የእቴጌ ጎንደር #ትናንት ይጠራ! ናልኝ አጤ ትናንት የእኔ ሸበላ - በመሸቢያ!

 

የእቴጌ ጎንደር #ትናንት ይጠራ! ናልኝ አጤ ትናንት የእኔ ሸበላ - በመሸቢያ!
 
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።"
 
 May be an image of one or more people and crowd
 
ሽው አለኝ - ሽው፤ የተሰራሽበት ቀመር ------በምልሰት
ትዝ አለኝ ትዝ፤ የተመሰጠርሽበት የልቅና - ፍጥረት
አንቺ ወይዘሮ እሜቴ፤ የሺ ዘመናት #የላቂያ ምህረቴ
እንዴት አለሽልኝ - የእኔ ውዴ?
የእኔ - ህሊናዊነቴ!
ህላዊነቴ!
 
እሙ የእኔ ልዕልቴ፤ ሥህነ - እመቤት - ፍቅርቴ
የናፍቆት የስስት ሃብል ትፍስህቴ፦
የጽናት #ጽላቴ፤ የትርታዬ - እትብቴ ብቃቴ፦
እንዴት አለሽልኝ የመኖር ዘይቤ አውራ የእናቴ
የማንነቴ ምስባክ ጥበበ - ትንግርቴ።
አንች የዘመን #ኮንፓስ፤ አንቺ የሜትሮፖል አናት - ህብስቴ
አንቺ የህብራዊነት ካንፓስ፦ የመኖር ግብረ ሰብ - ግርምቴ፦
የጀግንነት፤ የአንድነት፦ የህብረት መለዮ አሻራ - ጉልላቴ
እኮ እንደምን አለሽልኝ የእኔ ቀለበቴ፤ የውስጥነት - ብርክቴ?
 
… ሳማትርሽ ግን #ሳልመትርሽ ……
 
የተበጀሽበት ዘሃ ግራው፥ - ጥልቀቱ
የተቀመርሽበት የልቅናው፦ - ባዕቱ
የተዋህድሽበት የዊዝደም፥ - ጉልላቱ
የዕድምታ፦ የተደሞ፤ የቅኔ፦ የድጓ፥ የዝማሬ የተክሌ አቋቋም ህብስቱ
የንባብ፤ የመፃህፍት፦ የትርጉም ሃውልተ - የሚስጢራት - ቁልፍ መፍቻ ሟተቱ
የት ሄዶ ይሆን እንዲህ ዛሬ የአንቺ ውሎ እና አዳር የናዳ መገማሸሪያ
ሆኖ የተገኜውየሞገድ መቅዘፊያ፦ መዳረሻ _______
የቻለውም /// ያልቻለውም የሆነው የአፍ መፍቻ ማሟሻ????
 
#እ………
 
እኮ! ሆድዬ የእኔይቱ - የጣይቱ - የምንቴወቹ - ምነው - ምነው ምነው?
…… እንዲህ ወጀቡ በግራ ቀኝ ተበራከተ - የኛይቱ?
የድፍረቱ - የፍጥረቱ፦ የእላፊው፤ የጥድፊያው -------ውርክቡ
የእንቧይ ካባዊ- የሁካታው ጩኽቱ፤ የመዳፈር ወጋወጉ
ሳደምጥ -- ስሰማ፤
ወተትሽን ጠብቼ --- እንዳላደኩኝ
መናሽን ተመግቤ #እንዳላሰበልኩኝ
ከአንቺ በመፈጠሬ የሁለመናዬ መሳደድ፤ መገለልን ተቀብዬ
እንዳልኖርኩ፤ እንደማያውቀው ---- ዛላዬ
እንደ እመው ዝም፦ ጸጥ አልኩኝ
ግን ልክ ነኝን?
ዳኝው ---- እመዬዋ።
 
#ህእ……
 
የአሁኑስ - በዛ!
የአሁኑስ - ገለማ!
የአሁኑስ ከረፋ!
#ተገባሪ -------አንቺው፤
ማገዶይቱ ---------አንቺው፤
ይህም ሆኖ ዘላፊሽ ተበራከተ ---- ተዳፋሪሽ #ቃ አለ።
ህምታዬ! -------በዝምታዬ - ድውለት
እምታዬ! ----------በተደሟዊ - እልበት
በበዛ ትዕግሥት - በቆልተ --- ቁሊት
በዝግታ ረብ ------------#ታ
መዘግዬቴ፤ የብዕርና ብራናዬ ጥሞና
ሲስተጓጎል --- ያ ብሩኽ - ገና
ብርኃነ ልደቱ ቅጥ መጠን - ሲያጣ
ዓውደ ዓመቱ በልሙጡ - ሲቀጣጣ
ጣ --- ጣ - ሰላማውያን በአደባባዩ ሲሰጡ አካላቸው --- ሲቀጣ
አስቀድሜ ተውን ነበር --- ተማጽኜ
ግን ሰሚ --- አድማጭ ጠፍቶ፥
እንሆ መከወኛው በማቅ ተጥፎ - ተጣፍቶ
ሊቃውንቶችሽ በምንጣሮ ሰከኑ --- ውል ተከፍቶ፦
ግን ጥሞናዬን ዘለግ ማድርጌ ትክክል ነኝ???
ልዕልት ጎንደር ሆይ! - ህግ ነሽና ዳኚው፦
ቻይ እና ችሎት ሁነሺው ስለኖርሽ ባሊህ በይው።
 
