ነገረ አዲስ አበባ። #መስከረም 5/2011 ዓ.ም። #የነባርነት #ምነና። በጣም የዘገዬ #አቤቱታ ነው ለጋዜጠኞች አሁን ላይ አጀንዳውን ፊት ለፊት ማምጣታቸው። የት ነበሩ ሙሉ ስድስት ዓመት??? ነገስ???
በጣም የዘገዬ #አቤቱታ ነው ለጋዜጠኞች አሁን ላይ አጀንዳውን ፊት ለፊት ማምጣታቸው። የት ነበሩ ሙሉ ስድስት ዓመት??? ነገስ???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"
የኦሮሙማ ጠቀራዊ የዲሞግራፊ ፋሽስታዊ ጉዞ ከአቶ ለማ መገርሳ አንደበት።
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
- ዲሴምበር 16, 2019
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም። ከዚያ የከበደ መከራ ላይ ናቸው አላዛሯ ኢትዮጵያም ሆነ እማማ አፍሪካም።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
በቅድሚያ ዛሬ ህልም አዬሁኝ። የአዳራሽ ወንበር ፊቱን አዙሮ። ከንቲባ አዳነች አበቤ ነበሩ ሰብሳቢዋ። እሳቸውም በጀርባው ወደ ዞረው አዳራሽ ላይ ሆነው ሲናገሩ አዬሁኝ። መድረክ የለውም አዳራሹ። ልጆች እግራቸውን ግራ ቀኝ አድርገው፤ ፊታቸውን አዙረው፥ መደገፊውን ከሾንጎበታቸው ላይ አስደግፈው እንደሚቀመጡት ዓይነት የህዝብ ትዕይንት ነው ዛሬ በህልሜ ያየሁት።
አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ ክልል የተዛወረችው #መስከረም 5/2011 ዓም ነበር። እኔ ከዛች ዕለት ጀምሮ አቅሜ ብዕር ስለሆነ ሳስገነዝብ ቆይቻለሁኝ። ሃሳብ ማንም ያፍልቀው። ሊደመጥ ይገባል ህዝበ ጠቀም ከሆነ። የሆነ ሆኖ እጅግ ዳተኛ ድምፆች ስንት ነገር ከተናወፀ በኋላ ድምጽ ለመሆን እዬሞካከሩ ነው።
ትናት የተካደ ህዝብ ዛሬ ላይ ያለውን ደረስንልህ ጥሪ እንደምን እንደሚያስተናግደው ባለወልዱ ይመዝነው። በ97 ኑርልን። እናመሰግንኃለን ሊባል የሚገባው የአዲስ አበባ ህዝብ ሆኖ ሳለ ተመስጋኙ ሌላ ነበር። ለዚህ ነው የአዲስ አበባ ህዝብ መከራው አጉብጦት ጥግ አልባ መሆኑን ስለሚያውቅ ከፈጣሪው ጋር እዬተወያዬ የሚገኜው። የዕቃ ክህደት አይደለም፤ በዬዘመኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲከኞች ይካዳል። ሁሉም ይክዱታል። ሁሎችም ይበድሉታል። የማይክደው አምላክ ተስፋ ይሁነው።
የሆነ ሆኖ ………
#የበዕላት አከባበር በአዲስ አበባ እና በኦሮምያ ከተሞች ወከባ፤
#የሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እገዳ፤
#ታፍነው የሚሰወሩት በአዲስ አበባ የተለያዩ የግል እስር ቤቶች ጉዳይ፤
#ተደብድበው የሚለቀቁት ወገኖቻችን ጉዳይ፤
#ጠቅላይ ሚር አብይ በ100 ቀን ትጋታቸው #ድሬ እና አዲስ አበባን አላካተቱም ነበር። ነጠሏቸው። ይህ የሚያሳዬው ስውር አጀንዳ እንዳለም ነበር። ቴዲ ርዕዮት በስሜን አሜሪካ ጉብኝታቸው ዶር አብይን ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ እንቅልፍ የሚያስተኛ ሳይሆን የሚያነቃ ነበር።
#ከሱማሌ ክልል ያፈናቀሏቸውን ግማሽ ሚሊዮን የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወችን አዲስ አበባ እና ዙሪያው አምጥተው ማስፈራቸው፤
