚልሱንግ በኢትዮጵያ ዳግሚያ ትንሳኤው ስለመሆኑ ታዝቤያለሁኝ። ምን ዓይነት ስበስብ አገር እዬመራ ስለመሆኑ በቂ ጉልበታም ግብረ ምላሽም አግኝቻለሁኝ። አብሮ ለመወደቅ ያደመ በዚያም የከተመ። ለአቶ ጃዋር መሃመድ ሎሌነት ለማደር የማያወላውል ነፍስ? ማግሥትን ያዬ … ጸጸቱን ከቻለው ይቀጥል። 

ማከያ።

ሁሉም ሲታዘብ እንደባጀው ዶር አንባውቸው መኮነን ከብአዴን ሌላ ተጨማሪ ድምጽ እስኪያገኙ ድረስ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሚ/ር ደረጃ በመጀመሪያው የካቢኔ ምደባቸው አቆይተዋቸው ነበር። ቆይታውም ከሜቴክም ጋር ያያዟቸው የራሳቸው የሆነ ድብቅ አመክንዮ አለው። ማን እና ማንን ማጋጨት በማን ላይ ጥርስ እንዲነከስ ፈልገው ስለመሆኑ የሰሞኑ ሁኔታ ነጋሪ ነው። እንደ ሌላው ቦታ ዞጋቸው ቅራኔ ውስጥ እንዲገባ አይሹም። „በሞኝ ክንድ ዘንዶ“ ይለከባታል እንዲሉ።

ሌላው ከውስጤ ሆኜ ያደመጥኩት ጉዳይ እሳቸው ሲወደሱ ስንኞች፤ ኃይለ ቃሎች ጉልበታምነት ምቾት ሲሰጣቸው ሲወቀሱ ግን እረፍት የነሳቸው መሆኑን ተመልክቻለሁኝ።

ለቃላቶች፤ ለሥንኞች እንኳን የመቻል አቅማቸው፤ ነፃነት ለመስጠት ያላቸው አቅም ምንም ስለመሆኑም አሰተውያለሁኝ። „ቃል ይተክላል፤ ቃል ይነቅላል“ ሲሉ ይህንንም አምነው መቀበል ይገባቸው ነበር። በምሥጋና ውስጥ ያለ ኃይለ ቃል፤ በወቀሳ ውስጥም ነፃነቱ ሊታወጅለት ስለሚገባ።

እኔ ደግሞ ለቃላት ነፃነት የወጅኩት ሳይሆን የግጥም መፃህፍቶቼ የገዙ፤ ግጥሞቼን ያዩ፤ የቃላት ሞድ የተሠራላቸው ብቻ ሳይሆን ባሻቸው ቦታ እራሳቸውን እንዲገልጹ ርዕሱ ነፃነቱ የታወጀለት ስለመሆኑ የቀደመ መንገዴ ስለሆነ በጉለበታም ቃል ሊሰተካካል በሚገቡ አመክንዮች ሙግቴን መቀጠሌን በልበ ሙሉነት ልገልጻቸው እሻለሁኝ። ይህን እዘጋለሁ ሲሉ ደግሞ እንደ ለመደበኝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቤት እላለሁኝ። አልፈው ተርፈው በቃላት ነፃነት ላይ ጦር ለመምዘዝ የሄዱበትን እርቀት በማስተዋል ስላዬሁት።

አሁን ወደ ቀደመው … በነገራችን ላይ በህወኃት ዘመንም ሚ/ር ነበሩ ዶር አንባቸው መኮነን። ያም ጠዝትዟቸው ከእሱም ነበር የነቀሏቸው። ከመስከረሙ የአዋሳው የኢህአዴግ ጉባኤ ማግስት ሙሉ ድምጽ ማግኘታቸውን ሲያረጋግጡ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ካቢኔያቸውን በድጋሚ በአዲስ ለሁለተኛ ጊዜ ሲያደራጁ ተንሳፋፊ አድርገው ሥነ - ልቦናውን ድቅቅ አድርገው ሲያሹት ነበር የባጁት ያን ገናና አቅም።

