81 ንፁህ አማራወች በጅምላ ከእስር ቤት ተረሸኑ። የኦሮምያ ልዩ ኃይል በኦነግ የጫካ ክንፍ ጥምር ጆኖሳይድ ተፈፀመ።

81 ንፁህ አማራወች በጅምላ ከእስር ቤት ተረሸኑ። የኦሮምያ ልዩ ኃይል በኦነግ የጫካ ክንፍ ጥምር ጆኖሳይድ ተፈፀመ።
 
"ተረኝነት" እያለ የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ አዝሎ በመተርጎም አቅምን ሲቀብር የኖረው ፖለቲከኛ ተንታኝ፤ ጋዜጠኛ ዘጋቢ አሁን ያስረዳኛል። ዕጣ ነፍሴን አራት ዓመት ሙሉ አሁን ያለው የገዳ ሥርዓት ነው። የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤ ዬገዳ አስምሌሽን፤ ዬገዳ ዲስክርምኔሽን ነው። ከችግሩ ጭብጥ ካልተነሳን መፍትሄው ይርቃል። 
 
"ተረኝነት" የሚለው እጭ ላይ ያለ ፖለቲካ አዛይ እና ትጥቅ አስፈቺ ነው ስል ሰሚ አላገኜሁም ነበር። እኔከዚህም አልፌ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሴሪሞኒያዊ መፍነሽነሹን ትቶ የእስራኤሎችን፤ የስፔኖችን መንገድ ይከተል በማለት በትጋት ሠርቻለሁኝ። ለዚህ ነው ዛሬ ትግሉን እንመራለን ያሉት አንጨባርቀው፤ አንጨባርቀው መራራ ስንብት ሲፈፅሙ በተደሞ፤ በጥሞና በዝምታ እዬተከታተልኩ የምገኜው። ይህ ቀረ እምለው አንዳችም ጉዳይ የለም። የትግል አቅጣጫውን ፍንትው አድርጌ ፅፌ፤ አስገንዝቤያለሁኝ። ፀፀት የለብኝም። ተረኝነትን አጉልተው የሚያስጮሁት በግርዶሽ የሥርዓቱ ዋቢወች ናቸው። ይህን ዘመኑ ይገልጠዋል። እንደምን የትግሉን አቅጣጫ እያወኩ ሲያተራምሱት እንደባጁ።
 
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
- ዲሴምበር 16, 2019
• ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
 
ህብር እንደ ዘገበው።
 
"ዬኦሮሞያ ልዩ ኃይል እና የኦነግ ዬጫካ ክንፍ በጋራ በአማራ ህዝብ ላይ የጅምላ ግድያ መፈፀማቸውን ዬአማራ ማህበር በአሜሪካ በመርማሪወች መረጋገጡን ገለጠ። በምስራቅ ወለጋ ጉተንከተማ ላይ እዬፈፀሙ ነው ማለቱን የህብር ዘጋባ የአማራ ማህበር በአሜሪካን ዋቢ አድርጎ ህብር ዘግቧል።
 
በአንገር ጉተር ላይ ዛሬ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓም ከጥዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ተኩስ መከፈታቸውን ከአካባቢ ዬወጡ መረጃወች ይገልፃሉ። ከአንድ ሳምንት በፊት የኦሮሞ ተወላጆችን እዬለዩ ከአንገር ጉተር ከተማ እና ከአካባቢው እንዲወጡ በማድረግ የጀመሩት ዘር ማጥፋት እርምጃ መሆኑ እና ከቡድን መሳሪያ ጀምሮ የታጠቁ የኦነግ ጥምር ኃይሎች ከጥዋቱ 01- እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ ቀጥለዋል። እስካሁን በዛሬው ዕለት የተረሸኑ የአማራ ተጠቂወች ቁጥር እንዳልታወቀ ተዘግቧል።
 
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞናቱ በወንጌል ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል በአማራ ተወላጆች ላይ ዬጅምላ እስር የፈፀመ ሲሆን፤ ህዳር 19 እና ህድር 20 ቀን 2015 ዓም ከእስር ቤት አውጥቶ 81 ያህሉ አማራወች መረሸኑን ከህዳር 09 እስከ እስር እርምጃው ድረስ 47 ዬሚሆኑ ዬአማራ ተወላጆችም በክልሉ ልዩ ኃይል መገደላቸው ተገልፆል።
 
ከተገደሉት መካከል ከእነ ቤተሰቦቻቸው ዬተገደሉ እንደሚገኙ ዛሬ የሟቾች መረጃን ይዞ የወጣው ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ህዳር 19 እናህዳር 20 ቀን 2015 ዓም
 
"1) አቶ ጀማል ዳምጤ እሳቸውን ጨምሮ 5 ቤተሰቦቻቸውን፤
2) አቶ አበባው መኮንን እሳቸውንጨምሮ 6 ቤተሰቦቻቸውን፤
3) ሸህ ሙሳ ዬሱፍ እሳቸውንጨምሮ 5 ዬቤተሰብ አባሎቻቸውን፤
4)አቶ ሃሰን ሲራጅ እሳቸውንጨምሮ 3 ዬቤተሰብ አባላቸው፤
5) አቶ ከማል በድሩ ከእነ ባለቤታቸው 21 ዬቤተሰብ አባላታቸውን፤
6) አቶ ሙሳ አሊ እሳቸውንጨምሮ 7 ዬቤተሰብ አባላትን፤
7) አቶ አሊ ሃሳን እሳቸውን ጨምሮ 10 ዬቤተሰብ አባላትን፤ አካቶ 81 አማራወች ህዳር 19 ቀን እና ህዳር 20 ዓም በጉተር በኦሮምያ ጽንፈኛ ኃይሎች ከእስር ቤት ወጥተው መገደላቸው ታውቋል ይላል የህብር ዘገባ።"
ህዳር 24 ቀን 2015 ዓም
 
በጊዳ አያና ወረዳ አንዶጌ፤ ሻሾ በር ከባድ ተኩስ ተከፍቷል ዬአካባቢው ሚኒሻ እና አርሶ አየሮች ህፃናትን እና ሴቶችን ለመታደግ ሲባል ወደ ጫካ መሸሸታቸው ታውቋል። መከላከያ እዬመጣ ነው ቢባልም ከጥቃቱ ዬተረፋት መረጃ እስከሰጡበት ድረስ መከላከያ ትውር እንዳላለ ታውቋል ይላል ዬህብር ዘገባ። "ቤቱም እዬተቃጠለ ነው። ከሰላም ሚር ጀምሮ ድረሱልን ብለን ተማጽነናል ዬሚደርስልን ተቋም ግን አልተገኜም ዬክልሉ መንግሥት እና ሸኔ አንድ ሆኗል" ይላሉ ቃለ ምልልስ ያደረጉት። 
 
Hiber Radio Daily Ethiopia News Dec 03, 2022 | ሕብር ራዲዮ ዕለታዊ ዜና | Ethiopia 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04/12/2022

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።