ዱዳው የአብይዝም የኦሮሙማ ሌጋሲ አናባቢ አልቦሽ ነው፤ ሰደከበተ SDKBT።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ዱዳው የአብይዝም የኦሮሙማ ሌጋሲ
አናባቢ አልቦሽ ነው፤ ሰደከበተ SDKBT።
„አቤቱ ሰውነቶቼን ለአንተ ሰጠሁ።“
(መጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 3 ቁጥር 12)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31.01.2020
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
·
በር።
እንዴት ናችሁ ቅኖቹ የአገሬ ልጆች? እርህርህና የኦሮሙማን የዴሞግራፊ ጭካኔ ተረከብ እዬተባለ
ነው። የዛሬው እርስ ጉዳዬ ይህ ነው። መቼም ይህ ዘመን መልካሙን ነገርን አሳዬን ብለን ማሰብ ያለብን ይመስለኛል።
ፈተናው በራሱ ኢትዮጵያ በማን ውስጥ እንደ ተሰናበተች እዬተሰተዋልን ነው። ቀድሞውንም እሷ በውስጡ
የሌለችበት ነፍስ ሁሉ ሲምል ሲገዘት ዕድሜውን የሸኜበት፤ ትልሙም መክኖ ሲፈርስ ሲሰራ የተኖረበት፤ የውስጥ የክህደቱ የውድቀት ስምጥ
ሸለቆም ኮለል ብሎ የታዬበት ዘመን ነው። ያልወደቀ፤ ያልተንከባለለ፤ ያላዳጠው፤ ያልተነኳኮተ ማግኘት አይቻልም። ብልሁ ኢትዮጵያዊነት
ማጣሪያ ወንፊቱ በመዳፉ ነውና።
ዘመኑ ይመስገን ኢትዮጵያዊነት የታደመባት፣ አገር ኢትዮጵያ ተጠምዳ የተያዘችበት በማን መዳፍ
ሥር እንደወደቀች፤ እንዴትም እንደሚነግድባትም፤ በጥርስ የተያዘችበት ሁኔታም በአስተውሎት ፍንትው ብሎ ያዬንበት ወቅትም ነው። ከዚህም
በተጨማሪ ማን ለቃሉ እንደ አደረ፤ ማን ደግሞ ቃል አባይ እንደ ሆን፤ ማን ደግሞ ከሞቀው ዘፋኝ እንደ ሆነ፤ ማን አሸብሻቢ እንደሆነ
እያዬን ነው።
ስለዚህ ዘመኑን ባገኘው የአንገት ሃብል አስርለት ነበር። እኔው። እንደ ጉድ ነው የተንተረተረው
የህሊናው አቅም ሁሉ። ሲመከርባት፤ ሲዶለትባት የኖረችው ቅኒት ኢትዮጵያ ገመናውን ሁሉ አያዬችው ነው። ታዘበችው። ጡቷን አሽታ እንዳትረግም
እሱ አንድዬ ይሁነን ብቻ። እናት ካመረረች ባክኖ መቅረት ነው። ለዚህም ነው የተጠጉት ሁሉ ፍርሰት የነፍስ ማደሪያ ሆኖ የሚታዬው።
·
ኪናዊ ትዝብት።
መንገድ ላይ ናቸው ሁለቱም። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድና ዱዳው ሹመታቸው። መንገድ ላይ
ናቸው ስል የጠቅላይ ሚኒስተርነታቸው ሹመታቸውን ማንነትንም ማለቴ ነው። በሳቸው ማንነት ውስጥ ያለው የክብር ማንነት ዱዳነት
ይኸው ስለሆነ መግለጫው፤ መሄድ፤ መሄድ፤ መሄድ …. ። የዱዳው እና የአጓጉሉ የኦሮሙማ መንገዳቸው ቅዬሳ ሁነት እኔ ስመለከተው
ሰደከበተ SDKBT ነው። ይህ ነው ሌጋሴያቸው።
መቼም ይህን ችሎ ያነበበ ሰው የሰማይ መላዕክት መሆን ይኖርበታል። ለመሆኑ ይህ የፊደል ካብ
ሰደከበተ SDKBT ትርጉም ይሰጣልን? የሚያሳዬን አቅጣጫ ይኖራልን?
የኢትዮጵያ መሪ የዓለሙ ሎሬት ዱዳው መንገዳቸው ተወደደም ተጠላም
ይህ ነው። የዱዳው አብይዝም ሌጋሲ የማይነበብ ነው። በጥቁር
ቀለም ጥቁር ብትጽፉ አይነበብም። ማንበብ አይቻልም። ልክ እንደዚህ። እንደዚህ። ይህ ይነበባልን?። የውጭ ጉዳዩ፤ የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ ፖሊስው የተዘጋበት ነው። በቁልፍ
የተከረቸመ። የተቀበረም። ዳሽ እንኳን የመሆን አቅም የለውም። ዳሽ ምንም የለውም የሚል ምላሽ ይሰጣል።
ሚስጢረኛ ተደማሪዎችም የቤተ - መንግሥት ባለፍሪንባ ነፍሶች ይህን መክፈት ከቻሉ ሊቅነታቸው
በወርቅ መዝገብ ይመዘገባል። ዱዳው የአብይዝም ሌጋሲ ሰብዕና እንደ አወጣ ስለሚቸበቸብበት፤ ስለሚቀናበት። እምቅ አድርገው፤ ድፍን
አደርገው፤ ክድን አድርገው ይዘው በጋራ ይብተከተካሉ። ግን እንደ ተወጠረ አቁማዳ ፍንድትድት እያለ ሲያፈስ፣ ሲለቅሙ ይዋላሉ። ጉዞው
አንድም የዕውነት ቅንጣት የሌለበት የድቡሽት ቤት ነውና።
ዶር አብይ አህመድ መንገዳቸውን እሳቸውም ጠፍቷቸው ያው መንገዱን ፍለጋ እንደ ወጡ ቀርተዋል። አልተመለሱም። እራሳቸውንም ፍለጋ
ላይ ናቸው። ቅዬሳው በጥኒብራው* ተዘቅዝቆባቸዋል። ምን አልባት፤ ምን አልባት ዓጤ ጉግል ከተማለዳቸው ዕደለኛ ይሆናሉ። ኮከብ
ቆጣሪያቸው ሌንጮወዲማ ቢረዷዋቸው መቼስ አጤ ጉግል ታከተኝ እንዳይል ማህላ አለበት። የተቸገረን ሁሉ አሉሁኽ የሚል ብሩክ ርህርህና
የተሰጠው ቅዱስ ሰስለሆነ እኩል „ባዕድ ወገን“ ሳይል ፊት አይነሳቸውም … ጎራ ቢሉ … አነምንትሶ።
ጎሬ ከተማ ዉስጥ ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ተደረገ | ከአማራዉ ወገናችን ጋር ሊያጋጩን የሚሹ ጨቋኞችን እንፋለማለን
ይህ መልዕክት„ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ በአፍላው እንዲህ መራራ ስንብት ሳያደርግ፤ ኦሮማራም
የመቃበር ራት ሳይሆን፤ ሲፈልጉ ደግሞ ህዝቡን ሰብስበው እንዲህ ያስቃኙታል፤ „ከአማራዉ ወገናችን ጋር ሊያጋጩን የሚሹ ጨቋኞችን እንፋለማለን“
በዕለቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ነዋሪ ነበር የወጣው። ሲያሰኛቸው
ደግሞ ገጀራው፤ ቆንጨራው፤ ነዲዱን ሲኦሉን አምጥተው ይዶሉታል። ባልቦላው
በእጃቸው ነው።
ይህ ሁሉ መከራ የማን የእጅ ሥራ እንደ ሆን ማገናዘብ ይገባል። ተፈልጎ ነው ይህ ሁሉ ቀውስ
የሚደራጀውም፤ የሚመራውም። የአማራ ልጅ ሰቆቃ፤ እገታ፤ እንግልት፤ ጡት ቆረጣ፤ መታረድ፤ ተግድሎ መቃጣል፤ በድንጋይ ተቀጥቅጦ መገደል፤
እንደ ትርፍ ካፒታል የሚታይበትም ነው።
ዱዳው የአብይዝም ሌጋሲ የኦሮሙማ የሴራ ኢንፓዬር ስለመሆኑ
የተባለበት ዘመን „ከአማራዉ ወገናችን ጋር ሊያጋጩ የሚሹ
ጨቋኞችን እንፋለማለን“ ይህን በአስተውሎት መርምሩት እና ይህ ወሽካታ ቃና በሥልጣን ዘመኑ
ለ አማራ ህዝብ የወረደውን ማዕት፤ መኖርን ያከሰለበትን መንገድ፤ ሰብአዊነት ያዋረደውን፤ የተስፋ ድርቀተ ውችንፍሩን፤ የማጭበርበር
ዕለታዊ ተግባሩን ደግሞ ታደሙበት። የአረመኔነት ናዳ!