ወደ አማራ ክልል ሲሄዱ ለመጓጓዣ ብቻ ነው የተጠቀሙበት። ወደ አውሮፓ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ደግሞ ተገፊ ነበር ነፍሱ። የስሜን አሜሪካ ጉዞ ላይ አልተከተተም ይህ ቅኑ ብቁ ብጡል ነፍስ፤ የአውሮፓ ጉዞ ላይም የሚገርመው የጠ/ሚር ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ እያሉ መነሳታቸው ታውቁ እጩው አቶ ሽምልስ አብዲሳ አብረው ነበሩ በጀርመኑ ጉዞው፤ በሌላው ሁለተኛ ጉዞ ደግሞ አቶ ፍጹም አረጋ የአሜሪካ ባለሙሉ አንባሰደር ሆነው ተሹመው አቶ ሽምለስ አብዲሳ የጠ/ሚር ቢሮ የጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ተሰነባቹም ተሿሚውም የጠ/ሚር የጽ/ቤት የ ኦዴፓ ሰዎች ሁለቱም አብረው ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር ተጓዥ ነበሩ። በዚህ ውስጥ በጠ/ሚር/ ጽቤት ሙያዊው አማካሪ የሆኑት ዶር አንባቸው አልተገኙም ነበር። 

ዛሬ ከሞት በመለስ ሞቷውን አታጋይ አርማችሁ አድርጋችሁ የአቶ ጃዋር መሃመድን ዓላማ ለማሰካት አብራችሁኝ ሁኑ ደግሞ እያሉን ነው። የአዲስ አባባ ከንቲባነትም እጩነት ታስቦ የሆነውን ደግሞ አይተናል።

የሆነ ሆኖ የዶር ወርቅነህ ገበዬሁ የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ቦታ እንሚያስለቅቋቸው ሲያውቁ ደግሞ ያ ቦታ ለምን ለዶር አንባቸው መኮነን አልተሰጠም የሚል ሙግት እንዳይመጣ በድንገቴ የቦታ ሽግሽግ ወደ ክልሉ ምደባ ተመለከትን።

የዶር አንባቸው መኮነን አቅሙ እሳቸውን እንደሚፈትን አሳምረው ያውቁታል። ይህ ብቻ አይደለም ማህበራዊ መሰረቱን ለማናጋት የአንቦ ጉዞን ከእርምጃቸው ቀድሞ በፍጥነት አደራጀተው የልባቸውን ካደረሱ በኋላ፤ ተቀባይነቱን እንዲመለመል በማድረግ፤ ለሁሉ የተፈቀደው መብት አማራ ክልል ብቻ እንዲነፈግ ትእዛዝ በመስጠት ራሳቸው ባደራጁት ተቃርኖ ልባም የአማራ ሊሂቃንን አሳጡን። የሳቸው የቶለራንስ አቅም በዚህ ሲለካ በራሱ ቁልቁል ያሰኘዋል። ቶለራንስ አልፈጠረላቸውም።

አሁን ደግሞ „አንባቸውን ያላችሁ እሰኪ እንያችሁ“ ከእኔ ጎን በመሆን ለቁሙቀር የፕሮፖጋንዳ ምት ታደሙ እዬተባለ ነው። ለኦነግ ዓላማ የታገለ ካለ ይሞክረው። እኔ ግን ለ ኦነግ ዓላማ ለሰከንድ ስላልተጋሁኝ አልቀበለውም።

አንድ የአገር መሪ እራሱም የቶለራንስ መርህ ፈጻሚ ሆኖ የበታቹንም በዚህ መርህ ተግባራዊነት መምራት፤ መግራት ሲገባ አቅም ያነሳቸው እሳቸው ሆነው አንድ የፌድራል መንግሥቱን ዕዳ ሁሉ የተሸከመን ክልል ቅስሙን ሰብረው የሽንፈት መናህሪያ ካደረጉ በኋላ፤ እንዳሻቸው ህግ ጥሰው ከጠቀጠኩት በኋላ „ገድሎ እግዚአብሄር ይማርህ“ ዓይነት አዲስ ተውኔት አቀረቡ።

