የኢትዮጵያ አዲስ የኢኮኖሚ አቅጣጫ እና የአፈፃፀም ተጨማሪ #መመሪያወችን የኢኮኖሚ ባለሙያወች እንደምን ያዩታል??
የኢትዮጵያ አዲስ የኢኮኖሚ አቅጣጫ እና የአፈፃፀም ተጨማሪ #መመሪያወችን የኢኮኖሚ ባለሙያወች እንደምን ያዩታል??
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች አዲሱን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅጣጫ እንደምን እንደሚዩት ባለፈውም የራሴን ዕይታ አክዬ በርከት ካሉ ሚዲያወች ያገኜሁትን ሊንክ አክዬ አቅርቤ ነበር። ዛሬ በተጨማሪ ሁለት ባለሙያወች ዶር ዘለዓለም ተክሉ ሁለት ጊዜ በአዲስ ኮንፓስ ሚዲያ፤ እና አቶ ሙሼ ሰሙ በሃሳብ ገበታ የሰጡት ማብራሪያ ለአጠቃላይ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሊንኩን አያይዣለሁኝ። ይመለከተናል። ግንዛቤም ሊኖረን ይገባል በሚል ዕምነት።
አዲስ ለአፈፃፀም አጋዥ ይሆናል የተባለውም "#ፍራንኮ ባሉታን፦" በሚመለከት እስከ አፈፃፀም ሂደት ያለውን ሁኔታም እንዲሁ ባለሙያው ዶር ተክሉ ዘለዓለም የራሳቸውን አወንታዊ ዕይታ አቅርበዋል። ዶር ተክሉ ዘላለም በዘመነ ግንቦት 7 በዘርፋ ትንታኔ ሲሰጡ የምናውቃቸው ናቸው። እኔ በግሌ ባልገቡኝ ጉዳዮች፤ ሙግትም ሲኖረኝም በቅንነት፤ በአውንታዊነት በአክብሮት የሚያስተናግዱኝ የማከብራቸው ሊቅ ናቸው።
አቶ ሙሼ ሰሙ ምንም እንኳን ኮንታክት አድርጌያቸው ባላውቅም ሚዲያ ላይ የሚሰጡትን ማብራሪያ አዳምጣለሁኝ። የቀድሞው #የኢዴፓ መሥራች አባል፤ አካል የነበሩ በፖለቲካው ዘርፍ ትጉህ ከሚባሉ ሊቃውንት መሃል ሲሆኑ በኢኮኖሚም ባለሙያም ናቸው።
እርግጥ ነው በኢትዮጵያ ዬኢንተርኔት መቆራረጥ ምክንያት ሙሉ ዝግጅታቸውን ለማቅረብ፦ ሃሳባቸውን ለመግለጽ ዕድሉ ባይኖርም ታግሰን ላዳመጥነው ግን #ጠቃሚ መረጃ አግኝተናል ብዬ አስባለሁ። የሃሳብ ገበታ አዘጋጅ ልጅ ሞገስ ዘውዱ #ድጋሜ ቢያቀርባቸው እና ሙሉ ዕይታቸው ሳይቆራረጥ #ቢከልሱልንም እኔ ምርጫዬ ነው። በሳል የሆነ ዕይታ ያላቸው ባለሙያ ናቸው እና።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባላ እና ወጋግራ የሆነው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደ ባዕድ ሊታይ፤ ባይተዋር አድርገን ልንመለከተው የሚገባ አይመስለኝም። ኢኮኖሚ ጎጆውን ሁሉ ስለሚዳስስ ከተለምዶ አገላለጽ ወጥቶ በባለሙያወች የሚሰጠውን ትንታኔ #የእኔ ብሎ ማድመጥ ይገባ ይመስለኛል። የፖለቲካ ሥልጣን ካለ ኢኮኖሚ አቅም ምንም ነው። ኢኮኖሚ #ጉሮሮ ነው። ኢኮኖሚ #ሕይወት ነው። ኢኮኖሚ #ህልውና ነው። ኢኮኖሚ #ዲፕሎማሲም ነው። ኢኮኖሚ አገርን የማስቀጠል ሚናውም ጉልህ ነው።
ስለዚህ አንዱን አንጠልጥሎ፤ ሌላውን ጥሎ መጪ ከማለት ለሁሉም የሕይወት ዘርፎች በቂ አትኩሮት፤ በቂ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ይህ የሚሆነው ደግሞ አደብ ገዝቶ #ማድመጥ ሲቻል። አቅል ኑሮ አቅም ካላቸው ሙሁራን የሚሰጡትን ማብራሪያወች የእኔ ብሎ ከልብ፤ #በቅንነት፤ #በአውንታዊነት ለማድመጥ መፍቀድ ከተቻለ ሙሉ የህሊና አቅም ይኖረናል። በስተቀር ግንጥል ጌጥ ይሆናል ድካማችን። ስኬቱም ሩቅ።