#የጉለሌ ነዋሪወች ወደ ባህርዳር መሸኜታቸው፤
#የሬቻ ዋዜማ ላይ ያለው መንግሥታዊ ሁነት የሚሰጡ መግለጫወች፤
#ገና በጥዋቱ 5 የአዲስ አበባ ልጆች በአዲስ አበባ ከተማ መረሸናቸው፤
አዲስ አበባ ላይ ግድያ መፈፀሙ ሙሽራ ሳይቀር።
#በዙሪያው ባሉ ከተሞች የቡራዩ፤ የሰበታ፤ የለገዳዲ ሰቆቃ፤ የፍርሻ ጥድፊያው፦
#ከአማራ ክልል ለሚመጡ ወገኖች አዲስ አበባ የአትገቡም እገዳ።
#የገብሬ ጉራቻ የሹፌሮች፤ የተጓዦች እገታ እና እንግልት፤
#የወለጋው የአማራ በጭካኔ የዘለበ ጭፍጨፋ፦
//// 1300 የአዲስ አበባ ነዋሪወች መታሰራቸው፥ ሁሉም መሰረቱ አንድ እና አንድ ነበር። እያገናዘብኩ በሰፊው ጽፌያለሁኝ። መስፋፋት፤ መጫን፤ መዋጥ እንዳለም። ዲስክርምኔሽን፤ አስምሌሽን፤ ኤክስፓንዴሽን መሆኑን አበክሬ ገልጫለሁኝ። አዲስ አበባ ለኦሮሚያ ክልል፤ ለጠቅላይ ሚር አብይ መንግሥትም እንደ ደብረዘይት እንደ ናዝሬት ናት እያልኩ ሁሉ ጽፌያለሁኝ።
በአሻው ሰዓት ኦሮምያ ክልል ያሻውን የሚፈጽምባት ከተማ አዲስ አበባ እንደሆነች በጽኑ ገልጫለሁኝ። ማን ጌታ አለበትና??? ባልደራስ ነፍስ በነበረው ሰዓትም ፓን አፍሪካ ሙብመት ይጀምር ዘንድ በተደጋጋሚ አሳስቤው ነበር። የባልዳራስ ዓላማ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳዬው ከእኛ ውስጥ ጋር ቅርርቡ እንብዛም ሆኖ ነው ያገኜሁት። አብን አዲስአበባ ላይ እንዳይወዳደር የጉሮሮ አጥንትም ባልደራስ ነበር። በውሽልሽል ጥምረት መና ነበር የቀረው የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መንፈስ።
ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫው አሻራቸውን ሲያስቀምጡ በባልደራስ ብልጠት ተሸውዶ ይሁን አምኖበት አብን እራሱን ያፈረሰው ያንጊዜ ነበር። እኔ ጽፌበታለሁኝ። ምን ያህል የማህበረ ኦነግ ተስፋ በባልደራስ እንደተሳካ። አንድም የአማራ ድርጅት አዲስ አበባ ላይ አልተወዳደረም። አማራ የሚል ኃይለ ቃል እንዲሰወር ተደረገ። ለብልጽግና ከዚህ በላይ ስኬት አልነበረም። ለሽ ነው የተባለለት። እንዲያውም ወቅቱን በይናገሩ አጀንዳወች ባልደራስ እና የጠሚር አብይ ቢሮ በእልህ ብዙ አጥቂ እርምጃወች ተከውነዋል። ህዝቡም ተጎድቷል።
እኔ እንዲያውም በዚህ አያያዝ ወደ ሌላ ክልል ለመሄድ አዲስ አበባ #ቢዛ የሚጠየቅበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ብዬ ሁሉ የፃፍኩበት ጊዜ ነበረኝ። ዛሬም ይህ ተፈፃሚ እንዲሆን የተጋ መንፈስ የነፃነት ትግሉ ቋሚ ተንታኝ ሆኖ አያለሁኝ። በዚህ ውስጥ የሰከነ ከማህበረ ኦነግ መንፈስ የፀዳ እኛነት ይገኝ ከሆነ እናያለን። ሌላው የተደማሪ ነባር ታጋይ መግለጫ ሰጪነት ነው። ድብልቅልቅ፤ ዝርክርክ ያለ ጉድ ነው ያለው። አብረው ሲሠሩ፤ ሲደግፋ የነበሩ መንፈሶች ዛሬ ደግሞ አታጋይ መግለጫ ሰጪ ሆነው አያለሁኝ። በእነሱ ውስጥ የፀዳ ተስፋ ሊገኝ።
አንድ ሥርዓት መነሻ መሠረቱ #ዴሞግራፊ ከሆነ ተከታዩ #ፋሺዝም ነው። ይህን በዓለም ጦርነቶች ታሪክ አንብበናል። በእኛም በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደነበር ታሪክ ይናገራል። ቅኝቱ ያ ነው። ብዙ የህሊና ነቀላ እና ተከላ በመጠነ ሰፊ ደረጃ እዬተከወነ ነው። ኢትዮጵያኒዝም ማን አለው እና???
