የዶር አርከበ ዕቁባይ ሦስት ዓመት ልባም ጥሞና ለስኬት።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

 

·       ዶር አርከበ ዕቁባይ ሦስት ዓመት ልባም ጥሞና ለስኬት።

 

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠበቂ

በከበቡሽ የቁራሽ አንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 

„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።

 



·       ዕዶተ ጠባቂ ማናቸው አጀንዳወች ይለፍ የሚሰጥ ዕልፍኝ።

ዶር አርከበ እቁባይ የተመደ UNIDO ከመጨራሻወቹ ሦስቱ እጩወች አንዱ መሆናቸው ተደምጧል።

የተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ተቋም UNIDO በዳይሪክተርነት ለመመራት ነው የታጩት። ዕንቁ ዕድል ነው።

ለጭምት ፖለቲከኛ ይህ ከዕድልም በላይ ነው የሰማይ ስጦታ። አክብረው፤ ጥሞና ወስደው ሊቀበሉት ይገባል። ጸጸትንም ሊመግቡት ይገባል። ለፈጣሪ ከሳው ያ ነውና። እያንደንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊትም መልዕክትም ይዞ ይወለዳል የምለውም ለዚህ ነው።

የአፍሪካ ህብረት አህጉሩን ወክለው እንዲወዳደሩ በእጩነት እንዲቀርቡም ወስኗላቸዋል። ከጀርመን እና ከቦልቡያ ጋር እኩል ተወዳዳሪ ናቸው ዶር አርከበይ እቁባይ ኢትዮጵያን ወክለው።

·       እጬጌው ሂደት የቤት ሥራ።

ነገስ ዛሬ ፈቅዳ እና ወዳ በሥሞ ኢትዮጵያ ለምትሳጣቸው ይህ ሰማይ ጠቀስ ክብር ውለታዋን ይመልሱ ወይንስ ውለታ ቢስ ይሆኑ ይሆን? እጬጌው ሂደት ይመልሰው።

ልዕልት ኢትዮጵያስ አመድ አፋሽ ወይንስ ሞገስ አፋሽ ያደርጓት ይሆን?

በጭንቋ፤ በመከራዋ፤ በመከፈቷ፤ በልጆቿ ዕንባ ለሁሉም እኩል ደራሽ፤ ተቆርቋሪ ይሆኑ ወይንስ ይክዷት ይሆን? የእናት ኢትዮጵያ ጥቃት አውጪ ወይንስ ተበቃይ ይሆኑ ይሆን?

ጭምትነታቸው፤ ስክነታቸው ለራሳቸው ሰብዕና? ለድርጅታቸው ተልዕኮ? ወይንስ ለሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ክብር? በሳቸው አደብ ውስጥ ጽላት የሆነው አምክንዮ ምን ይሆን? ሥልጣን? ታዋቂነት? ሰውኛነትን ማገልገል? ተፈጥሯዊነት እራስን ዝቅ አድርጎ ማክብር? ፈርኃ እግዚአብሄርነት? ግን ሃይማኖት አላቸውን? 

መልካምነትን ይገፉት? ደግነትን ይገፈትሩት? አዛኝነትን ያስከፉት? አጽናኝነትን ፊት ይነሱት? ይቅርታ ጠያቂነት ይርቁት? የትኛው ይሆን የማግስት መደባቸው? ዕድሉ የፈጣሪ ታምር ነው።

ህወሃት እንዲህ ዘነዘናውን በአገር ወስጥ በቆመበት ወቅት እሳቸው ከዛ ድርጅት ተገኝተው ለዚህ ክብር ሞገስ እና ልቅና መድረስ ገድል ነውና ይህን ዕድል እንደምን እያስተናግዱት ይሆን?

