ልጥፎች

ከኖቬምበር, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፍቅር ተፈጥሮ ስልጣኔ ማስተዋል ነው። Die Natur der Liebe ist zivilisiertes Verständnis.

ምስል
Für mich ist die Natur der Liebe Wissenschaft. Es ist auch eine Philosophie. ለእኔ የፍቅር ተፈጥሮ ሳይንስ ነው። ፍልስፍናም ነው።

#ብክነት ካለ #ስኬት፦ ግን #በማገዶነት። የኢህአፓ እስረኞች ፎቶውን ብሎጌ ላይ አይፈቀድም። ግን ፌስቡኬ ላይ አለ።

  #ብክነት ካለ #ስኬት ፦ ግን #በማገዶነት ።  https://www.facebook.com/sergute.selassie/   "የቤትህ ቅናት በላኝ። "   የመዋለ ዕድሜ የኢህአፓ አባላት በአገራቸው ግዞተኛ ናቸው። ማፍቀር፤ መዳር - መኳል፤ መውለድ - መሳም፤ ዘር መተካት፦ ዓይንን በአይን የማዬት ሃሴት ተፈጥሯዊ ሂደቱም እስረኛ ነው። የቤተሰብ፦ የማህበራዊ ኑሮም፥ ጤናማ ግንኙነት ድፍርስ ወይ ያጎረፈ፦ ያጎፈረም ነው። በፖለቲካ የሚሳተፍ ትጉህ ሁልጊዜም ይገለላል ጥቃትም ይፈፀምበታል። ከዚህ አስፈሪ ሂደት ነገ ትውልዱ ምን ይማርበታል???   እነኝህ ምንዱባን በዘመነ ደርግ የኢህአፓ ታጋይ አፍለኛ ወጣት የነበሩ ይመስለኛል። #ሴት እህታችንም አለችበት። በዛ ዘመን ሴቶች ደፍረው ወደ ትግል መግባታቸው በራሱ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ #ጌጥ እንጅ እንደ ዕዳ ባልታዬም ነበር። ህሊና ቢኖር። አሳረኞቹ በዘመነ ህወሃት ታሠሩ፤ በዘመነ አብይዝም እስሩ ቀጠለ። ግዞተኛ በባዕት።   እኔ የታገልኩት የፖለቲካ እስረኛ #የክት እና #የዘወትር እስረኛ ዘመን የሰጠው ገዢ እንዲኖረው አልነበረም። የሚገርመው በዘመነ ህወሃት ከነበረው በናረ ሁኔታ በዘመነ አብይ የፖለቲካ እስረኛ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ከምል ተጥለቅልቋል ብል ይሻላል። ለዛውም በበቀል የተቁላላ፤ በቅሬታ ክምችት የተቀመመ። የሚገርመው የዚህኛው የጭካኔው ስታይሊንግ ከነበሩት ገዢወች የተለዬ፤ ያልተለመደ መሆኑ ነው።    በዚህ ዘመን የሚያስደነግጡ የአረማዊ ክንወኖች ያለፋታ ህሊናችን እንዲሸከም መገደዱ ስለ ሰብ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ አብሮ መንፈሱም፤ ጤናውም እንዲደቅ ተደርጓል። በምንኖርበት የስደት አገርም ትናንትም ያሳድዱናል፤ ዛሬም ያሳድዱናል። ለምን? ያ...

ድርድር የሰላም መቅኖ ነው። #የበኽሩ ድርድር የእውቀት ዘርፍ ነው። ብልሆች በፀሎት // በድዋ ከከወኑት እዮራዊ በረከትም ነው። ለተጨነቁም ፈጥኖ ደራሽ።

  #የበኽሩ ድርድር የእውቀት ዘርፍ ነው። ብልሆች በፀሎት // በድዋ ከከወኑት እዮራዊ በረከትም ነው። ለተጨነቁም ፈጥኖ ደራሽ።   "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)   ከማገዶወች ውስጥ የተወሰኑትን አቅር ቤያለሁኝ። ስማቸው እና ተግባራቸው አደባባይ ስለወጣ እንጂ ከ10 - 20 ሺ የሚጠጉ የአማራ ልጆች በአፋር በረሃ እንደታሰሩ አድምጠናል። እነኛ ምንዱባን ምን እንደ ገጠማቸው በተጨባጭ እምናውቀው ነገር የለም። የትኞቹ በህይወት ይኑሩ፦ የትኞቹ አካላቸው ጋር ይኑሩ፤ የትኞቹ በጤናቸው ላይ እክል ይግጠም እምናውቀው የለም። መሬት ላይ አማራን የሚወክል ተቋም የለም እና። በሌላ በኩል በሌሎች ክልሎችም ከፋኖ ጋር በተያያዘ የታሰሩ የአማራ ሊቃናት ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። በአማራ ክልልም የአማራ ልጆች ማሰቃያ #ማጎሪያ የአገር ውስጥ #ስደተኛ ካንፕ መሰራቱን ቢቢሲ የአማርኛው መረጃውን አጋርቶናል።   በሌላ በኩል በግል እስር ቤትም የሚኖሩ መከረኞች ይኖራሉ። በተለይ #ገላን እና #አዲስ አበባ። ህወሃት በገነባቸው የማሰቃያ ቀደምት እስር ቤቶችም በርካታ ትጉህ የአማራ ሊቃናት አሳራቸውን እያዩ ነው። እስረኞች ቤተሰብ አላቸው። ልጆችም ይኖራቸዋል። ትዳርም ይኖራል። ያቺ ዘመን ከዘመን በቃሽ ያላላት/// የማይላት አንድዬ የአማራ #እናትም አለችበት። መኖር + ስጋት ታክሎ የአማራ መላ ቤተሰብ በግፍ እዬታረሰ ነው። በኢኮኖሚ የተሻሉት ከተሞችን በማንደድ አብሮ በማደህዬት ፕሮጀክት ዛሬ እንኳን ለሌላ ለራስም አልሆን ብሎ የሰው እጅ ተመልካች የሆኑ ከስድስት አመት በፊት ግን የፕሮጀክት ባለቤት የነበሩ የአማራ ልጆች በርካቶች ናቸው። ጫካ የገቡትም የፋኖ ታጋዮች ቢሆኑ ቤተሰብ ይኖራቸዋል...

