"የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!" ፀሐፊ ቢኒያም መስፍን

ንኳን ወደ ከቡሽ ብሎግ ላም ጡልኝ።

 


 

·      #ወሳኝ ፋክት። ህሊና ላለው የዕውነት ቅንነት።

·       

በመጠነ ሰፊ ሼር ይደረግ። ይተርጎም በባለሙያ። አስቀምጡት። ትልቅ መፀሐፍ ይወጣዋል።

የትናት እና የዛሬ ፈተና ፈተና እንዳይመስላችሁ። እስኪ በቃኝ እሽት አደረገኝ። አሁን በስንት ድካም ጨረስኩት። አንድ ፁሁፍ ጀምሬ። ከባድ፣ ውስብስብ ነበር። እንኳንስ በጀርመንኛ በአማርኛ ለመፃፍም።

ቢያንስ መረጃውን በጭብጥ ማቅረብ ፅንሰ ሃሳቡን ግድ ይላል። የወልቃይት የጠገዴ ጉዳይ የኢትዮጵያን ዕድል ይወስናል የሰማዕታትን ዋጋ ያዘክራል።

አሁን ጎልጉል ላይ ያገኜሁትን አያይዣለሁኝ። የምትችሉ በእንግሊዘኛ ተርጉሙት። እባካችሁ። የሚገርማችሁ ሱር ኮንስትራክሽን፣ አይጋ ፎረም ለካ የማሰቃያ ቦታወች ዕውቅና የተሰጣቸው ናቸው።

ፀሐፊ አቶ ብንያም መስፍንን ከልብ አመሰግናለሁኝ። ጎልጉል ድህረ ገጽንም።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

20/07/2022

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

"የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!"

ፀሐፊ ቢኒያም መስፍን

በኲር ሐምሌ 11 ቀን 2014 . ዕትም

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

https://www.goolgule.com/15-concentration-camps-of-tplf.../

July 18, 2022 03:13 pm by Editor 1 Comment

በሕወሓት ማጎሪያና ጭፍጨፋ እስር ቤቶች የተፈፀመው ዘግናኝ ታሪክ እንደ ሚከተለው ይቀርባል። እንደ አቶ ገብረ መድኅን ገለፃ በወቅቱ ሕወሓት ሓለዋ ወያነ (የወያኔ እስር ቤት) ወይም 06 (ባዶ ሸድሸተ -ባዶ ስድስት) ብሎ በማቋቋም በተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ማጎሪያና ጭፍጨፋካምፖችነበሩት።

እነዚህን የማጎሪያና የጅምላ የመጨፍጨፊያካምፖችየመሰረተው ህቡር /ኪዳን በሚባል ታጋይ (በኋላ በስኳር ኮርፖሬሽን ግዥ ክፍል ቡድን መሪ እና የሕወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን አባል ሆኖ ሲሰራ የነበረ) ነው፡፡

አቶ ገብረ መድህን አርአያ እያንዳንዱ እስር ቤት (ሓለዋ ወያኔ 06) የተቋቋመበት ዓላማ የወልቃይት አማሮችን በጅምላ ለመፍጀትና የሕዝቡን መሬት ለመንጠቅ፣ ሕወሓትን የሚቃወሙ የትግራይ ተወላጆችን ለመግደል እንደሆነ ያብራራሉ። የግለሰቡ ገለፃ እንደሚከተለው አጥሮ ይነበባል።

የአማራ 30/40/50 Jahren Gnozide እውቅና የማይሰጠውም ለዚህ ነው። ከአለም ዋና ዋና ዜናወች ውጭ ነው። እውነቱን ሢረዱት ሁሉም ይጸጸታል። የአሜሪካ መንግሥት ይሁን፤ የአውሮፓ ህብረት። በተሳሳተ መንገድ ላይ ነው ያሉት።

1) ፃዒ ሓለዋ ወያነ tsai halawa TPLF

ይህ የማጎሪያና የመግደያካምፕበትግራይ፣ ዓድዋ ልዩ ስሙ ማይ ቂንጣል በሚባል አካባቢ የተመሰረተ ነው። እስር ቤቱ ከምድር በታች የተሰሩ 150 ክፍሎች አሉት። ቤቶችም ሶስት ሜትር ከመሬት በታች ተቆፍረው የተገነቡ ናቸው። በእያንዳንዱ እስር ቤት 100-150 ሰዎች ተጨናንቀው እንዲታሰሩ ይደረጋል። በእነዚህ ማጎሪያዎች ሰዎች የሚገደሉት በድደባና በጢስ በማፈን ነው።

ይህ እስር ቤት በዋነኝነት የወልቃይት አማሮችን ዘር ለማጥፋት ታቅዶ እንደተገነባ ይገለፃል። በዚህ እስር ቤት በተከናወነው የግድያ ዘዴ እስከ 1973 . ድረስ ወደ 15 ሺህ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ተገድለውበታል።