ከሳቸው የሚበልጡ፤ የሚሻሉም፤ አቻ የሆኑም ያላገኙት የማያገኙት የጠራ ሰውኛ ዕድል ነውና በጸሎት፤ በሱባኤ ቢቀበሉት ጥሩ ነው። የማይገኝ ዕድል ነውና። ግን ኢትዮጵያ ከዚህ ስታደርሳቸው ምኔ ነው የሚሏት ይሆን?

ለልዕልት ኢትዮጵያስ አብልታ፤ አጠጥታ፤ አስተምራ፤ አሳድጋ፤ በተለያዩ ዕድሎች አፋፍታ ለዚህ ያበቃች እናት ምድር ኢትዮጵያ ለውለታዋ ያቀዱት ነገር ይኖር ወይንስ ከዛው ዞጋዊ ቅርቃር ውስጥ ሆነው ሉላዊ ተልዕኮውን ያስተናግዱት ይሆን?



·       ይህ እንዴት ሆነ?

የሰከነ ህሊና የሰጣቸው ጸጋ ነው። ሦስቱን ዓመት ሙሉ ገብር አልገብርም በህወሃት እና በኦህዲድ የነበረው ፉክክር ጦርነት ከፍቶ ዓለም እራሷ በነገረ ትግራይ ተጠምዳበታለች ከምል ሌላውን ሉላዊ ኃላፊነቷን ሁሉ ርግፍ አድርጋ ትታ ይህን ስታሳሳ፤ ስታባዝት፤ ስትፈትል፤ ሸማ ስትሰራ ውላ ታድራለች። የዘመኑ የተግባር ሰሌዳዋ ሆኗል ነገረ ትግራይ።

ለትግራይ ይህ ዘመን የምጻት፤ የማት ዘመኑ ነው። እሳቸው ደግሞ አርምሞ ውስጥ ነው የባጁት። እጅግ የበዛ ጠንቃቃነት እና ቁጥብነት አይቻለሁኝ። ዓላማ ያለው ሰው ሊሆን የሚገባው እንዲህ ነው።

በዚህ ውስጥ የእናት ኢትዮጵያ ቦታ ቁርጭምጭሚት ላይ? ሻኛ ላይ ወይንስ ቋንጃ ላይ? ወይንስ የህሊናቸው ቤተ - መቅደስ የት ናት የኢትዮጵያ አድራሻ በሳቸው ሰብዕና ውስጥ? ጽላታቸው ወይንስ ማገዷቸው? ይህን ተጠያቂነት እና ኃላፊነት እንደምን ያስተናግዱት ይሆን?

·       ሁለቱ መታበውያን ፉክክር እና ጦርነት።

ከጫካ እስከ ቤተ - መንግሥት አማካሪነት የደረሱት፤ በተለያዬ ኃላፊነት የሠሩት፤ በአንድ ወቅትም የኢትዮ አፍሪካን መዲና አዲስ አበባን የመሩት {ከንቲባ} ዶር አርከባይ እቁባይ የሁለቱ መታብያን ፉክክርን እልፈኝ ብለው ባጅተዋል።

ሁሉንም የመገፋት፤ ግልምጫም ቢኖር፤ መጠላትም ቢገጥም በመቻላቸው ዋጥ አድርገው ይዘው ረጅሙን ጥሪያቸውን ሊያሳኩ ጫፍ ላይ ደረስዋል። ግንቦት 7 ያህል ጸረ ህወሃት፤ ጸረ ትግራዋይ፤ ጸረ ሰሜን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞችን ግልምጫ ችለው ይኸው ለቁንጮነት ደርሰዋል። ሉላዊ ሽልማቱንም አግኝተዋል። ሉላዊነት የመሪነት አቅማዊ ክህሎትም ታጭተዋል።

