የኢትዮጵያ ህፃናት #ዕንባ አባሽ ይናፍቃሉ። #አይዟችሁ የሚሏቸውን ይማፀናሉ።

 

የኢትዮጵያ ህፃናት #ዕንባ አባሽ ይናፍቃሉ። #አይዟችሁ የሚሏቸውን ይማፀናሉ። 
 
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት በዘመናቸው ስለምንድን ይሆን ለልጆች የሚሆን #የአይዟችሁ ቋሚ ተቋም መገንባት የተሳናቸው?
 
ማህበረ ቅንነት እስኪ ሼር አድርጉት ለአባቶቻችን እንዲደርስልኝ ሃሳቤ።
 
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፦
ሰው ግን አያስተውለውም።"
 
 
 
 
 
 
 May be an image of 1 person, child, smiling, scarf and tree
 May be an image of 1 person, child, smiling, tree and textMay be an image of 2 people and text
 
May be an image of 2 people and child
 
 May be an image of 4 people and text
 May be an image of 1 person
 May be an image of 1 person and child
 May be an image of 1 person
 May be an image of 1 person, child and tree
 May be an image of 4 people, child and people smiling
 
May be an image of 1 person and child
 May be an image of 1 person and clothes iron
 May be an image of 5 people and child
 May be an image of 1 person
 May be an image of 2 people and child
 May be an image of 1 person, child and smiling
 
May be an image of 3 people and child
 May be an image of 5 people, child and people smiling
 May be an image of 3 people and text
 May be an image of 1 person and child
 
 May be an image of 1 person, child and text
 May be an image of 1 person and child
 May be an image of 2 people and child
 May be an image of 2 people, child and text
 
 
የኢትዮጵያ ህፃናት፤ የኢትዮጵያ ልጆች #ዋቢ የላቸውም። #ሁነኛ የላቸውም። #ባለቤት የላቸውም። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ትርምስ ቀንበሩን የሚሸከሙት የኢትዮጵያ ህፃናት እና የኢትዮጵያ ሴቶች ናቸው። የመጀመሪያውን የልጆችን ሰቆቃ የሚሸከሙት እነሱው ናቸው። በዚህ 6 ዓመት እንኳን በጦርነት፤ በመፈናቀል፤ በተፈጥሮ አደጋ፥ በዓታችን ልቀቁ በሚል ሰይጣናዊ ዕሳቤ አሳራቸውን ያዩት የኢትዮጵያ #ህፃናት ናቸው። ልጅ ሆነው ልጅ አሳዳጊ ወላጅ የሆኑት እነሱው ናቸው። 
 
ከቡራዩ ጭፍጨፋ ጀምሮ በለገዳዲ ለገጣፎ፤ በደቡብ፤ በማህል ጎንደር፤ በመተከል፤ በደራ፤ በወለጋ፤ #በአዲስ አበባ፤ በሽዋ ሮቢት፤ በሻሸመኔ፦በአርሲ ነገሌ፤ በአጣዬ፤ በሐረር፤ በትግራይና በፌድራሉ ጦርነት በሙሉ አፋር ክልል፤ በአማራ ክልል፤ በትግራይ ክልል የቀጥታ ተጠቂወች ህፃናት ናቸው።
 
ወላጅ አልባ ህፃናትም በርካታ ናቸው። #ጤና፤ ትምህርት ለኢትዮጵያ ህፃናት #ቅንጦት ነው። #አትረገዙም#አትወለዱምም አለበት። ጽንስ ከመሐፀን ወጥቶ ተሰቃይቷል። አብረን እንፈር። የትውልዱን ህሊና ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ለማድረግ የአቅም እጥረት ያመጣው አሳር ነው። ጭካኔው ልክ የለው። 
 