እኔ በተፈጥሯቸው የጠፉ ነፍሶች አገር ሊያጠፉ ቧ ብለው መከፈታቸው ብዙም አይደንቀኝም። አጀንዳዬም
አይደሉም። አቅሙ የሚታደላቸው በቀጥታ በነፍስ ወከፍ ይሁን በተቋም ደረጃ በአጓጉሉ አናባቢ አልቦሽ የአብይዝም ሌጋሲ ነው። ሲከፈቱት የተልባ ስፍር ነው ጉራቸው ሆነ አቅማቸው። የሳሙና አረፋ። አንድ ጫን ያለ የሰራዊት
አሰሳ ቢካሄድ እግሬን አውጪ ነበር የሚሆነው።
ኢትዮጵያን ጽላቱ ያደረገ ሠራዊት ቢኖረን ማለቴ ነው። ለዚህም ነው አባ ትእግሥት
ጄኒራል ሳህረ መኮነን ሰማዕትነትን የተቀበሉት። ቀሪው በኦነግ ሳንባ የሚተነፍስ ዝንቅንቅ ይመስለኛል። ለነገሩ በማለዳው ነበር አዲስ
አደረጃጀት መዋቅር ተፈጥሮለት በምክትሉ ሥር ሁለመናው እንዲጠቀለል የተደረገው።
የሚገርመው ከንፍሮ ጥሬ የሚወጣው አምላክ ያተረፈው ነፍስ አለመኖሩ ነው ለኦሮሙማ መንፈስ ኢሰብአዊነት
ተጋላጭነት ያመሳጠረልን። ሁሉም የኦሮሙማ ሊሂቅነት ተራገፈ። ፖለቲካቸውም እርቃኑን መለመላውን ቀረ።
ሁሉም ቀፎውን ቀረ። ስሜቱ
ደነፋ፤ ደነፋ፤ ስሜቱ ተኩረፈፈ፤ ተኩረፈረፈ፤ ስሜቱ ኩፍፍ አለ ኩፍፍ፤ ስሜቱ ጎረረ ጎረረ ሁለመናው የሳሙና አራፋ። ጤዛ። በውስጡ
ብናኝ የተፈጠሯዊነት፤ የሰውነት ጠረን የለም። ትነት። ስንት ጲላጦስ ነበር ኢትዮጵያ ተሸክማ የኖረችው? ዘመን አንገዋለለው እንጂ።
·
ርህርህናም እዬታደነ ነው። ደግነትም ስደት ላይ ነው ያለው። ቸርነት እክል ገጥሞታል።
ርህርህናም ተሰደደ - በዘመነ ገዳ። ርህርህናም ታገተ - በዘመነ ሞጋሳ። ደግነት ታሰረ - በዘመነ
ኦሮሙማ። ቸርነት የበቀል ማወራራጃ ሆነ - በዘመነ ሜንጫ። እንዴት አይነት አሽዋ ዘመን ነው?
ቢያንስ የሰው ልጅ እንዴት ሰው ለስው
መተዛዘን እንዳይችል እንዴት ይታገዳል? ርህርህና፣ ቸርነት፤ ደግነት፤ መስጠት አልቀረላቸውም እያደኑት ነው? ዬትኛው ክፉ መንፈስ
ነው አገራችን ላይ የወረደው? ማዕት!
ሥምን መላዕክ ያወጣዋል እንዲሉ ጋዜጠኛ ወ/ት አውደ አዲስ ወጣት፣ ለግላላጋ፤ ቀንበጥ፤ ከአንድ
ጉልበታም ድምጽ፤ ቃናው እጅግ ሳቢ ከሆነ ድምጽ ፍሰቷ፤ የጣዕም ምቱ ልብን አንጠልጣይ ዜና ከአሥራት ሚዲያ አዲስ አበባ ስቲዲዮም
ያቀረበችውን በተደሞ፤ በአርምሞ ሆኜ ታደምኩበት። ድምፆዋ እራሱ የበቃ የጸደቀ ነው።
እርግጠኛ የሆነ ድምጽ ነው ያላት። አሥራት
ሚዲያ ታድሏል። የድምጽ ሥጦታ ለሚዲያ፤ ለተውኔት፤ ለሥነ - ጹሁፍ ለትዳርም የድምጽ ጣዕም ማማር አውራ ጉዳይ
ነው። እኔ የድምጽ ቃና አወጣጥን ማጣጣም በጣም ነው እምወደው አንዱ መስኬም ነው። „ርግብ በር ላይ“ መጽሐፌ ላይ እርስ ሰጥቼ
ጽፌበታለሁም። አሥራት በዚህ ዘርፍ ጸጋውን መዳፉ ውስጥ አስገብቷል። ዘገባው የህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ ልዩ ሪፖርት ነበረው።
አንዲት ወጣት ሴት አስተያዬት ስትሰጥ ርህርህና ማድረግ፤ ለተቸገረ መስጠት፤ ላጣ መለገስ፤ ቀን
ፊቱን ለዞረበት ደግነትን መሸለም፤ ቸርነትን በመሆን ማሳመር ፈቃድ አንዳላገኘም ተረዳሁ። ማህበረ ርህርህና እዬታደነ ስለመሆኑም
ተገነዘብኩኝ።
ምንድነው እነዚህ ሰዎች የሚፈልጉት? ምንድንስ ናቸው? ምኑ ማአት ነው የፈሰሰው? የአማራ ታዳጊ ወጣት ሴቶች በቃን!
ብለዋል። ይህን የበቃኝ መንፈስ ግርዶሽ ለመስራት ሲያሽሞነሙኑ
ይውላሉ የአብይዝም የዩንቨርስቲ ፈላስፋዎች የአማራ ሊሂቃን። በዚህ ሰልፍ ግን ተዋርደዋል። ገናም ውልቅልቃቸው ይወጣል። ተመስገን!