አይቶ እንዳላዩ፤ ሰምቶ እንዳልሰሙ በማለፍ ነው እዚህ ደረጃ የደረሱት። ዶር አብይ አህመድን ሁሉን እኔ አውቃለሁ፤ ሁሉንም እበልጣለሁ ዥንጉርጉር፤ አሳቻ፤ አሽሙረኛ፤ መሰቃኛ፤ ትዕቢተኛ መሪ ጋር አይደለም አብሮ መሥራት እኛ በርቀትም እንኳን እሳቸውን ለማድመጥ ምን ያህል ሸክም እንደሆነብን ይታወቃል። እሳቸው ግን ቻል አድርገው ሙያ በልብን ሰንቀው ይኸው ለሉላዊ ታላቅ ኃላፊነት እና ታላቅ ተጠያቂነት እጩነት ላይ ደረሰዋል።

የሚገርመኝ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ህወሃት አመድ ሆኗል፤ ተበትኗል ባዶ አድርገነዋል ጉራቸው ነው። የዓለምን ጤና ሚኒስተር የሚመራው የህወሃት መንፈስ ነው። ዶር ቴወድሮስ አዳህኖም የተገኙት ከህወሃት ነው። እሳቸውን ለኖቤል ሸልማት ያበቃቸው የህወሃት ህገ - መንግሥት ነው ኢህአዴግ ነው።

አሁንም የሚመሩበት፤ የሚተዳደሩበት በዛው በህወሃት ማንፌስቶ ሠራሽ ህገ - መንግሥት ነው። መትነን፣ ብን ማለት፣ እርሾ አልቦሽ ሲኮን ነው። ህወሃት ደርግን እንደዛ ቢል ያምርበታል። መራራው ስንብት እርሾ አልባ ነበር። ደግሞ ማገገም አልቻለም። ልቻል ቢልም ተቀባይነት የለውም።

ህወሃት ግን አሁንም መንፈሱ ያሰተዳድራል፤ ይመራል፤ ያተራመሳል፤ ያጫርሳል። ከእነሱ  ርዕዮት ውጪ ነፍስ ዘርቶ አለን የሚሉት አንዳችም ነገር የለም ኦነጋዊው ኦህዴድ።

አንድ ሰው ከተፎካካሪዎች ጋር ቆሞ ሞግቶ የሚረታ አላገኙም። ለምን? የህወሃት ተጠማኝ ስለሆኑ። አሁንም ህወሃት ርዕዮቱ ገዢ ነው። ካድሬውም፤ አንጠፊውም፤ ሻይ ቡና አፍይ ረዱም ሁሉም በህወሃት መንፈስ ነው እዬተገዛ ያለው ግንቦት 7 ጨምሮ እዬተነዳ ያለው።

·       ዶር አርከባይ ጥልቅ የቁጥብነት ሚስጢርነት ምን መማር ይቻላል?

በተለይ እንደ አብን ያሉ ወጣት ድርጅቶች ከዶር አርከበ ዕቁባይ ጭምት ሰብዕና፤ ቻይ ሰብዕና፤ ጨዋ ሰብዕና፤ ብልህ ሰብዕና፤ ቁጥብ ሰብዕና ቁጭ ብለው ሊማሩ ይገባል።

ኦህዴድ አንድም ቀን ትህነግ ብሎ መግለጫ አውጥቶ አያውቅም። አብን ግን ሲለቀልቅ ውሎ ያድር ነበር። ፈቅዶ እና ወዶ ጭቃ ውስጥ ተዘፍቆ ቅራኔ ሆይ! ናልኝ ወደ እኔ ብሎ ሲደክም ነበር።

የቅራኔ አያያዝ ሂደቱ ግርም ይለኝ ነበር። ሲመለከትህ ምርጫ የለም። በማይመለከትህ፤ ተጠዬቅ ባልተባልክበት ሄዶ መቀርቀር ግን የብልህነት የደም ማነስ ነው። ይህን በተጽዕኖ ፈጣሪዎች ላይም እማዬው ነገር ነው። የማያገባህ ነገር ሲነገርህ ስማው ግን አታዳምጠው። ሄደህም አትማገድለት።