አንድም ቀን በመንግሥታቸው ሥሙ አንባቸው ጓዴ ብለው በአብነት አንስተውት፤ በናሙና ጠቅሰዎት የማያውቁት ነፍስ፤ በሚያደራጁት አዲስ የወግ ትንተና በሉት አቅም ማሳያ ከቁጥር ያልገባ ሊሂቅ፤ በሚያደራጁት ቦርድ ከግምት ያልገባ ብቁ፤ በሚያደራጁት የጉዞ ሰሌዳ ከፋይዳ ያልተቆጠረ ሥም ስለሞተላቸው ዛሬ ደግሞ የሳቸው የደመነፍስ መንግሥት ማቆያ፤ የአቶ ጃዋር ህልም ስኬት ማሰንበቻ ሥራ ማስኬጃ አድርገው አቅርበውታል።

እኛ ልብ አለን። እኛ መንፈሳችን ሙሉዑ ነው። እኛ ከራሳችን ጋር ነን። እኛ ሚዛናችን ከቦታው ነው። አሰጋቸው ከተዋወቁት ጀምሮ እንደ ለመደባቸው ሲሰልሉት ኖሩ እሱም ረፍት ነሳቸው አቅሙን በፈለጉት መንገድ የኦፕሬሽናቸው ሰለባ አደረጉት። በዚህ ውስጥ የአቶ ዮናስ ደስታን በቀላጤ ከኃላፊነት ቦታ መነሳት እና መጪውን ዳመናንም ልብ ብሎ በማስተዋል መመርመር ይገባል።  በተገኘው አጋጣሚ ከሳቸው ጋር ትውውቅ ያለው አቅም ያለው አማራ በማንኛውም ሁኔታ እንደበረክት አይፈለግም።

የሆነ ሆኖ ትንሿ ኢትዮጵያ መሆኑ የሚገርለት ደቡብ እንደዛ ብሄራዊ ባዕል እስከሚመስል ድረስ ለሳቸው ሹመት አቀባበል ያደረገውን ጠንካራ የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በስል በትነው፤ በአደባባይ መሪዎች ዱላ ሲማዘዙ ዝምታን መርጠዋል።

ሽብር በአዋሳ እና የመንግሥት ዝምታ" በጸሐፊ አቶ ዳሞ ጎታሞ ( አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ እንደ ተረጎሙት።)

የኦነግን መንፈስ ደግሞ ለማስፈን የኦነግን እጬጌዎች ከቦታው በመላክ ብትንትኑን በኩሸኛ ዜማ አውጥተውታል። የቀኝ እጃቸው ልብ የተገጠመላቸው የአዲስ አባባ ዩንቨርስቲን ጨምሮ የብዙ ኮሚቴዎች አገራዊ ኢቤንቶች ልዕልት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ዛሬ አለሁ ቢሉም አዬር ላይ ነው ውክልናቸው ያለው።

ቤቱ ፈርሶ ጣሪያና ግድግዳው ተነቃቅሎ እሳቸው ግን የዛ ክልል መሪ ናቸው ተብለው አሉ እንዳሉ። ቤታቸውን አቅማቸውን እያሉ ነው ያፈራረሱት። ስለምን? የሳቸውም አቅም በተወሰነ ደረጃ ተፈሪ ይመስለኛል። ስለዚህ ይፋዊ ሉላዊ ውግዘት አይታከልበት እንጂ የማፍረስ ዘመቻው ይህ ሲዳማ ላይም ዕውን ሆኗል። ወላይታም ብዙ ነገር ገብሮበታል። ትቅቅፉ ከቀድሞ ጠ/ሚር አቶ ኃይላማርያም ደስአለኝ ጋር ደግሞ ያዬነው አይተናል።

ጅጅጋ ላይ በሊቀመንበሩ እና በምክትሉ ማህል ተሞክሮ ለጊዜው ከሽፏል አመራሩን ከሁለት ለመክፈል። ይህ ትግራይ ላይ አረናን ነጥሎ በመንከባከብ ከሰሞናቱም ተሞክሯል። አሁን እርገቱን አማራ ክልል ላይ ሆኗል።

እደሳትም ሹመትም ሸረትም ያልነካው የቤንሻንጉል ክልል አዲስ አባባን እንደ ማስፋሪያ አድርጎ ህወኃት እንዳቆዬው ሁሉ ኦዴፓም ለተጠባባቂነት የያዘው ክልል ነው ቤንሻንጉል። ሀረሬ እና ጋንቤላም ራሱን የቻለ የታመቀ መከራ ያለበት ነው። ጊዜ ጠብቆ ይፈነዳል። ሀረሬ ላይም እስካአሁን ትውር አላሉም ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
ሌላው ከዚህ ጋር አያይዤ ማንሳት እምሻው ብ/ጄ ከማል ገልቹ ቦታ እና የብ/ጄ  አሳምነው ጽጌ የምደባ ጊዜያቸውም ተመሳሳይ ነበር። በዛን ጊዜ ሊሰበስቡ ያሰቡት አቅም ስለነበር ያን አድርገዋል። ማዘናጊያ ነበር።