ህግ። Die juristische Ausbildung sollte von allen Studierenden unterrichte...

ምስል
  አለም አቀፍ የሰባዕዊ መብት ድንጋጌ የታህሳስ 10, «2048» አለም አቀፍ የሰባዕዊ መብት ድንጋጌ ያልኩት ግድፈት የታህሳስ 10, 1948 ተብሎ ይታረምልኝ። ለግድፈቱም ይቅርታ እጠይቃለሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

"የሶማሊያ ፌደራል መንግሥትን እና የጁባላንድ ግዛትን ውዝግብ ውስጥ ያስገባቸው ምንድነው?" BBC

" የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የጁባላንድ ግዛት ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሐመድ ኢስላም" ከ 9 ሰአት በፊት  https://www.bbc.com/amharic/articles/cgejv7d7x7po "የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካንን ጨምሮ 18 ዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ተቋማት እንዲሁም ሀገራት ረቡዕ ዕለት በጋራ ባወጡት መግለጫ በሶማሊያ ፌደራል መንግሥት እና በጁባላንድ መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ መሄዱ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የፌደራሉ መንግሥት እና ጁባላንድ “ከተንኳሽ” ድርጊቶች እንዲቆጠቡ የጠየቁት ተቋማቱ እና ሀገራቱ፤ “ገንቢ እና አሳታፊ ውይይት” እንዲያደርጉም አሳስበዋል። በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ላይ የተሰማራው የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ተልዕኮ እና የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ጭምር የተካተቱበት ይህ መግለጫ የወጣው በሁለቱ አካላት መካከል ያለው መካረር እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት ኅዳር 1/2017 ዓ.ም. ጁባላንድ ከፌደራል መንግሥት ጋር ያላትን ሁሉንም የትብብር ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች። ግዛቲቱ፤ አዲስ የምርጫ ኮሚቴ ማቋቋሟን ይፋ ስታደርግ የፌደራሉ መንግሥት እርምጃውን “ሕገወጥ” ሲል ፈርጆታል። ምንም እንኳ የምርጫ ኮሚቴው በፌደራሉ መንግሥት ተቀባይነት ባያገኝም የጁባላንድ ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ ምርጫ ተካሂዶ ማክሰኞ ኅዳር 10/2017 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አባላት ተመርጠዋል። አዲሶቹ የምክር ቤት አባላት ደግሞ ትናንት ሐሙስ አዲስ አፈ ጉባኤ መርጠዋል። በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ደግሞ የጁባላንድ ፕሬዝዳንትን ለመምረጥ ምርጫ ይካሄዳል። የግዛቲቷ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሐመድ ኢስላም በድጋሚ ይመረጣሉ...

"የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ አገልግሎቱ ተስተጓጎለ" BBC

    "የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ አገልግሎቱ ተስተጓጎለ"  https://www.bbc.com/amharic/articles/c8dm85jvl8zo   የፎቶው ባለመብት, BAHIR DAR UNIVERSITY 21 ህዳር 2024 "በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራተኞች በሚደርስባቸው ተደጋጋሚ ዝርፊያ እና የደኅንነት ስጋት በከፊል ሥራ ማቆማቸውን ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት “ጭምብል የለበሱ” እና ማንነታቸው አይታወቅም የተባሉ ታጣቂዎች በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ ስምንት ሰዎችን መዝረፋቸው የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ሥራ እንዲያቆሙ አድርጓል ተብሏል። በአማራ ክልል ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት በሆስፒታሉ “አልፎ አልፎ” የአገልግሎት መስተጓጉሎች እንዳሉ የጠቆሙ አንድ የሆስፒታሉ ሠራተኛ፤ ከሰሞኑ በተፈጸመ ጥቃት ባለሙያዎች የደኅንነት ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ተናግረዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሆስፒታሉ ሠራተኞች እና የሕክምና ተማሪዎች ጊቢው ያልታጠረ እና ጥበቃውም ያልተጠናከረ በመሆኑ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ተናግረዋል። “ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ ማንም አይወጣም። ከሕንጻው ወጥቶ ውሃ ለመቅዳት እንዲሁም ለመዝናናት መውጣት አይቻልም። ስጋቱ ያን ያህል ስለሆነ ሁሉም በሩን ዘግቶ ቁጭ ነው የሚለው” ሲሉ አንድ የዩኒቨርስቲው የሕክምና ተማሪ ስጋቱን ገልጿል። “ምንም ዋስትና የለንም” ያሉ ጊቢው ውስጥ የሚኖሩ እና ሌላ የመጨረሻ ዓመት የሕክምና ተማሪ (ኢንተርን ሐኪም) ባለፈው እሁድ ታጣቂዎቹ ለመዝረፍ ሲሉ ተኩስ ከፍተው እንደነበር ጠቁመዋል። የሆስፒታሉ ሠራተኞች እና ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ዝርፊያ ተከትሎ “እስከ መቼ” በሚል ጥ...