የማህበረ ኦነግ አፈፃፀሙ ድምፃቸውን አጥፍተው በቅደም ተከተል እያለዘዙ፤ እያደነዘዙ፤ እያፈዘዙም ነው። ወንዝ እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚባለው። በጣም የዘገዩ ንቅናቄወች አሁን አሁን አያለሁኝ። የማን ናቸው? ምን ይሆን መተማመኛው??? ኮንቢንስ እና ኮንፊውዝድ ማለትን ሰምተው አጣጥመው ሲዝናኑበት ባጅተዋል። እንቅላፋሙ የነፃነት ፍለጋ መንፈስ ዛሬ ምኑ ያባንነዋል? የት ነበሩ???? ያው መከረኛ የአማር ህዝብ መሪ መንፈስ ፋኖ ስለሆነ ሞቅ ሲል ከች ነው። ያ የምርጫ እርግጫም መንፈስ ሊሆን ይችላል። አዲስ ፓርቲ በአዲስ ሥምም ብቅ ይላል?
ጋዜጠኛ ይሁን አክቲቢስት፤ ፖለቲከኛም ይሁን ፀሐፊ፤ ዜጋውም ላም እረኛ ምን አለን ማድመጥ ይገባው ነበር። ምክንያቱም መዳንም መሰዋትም የወል ስለሆነ። በተለይ በጥዋቱ አሉታዊ ዴሞግራፊ ሥራ ላይ ሲውል አለመረዳት፤፦ከዛ አለመነሳት ፖለቲከኝነት ፈተና ላይ ይወድቃል። ከዘመኑ የፖለቲካ ባህሪ ጋር ስለሚተላለፍ። የሚገርመው ይኽው የዴሞግራፊ ጽንሰት ወደ ሌሎች ከተሞችም ወረድ ብሏል። ማዘናጊያ ነው ሲሉ ሰምቻለሁኝ። አይደለም። ኦነግ መርሁ መንፈስ ወረራ፤ መስፋፋት እና መዋጥ በቴዲ ርዕዮት ቋንቋ ስልቀጣ ነው። የማይችሉት ለጊዜው ትግራይ ላይ ብቻ ነው። ነገ ሲመጣ ነገ እራሱን እናያለን። ሂደቱ ግን ያ ነው።
መንግሥት ፈቅዶ ያደራጃቸው የነበሩ አሸባሪ በጥባጭ ቡድኖች ስጋት፤ ጭንቀት አምራቾች ነበሩ። ያ ደግሞ ለራሱ ለኦሮሞ ህዝብም ጠቃሚ አልነበረም። በአንድም በሌላም መንፈሱ ይጎዳል። ሰው ሲከፋው ትርፍ ነገር ሊናገር ይችላል። ወይንም በመንፈሱ መከፋቱን ሊያስቀምጥ ይችላል። ይህ በህወሃት እና በፌድራሉ ጦርነት ጊዜ ተደሞውን አንብበናል። ነገም ይህ አይደገምም ልንል አንችልም። ቅሬታ ቂመኝነትን ያመነጫል።
ቂመኝነት ጊዜ ጠገብ ሲሆን በቀልን ይወልዳል በጥላቻ ተለውሶ። ይህ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭትም ይመረትለታል። ምርጫው እራሱ እንደምን እንደተከወነ ከውስጥ ሁኖ ያዳመጠው አልነበረም። ትልልቅ ፖለቲከኞች ሳይቀሩ በሰላም አለፈ ብለው ሲፍነከነኩ ነበር። ግርም ይለኛል። ጠቅላይ ሚር አብይ ተግባራቸው ቀድመው ሠርተው የምርጫው ሰሞን የጫካውም፤ የቤተመንግሥቱም አውሎ ረብ አለ። ይህን መበለጥ መቀበል ዕውቅና መስጠት ይገባል።
ቀድመው የተሰሩ የተደራጁ ህዝብን የማሸበር፤ የማስጨነቅ፤ የመወጠር ሴራወች ለምን ዓላማ እና ተግባር ስለመሆናቸው ለፖለቲከኞች በዕድ ነበር። ከቴዲ ርዕዮት ሚዲያ በስተቀር የነበሩ ሚዲያወች ሁሉ ምርጫው እንዲሳካ በትጋት ነበር የሠሩት። ምርጫው ሲጠናቀቅ ተገልብጠው ሰው ይታዘበናል ሳይሉ ሥር - ነቀል ተቃዋሚ ሆነው አረፋ። ትናንት ለምን ለጠሚ አብይ አህመድ መንግሥት ደጋፊ፤ ዛሬ ፊርማው ሳይደርቅ ለምን ተቃዋሚ ብሎ የጠየቃቸው የለም። በዚህ ሂደት ህዝብ ተጎዳ። ነገም የሚያሳስበኝ በማይበረክት ልፍስፍስ ሃሳብ የሰው ልጅ ማገዶነት ነው።
አሁንም ኢትዮጵያን ማዳን?
