ህም! እባከወት ዴሞክራሲን ካለ ቦታው አያንገላቱት።

ህም! እባከወት ዴሞክራሲን ካለ ቦታው አያንገላቱት።
 
 
ለኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ለቲማቸው የተፃፈ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 


 
 
ሰሞኑን በነበረው ብሄራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት
ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ስለ ዴሞክራሲ አንስተዋል። መክፈቻ ሥርዓቱ በበላዩ ላይ ሲከረቸም ተሰማኝ። ሰቀጠጠኝም። ዴሞክራሲ በእናንተ ቤተ መንግሥት ምን እና ምኑ ነው? ነውር የሚባሉ ግድፈቶች አሉ።
ይኽኛው ግን ከነውርም የከፋ ነው። ለዛ ብንታደል አራት ዓመት የሰብል ዘመን በሆነ ነበር። ያዬሁት የጠፋው ትውልድ መልሶ ሲጠፋ ነው። 
 
ብዙ በጣም ብዙ የተገብርንበት ተግባር የኦነግ መጫወቻ፣ መንጨባረቂያ፣ መሳለቂያ ነው የሆነው። ይህም ሆኖ ትውልድ ተርፎ ቢሆን ድካሜ የቆጥ የበረከት በሆነ ነበር። ግን ዳጥ እና ምጥ ሆነ በረከታችን።
ያጣናው እንጂ የጨመርነው፣ የተነቀልንበት እንጂ የበቀልንበት አንድም አመክንዮ ዬለም። ዛሬን መሥራት ይቻላል። ትናንትን፣ ከትናንት በስቲያን ግን ማምጣት አይቻልም። 
 
ከመካከለኛው ዘመን የቀደሙ ትውፊት ትሩፋታችን ሁሉ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ከሥር ነው ነቀላ እዬተካሄደ ያለው። ጥንታዊነት በቢላርድ የማይገኝ የመንፈስ ኃብት ነበር። ዘመኑ ግን አሰደደው። ፈገፈገው። ጋጋጠው። 
 
እዛው የፓርላማ ጉባኤ ላይ ሃሳብ፣ ተጨማሪ አጀንዳ አንቀበልም ተብሎ ማንጓጠጡን አላዩም? አራት የአብን የፓርላማ ተወካዮች ጉባኤውን ትተው ሲወጡ አላስተዋሉም? 
 
ወይንስ እሳቸው ዬዚህን ጊዜ ሰርክ ቄራ፣ ሊኳንዳ ቤት የተከፈተለትን የአማራ ህዝብ መንግሥታዊ ፍጅት አላዬሁኽም፣ አልሰማሁህም ለማለት ወደ ኡራኖስ ወደ ተጓዙበት ሂደት ይሆን የተፈፀመው።
 
ለመሆኑ በሸንጓቸው ለምን ቀድሞ ጥያቄወች ለሳንሱርድ እንደሚላኩ ሊነግሩን ይችላሉ? እዛች አዳራሽ ተግባራዊ መሆን የተሳነውን ግዙፍ፣ ስልጡን ጽንሰ ኃሳብ እንደዛ አምጥተው ካልሆነ ቦታ፣ ባልሆነ ጊዜ ሲቀረቅሩት ደነገጥኩኝ። ቢያንስ ክብርት ሆይ በዝምታ ይተባበሩን?
ዴሞክራሲ ኢትዮጵያዊ ውስጥ በህልም እንኳን ማዬት አይፈቀድም። እንኳንስ ህይወት ሆኖ አኗኗሪ ሊሆን ቀርቶ። የቅልጣንም፣ የቅብጠትም ዓይነት አለው። 
 
ስለ ምርጫው ከሆነ ታላቅ ሙሁር፣ የሴቶች ሊቅ ስለሆኑ ሞገድ ጋዜጣ ልበወለድ ተፈፃሚ ሆኖ ነው ምርጫው የተከናወነው። ይህን በጀርመንኛ ለምርጫ ግሎባል ኤክስፐርቶች ሁሉ ጽፌዋለሁኝ።
 