ጥቁር የለበሱ የአማራ ታዳጊ እና ወጣቶች የሚያሰሙት የማህጸን ቁስለት ድምጽ ህሊናን ይሰውራል።
በጋራ ነው ስለ ሴት እናትነት፤ ሚስትነት፤ እህትነት ተፈጥሯዊ ጸጋዋ መረገጥ በቁጭት የሚናገሩት። መቼም ዘንድሮ ሆድ ብሶኛል እንኳንስ ይህ ተጨምሮበት
ዕንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም። ለዚህ ነው እኔ ገና ላልተፈጠሩት በሃሳብ ላልተጸነሱት የዛሬ 20/30 ዓመት ስለሚፈጠሩት ነገር
ይጨንቀኛል እምለው።
ለዚህም ነው የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የጫጉላ ሽርሽር አይደለም የምለው። ለዚህም
ነው ገና በጥዋቱ አንቦ ሄደው „ቄሮ ጀግና“ ያሉት አቶ ደመቀ መኮነን በአማራ መሬት ግን ይህችን መድገም ሲሳናቸው በግንቦት
5/ 2010 ዓ.ም አብይ ሆይ! በሚል እርእስ ባቀርብኩት ዘለግ ያለ አቤቱታዬ በጥዋቱ ዕውቅና ያልተሰጠው ችግር መፍትሄ አያገኝም
ብዬ ሙግት የጀመርኩት።
ያ ቀን የአንቦ የሙገሳ ቀን ትልቅ መልዕክት ነበረው። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ
ለምርኮኝነት ለቄሮ በአቶ ደመቀ ሞከነን አማካኝነት ሽልማት የተሰጠበት ዕለት
ነበር። አማራ ለእርድ የተሰጠበት ዕለት።
አቶ ደመቀ መኮነን አብረው እንዲሄዱ የተደረገውም በምክንያት ነበር። የዶር አብይ
አህመድ የአማራ ክልል ጉብኝት ላይ አልነበሩም ም/ ጠቅላይ ሚኒስተሩ። በተመረጡበት ክልል አልነበሩም። ሌላ ክልል ግን አብረው ሄደዋል።
እንቆቅልሹ ይህ ነው።
የዚህ ሁሉ መከራ ምንጩም ያ የተዘጋ ሚስጢራዊ የውል ሰነድ ነበር። የተጋድሎውን
ተስፋውን የቀበሩት አቶ ደመቀ መኮነን ናቸው። የአማራ ህዝብን ለ ኦሮሞ ፖለቲካ የበቀል እርድ አሳልፈው የሰጡት አቶ ደመቀ መኮነን
ናቸው። ለምን? ፈጣሪ ይመርምረው። እኛ አማራዎች ለአቶ ደመቀ መኮነን እንደ ባዕድ እንደምንታይ ነው እኔ አሁን አሁን እዬተሰማኝ
ያለው። የኦነግን ፍላጎት ሽፋን እዬሰጡ ቀጥ አድርገው እያስፈጸሙ ናቸው። ውስጣቸው የኦነጋዊ ጠረን ይሸተኛል።
ቃለ ምልልሱ ላይ የሳበኝ ውስጥነት ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ፤ መጠጊያ ላጡ የአማራ የዩንቨርስቲ
ወጣቶች እርዳታ በግል ለማድረግም እንደ ተከለከሉ አንዲት ወጣት ስትናገር አዳምጥኩኝ።
የሚገርመው እዛ ሜዳ ላይ የፈሰሱት ወጣቶች እያሉ የተጠቂ ቤተሰቦችን መንፈስ ለማገት፤ እንደ እኔ ዕሳቤ ዘግይተው አንድ በአንድ
ያጠፏቸዋል ብዬም አስባለሁኝ።
እንዴት ብሎ የዶር አንባቸው መኮነን እናት፤ የአቶ ምግባሩ አባት እናት በተከታታይ ቀናት አለፉ?
አሁንም የታጋች ቤተሰቦች ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ ነው። ፍልስ ነው የሚያደርጉት። መንቀል እርሾ አልባ ማድረግ የ ኦሮሙማ ጥልቅ ተልዕኮ
ነው።
የዚህ የጭካኔ ግርዶሽ አባት አለው፤ አቶ ደመቀ መኮነን። የዚህ ኢሰባዐዊነት፤ እናት አለው ወ/ሮ
ሙፍርያት ካሚል። ብአዴን መግለጫው ጠንከር ብሎ እንዲወጣ የሚፈለገው መሰረታዊ ምክንያት እርሾ የለሹ ክህደቱን ሪከበሪ ውስጥ ለማስገባት
ተፈቅዶላቸው ነው የሚከውኑት። ተቃርኖ ያላቸው ሆኖ መቅረቡ የአማራን ህዝብ መንፈስ ከሁለት ለመክፈል። እንደ ለመዱት። አታስታውሱም
አቶ ዮሆንስ ቧያለው ወጥተው ሲናገሩ እንዴት ይጨበጨብላቸው እንደነበር፤ ያ አብይዝም ላቀደው ለስሜን አሜሪካ ለሚኖሩ የአማራ ልጆች
ወጥመድ ነበር።
ብቻ ጠሚር፤ ም/ጠሚር፣ የሰላም ሚኒሰተር ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር በቤተ - መንግሥት ስብሰባ ላይ
መሆናቸው ከብዙ አቅጣጫ ጉዳዩን ሳናቆላምጥ ከደፍርነው የዜጎች የወደፊት ተስፋ ረመጥ ውስጥ ስለመሆኑ መረጃ ይልክልናል። እያዘናጉ
የአማራን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያቀላጠፉት ነው። በቀጣይ የሚተርፍ ዘር ይኖራል ብሎ ማሰብ ጸሐይ ጨለማን ትተካለች የማለት ይሆናል።
አሁን እዬሆነ ያለው ልክ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪን ከጠሚሩ እስከ
የክልል መስተዳደሮች፤ በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ፤ የሰላም ሚነስተር፤ የመከላከያ ሚኒስተር ቅዱስ ሲኖዶስን፤ የእርዱን
ተማህጽኖ ተከናውኖ የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍ ጉዳይ የውሃ ሽታ
እንደሆነው ማለት ነው።
ከዛ በፊት የገዴኦ ህዝብ ሰቆቃም እንዳይወጣ ታፍኖ ቆይቶ ሲፈናዳ የሆነውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር፤
የሰላም ሚኒሰተር፤ ጠቅላይ ሚኒስተር የሚዲያውን ዘመቻ ለማስቆም የተሄደበትን አስተውለናል። አሁን የአዲስ አበባ ህዝባዊ ሰልፍ ያው
በ አቶ ሽምለስ አብዲሳ ፈቃድ የሚከውን ነው።
በጎንደሩም ላይ ቢሆን የመንፈስ ጫና ለማሳደር ተደርድረዋል የኦነግ ካድሬዎች። ባህርዳር ቅዱስ
ጊዮርጊስ ላይ እርዳታ መስጠት አልተቻለም አይደለም ለእነዛ የአማራ ልጆች ስቃይ ባለቤት ሊሆን ቀርቶ ይህ ዱዳ የአብይዝም አረመኔ ሌጋሲ።
ለእኔ ምክትል ጠ/ሚር ከምል የኦነግ ካድሬ፤ የሰላም
ሚኒሰተር ከምል የኦነግ ካድሬ፤ ጠሚር ከምልም የኦነግ ካድሬ ብል ይቀለኛል። አቶ ንጉሱን በ እኔ መንፈስ ከተቀበሩ ከጅምሩ ነው።
ሚሊዬነም አዳራሽ አቶ ጃዋር መሃመድን ሊቀበሉ ሲረገርጉ። አይፈረድባቸው የአርሲ ጢቾ ጠናውያን ናቸው። „ክርስቶስ ለሥጋው አደላ“
እንዲሉ።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ጥቁር ለብሳለች ትንታጓ ወጣት እንዲህም ትላለች። „ትቆርጡት ይሆናል፤
ወይንም ላታቀርቡት ትችላላችሁ። እኔ ግን ኃላፊነቴን ተወጥቻለሁኝ ብላለች“። ቅኔያዊት!
