????? #አገራዊ #የምክክር #ኮሚሽኑ #በኽረ #ተልዕኮ #ምን #ይሆን?????
#ዓለም #ዓቀፍ #ሰውኛ #ጉባኤ #ባለፈው #ሳምንት #ያስተናገደችው #ኢትዮጵያ #በገዢዋ #የብልጽግና #መንግሥት #በአማራ #ህዝብ #ላይ #የድሮን #ናዳ #ሲፈስ #መዋሏን #ዓለም #ዓቀፋ #ሚዲያ #ቢቢሲ #ዘገበ።
"በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ትናንት ሐሙስ የካቲት 13/2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ አራት ቤቶች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 16 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጥቃቱ በዞኑ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገሽ ቀበሌ (ሐሙስ ገበያ) በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሐሙስ ረፋድ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በሦስት ሱቆች እና ሻይ ቤት ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
"[ድሮን] ስትዞረን ነበር" ያሉ አንድ የዓይን እማኝ ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ በግምት 100 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ የጥቃቱ ሰለባዎች መንገድ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህፃናት፣ ገበያተኞች እና ሻይ እየጠጡ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።
"ከፍተኛ ፍንዳታ" መፈጠሩን የሚናገሩት እማኙ፤ ወዲያው "አካባቢውን አቧራው፤ የቤቱ ፍርስራሽ በጭስ" እንዳፈነው እና ድንጋጤ እና ግርግር እንደተፈጠረ ገልፀዋል።
ሌላ የዓይን እማኝም በፍንዳታው አካባቢው በአቧራ ጭስ መሸፈኑን ጠቅሰው፤ በስፍራው ለመተያትም አስቸጋሪ እንደነበር ተናግረዋል።
በደቂቃዎች ውስጥ ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው ቤቶች ደርሰው የቆሰሉ ሰዎችን እንዳወጡ እና አስከሬን እንዳነሱ የተናገሩት ሌላ የዓይን እማኝ "የሚጫወቱ ህፃናት እና ቆርቆሮ ሊገዙ የመጡ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል።
ከሟቾቹ ውስጥ ሙሉጌታ በለጠ የተባለ የስምንት ዓመት ልጃቸው እንደሚገኝበት የተናገሩ አንድ እናት፤ ልጃቸው ሱቆቹ ደጃፍ ላይ ኳስ እየተጫወተ እያለ ስለመገደሉ ለቢቢሲ በሐዘን ውስጥ ሆነው ተናግረዋል።
ጥቃቱ ሲደርስ ተጠራጥረው የአንደኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ልጃቸውን ሙሉጌታ ፍለጋ፣ ፍንዳታው ወደ ደረሰበት ስፍራ መሄዳቸውን የተናገሩት እናት "ልጄን ንፁሃኖች [አስከሬን] መሃል እንኩት ብሎ [ሞቶ] አገኘሁት" ብለዋል።
ሙሉጌታ ሦስተኛ ልጃቸው እንደሆነ የተናገሩት እናት፣ አብሯቸው የሚኖር ብቸኛ ልጃቸው እንደሆነ ጠቅሰው "ቢያመኝ መድኃኒት ገዝቶ፤ ቡና አፍልቶ፤ ሻይ አፍልቶ የሚታዘዘዝ ልጄ ነው" በማለት በሐዘን በተዘጋ ድምጽ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ከደረሰባቸው ቤቶች አንዱ የሆነው ሻይ ቤት በአካባቢው ማኅበረሰብ ድጋፍ የተሠራ መሆኑን የተናገሩ አንድ ነዋሪ፤ በጥቃቱ የሻይ ቤቱ ባለቤት ልጅ የሆነው ታደሰ ጌታቸው የተባለ የ15 ዓመት ታዳጊ ሲገደል የስድስት ዓመት ሕጻን ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጸዋል።
የጥቃቱ ሰለባዎች "ንፁሃን ላይ አይጥልም" በሚል ድሮኗ በአካባቢው ስታንዣብብ መዘናጋታቸውን የገለፁት እማኙ "ሰብሰብ ብሎ እየተጫወተ፤ እያወራ የነበረ" ሰው ላይ ጥቃቱ መድረሱን ገልፀዋል።
ቢቢሲ የደረሰውን ተንቀሳቃሽ ምስል እና ፎቶዎች ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይችልም ጣራቸው የተነሳ፣ ግድግዳቸው የፈራረሱ ቤቶች፣ የወዳደቁ የጣራ ቆርቆሮዎች፣ አልባሳት እና ጫማዎችን በምስሎቹ ላይ ይታያሉ።