ለነገሩ የገዘፋ ፖለቲከኞች ሳይቀሩ በሰላም ተጠናቀቀ ብለው አመክንዮውን ሲያንቆላብሱት አዳምጫለሁኝ። ከዛ በፊት ቀውስ ተደራጅቶ፣ ቀውስ ተፈጽሞ፣ ህዝብ በስጋት የተቀቀለበት፣ ህዝብ በፍርሃት ደመመን የተዋጠበት ሂደት ከቁጥር አልገባም?
#ምርጫውን አሸናፊ ተሁኖ የተወጣበት ሚስጢር በጭልፋ፣
 
1) ስለምን የአማራ ክልል ሊሂቃን ተፈጁ?
2)ስለምን በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ታለመ?
3) ስለምን አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ተሰዋ?
4) ስለምን ዘዋይ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣ አጣዬ፣ ሽዋ ሮቢት ነደዱ? ጭፍጨፋስ እንደምን ተካሄደ?
5) ስለምን ቡራዩ ጭፍጨፋ፣ ለገዳዲ ለገጣፍ
6) ስለምን የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ታገቱ?
ስለምን የፖለቲካ መሪወች ታሠሩ?
9) በሙሉ ሎጅስትክስ በጫካው የኦነግ ክንፍ ሰርክ የሰው ልጅ የእርድ ቄራ ቤት ተከፈተ
10) ስለምን እንደ አሸን የፈላው የመንግሥት ደጋፊ ሚዲያ ከምርጫው በኋላ ሟሙ?
11) ስለምን ሚዲያ አይባቃን ያሉ ሰብዕናቸው ዛሬ ተሰበሰቡ?
12) ስለምን በተገኜው የስብሰባ ሂደት በደንበር ዘለል፣ 13) በድንኳን ሰበራ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የማስፈራራት፣ የሊቃናትን የማቃላል የዲስኩር ድርድር ሰማን?
13) ስለምን ጠቅላይ ሚሩ የአማራ ክልልን መፈናፈኛ ነሱት?
በዚህ ጫና ውስጥ ያለፈ፣ ያለ፣ የሚኖር ማህበረሰብ ሌላ አማራጭ እንዳያይ፣ በስጋት ተወጥሮ ተፈጥርቆ ተይዞ ነበር ምርጫ የተከወነው።
14) አሸናፊው ደንብ የሌለው፣ ፕሮግራም የሌለው፣ መሪ ዕቅድ የሌለው። ፖሊት ቢሮ የሌለው። ሥራ አስፈፃሚ የሌለው። ጠቅላላ ጉባኤ ያላካሄደ በምርጫ አሸነፈ ማለት የዴሞክራሲ ስቅለት ነው ለእኔ።
 
ለዛውም ተዘቅዝቆ። ሻሸመኔ የሰው ልጅ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ፣ ተከቦ ሲሳቅበት እንዳዬነው ዕውነተኛ ትዕይንት። ምን ያላዬነው አለ? በዚህ አሳንጋላ ዘመን። 
 
ዬተመረጠው የቁጥጥር እና የኤዲቲንግ ኮሚሽን የሌለው። ተጽዕኖ ፈጣሪወችን ሰብስቦ አሸናፊ ፓርቲ ሆኖ ወጣ። አንድም ቅንጣት የፖለቲካ ድርጅት የአደረጃጀት፣ የአመራር መርህ የሌለው፣ በስማ በለው በዳቦ ሥም "ብልጽግና" ብሎ እራሱን ሰይሞ ተመረጠ።
ይህ ማለት ይሆን ዴሞክራሲያችሁ? ወይንስ ዘግይቶ በተካሄደው ጉባኤ ፕሬዚዳንቱ አስመራጭ ኮሜቴ ሰብሳቢ ሆነው እራሳቸውን ጠቁመው፣ በራሳቸው ላይ ድምጽ ያሰጡትን የአንዳለጠኝ ፖለቲካ? ኧረ በህግ አምላክ? ለነገሩ ፍትህ ሚኒስተርን የፌድራል ፖሊስ ነው ለካ የሚያዘው። 
 