ከተሞችን ማዳን?
አማራን ማዳን?
ኢትዮጵያኒዝምን ማዳን? ----
በሚመለከት በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲሸጋሸጉ በፖለቲካ ማንነት ቀውስ ሲዳክሩ የኖሩ ነፍሶች እንደምን ዘላቂ #ወህታን ሊያስገኙ እንደሚችሉ አብረን እናያለን። ከአሜሪካ አዲስ አበባ ድረስ ለብልጽግና አሸናፊነት ለምርጫው ስኬታማነት የተጓዙ ታዋቂ እና ተጽዕኖ ፈጣሪወች ሁሉ የኢትዮጵያኒዝም አቀንቃኞች ነበሩ። የጠቅላይ ሚር አብይ "ብልጽግና" በምርጫ ህጋዊ ዕውቅና ያገኜው ተፈቅዶለት ነው። ቀድመው ሊፀዱ የሚገባቸው ክንውኖችን የሠሩት ጠ/ ሚ አብይ አህመድ አሊ እጣ ነፍሳቸውን ነበር። ዛሬም እንዲሁ። በነገራችን ላይ ተጀምሯል።
ካቢኔ፤ ፌድሬሽን ምቤት፤ ፓርላማ ወዘተ አይደለም ሞተሩ። ጄኒሬተሩ ጠሚር አብይ አህመድ ናቸው። እሳቸውን የሚያስንቅ ሃሳብ አፍልቆ፤ አደራጅቶ፤ አቅናጅቶ መምራት የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ተግባር ነው። እስከ አሁን አላዬሁም። ይህም ቢሆን በተመሳሳይ መንገድ እና ዘዴ የሚሳካ አይሆንም። ፕሮፌሽናል ሰላይ እኮ ናቸው ዶክተር አብይ። ከሩቁ ጠረኑን የማሽተት አቅም አላቸው። ሙያቸው ነውና። በዚህ ልክ ነው ተቃዋሚው አቅሙን እራሱ ፈተና ላይ ሊያስቀምጥ የሚገባው። ይችላልን????
በተረፈ ውዶቼ እንዴት አደራችሁልኝ። ምንጊዜም፤ ለምንጊዜም መርህ እና ዕውነት ላይ መጽናት ለትውልድ ይሆናል። ምንም እንኳን እውነት አጃቢ ባይኖራትም። ለሰው ልጅ መከፋት ማዘን ተፈጥሯዊ ነው። እንዲመራን እንፍቀድለት። ሰው መሆናችን እንዲያሸንፈን እንፍቀድለት። የሰው #ሩብ ጉዳይ መሆን ነው አገርን ከዚህ ቅርቃር፤ ህዝብንም ከእንባ ያላወጣው።
እንደ እኔ ዕይታ ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ቲም ከሳይለንት ማጆሪቲው የተውጣጣ፤ ሊቅም፤ ሊሂቅም ኢትዮጵያን ቢመራት ባይ ነኝ። የኢትዮጵያ ተፈጥሮ ለዘመን አመጣሽ ፖለቲካ የተፈጠረ አይደለም። ለእምዬ ኢትዮጵያ ግጥሟም አይደለም ብዬ በጽኑ አምናለሁኝ። ጠሚር አብይ አህመድም የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ምርጫዬ ነው።
መፍቀድ - አለባቸው። በሰተቀር ዓለም አይታው የማታውቀው ፈተና ፊትለፊት ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ተደግኗል። ከዬትኛውም ዘመን የዓለም መሪወች ጋር እሳቸውን ማለካካት አላስቻለኝም ድርጊታቸው። ለዚህም ነው #አሳቻ የምላቸው። በእልህ፤ በቁጣ፤ በኃይል ሁለመናው ይከብዳል። መስዋዕትነቱም ግዙፍ ይሆናል። ስለዚህ ሰክኖ ማሰብ ጥፋትን፤ ውድመትን ይቀናንሳል።