አሥራት ዜና:- ጥር 19፣ 2012 ዓ.ም. | ASRAT News January 28,
2020
በምቾት እና በድሎት ተቀምጠው የጭካኔውን ልክ እያወቁ መረጃውም እያላቸው መንፈስን ማህል ላይ
ለሚገትሩ ወገንተኞችም የላከቸው መልዕክት ሰው እንሁን ነው። ሰው መሆን ግለጹን
የአማራን የዘር ማጥፋት ዕለታዊ እርምጃዎችን ታዝባ፤ ርህርህና ሳይቀር እንደታገተ ነው የምትገልጸው።
በንግግሯ ውስጥ በውስጧ የሚንቀለቀለው
ደግነት እዬተቃጠለ መሆኑን ተቀብላ ለመንፈሱ ዋቢ ጠበቃ ሆና ነው ያዬኋት። የተቃጠለውን መንፈሷን እንዲህ ትገልጸዋለች „ ፒጃማ ለብሰው፤ ሙሉ እቃቸውን ትተው ነፍሳቸው
ለተረፉት ወጣቶች ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ለተጠለሉት ከእኛ ከራሳችን ዳቦ እንስጥ ብንል አይቻልም ነው የተባልነው። ለምን? ተካፍሎ መብላት አብሮነታችን የት ሄደ? አንድነት!
አንድነት! በታሪክ ብቻ። ላሊበላን አክሱምን እያዬን ብቻ መደሰት። እኛ ታሪክ አንስራ እስኪ ታሪካችን እናቆዬው።“ መስራቱ ቀርቶ ማቆዬቱን አልቻልንም ነው። የአማራነት እኛዊነት በልቅና ልዕልና።
ከዚህ ላይ የኦሮሞ ሊሂቃን፤ አክቲቢስቶችን፤
ጋዜጠኞችን፤ የዘመኑ መሪዎችን አንድ ላይ አምጥታችሁ አቅማቸውን ብትለከቱ ይህን አመክንዮ መሸከም አይችሉም። አስወጡ፤ ገዳማትን
አፍርሱ ቅዱሳን ደናግልን አባሩ፤ ንቀሉ፤ ቋንቋውን አትናገሩ፤ ኪነ ጥበብ እኮ እራሱ ታግዷል፤ አትገበያዩ፤ ምንም የታሪክ አንድነት
የለንም፤ ለትግሬው አክሱም፤ ለአገው ላሊበላ፤ ለኦሮሞ እሬቻ፤
እሷ ደግሞ ተካፍሎ መብላት አብሮነታችን የት
ሄደ? አንድነት! አንድነት! በታሪክ ብቻ። ላሊበላን አክሱምን እያዬን ብቻ መደሰት። እኛ ታሪክ አንስራ እስኪ ታሪካችን እናቆዬው“ አማራ የሥነ - ልቦናው ጥግ ይህ ነው። እኛነት! የአማራ ወላጅ ታሪካዊ ድርሻውን በሚገባ
ተወጥቷል።
የአማራን ህዝብ አስተዳደግ፤ አኗኗር፤ ትውፊት፤ ትሩፋት፤ ባህላዊ ዕሴት የሚገልጽ ጉልበታም አመክንዮ ነው ያነሳቸው።
ህይወቱን እሷ እዬኖረቸው ነው። ያን ነው የገለጸችው። በዚህ ንግግሯ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ዘውድ ደፍቶ ታገኙታላችሁ። የአማራ ህዝብ
እንዲህ ነው ልጆቹን ኮትኩቶ የሚያሳድገው።
ይህን መንፈስ ለመስበር ነው ጠሚር አብይ አህመድ እንቅልፍ ያጡበት፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ
በስውር ማረጃ ለአማራ ህዝብ የሚያዘጋጁበት፤ የሰላም ሚኒስተሯ ላይ ታች የሚባዘኑበት። በጠቅላላ ጣሊያን ቀብሮት የሄደውን ፈንጅ
ድልዳል ሠራለት ህዋህት አሁን እነሱ አፈነዱት። ድጋፍ ሰጡት። ከበከቡት። የ እኔ አሉት። እኔ የሚሰማኝ ሙሰሎኒ መቃብሩን ጥሶ እንደተነሳ
ነው።
ማንኛውም ጸረ አማራ መንፈስ ሁሉ በጠቅላላ አማራን ለመውቀስ፤ ለማሳደድ ከመነሳት በፊት ወላጅ
ነኝ ያለው ሁሉ ይህን ትውልዳዊ ኃላፊነቱን ይወጣ። የአማራ ህዝብ ማለት ንጥር ሰብዕና ያለው ህዝብ ነው። አማራ ትውልድን እንዲህ
ነው የሚገነባው።
የአማራ ወላጅ 28 ዓመት ሙሉ በፖሊሲ ተቀርፆ አብሮነት ጦር ቢመዘዘብትም፤ በእሱ የዘር ማጽዳት ቢከወንም ሙጫ
ሆኖ፤ ራሱን ገብሮ አቆይቶታል ኢትዮጵያዊነትን። ይህን ለመስበር ነው ዱዳው የአብይ ሌጋሲ በትጋት እዬተንቀሳቀሰ ያለው። በኃይልም
ነው እዬደፈረው ያለው።
የሚገርመው መንፈሳዊ ትሩፋትንም ለመሳቀጠል አልመቻሉን እያዬን ያለነው። ርህርህና መታገዱ በቡራዩ፤
በለገዳዲ ለገጣፎ፤ በጌዴኦ አሁን ደግሞ በታገቱት ተማሪዎች እያስተዋልን ነው። ወረራው በሁለም መስክ ነው። ርህርህና እዬታደነ ነው።
እነሱ አያደርጉት ርህርህና ለሚያደርግ ፍጡር ስለምን
ነው የሚታገደው? ያ ሁሉን መከራ የተቀበሉ ልጆች በተጨማሪ እንደ ጌዴኦ ህዝብ በራህብ ይቀጡ ነው እኮ የሚባለው ተፈናቃይ የአማራ
የዩንቨርስቲ ተማሪዎች። ምን ጉድ ነው? አንድም ቀን ሊያድር የማይገባው ጲላጦሳዊ መንፈስ ነው ሥልጣን ይዞ ያለው። ርህርህና እንደምን
ይገፋል? ርህርህና ስለምንስ ጠላት ይሆናል? ደግነት ነፃነቱን ስለምን ይቀማል? ቸርነት ስለምን ጨለማ እንዲወርሰው ይደረጋል?
·
ለአማራ ህዝብ
መሪው ህሊናው ነው!