የእድር ያህል እንኳን አቅም የለውም ዬምርጫው ሂደት። በአራቱ መዓዘን ጭንቀት ተዘርቶ፣ ጭንቀት በቅሎ፣ በጭንቅ የተከወነ መሆኑ ላይበቃ ተመራጩ ደግሞ የጨረቃ ፓርቲ። ይህ ውሽልሽል ሂደት ዴሞክራሲ ሳይሆን #አናርኪዝም ነው።
 
ቀድሞ ነገር በውራጅ አባላት፣ በትውስት አካላት የፖለቲካ ድርጅት ተመሥርቶ አያውቅም። ታሪክ ይህን አስተናግዶ አያውቅም። የኢህአዲግ ውራጅን ለብሶ ዴሞክራሲ? አሁንም ከህወሃት ጋር ድርድሩ ይኽው ነው። ውልቁን ወታትፈን አብረን እንቀጥል። ይህ ነው ዝክንትሉ ገመና። ይኽን የተሸከመ አካል ስለ ዴሞክራሲ ማንሳት መብቱ ሊሆን ባልተገባ ነበር።
 
#አደራ መብላት።
 
ይቅርታ ጠይቃችሁ ምህረት ላደረገ ህዝብ አደራውን ቅርጥም አድርጋችሁ በልታችኋል። ወልዳችሁ፣ ከብዳችሁ፣ አስተምራችሁ፣ ቀለብ አቅርባችሁ እንዳሳደጋችሁ ሁሉ በሃሳብ የተለዬውን ሁሉ ጋዜጠኛ፣ አክቲቢስት፣ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች፣ ንቃት ያላቸውን ሰርክ እያሠራችሁ የገቢ ማስገኛ የጉልት ገብያ ፕሮጀክት ያደረጋችሁት ውልቅልቁ ሂደት ዴሞክራሲ እንበልላችሁ ይሆን? ለአንድ እስረኛ ዋስ እስከ 100ሺህ ብር ልቅምጥ ታደርጋላችሁ። ይህ ደግሞ ሌላው ዬዘረፋ ዓይነት ዬተፈቀደለት። 
 
አራቆታችሁት። በዘበዛችሁት። መዘበራችሁት። ለዚህ ማባረጃ የሆነ ትሪኪ ፊልም ደግሞ ይኖራል። የድሆችን ቤት መጠገን። ጥቅሉ ዝርክርክ ተግባር መጋረጃው ይህን መሰል ወዘተረፈ ትርኪ ምርኪ ነው። ትርፋ ከኪሳራው ያመዝናልና።
 
ሞገድ ልበወለድ ጋዜጣ ወንጀል ያቅዳል። ለዕቅዱ 5 ሚሊዮን ሊፈጅ ይችላል። ወንጀሉ ሲፈፀም እና የሞገድ ጋዜጣ ሲወጣ እኩል ይሆናል። ጋዜጣው እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ ይችላል። ይህ ነው የአራት ዓመቱ ትወና። 
 
ዴሞክራሲ የሃሳብ ነፃናት ነው። ሥልጡን ነው። አሸናፊው ሃሳብ ገዢ ነው። ለሃሳቡ ግን ሰፊ መድረክ ይሰጠዋል። ይብላላል፣ ይበስላል። ሰሞኑን በተመድ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን የፀደቀ የአጥኚ ቡድን የዓንድ ዓመት የማረዘም ጉዳይ ነበር። ልዩነቱ ጠባብ ነበር። ግን በድምጽ ብልጫ አለፈ። ስለዚህ በአባል አገሮች በአልደገፋትም፣ በተዕቅቦ ባሉት አገሮችም ተፈፃሚ ይሆናል።
 