ካለ ጥሪው ገብቶ መማገድ እጅግ በጣም የበዛ ጅልነት ነው። ግርባው ብአዴን ህወሃት መንፈሱ ስለሚያባንነው፤ ስለሚያስበረግገው ሥራ ፈትም ስለሆነ ይለቅልቅ።

ይገርመኝ የነበረው የአብን ነበር። ስለሆነም ትልቅ ማገር ሊሆኑ ሚችሉት፤ ተስፋ ያደረጉትን የኢትዮጵውያን ልብ በብዙ ሁኔታ አጥቷል አብን። ረቂቅ ስለሆነ ሊያው አይችልም። ይኑር ብቻ መባል እና መኖሩ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት ተስፋ ነው መባል አንድ አይደለም።

ድንጋይ ልሳን አውጥቶ መናገር ቢቻል አውሮፓም፤ ስሜን አሜሪካም ያሉ ድንጋዮች ሳይቀሩ ስለ ትግራይ ፕሮፖጋንዲስት በተሆነ ነበር። ይህ ሁሉ ሆኖ ዶር አርከበይ እቁባይ ትንፍሽ የለም። ህወሃት በጠራቸው ጊዜም የተመካከሩት ባይታወቅም አልሄዱም። ለምን? ዓላማቸውን ያወቁ ግባቸው ለመድረስ ዊዝደምን ስለሰነቁ ስለታጠቁም።

 የሦስት አመት የሰክነት፤ የጭምትነት፤ የመቻል ተጋድሎ ለፍሬ እዬበቃ ነው። መታጨቱ በራሱ ድል ነው። እንዲህ ዓይነት ሰብዕናወች ኢትዮጵያዊነት ከዋጡ ያጓጓሉ። እሳቸው በኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸው አቅም አሁን ላይ ይህ ሊሆን ይቻላል ብዬ መተንበይ አልችልም።

ያደጉት ከህወሃት ጋር ነው። ህወሃት ደግሞ ጸረ አማራ፤ ጸረ አርቶዶክስ ተዋህዶ፤ ጸረ ኢትዮጵያ ነውና። ቅይጡ ነገር ግን ህወሃቶች እራሳቸውን ተጻረው መፈጠራቸው ነው። ሌሎች ጸረ ስሜነኛ እና ጸረ ስሜን ፖለቲካ ናቸው እነሱም ያን ነው የሚያራምዱት። ለራሳቸው መጥፋት 40 ኣመት በላይ ኳተኑ። ይኸው ተመልሰው ሽምቅ ተዋጊ ሆኑ።

ዛሬም ሚዳያወቻቸው፤ ፕሮፖጋንዲስቶቻቸው ብቻ ሳይሆን ዓለምን በተሳሳተ መንገድ በመውስድም ከትናንቱ በባበሰ ሁኔተ ሳይጸጸቱ በጸረ አማራ ትርክታቸው ቀጥለውበታል። ዕድሜም ውድቀትም የማያስተምረው ድርጅት ነውና ህወሃት።

ሰው ለመሆን መንገድ ያልጀመረ ድርጅት። በዚህ ውስጥ የዶር አርከበ እቁባይ መፈተኛ ጊዜ አሁን ሳይሆን ዓለም አቀፉን ውድድር አሸንፈው ቦታውን ከያዙ በኋላ በሚኖራቸው የተግባር መሰመር የሚታይ ይሆናል።

የቀደመውን የሆነ ሁሉ መከራ ይክሳሉ ወይንስ ጨምረው ይበድላሉ? ይጸጸታሉ ወይንስ ይበቀላሉ?ይቅርታ ይጠይቃሉ ወይንስ ይታበያሉ? እጬጌው ሂደት ይመልስው።

እኔ ቅን ሴት ስለሆንኩኝ ጊዜ ሰጥቶ ማዬቱ ነው ምርጫዬ። አሁን አይደለም በቀደመው በደል ስለ አማራ እና አማራነት ቀርቶ የወጡበት ማህበረሰብ ለከት ያጣ በደል ላይም የበዛ ቁጥብ ናቸውና።