ብ/ጄ ከማል ገልቹ እሳቸው እንደነገሩን ባለሥልጣኖችን ማግኘት እጅግ ከባድ እንደነበር እና የኦዴፓን ሆድ ዕቃንም ገልጽውልን፤ ከሥልጣን ሲሳነበቱም ድንገቴ እንደነበር ነገረውናል። ነገር ግን በህይታቸው ላይ አደጋ አልደረሰባቸውም። ዓለም አቀፍ ውገዘትም አልተሰነዘረባቸውም። 

የጠ/ሚሩ አብይ የዞጋቸው አባል ስለሆኑ ስተናገሩት፤ ስለወቀሱት፤ ስለዘረገፉት ሚስጢር እና ስላስከተለው የፖለቲካ ክስረት ግን እንዲህ ሞት ቀርቶ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ዘመቻም አለዬነም አልሰመናንም። ስለምን? ጅ/ ከማል ገልቹን ከሞት ያተረፋቸው ኦሮሞነታቸው ብቻ ነው።  

የኢትዮጵያ ህግ ለ ኦሮሞ ልጆች ገዢም አሰተዳደሪም አይደለምና። አቅም ካቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይህን የሃቅ የወርቅ እንክብል ይድፈሩት። የ አማክንዮ ፈሪ እንደሳቸው አላየሁም ለዛውም የወጣላቸው ተናጋሪ ናቸው ክህሎቱም ብድር 
የሚያስኬድ ሳይሆን።

LTV WORLD: LTV WEKETAWE : ኦዲፒ ካፈጣጠሩ ጀምሮ ችግር አለበት - / ከማል ገልቹ
Published on Apr 23, 2019

LTV WORLD: LTV WEKETAWE : ቂምን ለመወጣት ህዝብን መጉዳት አያስፈልግም - / ከማል ገልቹ

Published on Apr 23, 2019

የብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ቃል ግን እያንዳንዱ ስንኝ በጥርስ የተያዘች ናት። ለምን ሲባል አማራ ስለሆኑ ብቻ ነው። አቅሙን የሚያውቁት ዕድሜ ልካቸውን ሲሰልሉት የነበረን አስፈሪ መንፈስ አጣብቂኝ ውስጥ ከተው እንዲህ ዓለምን እንያድምበት ያደረጉት ነፍስ ደግሞ ዓለም አቀፍ ውግዘትን አጭተው የፈጸሙትን አይተናል። ለምን ሲባል ቁልጭ ያለ ዘረኝነት ነው። እያጣጣሙ እንዲውጡት እምናገረው እሳቸው ዘረኛ መሆናቸውን ነው።

የጠ/ሚር አብይ አህመድ ዘረኝነታቸው ልክም መጠንም የለውም ግን በስልት ነው። ጥበብ አለበት። አማራ ሊሂቃንን አቀረብኩ ሲሉ በምን ስሌት እንደሆን የትኛውን ገፍትረው የትኛውን የህሊና ቤተኛ እንደሚያደርጉት ልብ ያለን ሰዎች አሳምረን አንቀርቅበን እናውቃለን።

ሌላው ግን አብይን ያመነ ጉም የዘገነ ነውና አብረን አለን የሚሉትም ቢሆኑ ነገ የእነሱ እንዳልሆነ አውቀው ቀናቸውን ተራቸውን ይጠብቁ። ይህ ፉከራ ሳይሆን ማስተዋል ይኑር ድጋፉ ባይጠላም ሰባራ መንገድ ስላለ አስተውሎ መጓዝ ይጠቅማል ለማለት ነው።