ቢመርም፣ ቢጎመዝዝም። አውሮፓ ህብረትም ጫን ያለ ሪዞልሽን አሳልፏል። ሁሉም በኢትዮጵያ ላይ ነው። በአባላት አገሮች በቀጥታ ተፈፃሚ ይሆናል። በኢትዮጵያ ተፈፃሚ ዬሚሆነው ጉዳዩ ተመድ ላይ ቀርቦ ከፀደቀ ነው። ለምን? ኢትዮጵያ የተመድ አባልም መሥራችም አገር ስለሆነች። 
 
ይህ ሂደት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ማዕቀፍ የማይታሰብ ነው። አቅል ዬለም፣ የቀደመ፣ ጠቃሚ ሃሳብን የማክበር፣ የመቀበል ቀርቶ በራሱ ጊዜ እንዲንቀሳቀስ ትፈቅዳላችሁን ጥያቄ ለኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ነው?
 
አይደለም ዴሞክራሲ ስለ ሰባዕዊነት ማሰብ አይፈቀድም። ለሰው ልጅ ማዘንም አይፈቀድም። አይዟችሁ ማለትም አይፈቀድም። ወንጀል ነው ያስከስሳል፣ ያሳስራል፣ ያሳፍናል፣ ያስገድልላል፣ ዬሰው እርድ በዓይነት ነው። በተለይ አማራ፣ ወጣት፣ ተወዳጅ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆነ ስንብት ነው። በስውር ብዙ እማይታወቁ በህብረ ብሄራዊ ባዕላት ደምቀው ዬሚታዩ ወገኖች ዋጋ ከፍለውበታል።
 
ለመሆኑ ዬ21ኛው ምዕተ ዓመት የኪነ - ጥበብ በአራት አመቱ በዘመነ አብይዝም ትንፋሹ አለን? ማነው ተዋናዩ? ስንት ተጽዕኖ ፈጣሪ ተፈጠረ? ዴሞክራሲ መብቱስ አለው ኪነ ጥበብ? ይህ ሁሉ ማት እዬወረደ ዝምታው የመርግ ያህል ሆኖ ስለማይ።
 
ዬባሰ ሊመጣ ይችላል። መካች የሃሳብ አቅም ስለማላይ። ግን በሕይወት ዘመኔ እንዲህ ዓይነት አሳቻ ዘመን፣ አሰቃቂ የመርዶ ዘመን አላዬሁም። በተነን። ድሮ እኮ አንድነታች እራሱ ተፈሪ ነበር። አሁን ግን አለመተዋወቃችን ዘመን ሰጠው። በዚህ ውስጥ ዴሞክራሲን እባካችሁ አታንገላቱት። ተፋታችኋል። ተለያይታችኋል።
 
#ሩህ እና ሂደቱ። እንደ መከወኛ።
 
መኖር፣ መተንፈስ፣ በድህነት አንገት ደፍቶ መቀጠል የሰው ልጅ በተሳነው #ልስን ሥርዓት ውስጥ ዴሞክራሲ????? ለትናጋ አቃቢ ህግ ቢኖረው ምን አለበት? ትንሽ ቢሰቀጥጥ።
 
ዴሞክራሲ ቀለም እንደ መቀባት ቀላል ሂደት አይደለም። #አደብ ያለው #ትውልድን መፍጠር ይጠይቃል። አደበ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ደግሞ #አቅል ያለው ምራቁን የዋጠ ቲም ወርክ ይጠይቃል። 
 
በአንድ ሰው የህሊና ትርትር ዳንቴል በፒኮክ ሠረገላ ቀኑ ለጨለመባት አገር እና ህዝብ ዴሞክራሲ ስላቅ ነው።
ብዙ መከራ ታልፏል። ተመልሰን እምንገኜው ወደ ኋላ 500 ዓመት ተመልሰን የገዳ የምፃዕት ዘመን ላይ ነን።
#ደም እና ጽዋ። 
 
#ውድመት እና ዋይታ።
#ጭካኔና ክህደት።
#ግለት እና መስፋፋት።
#መጫን እና ፍጅት።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
 
ክብረቶቼ ደህና ዋሉልኝ። አሜን።
 

 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/10/2022
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።