ዝምታቸው አስፈሪ ቢሆንም ለስኬታቸው መሆኑ ስለሚገባኝ። ምክክርም ይኖርበታል ብዬ አስባለሁኝ። እሳቸውን አንስቶ የሚያብጠለጥል የለም።

አቶ እስክንድር ነጋን በደቦ ሲያብጠለጥል የነበረው ሁሉ የልቡ ደረሰ መሰል አቶ ገለታው ዘለቀን ንክች አያደርግም። ብዙ ዓይነት ቡፌ ነው በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚታዬው። አደብ እና ማስተዋልን ይጠይቃል። ለክልፍልፍ ፖለቲከኛ አይሆንም የኢትዮጵያ ፖለቲካ።    

·       እንደ ሥርጉተ ዕይታ ዶር አርከበ እቁባይ ያሸንፋሉ ብዬ አስባለሁኝ።

 

(1)          ትግራይ ተጎዳች ብሎ ያስባል የዓለም ህዝብ ስለዚህ እንደ ካሳ ሊቆጠር ይችላል።

(2)          ክህሎቱም፤ ልምዱም፤ የበዛው ጭምትነቱም በቂ ነው።

(3)          ሦስት አይበገሬ ባላዎች አሏቸው። የአሜሪካው ነጩ ቤተ - መንግሥት ላይ ሁለት አንቱ ባላ አላቸው እና የዓለም የጤና ድርጅት አስኳልም አላቸው።

ብዙ ሰው ህወሃት በሎቢስቱ አማካኝነት አሸነፈን የሚሉ አሉ። ሺ መካች እያላቸው ምንም የሎቢ ሰው አያስፈልጋቸውም። ህወሃት ልባም ነው። ድርጁ ተግባር ነው የሰራው።

የትምህርት ሥራ ውጤት በቅርብ ጊዜ አይታይም። ግን ህወሃት ብዙ በጣም ብዙ ሥራ ሠርቷል በ27 ዓመት ውስጥ። ብድሯ ኢትዮጵያ ነበረች ነገረ ትግራይ ደግሞ አውራ።

የተንጠራራ ትምክህቱም ያ ነበር። በውጩ ዴፕሎማሲ ዘርፍም መሰረት ያለው አቅም ነበር የገነባው ህልሙ ለ100 ዓመት ነበርና። ብዙ ህሊናዊ ተግባራትን ከውኗል።

እንዲያውም እልህ እና ማንህሎኝነቱን ትቶ የወልቃይት እና የጠገዴ ጉዳይን ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ወደ ባለርስቱ ካሳ ከፍሎ መልሶ ቢሆን ኖሮ ነቅናቂም አልነበረውም።

የአህጉሩ ሪኮመንዴሽንም የዓለም ጥቁር ህዝቦችን ቀልብ የመሳብ ጣዕም ይኖራዋል ብዬ አስባለሁኝ።

·       የጨመቱ ሰብዕናዎች ዕውቀት ካከሉበት ግባቸው ቅርብ ነው።

ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እጅግ ከለፍላፋ ናቸው። ቁንጥንጥ ናቸው። አድብ የነሳቸው ናቸው። ጥጋብ አይችሉም። እናም  በአንድ ጊዜ ፈልተው ተንተክትከው ላፍታ በረዶ ሆኑ። ዓለም መሰከረ ያሉት የሳሙና አረፋ ሆኖ ዓለም መሰከረብን፤ አገለልን ብለው ደጅ ጥናት በዬቦታው ልከዋል።

ሳይታዩ ታመኑ፤ ታይተው ተነኑ። ለምን ጭምት አይደሉም። አደብ የላቸውም። አቅል የላቸውም። የበታችነት፤ ስሜታዊነት፤ ፋንታዚነት፤ ቂም አርግዞ በቀል ፈልፍሎ ተፈጥሮን መቀጥቀጥ ላይ በፍጥነት ተጉበት እንሆ በዓለም የተጠሉ፤ የተወገዙ ዓለም የተጠዬፋቸው ሆኑ። ከሄሮ ወደ ዜሮ ወረደው ተነኮቱ።

