ዬሀሮ አዲስዓለም ጉዳይ።

 

·      ዬሀሮ አዲስዓለም ጉዳይ።

 

ይድረስ ለማከብረወት ለዶር ዳንኤል በቀለ ዬኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር።

 

አዲስ አበባ

 

ድጋሜ አቤቱታ።

 

30/11/2022 ዕለት አመልክቻለሁኝ። ከተለያዩ የወለጋ አካባቢወች የተፈናቀሉ 30 -45 ሺህ የሚደርሱ የአማራ ተፈናቃዮች እጅግ በሚያሳስብ ሁኔታ ከበባ ውስጥ ናቸው። ይህ ሌላ እራስን የማዳን እንቅስቃሴ ከተለወጠ የማይበርድ እሳት ያቀጣጥላል።

 

አስፈላጊ እና ሴንሲቲብጉዳዮች ሲገጥሙ ተቋመወት እንደምን አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ አውቃለሁኝ። ለዚህም ጉዳይ ከምንም ነገር ዬቀደመ እርምጃ ካልተወሰደ ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል።

ቁጥሩ በትናንቱ የጥዋት መረጃ ላይ ኢትዮ ኒውስ 45 ሺህ ብሎ የዘገበ ሲሆን ትናንት ከሰዓት መረጃውን አሻሽሎ 30- 45 ብሎ ነበር። ዛሬም ተቀራራቢ ግምቱን ዘግቧል።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ ነፍስ የወፍ ያህል ክብር እንደሌለው ባውቅም ቢያንስ ለእርስወ ማመልከት የተሻለ ሆኖ ስላገኜሁት ደጋግሜ በትህትና ማሳሰብ ግድ ብሎኛል።

 

በኦሮምያ ያለመከሰስ መብታቸው ተረግጦ ስለታሰሩ ዬከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በአፋጣኝ በወሰዳችሁት እርምጃ ፍትህ ቀና ብላለች። በአማራ ህዝብ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ወከባ፣ ማሳደድ፣ ማፈናቀል፣ የስጋት ጫናስ????

 

በዬዕለቱ ዬአማራ ደም ይፈሳል ዛሬም ዬስድስት ንፁኃን ነፍስ እንዳለፈ ከኢትዮ ኒውስ አዳምጫለሁኝ፣ ባለፈው ቀንም 20 በላይ???? እስከመቼ ተቋመወት ግልፅ አቋም ይዞ ከዚህ በከንቱ ከሚፈስዕንባ ጎን ይቆም ይሆን? ተስፋ ዬእግዜብሄር ነው እና በተስፋ እጠብቃለሁኝ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅኝቱ ዬአማራን ህዝብ ያገለለ፣ የሚገፋ፣ አትኩሮትም ዬነሳ ነው? ይህን የላይኛውም ያያል።

 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

02/12;2022

ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር ከተማ።

ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

 

የቀደመውን አቤቱታዬን አባሪ አድርጌ አያይዠዋለሁኝ።

~~~~~~~±±±±±~~~~~~~~

አስቸኳይ ትኩረት ለሀሮ አዲስ ዓለም ዬአማራ 45 ተፈናቃዮች።

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣

አዲስ አበባ።

 

ዳዩ 45 ሺህ ዬሀሮ አዲስዓለም ዬአማራ ተፈናቃዮችን ይመለከታል።

 

ጤና ይስጥልኝ የማከብረወት ዶር ዳንኤል በቀለ። እንዴት ሰነበቱ? መከራው አዛለን በእጅጉ። እኛ ከዚህ ሆነን ዬዛልን በጋመው እሳት ውስጥ ያሉትስ?

ከተለያዩ የወለጋ ቀበሌወች፣ ወረዳወች የተፈናቀሉ 45 ሺህ የሚጠጉ ዬአማራ ተወላጆች በዚህ ሁለት ቀን ካልተደረሰላቸው የከፋ ችግር ሊገጥም እንደሚችል ከአንድ ሰዓት በፊት ከኢትዮ ኒዊስ ያገኜሁት መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ኦፕሬሽን የመንግሥት የወረዳ አካላት አንዳንዶቹ እንደሚሳተፋና አደጋውም የከፋ ሊሆን እንደሚችል የደረሰው ዘገባ ዕድምታ ያመለክታል። እባከወት ፈጥነው ይድረሱላቸው።

 

ሌላው በኬሬም ወረዳ የሚኖሩ አማራወች ተፈናቅለው፣ ታርደው አብዛኛው የወረዳው ቀበሌ ከአማራ ፀድቷል። የሚገርመው ህይወታቸው ዬተረፋት እንዳይመለሱ ቤታቸው ተቃጥሎ፣ ንብረታቸው ተወስዷል።

የዚህ ዕድምታ ሚስጢሩ የህግ ባለሙያ ነወት እና በጭልፋ ሳይሆን መሰረታዊ ፕሮጀክቱን ይደርሱበታል ብዬ አስባለሁኝ።

https://www.youtube.com/watch?v=Uydhf_DOGaA

የኤርትራ ጦር የሚወጣበት ቁርጥ ቀን ታወቀ! | ዓዲግራት.! ማይጨው.! ኮረም.! ኪረሙ!

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

01/12/2022

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር ከተማ።

የአማራ ህዝብ ግፍ የት ያደርስ ይሆን????

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።