ሁለቱም ብ/ጄ አሳምነው ጽጌም ሆነ ዶር አንባቸው መኮነን ጋር በቅርበት ይተዋወቃሉ ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር። ዶር አንባቸው መኮነን አብይን ወደ ጠ/ሚር ለማምጣት ያደረጉት ተጋድሎ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው። አሁን ደግሞ የሞት ጽዋ የሰኔል እና የቹቻ መደመር አዬን። በነገራችን ላይ መጸሀፍ እዬተጻፈለት ነው የተባለው ነገረ መደመር እንዴት ነው መጠቀን? ወይንስ እንጦርጦስ ለምርምር ተላከ ይሆን። ድምጡ እኮ ክው ብሎ ደረቀ።  

በሌላ በኩል ብ/ጄ አሳምነው ጽጌን እንዴት ቤታቸው ድረስ ሄደው ቤታቸውን ሰልለው እደወረሱት እሳቸውንም ወደ ቀራንዮ ገዳ እንዳስደረጉ ከሰሞናቱ ሰምተናል። ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዬትኛው ሰብናቸው ነበር ይሆን የተመሰጥነው? የትኛውን ሰብዕናቸውን ይሆን የተስፋችን ፏፏቴ አድርገን ያመለክነው? ስንትስ ገጸ ባህሪ ነው ያላቸው?

አሁን የቀደመው ማንታቸው ተለውጦ ቁንጮ ሆነዋል። ይህ ነው አደጋውን በቀጣይነት … ውስብሰብ የሚያደርገው። በየት ባገኘሁት፤ እንዴትስ ልብሱን ነክቼ የበረከት ባለጸጋ በሆንኩ ብሎ ሲድህ የነበረው እና የተሳካለት ሁሉ ያገኛታል እጬጌ ሂደትን ይጠብቅ።

ለመሪነት በዚህ መሰል መሰሪነት የአንድ ሰው ጉዳት ሳይሆን የህዝብ ጉዳት ሲታሰብ ያርመጠምጣል፤ ይጨንቃል፤ ያስፈራል። ጉዳዩን የመደገፍ እና የመቃወም ሳይሆን አዲስ ትውልድ ለመገንባት በዚህ መስመር ከሆነ ዕዳው ተከፍሎ ነው የማያልቀው።
መተማመን የሌለበት፤ ጥርጣሬ የሰፈነበት ትውልድ ለራሱም አይሆን እንኳንስ አገርን ያህል ነገር ለመረከብ። አገር ጨርቅ አይደለችም በቦንዳ የምትለካም የምትሰፈር። አገር ሸቀጥ አይደለችም በኪሎ የምትመዘን በጫን የምትሰፈር። 

ጫን ማለት 10 ማድጋ ማለት ነው። 10 ማድጋ ደግሞ 10 ጊዜ 25 ኪሎ ማለት ነው። አገር ከወገብ በላይ እና ከወገብ በታች አይደለችም። እንዲህ ኩሽኛ ሴምኛ፤ ስሜን ደቡብ ተብላ በመንፈስ የምትባትል። አገር ሙሉዘኩሉ ናት። አገር ሙሉ ናት።

በአማራ ላይ ዘምቶ አገር እምራለሁ ማለት በራሱ ፍልስፍናው ኩስምን ነው የወደቀም ነው። እውነቱ ቢነገር እሳቸውም ዶር ለማ መገርሳ ግጥም አድርገው ነው የሚጠሉን። አቅማችን አይወዱትም ይፈሩታልም። ለዚህም ነው ያ ረዘም ያለ የዴሞግራፊ ትልም ዕውን እንዲሆን የተደረገው። ቂመኛም ናቸው። 

እግዚአብሄር ሲጣላን ከቂመኛ መሪ ኢትዮጵያን የሚታዳገት ዘመን ታጣ። ቂመኝነት መከራ ነው። ያ ተስፋ የተደረገ መንፈስ እንዲህ ውኃ የበላው ቅል የሆነውም የቂም ሰለባ ስለሆነ ነው።

በዬወሩ ነው አዳዲስ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ክሽፈት እምናዳምጠው። እንዲያውም እንደ እኔማ ነገ ደግሞ በዚህ ዙሪያ ተከሳሹ ማን ይሆን ባለተራ ብያለሁኝ … የቤተ መንግሥቱ ምግብ አብሳዮች፤ አንጣፊዎች ወይስ ማን? ተሹፌሩም ተፈስታሉም ፖለቲካ በመለስ ማለቴ ነው።