በሌላ በኩል ተፈጥሮም ሲቆጣ ተጎጂወች ልጆች ናቸው። በድርቅ ይሁን በመሬት መንሸራተት፤ በጎርፍ ይሁን በመዓበል ነውጥ። በሁሉም ዘርፍ የሚጠቁት ልጆች ናቸው። ወላጆቻቸውን ያጣሉ፤ እነሱም የቀጥታ ተጠቂ ይሆናሉ። እኔ የህፃናት፤ የሴቶች እና የወጣቶች ሚ/ር ምን ሠርቶ እንደሚያድር አላውቅም። አለ ሲባል እሰማለሁኝ። ዕንባ ጠባቂም የሚባል የኢትዮጵያ ተቋም አለ።
 
ኢትዮጵያ ዕንባ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ደምም በከንቱ የሚፈስባት አገር ሁናለች። አጥቂውም አይጠየቅም። ህጉም አይተረጎምም። አሉ የሚባሉ ተቋማትም ፍትህ አልባነትን፤ መጠጊያ አልባነትን እንደነኝህ ዓይነት ጉዳዮችን እያጠኑ ፕሮጀክት አዘጋጅቶ ዕልባት እንዲያገኙ ማድረግ ይገባቸው ነበር።
 
የሃይማኖት ተቋማት በኢትዮጵያ ደህና ካፒታል ያላቸው ናቸው። #እናስተባብርም ቢሉ ይችላሉ። ተደማጭ ናቸው። ሙሉ አቅምም አላቸው። ቢያንስ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት አንድ #ለልጆች የሚሆን #የአይዟችሁ#የአለንላችሁ ግብረ ሰናይ ድርጅት አቋቁመው መኖራቸው ሕይወት እንዲዘራ ቢያደርጉ መልካም ነው። እማሳስበው በትህትና እና በአክብሮትም ጭምር ነው። ይህን ሃሳብ እማነሳው ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በ2011 እ.ኢ.አ በብሎጌ ላይ ሃሳቡን አቅርቤ ነበር። አድማጭ ባያገኝም።
 
እዚህ እኔ በምኖርበት በእምዬ ሲዊዘርላንድ ሁሉን የበጎ አድራጎት ጉዳይ መንግሥት #አይሸፍንም። የሥራ ክፍፍል አለ። #ጎደሎውን የሚሸፍኑ፤ #ቀዳዳውን የሚደፍኑ #የሃይማኖት ተቋማት ናቸው። በተለይ የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት ተቋማት። ለዛውም ከእኛ አገር እንደሚታዬው የበዛ ተከታይ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም። ግን ለደግነት፤ ለርህርህና፤ ለችግር ደራሽነት እጅግ በጣም ቅርብ እና ትጉህ ናቸው። ቤተ - ጽድቅ ናቸው ብዬም አምናለሁኝ። "ስራብ ………" ዕውን የሆነበት። 
 
በውነቱ የሃይማኖት ተቋማት #ከአዘነው ጋር ለማዘን #ቅድመ ሁኔታ ሊያስፈልጋቸው አይገባም ባይ ነኝ። ይህ ሁሉ ህዝብ ሲፈናቀል ልማት በሚባል አዳዲስ ፕሮጀክት፤ በእርስበርስ ጦርነት፦ በተፈጥሮ አደጋ፤ #ታቅዶ በሚከወን ቀውስ የሚሰቃዩ ህፃናትን፤ የሚያለቅሱ ዕንቡጦችን ጉዳይ በቸልታ ማዬታቸው ይገርመኛል። የእነሱ ቤተሰቦች እኮ ናቸው የመከራው ተሸካሚወች። አባሎቻቸው እኮ ናቸው ፈተና ላይ የሚወድቁት። መባ፤ አሥራት በኰራት የሚያዋጡት። 
 