ስክነት፤ ርጋታ፤ አርቆ ማሰብ፤ ፀሎት፤ ድዋ፤ ሱባኤ፤ ምህላ በግልም በወልም ማድረግ ይጠቅማል። ኢትዮጵያ ለእኔ ኢመርጀንሲ ሩም እንዳለች ነው የሚሰማኝ። ነገረ አዲስ አበባ ትኩሳቱ አህጉራዊም፤ ግሎባላዊም ነው። ግን ርጉ የሆነ የሃሳብ #ልቅና እና #አቅል አብዝቶ ይጠይቃል።
ከሁሉ በላይ ቅንነትን መቀበል፤ በዛ ውስጥ ለመኖር መቁረጥ ያስፈልጋል። ቅንነት መንፈስ እንዲሰበስብ አለቅነቱ ቢሰጠው ብዙ ዝበቶች ሊታረቁ ይችላሉ። የተበተነ ፍላጎትን፤ የተበተነ አቅምን ሊሰበስብ የሚችለው ቅንነት ብቻ ነው።
የአጣዬ ከ11ጊዜ በላይ መቃጠል፤ የሻሸመኔ፤ የዝዋይ፤ የሽዋ ሮቢት ጥቃት እኮ የዴሞግራፊ ጽንሰ ሃሳብን የማስፈፀም ፍሬ ሃሳብ ነው። የነባርነት ምነና ነው የዘመኑ ፖለቲካ ባህሪ። ነባርነትን አስመንኖ አዲስ የሆነ መንፈስን ሲቻል በውድ፤ ሳይቻል በግድ መጫን ነው። ከህወሃት ጋርም፤ ከፋኖ ጋርም ያለው ጦርነት ምክንያታዊ ጭብጡ ይህ ነው። መዋጥ፤ ጭነት ማሸከም፤ አዲስ የኦሮማይዜሽን ፍልስፍናን ማዋህድ ጉዞው ይኽው ነው። መሠረታዊው የብልጽግና ዓላማ እና ግብ ይሄ ነው። ይህ ለኦሮሞ ህዝብ ጠቀም አይደለም።
በዚህ የሚቆምም አይሆንም። እማማ አፍሪካም ቀጣይ ናት። ከምልክቶቹ በፊት እኔ በስፋት ጽፌበታለሁኝ። ሂደቱ በግርግር ፖለቲካ ሊገታ አይችልም። ከሥልጣን መንበር ካለ ጋር ትግል የበዛ ጥንቃቄ እና ተግባራዊ ክንውኑ ስክነትን መዋጥ ይኖርበታል። ግልብልቡም፦ ፍላቱም ቢያጠብቀው እንጂ መከራውን አይገታውም። ሁሉም ወደ ቀልቡ ተመልሶ ለውስጡ ቡርሽ ሊገዛለት ይገባል። ለኢትዮጵያ መርዛማ እና ጨካኝ ፖለቲካ ጥሞና ያስፈልገዋል። "ታጥቦ ጭቃ አድሮ ጥጃ" ነውና።
አብዝቼ ዝም እምለውም ቀድሜ በብዙ ጉዳዮች ላይ ስለፃፍኩበት ነው። እራሱ ብልጽግና አመሰራረቱ ጣሪያ እና ግድግዳ ተዋቅሮለት የተደራጄ አይደለም። ፎርማቱ አናርኪ ነው። ለዚህ ነው የሚያረገርገው። አስተሳሳር መርህ የለውም። የትውስትም ነው። የተዳበለም ነው ከገዳ ምልከታ፤ ከኢህአዴግ አስተምህሮ ጋር። የበዛ ጥንቃቄ በማስተዋል ነው ቀጣይ ፍላጎቶች ሊደራጁ የሚገባቸው። አዬር ላይ የማዬው የተደራጄ አቅም አላይም።
በገዢውም በተፎካካሪውም።
ቸር አስበን ቸር እንሁን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን።
እግዚአብሄርም ይርዳን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16/10/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