በውነቱ ለእኔ ትዳርም የላቸውም። ባለቤታቸው ብልህ ቢሆኑ ብዙ በጣም ብዙ ነገር ሊያድኗቸው ይችሉ ነበር። ከአውሬነት ወደ ተፈጥሯዊነት ሊመልሷቸው ይችሉም ነበር። ዓለም እንዲህ ሲጠዬፋቸው ቁሞ ለመሄድ ይከብዳል። እኔ ጌጡንም ልብሱንም ሳይ ሙት መንፈስ ለብሶ የሚሄድ ነው የሚለስለኝ። ምክንያቱም ሰው ጠላህ ማለት እግዚአብሔር ጠላህ ማለት ነውና።፡

ለዛውም በጨካኝነት፤ በአራማዊነት። ሎቱ ስብኃት ነው። ቁጥር አይደለም ጉዳዩ አንዲትም ሴት ትሁን በባዕድ ወታደር እንዲህ ክብሯ ሲጣስ መንፈሷ ሲደቅ፤ ህፃናት ወላጅ አልባ ተብትነው ሲቀሩ ሴትነት? እናትነት? ሚስትነት ምንድን ነው ትዳሯን፤ ባሏን ካልቀጣች በሰባዊነት አግባብ? በራህብ እንዲህ ከደቡብ እስከ ስሜን ከጌዴኦ እስከ ትግራይ ሲቃጣ የሰው ልጅ ትዳር ምን ይባል? 

የሆነ ሆኖ ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ዶር አርከበ ዕቁባይ ሁሉን ችለው፤ ሁሉን ታግሰው፤ ሁሉንም መዝነው በማስተዋል ተጉዘው፤ ከህወሃት ተገኝተው፤ ክህወሃት ጋር ሠርተው፤ እራሳቸውም ህወሃት ሆነው እንሆ ለሉላዊ ኃላፊነት እጩነት በቁ። ጭምትነታቸው ግን ለሲዊዝ ይመጥናል። ሲዊዝ እጅግ የጨመተች አገር ናት። ቀስ ላሉ ለሰከኑ ሰወች ሁሉ ህይወት የሆነች።፡

·       ይገርመኛል

ሁሉ ያላቸው ሰዎች በማይመለከታቸው ጉዳይ ዘው እያሉ ክብራቸውን፤ ጥሪያቸውን፤ መክሊታቸውን፤ ጥሪታቸውንም ሲያጓጉለት አያለሁኝ። በሚያገባቸው ጉዳይ እንኳን፤ በሚመለከታቸው ጉዳይም እንኳን ዘውታን በዶር አርከበይ እቁባይ አላዬሁም። ጨመቱ። ሰከኑ። ታቀቡ።

ራሳቸውን ገዙ። እናም እዚህ ደረሱ። ግንቦት 7 እዬለ ከዚህ መድረስ ቀላል ተጋድሎ እንዳይመስላችሁ። ብዙ መሰናክል ነገር ይሞክራል። እሱን አሸንፎ እዚህ መድረስ ከባድ ነገር ነው። ግን ቻሉ።

አንድ የአማራ ሊቅ ግን ይህን ማድረግ አይችልም። ለዚህ ቦታም አማራ ሆኖ ቢሆን ቢሞክረው አይቻለውም። ዶር አንባቸው መኮነን ቦታውን ይመጥኑ ነበር።

አይደለም ለግሎባል ኃላፊነት ለአዲስ አበባ ከንቲባነት አትመጥንም ተብለው በተንሳፊፊነት የሚቻለውን ያህል በዶር አብይ አህመድ ተቀጥቅጠው ከዛ ክልልህ ሂድ ተብለው በጥይት ተደብድበው ነው የተገደሉት።