ትልቁ ተስፋዬ የአማራ ወጣቶች ያሉበትን መጠራቅቅ፣ የፊት ለፊት መከራቸውን በሚገባ አይተውታል።
ለሰከንድ ኑሯቸው ከሚሰጣቸው ግብረ ምላሽ ውጩ በምንም ነገር እንዳይዘናጉ አበክሬ እነግራቸዋለሁኝ። የአማራ ህዝብ አክቲቢስት፤ ካድሬ፤
መሪ አልፈለገም መከራውን ለመጋፈጥ። መንገድ ላይ ተቋርጦ ቢቀር በራሱ ነው ያፈረበት አታጋዩ ሁሉ የአብይዝም የሞገሳ ተጠማቂ።
በቃችሁን ብለው ለተዋቸው የአማራ ታጋዮች ሁሉ ቀኑ መዶሻ አዘጋጅቶላቸው አይቻለሁኝ። የታመሱበት
የሴራ የመፈንቅለ መንግሥት ሴራ ድርንም በጣጥሶ እና ቆሻሻ ውስጥ ጥሎ በአኃቲ ልቦና መንፈሱን በቅዱስ ድልድይ በንጽህና ገንብቶታል
አማራ ፍቱኑ።
የህልውና ተጋድሎ በዬፌርማታው የሚንጠባጠቡበት የተጋድሎ አይነት አይደለም። ህልውና ተጋድሎ ጋር
መፋታት የሚቻለው መቃብር ውስጥ ሲገባ ብቻ ነው። የእረፍት ጊዜ አያስፈልገውም የህልውና ተጋድሎ። በብቅ ጥልቅ የተቆራረጠ ተጋድሎ
የአማራ ህዝብ ዘላቂ ነፃነት አይገኝም። የአማራ ህዝብ እንደ ኩርድሾች፤ እንደ አርመን፤ እንደ እስራኤሎች መሰል ችግር ውስጥ ነው።
ይህን ደግሞ እንደ ከብት በአሞሌ ጨው እዬተታለሉ ሳይሆን፤ አማራ በሥነ - ልቦና አቅሙ ልክ መክቶ የአገር ባለቤትነቱን መረከብ ትውልዳዊ ድርሻ ነው።
ዬትኛውም ሚዲያ ያልጠራ መንፈስ ሰብዕና ካለው አቅምን ማበከን አያስፈልግም። መተው። የራስን መንፈስ፤ እንዲሁም ለሰብዕዊነት ያደሩ
ሞጋች ሰብዕናዎችን ዕድምታ ብቻ እያዳመጡ በትክክለኛው የትግል መስመር ገብቶ መፋለም ነው ይህን ጥቁር ፋሽስታዊ ዘመን።
ከሰሞኑ እኮ አቶ እስክንድር ነጋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪ እስቴዲዮም ገብቶ
እስፖርታዊ ጨዋታ ለማዬት ተከልክለዋል። አቶ ስንታዬሁ ቸኮል ታስረው እንደነበርም አዳምጠናል። ጥቁራዊ አፓርታይድ።
ባለፈው ጊዜም አቶ እስክንድር ነጋ በሰኔው 15 ቀን 2011 ዓ.ም ከባህርዳር ህዝብ ጋር እንዳይገናኝ
ነበር ያ ሁሉ ዲሬቶ የመፈንቀል መንግሥት ድራማ። አሁንስ ተገለጠ ይሆን? ከዚህም ታልፎ በአውሮፕላን ትኬት ቆርጦ አትጓዝም ተብሎ
ታግዷል። የውጭ ጠላት ቢይዝ እንኳን ይህን ያክል አይሆንም። የኢትዮጵያ አዬር መንገድ የገብያ ህጉ ዲስክርምኔሽን ሲፈጸምበት ደንበኞቹ
ሲስተጓጓሉበት ዝምታን መርጧል።
ሃሎ! አማራነት የቁም እስር ሆኗል። ከዚህ በላይ ምንድን ነው የሚጠበቀው? ምንድን?
በአገር መሬት መማር፤ መኖር፤ እስፖርት ማዬት፤ በፈለግከው መጓጓዣ የመጓዝ ነፃነት ማጣት ምንድን ነው ይሄ? ምን እንበለው? ማንስ
እንበለው? ከምንስ ይመደብ?
የሆነ ሆኖ ይህ ሁሉ መከራ እያለ „የተሻለ ሁኔታ አለ“ ለሚሉ አማራዊ ነፍሶች ገሃነም ነው ያዘዘላቸው
ታሪካዊው ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም። ለአማራ ህዝብ መሪው ህሊናው ነው እምለውም ለዚኸው ነው። ሁልጊዜም በዬዘመኑ እንደ አስደመመ ነው የአማራ ህዝብ። ለዚህም ነው በዬሄደበት እዬታደነ
ፍዳውን የሚከፍለው። የሚፈራውም። ለአማራ ህዝብ ልክ እንደ እስራኤሎች የጽዮናዊነት ጽናታዊ ትግል ነው የሚያስፈለግው። ጠንክሮ ተጋድሎውን መቀጠል ነው።
በጣም ነው የገረመኝ። በጣምም ነው የደነቀኝ። እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ነው ታዳጊ ሴቶች፤
ወጣት ሴቶች ያዬኋቸው። ነጋቸው
እዬተቃጠለ ስለመሆኑ በሚገባ ገብቷቸዋል። የአማራ ትውልድን
በጭካኔ የአቃጣዩ ተባባሪ ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰተር ደመቀ መኮነን ናቸው። ክብሪት። የጭቃ እሾኽ። ያን ሁሉ የደም አላባ ያስተናገደችው
ሰማዕቷ ባህርዳር ዝምታዋ፤ ትዕግስቷ፤ ችሎቷዋ ከዋጋ አልተቆጠረላትም። እንዲያውም በመባስ ላይ ነው ሁለመናው
የቀጠለው። ስለዚህም ታሪክ እራሱን ገለጠ።
በዚህ ህዝባዊ የቁጣ ሰልፍ ጎልምሶች ጉልህ ተሳትፎ ነበራቸው፤ ፊደላቱ ያን የውስጥ ስሜት ለመግለጽ
ፈጽመው አይችሉም። በቃን ብለዋል! ይበቃል ብለዋል! አማራነት እንዲህ እራሱን
ነፃ ማውጣት አለበት። ተስፋን ማዬት ችያለሁኝ። የአማራ ህዝብ አቅሙን ቆጥቦ ለማስተዳደር ብቃቱን አይቻለሁኝ። ከእንግዲህ
አማራ እራሱን የሚያስከብረበት ላይ ብቻ አቅሙን፤ ጉልበቱን፤ ችሎታውን መዋለ ንዋዩን፤ ማደመጡን ለራሱ የሁለመና የነፃነት ተጋድሎ ብቻ ማዋል ይኖርበታል
ብዬ አምናለሁኝ።
ግን ቂመኝነትን፤ በቀለኝነትን፤ ጥላቻን መጠዬፍ ይኖርበታል። ትውፊታችንም አይደለም። ታሪካችንም
አይደለም። ስለዚህም በዬትኛውም ሁኔታ አብረውት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን ዘብ ሊቆምላቸው ይገባል። ነቅቶ ሊጠብቃቸው ይገባል።
በጠያፉ በ ኦሮሙማ መንገድ፤ በነውረኛው አቅጣጫ አብሮ መንጎድ አይገባውም የአማራ ህዝብ። ተፈጥሮውም አይፈቅድለትም።
