#ማን ተጫወተው? ለእንግሊዞች ለዋንጫ ውድድር እግዚአብሄር ነው የፈፀመላቸው ማለት ይቻላል።

#ማን ተጫወተው?
ለእንግሊዞች ለዋንጫ ውድድር እግዚአብሄር ነው የፈፀመላቸው ማለት ይቻላል።
 
ያን አሰልቺ ላንግባይሊክ፤ እጅግም አድካሚ ለተጫዋች ብቻ ሳይሆን ለተመልካች የአጨዋወት ዘይቤያቸውን ይዘው በፔናሊቲ ሎተሪ ዛሬም ሆላንድን ሁለት ለአንድ ረተው ለዋንጫ ተፋላሚ ሆነዋል። ግርም ነው ያለኝ። በግል ያላቸውን ብቃት ሳያቀናጁ ለዋንጫ መብቃት የእግዚአብሄር ሥራ ነው ማለት እችላለሁኝ። በግል በጣም ቀልጣፋ ኮከቦች እንዳሏቸው አስተውያለሁ። 
 
ዛሬን በጎል እልልታ አህዱ ያሉት መጀመሪያ ለግብ የበቁት ሆላንዶች ነበሩ። እንደ ጀርመኑ Das Erst ትንታኔ ሆላንዶች ለዚህ ዕድል ለመብቃት 20 ዓመት ጠብቀዋል ብሎ ነበር። ዛሬ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እንግሊዞች ተስለው ነበር የቀረቡት። ባይቀጥሉበትም። አቻ ያበቃቻቸውን ግብ ያስቆጠሩት በለመዱት ፔናሊቲያዊ ዕድል ቀንቷቸው ነው።ከእረፍት መልስ ሁለተኛውን ግብ አክለው እንሆ ሆላንድን ረተው ለዋንጫ ደረሱ። ይገርማል። 
 
ትናንት ብቃታቸው በግል እና በቡድን በቋሚነት እያሳዩ የመጡት ስፔኖች በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ፈረንሳይን ሁለት ለአንድ በሆነ ጎል ብቻ ሳይሆን በጨዋታ ብልጫ በአቅም፦ ብቃት ፈረንሳይን ሸኝተው እነሱ ለዋንጫ አልፈዋል። #ይገባቸዋልም። ዬፈረንሳይ ቡድን ካታር ላይ ለዓለም ዋንጫ ያበቃው ያ ታይቶ የማይጠገብ ቅልጥፍናው እና አርቱ ብቃቱ ሸሽቶት ከዚህ ግባ የሚባል ጨዋታዊ ትዕይንት ሳያሳይ ነው ከዚህ የደረሰው።
 
#ኦስትርያ#እምዬ ሲዊዝ፤ #ቱርኪ፤ የክርስቲያ ሮናልዶ እና የፔፔ ፖርቹጋል፦ እንዲሁም ቀደም ብሎም #ኮራ ተሰናብተው #የእንግሊዝ እና #የፈረንሳይ ቡድን እዚህ መድረሳቸው ለኳስ ብቃት ብቻ ሳይሆን #ዕድልም ልል ችያለሁኝ። 
 
ጀርመን በአገራቸው በሚካሄደው ውድድር ባይተዋር መሆናቸው በውነቱ ትንታጓን የእኔ ልዕልትን የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር ዶር አንጌላ ሜርክልን ዘመን ያምጣ ነው እምለው። ልጆቻቸው እንደ ዓይናቸው ብሌን የሚንከባከቡ ናቸው እና።
 
ወደ ረንሳይ ምልሰት ሳደርግ፦ የአገራቸው የፖለቲካ ምርጫ የተወሰነ ጫና ይኖረዋል ብዬ አስባለሁኝ። በዛ ላይ ኮከባቸው እማፔ በአፍንጫው ላይ በደረሰው ቀላል ጉዳት በማስክ ጨዋታው የከበደው ቢመስልም፤ በትናንትናው ጨዋታ ከማስክ ውጪም የመጀመሪያ ዕድል ቡድኑ ቢቀናውም፦ በመደበኛ ጨዋታ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ኮከቡ እንሆ ተረታ። ጨዋታው አልተራዘመመ ነበር። ከዚህ አንፃር ሲታይ የእምዬ ሲዊዝ ልጆች ምን ያህል ጠንካራ መሆናቸውን ያሳያል። 
 
እንግዲህ ፈረንሳይ እና ሆላንድ ለደረጃ፤ እንግሊዝ እና ስፔን ለዋንጫ ፍልሚያቸውን ይቀጥላሉ። #ሆላንዶች ቢያንስ የሦስተኛ ደረጃ ዕድል ቢያገኙ ምኞቴ ነው። ለደጋፊወቻቸው ስንቅ ቢሆን።
 
በተረፈ የዋንጫው ፍልሚያ ከእንግሊዝ ጋር ብዙም ለእኔ አያጓጓኝም። ጨዋታቸው ሞናትነስ ነውና። አይገባኝምም። እንግሊዝ ሊግ ላይ እግር ኳስን ይጫወቱት፦ ይጠብበትም። EM & WM ግን የማዬው አቅም እምብዛም ነው። 
 
መቼስ እማናዬው የለም #እንግሊዞች ------- #እስፔኖችን አሸንፈው ዋንጫ ከበሉ እራሱ አማኑኤል ይጠዬቅበታል። በዚህ ይከወን። 
 
ደህና እደሩልኝ። ነገ ሽክ ባለች አውድዮ እንገናኛለን። ቸር አስበን ቸር እንደር። ቸርም ፈጣሪያችን ያገናኜን። ደህና እደሩልኝ። ኑሩልኝም። አሜን።
 
አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።