2) ዓዲ መሐመዳይ ሓለዋ ወያነ adi mehamdaye halewa TPLF

ይህ ማጎሪያና መግደያ በትግራይ ሽሬ አውራጃ ልዩ ስሙ ሽራሮ በሚባል አካባቢ የተገነባ ነዉ። በዚህ ማጎሪያ ከመሬት በታች የተገነቡ ብዙ የእስር ቤት ክፍሎች እንደነበሩና ታሳሪዎች ደግሞ በሙሉ የወልቃይት ጠገዴና ጠለሞት አማሮች (ወንዶች፣ ሴቶችና ሕጻናት) ናቸው።

ማጎሪያው በወንዶች ብልትና በሴቶች ጡት እስከ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝን ክብደት ያለው ነገር በማንጠልጠል ግፍ ይፈፀምበት የነበረ ነው። እስር ቤቱ አርባ አምስት ጠባቂዎች ወይም ገዳዮችን ያካተተ ነበር። በዚህ ግፍ በተሞላበት የእስረኞች ማጥፊያ ብዙ ሺህ አማሮች በጅምላ ተጨፍጭፈዋል።

3) ወርዒ ሓለዋ ወያኔ werie halewa TPLF

እንደ አቶ /መድህን ኣርዓያ ገለፃ ይህ እስር ቤት በትግራይ፣ ዓጋመ አውራጃ ልዩ ስሙ ኣዴት በሚባል አካባቢ የተመሰረተ ሲሆን ዋና አላማውም የቀድሞ መንግሥት ሠራዊት ምርኮኞችን ለመግደል ታልሞ የተፈጠረ ማጎሪያና መግደያ ነው። በእዚህ እስር ቤት ግድያ ይፈፀም የነበረው በኪኒን መልክ በሚሰጥ መድሃኒት፣ በጋለ ብረት ሆድን በመተኮስና ያበዱ ውሾች በሚገደሉበት ሳይናይድ በተባለ መርዝ ነበር። ይህ እስር ቤት እስከ ሰባት መቶ ሰባ የሚደርሱ የቀድሞ መንግሥት ወታደሮች የተፈጁበት ነበር።

4) ቡንበት ሓለዋ ወያነ Buenbte halewa TPLF

ይህ እስር ቤት ሕንፍሽፍሽ ፈጥራችኋል የተባሉ የሕወሓት ታጋዮች 1969 . የተፈጁበት ነው። ይህ እስር ቤት ሰላሳ ገዳይና ጠባቂ አባላት ነበሩበት።

5) ሱር ሓለዋ ወያኔ ይህ ማጎሪያ እና መግደያ ስሙ ከቡንበትነት ወደ ሱርነት የተቀየረና በትግራይ፣ ሽሬ አውራጃ ልዩ ስሙ ሸራሮ አፅርጋ በሚባል አካባቢ የሚገኝ አደገኛ እስር ቤት ነው። በዚህ እስር ቤት ሁለት በሁለት ካሬ ሆነው ከመሬት በታች ተቆፍረው በተሰሩ ክፍሎች እስረኞች ይታሰራሉ። በአንድ ክፍል እስከ 200 ሰዎች ይታሰሩበት ነበር። በዚህ እስር ቤት ከአስር እስከ አስራ አምስት ሺህ በላይ አማራዎች በግፍ ተፈጅተውበታል።

6) ዓዲ በቕሊዒት ሓለዋ ወያነ adie beqeletie halawa TPLF በእዚህ እስር ቤት ግድያ የሚፈጽመው በመርዝና በሚስጥር በሚሰጥ መርፌ ነው።

7) ዓይጋ ሓለዋ ወያነ Ayega Halawa TPLF

የራሱ ታሪክ ያለው፤ ለወልቃይት ጠገዴ ቅርብ የሆነና ብዙ የዚህ አካባቢ አማራዎች የተፈጁበት እስርና መግደያ ቤት ነው።

ባህላ ሓለዋ ወያነ Bahele Halawa TPLF

ይህ እስር ቤት የትግራይ አርበኞች እና የወለቃይት ጠገዴ አማሮች የተፈጁበት ነው።

9) ፍየል ውሃ ሓለዋ ወያነ Feyele wehaa halawa TPLF

ይህ እስር ቤት በወለቃይት ጠገዴ የሚገኝ ሲሆን 15-20 ሺህ አማሮች የተፈጁበት ነው።

10) ግህነብ ሓለዋ ወያነ gehenebe Halawa TPLF

ይህ እስር ቤት ማይ ገባ አካባቢ በቃሌማ ወንዝ ዳርቻ የሚገኝ ሲሆን 200 የጉድጓድ እስር ቤቶች የነበሩበትና አብዛኛው ጨለማ ቤቶችን ያካተተ ሲሆን ሟች ራሱ መቃብሩን የሚቆፍርበት ነው።

በእዚህ እስር ቤት አብዛኛው እስረኛ በጨለማው ምክንያት የሚታወርበት እንዲሁም የሴቶችና ወንዶችን ብልት በመተኮስ የሚገደልበት ነው። ብዙ ሺህ የወልቃይት አማራዎች እንደተገደሉበት ይገመታል። በዚህ እስር ቤት 1969-83 . እስከ አርባ ሺህ የሚገመቱ የወልቃይት አማሮች አልቀዋል፡፡