አማራ ትልቅነቱ መለኪያው ሰዋዊነቱ እና ተፈጥሯዊነቱ ነው። ይህ
ህገ - መንግሥታችን ነው። በሌላ በኩል የፍትህ ሰውነትም መለኪያው አሁን ነው። „በህግ አምላክ“ በመሆን መከብር ይኖርበታል። የሥነ
- መንግሥት ትውፊታችን ለእያንዳንዱ የአብሮነት ውሎ አዳር ዘብ መሆን አለበት። የሰፈር ሚሊሻ መሆን ይኖርበታል የ አማራ ህዝብ
በነፍስ ወከፍ። እነሱም የእኛ እኛም የእነሱ ነን።
አንዲትም የህዝብ አገልግሎት መስጫ ማቃጠል አይኖርበትም። የአማራ የማንነት እና ይህልውና ተጋድሉ
ምራቁን የዋጠ መሆን አለበት። ይህ ቀን ያልፋል፤ ያ እንዳለፈው ሁሉ። ትውልድ ግን ቀጣይ ነው። የ አማራ ህዝብ ታሪኩን በሙሉ አቅም
እና ችሎታው ማስቀጠል ይኖርበታል።
እያንዳንዱ የአማራ ልጅ እኔም መንግሥት ነኝ ብሎ ይህን ኃላፊነት በተግባር እንዲተባ ማድረግ
ያስፈልጋል። ይህ ውርሳችን ነው። አሁን ተመሳሳይ ድራማ የእሾሁ የቲም ንጉሡ አባላት አማራ ክልል ላይ ሊሰሩ ይችላሉ።
ያው የአማራ
ህዝብ የኦሮሙማ ጭካኔ ወራሽም እንዲሆን ይፈለጋል። አማራ ከደሙ ጋር የተዋህደውን መልካምነት፤ ቸርነት፤ ርህርሀና እራሱን እራሱ
እንዲያጠፋ ይፈለጋል። ከትውፊታችን ከወጣን እራሳቸውን በራሳችን ነው የምናከስለው። ስለዚህ በአፈጣጠራችን ቁመና ልክ መሆን ይኖርብናል።
አብዝተን እናስተውል። መንተክተኩን፤ ቱጋታውን፤ መታበዩን፤ አረመኔያዊነቱን ለባለቤቶቹ መሸኜት ነው።
የአማራ ህዝብ ለራሱ ችግር እሱ እራሱ ብቻ ነው ያለለት። ማንም የለውም ካለ ፈጣሪው፤ ካለ አላህ
በስተቀር። የአማራ ህዝብ እራሱን ሳይሸሽ በራሱ ውስጥ እንዲህ መቆም መቻሉ በራሱ የድል ዋዜማ ነው ለእኔ። ከሁሉ የኦነግን የበላይነት
ህጋዊ ለማስደረግ የተፈጠረው፤ ቃሬዛ ላይ ያለው ኦሮማራ መቃብር መላኩ የአማራ ትውልድን ተስፋ እራሱ እንዲወስንበት ያደርግለታል።
ከዚህ ቀጥሎ የአማራ ሊሂቃን፤ የጥበብ ሰዎች፤ ወይንም የሽማግሌዎች ጉባኤ ኦሮማራን ከሞት ለማነሳት
ይሞከራል። ሊከወንም ይችላል። እስግሮ ደግሞ ስቃዩን ማስተጋሻ፤ ማስትሽ ማበጀት የአብይዝም ሥር ሰደድ የሴራ ድር ነው። የአማራ
ህዝብ ይህን ሸፍጥ ከጆሮው እንዳያንጠለጥለው አብክሬ እናገራለሁኝ።
የአማራ የሥነ - መንግሥት ውርስም በህዝባዊ ሰልፉ ላይ የታዬው የጨዋነት ልክ ሁለመናን ያለመልማል።
በሰኔ 15 የ አማራ ሊሂቃን የታቀደ ጭፍጨፋ ተደሞው ታሪኩን ጽፏል። የአማራነት ቻይነት እና ጨዋነት ሁለመናው ጽናትን ይለግሳል።
ብርታትን ያጠጣል። አቅምን ያፀደያል። ተመስገን!
በትውስት አጀንዳ ሳይጠለፍ የአማራ ህዝብ እንዲህ በራስ ጉዳይ ውስጥ መከራን ለመቀበል መጠንከር
በራሱ ዓይነታ ጉዳይ ነው። ራስን ችሎ በአማራነት የመፍትሄ ተጋሪ መሆንም መታደል ነው። በአማራነት በበቃ አቅም እራስን
ዕውቅናን አስገድዶ ማሳወጅም የልቅና ልዕልና ብልህነት ነው። ተመስገን!
ልፍስፍሱን ጊዜ አትስጡት። በዬትኛውም መድረክ ብቅ ጥልቅ
ሲልም አታዳምጡት። የአማራ ህዝብ የግለሰቦች የተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሰብዕና ግንባታ ላይ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ይገባዋል
አማራ። የገደለው የጎዳው እሱ ነውና። መድከም አያስፈልግም ከራስ መንፈስ ውጪ የሰብዕና ግንባታ ለሌላ ማድረግ። ከእኔ በላይ የደከመ
የለም። መታረድ ነው ትርፉ። ይህ ማለት ግን መልካምነት ሲታይ በልኩ ማመስገን አይገባም ማለት አይደለም። ገብቶ መማገድ ግን ሙሉ
ለሙሉ መቆም አለበት።
እግዚአብሄር አላህ የሰውን ልጅ የፈጠረው አይነተኛ ዶግማዊ ጉዳይ ለምስጋና ነውና፣ አብነት ያለው
ጥሩ ነገር ለፈጸሙ የትኛውም ዜጋ፤ ተቋም፤ በአንድ ቃል ሳያጋኑ „እናመሰግናለን“ በቂ ነው። መፍትሄ ያለው ለአማራ ህዝብ በእጁ
ነው።
የራሳችን የአብን እስረኞ፤ የራሳችን ተገዳዮች፤ የራሳችን ተፈናቃዮች፤ የራሰችን ታጋቾች፤ የራሳችን የቁም እስረኞች፤ የራሳችን
ብቁዎች አሉን። እስከ አሁንም እያስገደለን ያለው የራሳችን ቤት አያፈረስን የሰው ቤት ማሟማቁ ነበር።
ይህ ደግሞ ወደፊትም ፋይዳ ቢስ መሆኑን ተገንዝቦ አቅምን ቆጥቦ በጥንቃቄ ማስተዳደር ይገባል።
ይህን ያክል አብይዝም አይቀናጣም ነበር በአማራ ትክሻ ተጽዕኖ ፈጣሪ ያደረግነው ነፍስ ሁሉ አቅም ለዚህ ገዳይ መንፈስ ባያዋጣ ኖሮ።
ሰብዕናው ጠንክሮ በጥዋቱ ሞግቱ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ የገዳ ሥርዓት ጥጋብ አይታይም ነበር። በጥዋቱ አቅም የላቸው ሁሉ ልክህን እወቅ
ቢሉት እንዲህ አማራነት በበቀል አይታረስም ነበር። ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በቅንነትም ቢሆን እነሱም ሽፋን ለጭካኔ እዬሰጡ ስለመሆን ልብ
ሊሉት ይገባል። አቅማችን እንቆጥብ። ይበቃል!