ምንግዜም ከዕውነት፤ ከመርኽ ጎን ቆመን ማንኛውንም ሀገርኛ ዘይቤወችን የእኔ ማለት የሚገባ ይመስለኛል። ህግን በሚመለከት ባለሙያወች አሉን። ማህበራዊ ኑሮን በሚመለከት ተፈጥሯዊነቱ ተጠብቆ በዘርፋም ባለሙያወች አሉን። ታሪክን፤ ፖለቲካን፤ ፍልስፍናን፤ ሳይንስን አስመልክቶ አራት ዓይናማ ባለሙያወች ኢትዮጵያ አሏት። #እህ ብሎ ለማድመጥ፤ ለመደመጥም ከፈቀድን።
የእያንዳንዱ የህይወት ፍልስፍና በአፈጣጠሩ ላይ ለሁላችም እኩል ነው። በአፈፃፀም እና ተጠቃሚነት ላይ ነው ልዩነት ሊኖር የሚችለው። ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ሲሆን ቢያንስ ጽንሰ ሃሳቡን ለማወቅ፤ ለማድመጥ ድንበር ባናበጅለት የተገባ ይመስለኛል። መማር፤ ማወቅ ቢጠቅም እንጂ #አለሎ ድንጋይ ይዞ ጭንቅላታችን ስለማይፈልጠው።
እንዲያውም ለህሊናችን በቂ ሙቀት ለግሶ ሙሉ አቅም እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል።
ከዶር ዘላለም ተክሉ እና ከአቶ ሙሼ ሰሙ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መሪ ሚዲያ ለዘርፋ #መቅድም ነው። ኢኮኖሚ ተኮር፤ ስኬት ተኮር፤ የአመራር ብቃት ተኮር ነውና።
ሚዲያው ልክ የትወናን ሙያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያበረታታ የነበረው የማለዳ ኮከቦች፤ የጥበበኛው ቅኑ የአቶ ፍፁም አሰፋ አይነት አዲስ ምዕራፍ ነው #መሪ ሚዲያ። አዘጋጆች አቶ ከንዓን አሰፋ እና አቶ ጥጋቡ ኃይሌ የተደራጄ ተግባር እዬከወኑ ነው። እራሱ የአጠያዬቅ ቃናቸው እጅግ ሳቢ እና ጥንቁቅም ነው። ሁለቱም የየራሳቸው የሚመሩት ድርጅትም አላቸው።
ሰሞኑን የሥራቸውን ሂደት ግምገማ ባደረጉበት ሰዓትም #አዲሱን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ አቅጣጫ ትንሽ ስለነካኩት የእሱንም ሊንክ እጨምራለሁኝ። እነሱ እንዲያውም ቀደም ብለው ባለሙያወችን ጋብዘው ተነጋግረውበት ነበር - በነፃ የገብያ ሥርዓት ጉዳይ። እኔም አስታውሳለሁ ሼር አድርጌዋለሁኝ ብሎጌም ኤክስ አካውንቴም ላይ። በጣም ተስፋ የማደርግባቸው ስክን ያሉ ወጣቶች ናቸው አቶ #ከንዓንወጥጋቡ።
በተረፈ ሸበላ ጊዜ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
«በፍራንኮ ቫሉታ ተጠቃሚው ማነው?»
«ሰሞንኛ ጉዳዮች፣ ቆይታ ከዶክተር ዘላለም ተክሉ ጋር»
«የሳምንቱ እንግዳ "አገር-በቀል ወይስ አገር-ነቀል ፖሊሲ"
«ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ የቢዝነስ ሰዎች ጋር የማዉራት እድል ማግኘት ትልቅ እድል ነው - Season 9 Bonus Episode»
MERI PODCAST
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/08/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ዕውነት ጋራጅ አያስፈልገውም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