ጥቃቱ ከደረሰበት አካባቢ በቅርብ ርቀት ሱቃቸው ውስጥ እንደነበሩ የተናገሩ ሌላ የዓይን እማኝ ጥቃት የደረሰባቸው ሱቆች የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ እና የቆርቆሮ ማከፋፈያ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የጥቃቱ ሰለባዎች በአብዛኛው "ቆርቆሮ ሊገዙ የመጡ" ሰዎች መሆናቸውን ገልፀዋል።
አስከሬን ተደራርቦ እና ከባድ ጉዳት ደርሶበት ማግኘታቸውን የተናገሩ አስከሬን ያነሱ የዓይን እማኝ ደግሞ "ደኅና ነው፤ ይተርፋሉ ያልናቸው በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ወዲያውኑ ነበር የሞቱት" ሲሉ ስለ ደረሰው ጉዳት ተናግረዋል።
12 ሰዎች ቆስለው በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ የግል ክሊኒክ መምጣታቸውን ያረጋገጡ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የጤና ባለሙያ፣ ሁለት ታዳጊዎች ወደ ክሊኒኩ እንደመጡ ወዲያ ሕይወታቸው እንዳለፈ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ከ10ሩ ቁስለኞች መካከል አራቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተናገሩት ባለሙያው፤ ክሊኒኩ አነስተኛ በመሆኑ ቁስለኞቹ ተኝተው መታከም ባለመቻላቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል።
በአካባቢው የደኅንነት ስጋት ምክንያትም ቁስለኞቹን ለተሻለ ሕክምና ሪፈር ማድረግም እንዳልተቻለ የሕክምና ባለሙያው አክለው ተናግረዋል።
ሕጻን ሙሉጌታን ጨምሮ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት በዕለቱ ሐሙስ በአካባቢው ባለ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መፈፀሙን የተጎጂ ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን፤ ማንነታቸውን መለየት ያልተቻሉ የሰባት ሰዎች አስከሬን በአንድ ላይ መቀበራቸውንም ተናግረዋል።
ጥቃቱን ተከትሎ የአካባቢው ማኅበረሰብ ስጋት እና ድንጋጤ ውስጥ መሆኑን የተናገሩ አንድ ነዋሪ፣ ጥቃቱ ለምን እንደተፈፀመ ሕዝቡ ግራ እንደገባው በመጥቀስ "ምን አድርገን ነው?" በማለት እየጠየቀ እና "እየተጨነቀ" ነው ብለዋል።
"የአካባቢው ማኅበረሰብ በጣም ነው ያዘነው። መንግሥት እንደዚህ ያደርጋል ብለንም አልጠበቅንም። የደም ጎርፍ ነው የነበረው። ንፁሃን፤ ሕፃናት ወዳድቀው፤ ቤቱ ፈራርሶ ሲታይ ሰው መሆን በራሱ ያስጠላል" በማለት ያሉበትን ሁኔታ ገልፀዋል።
"ቤቶች ተዘግተዋል። ከፍተኛ ድንጋጤ ነው ያለው፤ ከፍተኛ ሐዘን ላይ ነው ያለው። ዛሬ እኔ ቤት ወደቀ፤ ነገ እኔ ቤት ይወድቃል በሚል ስጋት ላይ ነው ያለው። [ሐሙስ] ማታ ቤቱ ያደረ ሰው የለም" ሲሉም አክለዋል።
በእነገሽ ቀበሌ እና በአጎራባች የገጠር ቀበሌዎች የፋኖ ኃይሎች እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን፤ በየጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ዋና ከተማ ግንደ ወይን ከተማ ደግሞ የመንግሥት ኃይሎች እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት የቀጠለ ሲሆን፣ በግጭቱ መካከል በሁለቱም ኃይሎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች ንጹሃን ሰዎች ሰለባ እንደሚሆኑ የመብት ድርጅቶች በተለየዩ ጊዜያት ያወጧቸው መግለጫዎች ያመለክታሉ።
የመከላከያ ሠራዊት የድሮን ጥቃት የሚፈጽመው ታጣቂዎቹን ለማደን እና ለማጥቃት ብቻ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ከዚህ ቀደም መናገራቸው ይታወሳል። "
በምሥራቅ ጎጃም በድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ 16 ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ቤተሰቦች ተናገሩ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