·
የአብይዝም
የሴራ ኢንፓዬር።
ዬጌዴኦ ህዝብ ታፍነው ያን ያህል ህዝብ ልክ እንደ ናዚ ዘመን እንደ ኦሾቲዝም ካንፕ በታመቀ እገታ
ውስጥ ሆነው በራህብ ሲቀጡ፤ እርዳታ እንዳይደርሰላቸው ሲደረግ፤ ከዛ በፊት እንደዛ እጅግ በሚሰቀጥጥ ሁኔታ የቡራዮ፣ የጋሞ ወገኖቻችን
ከጭፍጨፋ ነፍሳቸው ለተረፉ ለተጎዱ፤ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ለጋሱ የአዲስ አበባ ህዝብ በራሱ አነሳሽነት እርዳታ ሲያደርግ እገዳ ተጣለ።
የአዲስ አበባወጣቶች ታሰሩ፤ በአደባባይ ተረሸኑ - ሰማዕትነት ተቀበሉ። በበቀል ሁለመናው ታረሰ።
እስከ አሁንም እስር ቤት የሚማቅቁም አሉ። አዲስ አበቤ ሰልፉ ማካሄድ ከቻለ የእነዛን ምንዱባን ፎቶ ይዞ መውጣት ይኖርበታል። ግን
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቀፈቀዱ ነው ሰልፉ የሚከወነው። አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ ተላልፋ ተሰጥታለች።
የሆነ ሆኖ እነዛ ቀሪ እስረኞች አንድ ዓመት ሙሉ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ነበር። ባለቤትም የላቸውም።
ባሊህ ባይ ያጡ። ይህ አናባቢ አልቦሽ ዱዳ የኦሮሙማ ሌጋሲ ርህርህናን ተጻሮ ቆሞ፤ ጭካኔን መንገዱ አድርጎ ነው እንደ ትልቅ የስኬት
መገኛ ተደርጎ „የኢትዮጵያ የብልጽግና ጊዜ ነው። የኢትዮጵያ
የብልጽግና ጊዜ ነው።
የብልጽግና ጊዜን ማቆም የሚችል ኃይል የለም።“ እዬተባለ „ብልጽግና“ ሲደለቅ
ሲሰማ ምነው ፍርድህ ዘገዬ ያሰኛል። እርህርህና ማዕቀብ ሲጣልበት ምን ሊባል ይችላል? የሰው ልጅ ለሰው ልጅ እርዳታ ቢሰጥ ምንድን ነው ነውሩ? ምንድን ነው ኃጢያቱ? እዛ ተንገላተው፤
እዛ ተገፍተው፤ እዛ ተጎሳቁለው ንብረታቸውን ሳያነሱ ባዶ እጃቸውን በፒጃም ህይወታቸው ተርፎ፣ ሁሉን ነገር ተቀምተው ወንዶች የሴቶችን፤
ሴቶች የወንዶችን ልብስ ተውሰው ነፍሳቸውን ይዘው ሲገቡ ባሊህ ባይ የላቸውም በባህርዳር ከተማ በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና። እንኳንስ
ሊንከባከቧቸው የሚረዷቸው ነፃነት ተነፈጉ። ይህ የሚከወነው ቃሬዛ ላይ ያለው በብአዴን ነው።
እንጉልቻሙ ብአዴን ለደላው ጃኖ ሲያለብስ፤ ተክሊል ሲደፋ ይገኛል። እነሱን ከዛ አስቀምጦ እርዳታ
የሚደርጉላቸውንም ጻድቃንን አግዶ ጥምቀት የከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የካባ እና የፊርማ ሥርዓት እንደ ታቦት ተከብክበው ይከውን
ነበር ጎንደር ላይ። ግፉን እዩት። እነዚህ አይዞችሁን የተነፈጉ ምንዱባን የተጠጉት ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ነው። ይህን ያዬ ወገን
ያለውን ሲሰጥ ደግሞ ይከለከላል።
በዚህ መንፈስ የዓለሙን ቀይ መስቀልማህበረሰብ The Internation Red Cross
Society፤ የዓለሙን የጤና ድርጅት World Health
Organization:( WHO) ፤ የአለሙን የህጻናት መርጃ ድርጀት The United Nations Children's Fund (UNICEF) እና ሌሎችም ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እስከ ዓላማቸው ይክሰሉ፤ ይቀበሩ እዬተባለ ነው። የተቋቋሙበት መሰረታዊ ዓላማ ርህርህና ነው። ይህን ነው መሞገት ያለበተ ለህዝብ ቁሜያለሁ የሚል የፖለቲካ ድርጅት ሆነ „እኔ ሰው ነኝ“ የሚለው መንፈስም። ለዚህ ነው እኔ የሶሊዳሪት ትግል ያሰፈልገዋል የምለው።
ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ የተግባር ክህሎት ይጠይቃል። ይህን ጭራቃዊ ጉዞ መልክ ለማስያዝ። ለነገሩ እኛ „ለሰብዐዊ መብት አለተደራጀንም“ የሚሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችንም ሰምተናል። „ኮሽ ባለ ቁጥር መግለጫ አናወጣምም“ አለበት እኮ። ይህንም ኢሰባአዊ አቀቋምም ጆሮ አልሰማም አይልም። ሰምተናል። ይህንንም ተስፋ አድርገው ሲከበክቡ የሚታዩ ሰዎች አሁን ላይ ውጭ አገር ሳይቀር እያዬን
ነው። እኩሌታ መደመር። ለምን አይጠቃለሉም።
የሆነ ሆኖ 50% ሴቶች የካቢኔ አባል መሆን በዓዋጅ በዓለም አደባባይ በተነገረላት አገረ ኢትዮጵያ?
ሴት ፕሬዚዳንት በሆነባት አገረ ኢትዮጵያ? ለጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ሴት የፍትህ ቁንጮ በሆነባት አገር ኢትዮጵያ? „ለተባረከች
አገር የተባራከ ትውልድ“ በቀዳማይ እመቤት ቢሮ በዓለም መድረክ በሚፈላሰፉባት፤ ቃል ተገብቶ፤ „ዴሞክራሲ ነፃና ፍትኃዊ ምርጫ“
በሚቀነቀንባት አገረ ኢትዮጵያ? የሴቶች የህፃናት እና የወጣቶች ሚኒስተር ባለባት አገረ ኢትዮጵያ? የወጣት ልጆች መንፈስ እንዲህ
በበቀል ሲወቀር፤ ሲፈለጥ፤ ሲቀጠቀጥ፤ ሲሰነጠቅ ዝምታ ውርዴትም ውርዴም ነው።
የሴት ሊሂቃን ቀሚሱ እንዴት ተዋህዶ፣ እንደምንስ ተስተካክሎ እንደሚለበስ እራሱ ይከብዳል? ለመሆኑ
ሴት ሆኖ ጭካኔን እንዲህ እያዩ ማለፍ ልጅ ያወጣልን? ቀንበጥ ወንድ ልጆችም አሉ የታገቱ። ለወላጅ ሴት ሆነ ወንድ ልጅ እኩል ነው።
ይህን ያህል አረመኔያዊነት፤ ይህን ያህል የሰዋዊነት ቅጣት፤ ይህን ያህል ለተፈጥሮ ጭካኔ ከዬት
ነው የሸመቱት የኦሮሙማ ሊሂቃኑ? ከዬት ነው የተማሩት አቶ ደመቅ መኮነንስ? አሁን በዛች አገር ትውልድ እንዴት ሊገናባ ይሆን?