ለነገሩ እነሱም ቁጥብ አይደሉም። ንግግር ላይ ሊጠነቀቁ የሚገቡት ብዙ ነገሮች ነበሩ። የአቶ ምግባሩ ህልፈት አዲስ አበባ „የኗሪወቿ ናት“ ማለታቸው ነበር ለሞት የዳረገው።

ይህ ጥያቄን ዶር አርከበይ እቁባይን አልተጠዬቁትም። እንዲያውም ቅርብ ጥያቄ ሊሆን የሚገባ ለሳቸው ነበር ከአቶ ምግባሩ ይልቅ። የአዲስ አበባ ከንቲባ ስለነበሩ። ሁሉን እንዲሸከም የሚፈለገው ግን የአማራ ሊቃናት ወይንም የአማራ ህዝብ ነው። ማገዶነቱንም ግማዱንም። 

ከጦርነቱ ማግሥት ጀምሮ በአማራ ጋዜጠኞች፤ በአማራ ጦማርያን፤ በአማራ ጸሐፍት፤ በአማራ ሊሂቃን፤ በአማራ አክቲቢስቶች ላይ፤ በአማራ ሊቃናት ላይ ማት ነው የሚፈሰው።

„በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት“ ሆኖ። አንድም የተጋሩ ልሳን በዶር አርከበይ ላይ፤ በዶር አረጋይ በርኽ ላይ ምንም ሲል አይደደመጥም። ቢልም እንደ አማራ በጥላቻ ተሞልተው ማቱን አያፈሱም፤ ቦንቡን አያዘንቡትም።

የሚገርመው ዕውነት ለሆኑ አመክንዮች እምንተጋ እያለን ነው አብረን አምንወቃው። እነሱ አንዲትም አቅም ለአማራ አያዋጡም። እንደ እኛ እናታቸው በአራስ ቤት አላበደችም እና።

እኛ ግን እንሱ በተፈጠሩበት ስላልተፈጠረን ማዕከላዊ በሆነ ሁኔታ ተጎድተንም፤ ጉዳታችን ቻል አድርገን ጸረ ሰውነትን፤ ጸረ ተፈጥሯዊነትን ተዋግተናል፤ ታግለናል። ተግተናልም። ምንም እንኳን ለክሬደት ብለን ሳይሆን ሰው መሆን መቻልን ጠንቅቀው ወላጆቻችን አስተምረው ስላሳደጉን። አስተዳደግ ይወስናል። በአስተዳደግ አልተበደልነም።

ጦርነቱን ፌስቡክ ላይ ፊት ለፊት ወጥቼ ነበር ያወገዝኩት። ከጦርነት በቀል እና ቂም እንደሚታፈስ ስለማውቅ። ይህም ሆኖ ዘለፋውም፤ ቦንቡንም አብረን ነው የተቀጠቀጥንበት።

ምስጋናው ቀርቶ። ጦርነቱን የደገፉት፤ ህግ የማስከብር ነው ብለው ያጀቡት፤ አብያዊ አብርሃም ሊንከን የናፈቃቸው ደግሞ ጃኬታቸውን ቀይረው አብረው ተባባሪ አብይዝምን፤ ሻብያዝምን ረጋሚ ሲሆኑ ተሞጋሽ ተመስጋኝ ሆነው አያለሁኝ።

ሚዛን የለሹ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከትናንት እስተዛሬ ይኽው ነው። ሌላው ቀርቶ ልሳና ህወሃት ኢትዮ ፎረሞች፤ አውሎን ጨምሮ አማራወች ናቸው አዘጋጅ እና አቅራቢ።

አቶ ልደቱ አያሌው ሞታቸውን የመረጡት ዕውነት ባሉት ነገረ ትግራይን ስለወገኑ ነው። ኢንጂነር ይልቃልም ሲብጠለጠሉ የባጁት በዛው ጉዳይ ነው። እውሩ የህወሃት ደጋፊ እና ድርጅቱ ደግሞ እነሱ እንኳን አሉ የለም።