11) ዓዲ ጨጓር ሓለዋ ወያነ adie Chegwara Halawea TPLF ይህ እስር ቤት ብዙ አማራዎች እና ፀረ ሕወሓት አቋም የነበራቸው የትግራይ ተወላጆች የተገደሉበት ነው። 1970 ዎቹ መጀመሪያ ሕንፍሽፍሽ(ትርምስና ማደናገር) ፈጥራችኋል በሚል ታጋዮች የተገደሉበት እስር ቤት ነው።

12) በለሳ ማይ ሓማቶ ሓለዋ ወያነ Belesa maye Hamto Halawa TPLF ይህ እስር ቤት በትግራይ ዓድዋ አውራጃ ገርሑ ስርናይ አካባቢ ልዩ ስሙ ዕገላ በተባለ ቦታ የተመሰረተ ነው። ብዙ የወልቃይት አማራዎች እንዲሁም ፀረ ሕወሓት አቋም የነበራቸው የትግራይ ተወላጆች የተገደሉበት ነው። እስር ቤቱ ሃያ አምስት አባላት የነበሩት ገዳይ ነበረው።

በዚህ እስር ቤት እስረኞች የሚመረመሩት በግርፋት፣ በእሳት እና የጋለ ብረት በማቃጠል፣ አስተኝቶ ከግንድ ጋር በማሰር (ራቁትን) በወንድ ብልትና በሴት ጡት አሸዋ በማንጠልጠል የሚከናወን ነበር።

እስከ ሚያዝያ 1972 . ድረስ በአረጋዊ በርሄና ስብሀት ነጋ ፍርድ ሰጭነት 153 የትግራይ አርበኞች፣ 232 ታጋዮች ህንፍሽፍሽ ፈጥራችኋል የተባሉ እንደ እነ ወርቅ ልዑል፣ ግራዝማች ታደሉ የመሳሰሉት የተገደሉበት ነው። ሟቾች በአንድ ጉድጓድ በጅምላ የሚቀበሩበት እስር ቤት ነበር።

13) ዓዲ ውእሎ ሓለዋ ወያነ Adie Welo Halawa TPLF

በዚህ እስር ቤት ብዙ ሺህ አማራዎች ተገድለዋል፡፡

14) ዓስገራ ሓለዋ ወያነ asegra Halawa TPLF

ይህ እስር ቤት በአፋር ክልል አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ብዙ ዜጎቻችን የተፈጁበት ነው።

15) ማርዋ ሀለዋ ወያነ Marewa Halwa TPLF

ይህ እስር ቤት ዓድዋ ገርዑ ስርናይ ኸውያ አካባቢ የሚገኝ እስር ቤት ነው። Consnetration camp Ye dugenie

የዱጋ ዱግኒ ማጎሪያ ማሰቃያና ግድያ ካምፕ ይህ ማጎሪያና ማሰቃያ (concentration camp) በቀድሞ የሽሬ አውራጃ አስገደ ወረዳ ዱጋ ዱግኒ ቀበሌ በሚገኘው ተራራ ስር ከመሬት በታች በሁለት ሜትር ጥልቀት ተቆፍሮ የተሠራ እስር ቤት ነው።

የስቃዮች ሁሉ ማማ በሆነው በዚህ የማጎሪያና መጨፍጨፊያ እስር ቤት በምሽግ መልክ የተሰሩ በርካታ ክፍሎች ሲኖሩት በአንድ ክፍል 70-80 ሰዎች ተጨናንቀውና ተፋፍገው ያለመኝታ ወይም በፈረቃ በመተኛት ስቃይንና ሞትን የሚጠባበቁበትና የወልቃይት ጠለምትና ጠገዴ ኢትዮጵያውያን አበሳ፣ ስቃይና የሞት ፅዋ የጨለጡበት ነው።

ይህ ማጎሪያ፣ ማሰቃያ እና በጅምላ መግደያ 1972 . ጀምሮ ግፍ ሲፈፀምበት የቆየና በተለይ 1976 . ጀምሮ ለሁለት ዓመታት 3500 የሚልቁ የወልቃይት ወንድና ሴት ሽማግሌና ህፃናት ዜጎቻችን የማቀቁበት በጣት የሚቆጠሩት ከመትረፋቸው በስተቀር አብዛኛዎቹ በስቃይ ተገድለው ሬሳቸው ወደ ገደል የተወረወረበት ነው።

ወያኔ የወልቃይትን ሕዝብ በገፍ ከፈጀ በኋላ ስልጣን ሲቆጣጠር ደግሞ የአማራን ርስት ወደ ራሱ ጠቅልሏል፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል አሁን ወልቃይት ወደ ቦታው ተመልሷል፡፡ ሕውሓት ከማይደራደርባቸው ጉዳዮች መካከል የወልቃይት ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልጻል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ አማራውስ በወልቃይት ይደራደራል?

በኲር ሐምሌ 11 ቀን 2014 . ዕትም

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።