የሆነ ሆኖ ዘመቻቸው አዬር ላይ በራሱ ጊዜ አቅም አጥቶ መቅኖው በፈሰሰ ቁጥር ብስጭታቸው እያዬለ ራሳቸውን ተቃርነው በሽታ ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ማድረግ ያለባቸው ይመስለኛል። እሳቸው የሁሉም ነገር እጬጌ አዋቂ ስለሆኑ ምክር መስጠት ድፈረት ቢሆንም።

የሆነ ሆኖ እኛ አዲሱን ትውና ለማዬት እንጠብቃለን። እሳቸውም አይሰለቻቸውም ድብቁን ዓላማቸውን ለማሳካት በተራመዱ ቁጥር አዲስ ትውና ከመስራት አይቆጠቡም። ይልቅ የ አጭር ፊልም ፕሮዳክሽን ቢጀመሩም ቢያንስ በሽልግ ያተርፋሉ።

እርምጃውን እደሚያስጥሉም ነገረውናል። የእርግማኑ ብቻ ሳይሆን ከእጃቸው የወደቀውን ህዝብ የግርፋቱን፤ የእስሩን፤  የአፈናውን እንደሚገፉበት ተገልፆል። እኛም ዝም አለማለታችን አሳምረን በልበ ሙሉነት እንነግራቸዋለን። 

ማስፈራሪያቸውን ግን እዛው የሳቸውን እግር ተከል ተደማሪዎቻቸውን ይንገሯው። አቅመ ቢስ ስለሆኑ አቅም አለበት በተባለቦት ቦታ ሲኳትኑ አብረው በመስመጥ ላይ ስለመሆቸውም አይርሱት። ለነገሩ ፍርሰት እጣው የሆነ የተጠጋው ሁሉ እንዲህ ናድድድድድድ ….

ሌላው ማንሳት እምሻው ግን አውሮፓ ያለን ኢትዮጵውያን እኛ ግፉአንን በሹመቱም፣ በሽልማቱም፣ በውዳሴውም፣ በሠርግና መልሱ፣ በቅልቅል እና ግጥግጡ ተረስተን ባጅተን አሁን እርግማን ተልኮልናል። ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ አሜን ብሎ ተቀብሎታል፤ እኔ ደግሞ የቀረ ካለ ይላክልን በረከት ስለሆነ ባይ ነኝ።

እኔ የእንቅልፍ አልቦሽ ሆኜ ቀፎኝ የባጀው ሰኔ ወርን እንቅልፍ አጥቼበት ሰነባብቼ በሰላማዊና በጸጥታዊ እንቅልፍ አግኝቼ አደርኩኝ። የውነት ውዶቼ ለሽ ብዬ ተኛሁኝ። ስለዚህ እርግማኑ ስለተመቸኝ ሁለትሽን፤ ሶስትሽን አራትሽን ይድገሙት ይሰልሱት ብያለሁኝ። ይህ ምን ማለት ነው? ቀጣይ እርግማን እዬጠበቅኩኝ ነኝ እንደማለት … ምነው ስናወድሰውት አልተመረቅነም?

… እንደ አውሮፓ ለሳቸው ልዕልና የሞገተ፤ የጻፈ፤ ብዙ ብዙ ረቂቅ ተግባር የከወነ በግልም ውገዘትንም ያስተናገደ አልነበረም። ግን ያዬነው አዬን፤ የሰማነው ሰማን ለአገር ከሆነ ብለን ደግሞ አርፈን ከተቀመጥንበት እሱም እረፍት ሲነሳቸው እርግማን ተጋሩ ተብለናል። ለመሆኑ እኛ አውሮፓ የምኖር ኢትዮጵውያን ትዝ ብለናቸው እናውቃለን?!