አማራ እያለ፤ የኣማራ ሊቃናት እያለ፤ አልፎ ተርፎም የአማራ ህዝብ እያለ አብሮ ሲቀጠቅጥ ውሎ ያድራል። የሚገርመኝ ቃላት ምርጫው ነው። ለእስሳት የማይሰጥ ቃላት ነው ስንሸለም የባጀነው። እኛ ደግሞ ከቋሚ ሰውኛ ተግባራችን ዝንፍ አላልነም። እነሱ ያርግርጉ።

·       ሞክራሲ።

አቶ አርከበ ዕቁባይ ዴሞክራሲ ለሚባለው መርኽ ተገዝተው አይቻለሁኝ። በድምጽ ብልጫ ከተመረጡት መሪያቸው ሥር ሆኖው ለመሥራት ፈቅደዋል። ይህ ታላቅነት ነው እንጂ በሲነሪትም፤ አሁን ባዬሁት ስክነትም ዶር አርከበ ዕቁባይ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ይበልጣሉ። አሳምረው ይበልጣቸዋል። አይመጣጠኑም።

ግን ሳይታበዩ፤ እልኽ ሳይጋቡ፤ ሳይፎካካሩ የውሰኔውን ድመጽ አክብረው እዚህ ደርሰዋል። ይህን መሰል ብቃት በዶር ደሳለኝ ጫኔም አይቻለሁኝ። ሁለቱንም በዴሞክራሲ ፍላጎት አፈጻጸም እና ተገዢኒት እኩል ጥራት ያለው ብቃት አይቻባቸዋለሁኝ።



እርግጥ ነው እንደዛ ለተሽቆጠቆጡት ለዶር አንባቸው መኮነን ግን የዶር አርከባይ ላይ የታዬው ታገሽነት በዶር አብይ አህመድ የለም። ሊዮዋቸው አልፈለጉም ጨረሷቸው።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ዴሞክራሲ ፈለግከውም // አልፈለግከውም፤ ወደደድከውም // አልወደደክውም፤ የብዙኃን ድምጸ ውሳኔ መቀበል ግድ ነው።

ስትቀበለው በጎሬጥ አይተህ ሳይሆን፤ አሽሟጥጠህ ሳይሆን፤ አጣጥለህ ሳይሆን ደስ ብሎህ ወደኽው ለአሸናፊው ሃሳብ መገዛት፤ አሸናፊው ሃሳብ ለስኬት እንዲበቃ መትጋት ነው።

የራስህን ሃሳብ ብቁ አድርገህ ለማውጣት የቀረህን የቤት ሥራ እንዳለህ አስበህ ለዛም ጎን ለጎን መትጋት ነው ዴሞክራሲ። ዴሞክራሲ ከደምህ ጋር ሲዋህድ ቲም መሪም የመሆን አቅምህ እንደመስታውት ፍንትው ብሎ ይታያል። አሁን ለእኔ ዶር አርከበ እቁባይ ለተመድ ድርጅት UNIDO ቲም ሊደርነት ብቁ ሆነው ነው የሚታዩኝ። ለመመራት የፈቀደ ለመምራት አይቸግረውም እና።

·       ልከውነው።

ቁምነገሩ ትውልዱ ከዶር አርከበይ እንቁባይ ምን ይመራል ነው። ትውልዱ ብቻ ሳይሆን አቅም ያላቸው ተጽዕኖ ፈጣሪወችም ከሳቸው አብዝተው ሊመሩት የሚገባ ጉዳይ በማያገባቸውም /// በሚያገባቸውም ጉዳዮች ላይ ማስተዋልን መመገብ እንዳለባቸው ነው። ወርቅ ከቀለጥ ይፈሳልና። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

14.06.2021

መቻልን የሰነቀ ጥረት ለግብ ያበቃል!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።