ይህን እያሰብኩኝ የባጀውን የወግ ገባታ ክምር ሲሰላ፤ ሲመዘን ከንቱ ክሰላማ
ይሆንብኛል።
በዚህ ጭካኔ ውስጥ ትውልድ እንዴት የአደራ ቤተኛ ሊሆን ይችላል? ሞጋሳ፤ ገዳ፤ ኦሮሙማ ትውፊታችን እስከዚህ ድረስ
ነው የሚመነጥረው የመንፈስ ማረፊያዎችን ሳይቀር ርህርህናን - ትህትናን - መተዛዘንን - አብሮነትን - ቸርነትን - ፍቅርን -
እኛዊነትን። ለዚህም ነው እኔ ጉዳዩ „የፈረቃም፤ የተረኝነትም፤ የወያኔ የመተካካትም አይደለም ከዚያ ያለፈ ነው“ ነው የምለው።
የፖለቲካ ሙጉቱም እጭ ላይ ነው ያለው እምለውም ለዚህ ነው። የሚያጽናናው የፖለቲካ ሙግቱን ሳይሆን
ኑሮውን እዬኖረ ያለ የአማራ ህዝብ ከአምክንዮ ቁንጮው ላይ ነው።
ይህ እጅግ በጣም እጅግ የሚየበረታታ ነው። አብነቱም አንቱ ነው። እጬጌ ነው። ለዚህ ነው ባለፈው የ50በ60 ያረጠ ፖለቲካ ስጽፍ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ስለመኖሩ የኢትዮጵያ
ፖለቲካ አያውቀውም ያልኩት። ይህን ስለሚተላለፍም ነው ዳጥ ውስጥ ሄዶ የሚቀረቀረው ራዕዩ ሁሉ።
ማህራዊ ንቀተ ህሊና በራሱ ጊዜ ለምቶ የሚፈናዳ ጉዳይ ነው። ከእንግዲህ የአማራን የማንነት እና
የህልውና ተጋድሎ አክብሮ ተነስቶ ጥያቄዎቹን መፍታት ካልተቻለ መጪው ጊዜ ይከበዳዋል ከላይ ከላይ፤ መታበዩ ጫን የሚያስተነፍሰው
አነባቢ አልቦሹ ዱዳው የአብይዝም
የኦሮሙማ ሌጋሲ ሰደከበተ SDKBT። ባባዶ ተኮፍሶ እንደ ጎማ እዬተነፋፋሰም ነው። ተነባቢ ለመሆን አናባቢ ያስፈልገዋል።
ያ ደግሞ ድርቅ የመታው ነው። የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የ22 ወራት ጉዞ ይሄው ነው ዱዳ የኦሮሙማ ሌጋሲ ጉጉል መንገድ።
·
ሰውነት።
የሰውነት ፍልሰት በመንፈስ ይታያል ኢትዮጵያ ላይ። ለፖለቲካ ድርጅት፤ ለሲቢክስ ድርጅት፤ ለሃይማኖት
ተቋማት፤ ለመንግሥት አካላት፤ አገር ካለ ሰው ምንድ ነው? ህንጻው መዋቅሩ ድርሳኑ አንቀጻቱ ምን ይሰራሉ ስለማንስ ነው የተጻፉት?
በዬጊዜው የሚዘጋጀው ያፓርቲ መመሪያ ቀላጤስ?
ሰው የሌለው ቤተክርስትያን፤ ሰው የሌለው መስጊድ፣ ሰው የሌለው የፖለቲካ ድርጅት፤
ሰው የሌለው የሃይማኖታዊ ስብከት፤ ሰው የሌለው መዋቅር፤ ሰው የሌለው መንግሥት፤ ሰው የሌለው አገር? ምን ይባል? ሰው የሌለበት
ቅዱስ ወንጌል እና ሰው የሌለበት ቁራዕንስ ለማን ተፈጠሩ? ለማንስ ያገልግሉ? ማንስ ይተርጉማቸው? ሁሉም መንኮራኩር ውስጥ እዬተናኮሩ
እንኩሮ ሆነው እንዳሉ ነው የሚሰማኝ።
ሰው ሆነህ የርህርህና ነፃነትን አግደህ፤ ደግነትን ኮርኩመኽ „ትበለጽጋለህ“ የመግደያ ፈንጅ ነው ለእኔ „የጨረቃው ቤት የብልጽግና ድርጅት 50በ60 ደመነፍስ
ቅኝት። አካልን ብቻ ሳይሆን የመኖር መንፈስን የሚጻረር የሚያርድም።
እንዴት የሰው ልጅ የራሱን ያለችውን አካፍሎ ለማደር ስለምን ይከለከላል? ሃጤያተኛ እንደኛም
ሁኑ እኮ ነው። በጭካኔ ውስጥ ከትሙ። ይህን ሁሉ መከራ በህዝብ ላይ እንዲፈስ የፈቀደው ግርባው ብአዴን፤ ጉልት ድንጋይ፤ አምልኮተ
ጣኦት አድርጎታል አናባቢ አልቦሹን ዱዳው የአብይዝም ኦሮሙማ ሰደከበተ SDKBT። መንገድ የለሽ፤ አቅጣጫ የለሽ ፍልስ ትልም። ግርባው ብአዴን
ይህም ማዕረግ አድርጎ ሲሳለመው፤ ሰጊድ ለኪ ሲል፤ የጸጋ ስግድት ሲሰግድለት ውሎ ይመሻል፤ መሽቶ ይነጋል።
·
እርገት ይሁን።
እኔ የሚገርመኝ ህዋሃትን ያን ያህል ታግለህ፤ በዛው ማንፌሰቶ ሠራሽ ህገ - መንግሥት ውስጥ
ተጥደህ፤ በዛው መዋቅራዊ አደረጃጀት እዬተንከበከብክ፤ በዛው የሙት መንፈስ ዕራይ እዬዳነስክ „እኛ ብንሆን እምንሠራውን እዬሠራ
ነው ስለምን እንቃወማለን“ ብለህ ደግሞ ትኮፈሳለህ። ማረጥ። የሚበረታተው ጨካኝ መንፈስ አማራን ስለቀጠቀጠ መንገድ ተገኜ ተመስሏል።
ነገ ሁሉም ተራውን ጠብቆ ይደርሰዋል።
የሆነ ሆኖ ብስል ከጥሬ፤ ጮርቃ ከእሸት፤ ፍሬ ከሰብል ለይቶ የሚያውቀው የአማራ ህዝብ ልኩን
አሳይቷል። በነፍስ ወከፍ ማንዘርዘሪያውን ቤተኛ በማድረጉ እያንገዋለለ በራሱ ሃቅ ዙሪያ የሃሳብ ብርቱ ሃዲድ ፈጥሯል። ተመስገን!
አማራ መሆኔን በክብር እወደዋለሁኝ! ለሙሉ ሰውነት ያሳጣኝ አንዳችም ነገር የለምና ስለምንስ
አማራነቴን እሸሸዋለሁኝ? አማራነቴ ማዕርጌ ነው። አማራነቴ ውስጤ ነው። አማራነቴ ከአውራው ማንነቴ ከኢትዮጵያዊነት የሚቀዳ ደሜ
ነው። በአማራነቴ እና በኢትዮጵያዊነት ያለው ድልድይ ዕውነት እና እኛዊነት ብቻ ነው።
በእኔ ህሊና ውስጥ በአማራነቴ፤ በጸሐፊነቴ፤ በአደራጅነቴ እና በሴትነቴ ያለው ማንነቴ በሰብዕናዬ
ልክ እኩል የዕውቅና ጸጋ አላቸው። እኔ፣ እኔን መሆን ከተሰናው በጊዜ እኔ፣ እኔን ማሰናበት ይርብታል። አማራነቴ በመገፋቱ ውስጤን
በጽናት አቅም ይገነባዋል ያፋፋዋልም።
·
መፍቻ።
ጢንብራ … በግንባር ክንብል ማለት
በራስ ሳይሆን በግንባር መቆም።
አማራነት ህላዊነት!
አማራነት ህሊናዊነት!
አማራነት እራሱን በራሱ ነፃ ማውጣት አለበት!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