የሆነ ሆኖ እርግማኑ ፈጣሪ እንደሳቸው ዞግ ስለሌለው በሚፈርደው ላይ ፈርዶ እናያለን። መጋቢት አንድ ቀንም የሳቸው ኃጢያት ነው አላዛሯ ኢትዮጵያ ያን መከራ ያስተናገደችው። አንድ ነፍስ ላሰጋቸው የባልደራስ ጉባኤ ቤተ መንግሥት በአንድ ጀንበር ጉባኤ ሲያሰናዳ የሰማይ መጋረጃ ተገልጦ ቅዱሳኑ ሰማዕትነትን ከፈሉበት። በሳቸው ኃጢያት። አሁን ባህርዳር ላይም ከዚኸው ስጋት የመነጬ ነው የጥድፊያ ሰብር ጉባኤ የክልሉ ሊሂቃን እንዲቀመጡ የተፈለገበት። አተርፍባይ አጉዳይ ሆኑ እንጂ።

ወደ ቀደመው ስመለስ መጋቢት አንድ የሳቸው ህይወት መትረፉ እንጂ ያ ሁሉ ነፍስ በዛ መልኩ አስከሬኑ እንደዛ ሆኖ መቅረቱ ከቁጥር የገባ አይደለም። የማያንቀላፋው አምላክ ለሳቸው ብቻ ነው የቆመው። ይህን ጊዜ ነበር ለሳቸው ብቻ የቆመው እሳቸውን ብቻ እዬተንከባከበ ያለው የማያንቀላፋ አምላክ ያን ቁጣ የላከውን ተደሞ ብልቱን ራሱ ያላገኙት መሆኑን እምናስተውለው። ቀድሞ ነገር የእሱን የፍርድ ቀን መጠበቁ ግን ወድጄዋለሁኝ። ሚዛኑ የማያወላዳ ነው እና።

ወደ ፓስተርነት ተሻገሩ ስለሚሉት ግን ፓስተር ዞግን ብቻ ተንከባካቢ ከሆነ፤ ሴራ እያደራጀ በቀውስ ሰብዕና የሚገነባ ከሆነ ይህም ዶግማውን እሚያፋልስ ይመስለኛል።

እሳቸው ህግ አልባዎቹን የዞጋቸውን ቤተኞች፤ ህግ ጣሾች ሳይሆን እዬተፋረዱ ያሉት ሌላውን ባይተዋሩን፤ ትርፍ ዜጋውን ነውና … ስለዚህ ፓስተርነቱንም አያሟሉም ለማለት ነው። ፓስተር ለመሆን ራሱ የመስበክ አቅማቸው ሳይሆን ሁሉንም በእኩልነት የማዬት፤ የልብ ንጽህና አቅማቸው ራሱ የከሳ ነው። ቀለሙም ግራጫማ ነው።

ለዚህም እንዲረዳቸው ነበር የአማራን ሊሂቃን እልቂት ከማወጃቸው በፊት የቤተ መንግሥት የፕሮቴስታንትን አማንያን ጉባኤ ሰብስበው ነበር በዋዜማው፤ አሁን ያን ድልድይ ለማጠነከር ነው ይህ ዓዋጅ።

እውነት ሃይማኖት የላትም። እውነት ሃይማኖቷ እውነት ሆኖ መገኘት ብቻ ነውና። ይልቅ ይህን ማምታቱን ትተው ወደ ተከበሩበት ሰብዕና ተመልሰው እውነት ይሁኑ። ኢትዮጵያን መናህሪያ አልባ ለማድረግ፤ አህጉሩን መዲና አልባ ለማደረግ እዬተጉ ለኢትዮጵያ አንድነት ማሰብ የድቡሽት ቤት ነውና።

ኢትዮጵያዊ ቀለማቸው እየፋደሰም ነው። አቅም ማለት ፍልስፍናው አልገባቸውም። ስለሆነ በቅጡ መያዝ ተሰኗቸው እዬተነነ ነው። ትነቱን አሰባስቦ ደግሞ ማገገሚያ ህክምና ጣቢያ ውስጥ ለማስገባት ራሱ የስልት እና የጥበብ አቅም ይጠይቃል። ለዛም አልታደሉም። ያወጣኛል ያሉት ኃይል ነው። ይቀጥሉበት። እኛም በሃሳብ እንሞግታቸዋልን። አሸናፋዊን ሂደት ይዳኘዋል።

ውድ የአገሬ ልጆች መነሻችሁም መዳረሻችሁም የዴሞግራፊ ዕውንነት በኢትዮጵያ ባጉም ባጉም እያለ ያለበት ሁኔታ ይሆን ዘንድ በታላቅ ትህትና እያሳሰብኩ ዛሬን በዚኸው ልከውን።

ውዶቼ የኔ ቅኔዎች ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።