አሁንም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ህብረት ሰብሰብ ብለው ቢነጋግሩበት እና የችግሩ ተጋሪ ለመሆን ንቅናቄ ቢጀምሩ መልካም ነው ስል በትህትና አመለክታለሁኝ። አይደለም የልጆች #የአይዟችሁ ማሳደጊያ ተቋም፦ ቢተባበሩ በአንድ ላይ ቢሰሩ ት/ቤት፤ ኮሌጆችን፤ ዩንቨርስቲወችን፦ #ሆስፒታሎችን ሳይቀር መገንባት ሁሉ ይችላሉ። ቢወጥኑት የውጭ ደጋግ የእርዳታ ድርጅቶችም ሊያግዟቸው ይችላሉ። መንገዱ ቀና ነው ለቅኖች እና ቅን ሃሳብ ላላቸው። አማላካችን አለና። 
 
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ለደግነታቸው #ምልክት፤ ለርህርህናቸው የተግባር #ዓርማ፤፦ለአጽናኝነታቸው #የአይዟችሁ ተቋም ቢገነቡ ከዚህ በላይ በሰማይ ታላቅ ሐሤት ይኖራል ብዬ አላስብም። በመልካም ሃሳብ ውስጥ #ጽድቅ አለ። በበጎ ሃሳብ ውስጥ #ምርቃት ይኖራል። በርህርህና ውስጥም ሚስጢር ይገለጣል። ሚስጢሩ ጥበብን ያጎናጽፋል። ጥበቡ ያሰቡትን የሚያሳካ የስልት መሐንዲስ ይሆናል።
 
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት አብረው መሥራት ባይችሉ እንኳን፦ የድርጊቱን አመክንዮ መከፋፈል ይችላሉ። የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ በሚል። ህፃናት፤ ታዳጊወች በሚልም ኃላፊነቱን መከፋፈል ይቻላል። ወላጅ አልባ ህፃናት እና የሌላቸውም በሚል። በጎ ነገር ሲታለም የእግዚአብሄር የአላህ መንፈስ እራሱ ይተገብረዋል።
አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ዘመን ጩህት የበረከተበት መራራ ዘመን ነው። - ለእኔ።
 
 ጩኽቱን ለማጨመት ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን አቋቁሞ በመንቀሳቀስ ማቀዝቀዝ ይቻላል። መራራውን ዘመን ለመሻገርም፤ ዕውቅና ሰጥቶ ተመካክሮ ለመሥራት እራስን ማሸነፍ ቢቻል "ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳህኒቱ" የአቨው ይተበኃል ዕውን ይሆናል። ጭካኔውንም - ያስታግሳል። ጥላቻውንም መልክ ማስያዝ ይቻላል። ሁሉም የድርሻውን ለመከወን በቅንነት መንፈስ ቢነሳ ዕንባ አባሽ መሆን ይቻላል። ለመልካምነት ቅንነት አዲስ ተስፋ ጠራጊ ነው።
 
ነገን ለማን?
ማግስትን እንዴት?
 
ሁለቱ መጠይቆች የሃይማኖት ተቋማት ዶግማና ቀኖናችሁን ማን ይረከባል። የእግዜሩ፤ የአላሁ መንገድ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ በላይ ነው። ፈተና ሊኖረው ይችላል። ግን ደፍራችሁ ብትጀምሩት ተስፋ ትሆናላችሁ። ብቻ ቅንነትን ሰንቁ። ለልጆቻችሁ እባካችሁ ድረሱላቸው። አለንላችሁም በሏቸው። 
 
አይዟችሁ እኛ ክንዳችን ሳንተራስ እንደ አለቀሳችሁ አትቀሩም እባካችሁ በሏቸው። ጠንካራ ተቋም ፍጠሩ እና ለልጆቻችሁ ዋስ ጠበቃ ዋቢ ሁኗቸው። "ድር ቢያብር ……" እንዲሉ።
 
አስተያዬቴ ሁሉ በትህት እና እና በአክብሮት ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልንም።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
30/08/2024
 
ልጆች የሁላችንም ልጆች ናቸው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።