የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ዕጣ ፈንታ በዬኔታ ጎደና ያዕቆብ ዕይታ በዕድምታ። 27.08.2021


የዕውነት የኔታ የሆኑት የኔታ ጎዳና ያቆብ ስለ አማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ የ እኔም የውስጥ ዕንቁ ዕይታ ነው እና ጹሑፉን በንባብ ሳቀርበው በሐሴት ነው። የኔታ ጎዳና ያቆብ በፖለቲካ ሳይንስ፤ በሥነ ሃይማኖት፤ በሥነ ፍልስፍና፤ በ አገር ውስጥ ደህንነት ከባችለር እስከ ማስተርስ ዕወቀት ሰላላቸው ብቻ ሳይሆን ከችግሩ ውስጥ ስለሚነሱ ይመሰጡኛል። 

ከሁሉም በላይ ለሁሉም የማህበረስብ ከፍል እኩል መሆናቸው ውስጤን ያረጋጋዋል።ዕውነትን መወገናቸው፤ መርህን የ እኔ ማለታቸው፤ ለተበደሉ መቆማቸው ይጨርስላቸው እንጂ ኢትዮጵያን እናፍቃት ዘንድ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ከፍተውልኛል። እናም በጥሞና አዳምጣቸዋለሁኝ። በ አክብሮት እከታተላቸዋለሁኝ። 

ዛሬ ላይታዬኝን ቢችልም ነገ ጎዳና የሚባል ትውልድ እንድናፈቅ አድርጎኛል። ዘመኑ ትውልዱ ያሳስበኛል። እረኛ እለቦሽነቱ፤ ብክነቱ እኔ ያለፍኩበት ድካሜ ሁሉ፤ ይቅርብኝ ብዬ ያሳልፍኩት ወርቅ የወጣትነት ጊዜዬ ሁሉ ብዙ ወጣቶች እንዲህ እንደ እኔ እንደሚሆኑ ሳስብ ይከፋኝ እና እንዲህ አዲስ የምህንድስና ተስፋ ሳይ ተስፋዬ ይረጋጋል። ነገን አስብ እና እጽናናለሁኝ። እኔ እዬደከመኝ ነው። ግን ለነገ የሚሆን የ ዕውነት ስንቅ በ እኒህ ሊቀ ትጉኃን አዬለሁኝ። እናም ተስፋዬ ሽልማት እንዳገኜ አስባለሁኝ። 

የደከመኝ ሰዓት ቢሆን ትንሽ ልደከም ብዬ ጹሑፋቸውን ለዛሬ 10/15/20 ዓመት እንዲህ በንባብ ሰርቼ አስቀምጣለሁ። አንድ ቀን  ኢትዮጵያ እናቶች ጎዳና የሚባል ልጅ ይኖራቸዋል። ልጆቻቸውን በጎዳና ሥም ይጠሩ ይሆናል ማን ያውቃል። ጎዳና የሚባል ትውልድም ይናፍቀኛል። ተስፋ ... ሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር .... 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።