#ህ ………
 
…… ብቻ ---- ልዕልቴ
……… የእኔ ውበተ ፀዳል -- እውነቴ
የግንባር ሥጋዋ በዕቴ------
በምሰማው - በማደምጠው
በሽታሽቶ #በሚገርፋሽ -
ሳይደክማቸው በምላስ መዶሻ #በሚደበድቡሽ
በፋሳዊ ---- አንደበታቸው______ በሚቀጠቅጡሽ፦
ከአንቺ የተነካካ ሁሉ ፍጥረተ ነገሩ ሲለበለብ በወልዮሽ
ዕለትሽ ቀራኒዮ ይሆን ዘንድ በተለሙሽ፥
የዬዘመቻው ጥሪ የአንቺ ፍሬ የአብርኃም ------------በግነት
አይበቃም! ወይ - የመቀነስ ከርቤነት።__________???????
 
***
 
ልክሽን ---- ሳያውቁ፤ ካለልካቸው፦ እላፊ ሄደው በሚያብጠለጥሉሽ፤
አብረው ተባብረው #በሚጠባብሱሽ - በሚቀቅሉሽ፤
አንቦልቡለው በሚድጡሽ- በሚጠቀጥቁሽ፤
በሚደልዙሽ ሁሉ በውነት ---- አዘንኩላቸው፤
ልክን አለማውቅ ከልክ አለማድረስን
የአንቺው ይትብኃል ----------------ሲመሳጠር ቁጭ ብዬም አስተዋልኩኝ
ተማርኩበት።
ከ"ሀ" ተነስቼ ፊደል ቆጠርኩበት ~~~~~~~
"ፐ" ላይም መዳረሻዬን አግኝቼ እርገትን አስተዋደድኩበት፦
እታለም፤ እናታለም፤ እናና ___ እናኑ እናትዬ -- ማንጠግቦሽ -- ወለላዬ በጥልቀት ምከሪ
በምጥቀት ከፈጣሪሽ ጋር ዘከሪ፦
ወንፊት ግዢ ማንዘርዘሪያን --- ድፈሪ
ትርፍና ኪሳራውን በቅመመ አስሊ ---
መንሹን አክይና --- አስማሚ
ሰብልሽን ---- አጠቅሚ።
 
ናፍቀሽኛል!
ጥቃትሽ ቆርቁሮኛል!
ቁርጥ ውሳኔ እንደሚያስፈልግሽ አምኛለሁኝ!
ትናት በሆነው ፍካት፤ ልጅሽ ሁሉንም ሆኜ አሳክቸልሽ ነበር፤
ያን ግን በቅጡ የሚያስተዳድር ብልህነት ተሰወረ፤
እንሆ ______የማይገኝ ዕድል ______°°°°° በካከነ
ግን ሁሌም ቅብአሽ አለና --- እንደ አበራሽ
ሁሌም - እንደተቀናብሽ ~~~~
እንደ ቀደምሽ መኖርሽ ___ ሥጦታሽ!
 
 
የእኔ ሚዛን፦ ቅድስትዬ - በጉዳትሽ ሁሉ ከውስጤ አነባለሁኝ
ለልባዊቷ ጎንደሪና ቀኗን አምጣላት፦
ከሱናሜው ገላግላትም ብዬ እጸልያለሁኝ፦
እሱን አንድዬን አማኑኤል አባቴን፦ እማጸናለሁኝ፤
የፍጡራን ደም ብትን አፈርሽ የማይቀምስበትን ዘመን ሱባኤ አልማለሁኝ
እመቤቴን፦ ውጽፍተ ወርቅንም፦ ቀኑን ከቀኑ አሳትርቀሽ አማልጂን እጠይቃለሁኝ
መሰዋትሽ፤ በከንቱነት ሲወራረድ አያለሁኝ፤ አደምጣለሁኝ፤
ቀና ስትይም አይሹቱም ያወግዙታል፤ ያቃልሉታል ……
ብቻ ፈተናሽ _______የፊደል መማሪያሽ ይሆን ዘንድ እመኛለሁኝ።
 
……… #በመቀጠል ለተዳፋሪወችሽ ግን አያውቁሽም - እና………
 
እግዚኦ! አልኩ አከልኩት - መሃከነ!
ማረን አልኩ ጨመርኩት - ተሳህለነ!
አንቺ ወይዘሮ እሜቴ፤ የእኔ መጠሪያ የሚስጢሬ ሟተቴ
የእቴጌወች፤ የነገስታት፤ የወይዛዝርት፤ የአንቱወች፦ የአራት ዓይናማ ~ትንግርቴ
የሥልጣኔ - አብራክ፤ የባህል - አውራ፤ የማህሌት - የጽጌ ወይን #ሐረጋት
የበሞቴ፤ የአፈር - ስሆን፤ የእሽታ እመቤቴ!
የሙያ ድንቅነት - ህይወቴ፤
ሁልጊዜም ዕንቁ፤ የምንጊዜም መራሂቴ
ነሽ የገብረ አጋይሥት ሰናይቴ።
የድቁና፤ የቅስና፤ የቆሞሳት መላከ ብርኃናት፤
የሸኽወች፤ የሃጂወች የድዋ፥ የሱባኤ ተፈጥሯዊ እናት
የህብር - የአብሮነት የተፈጥሯዊነት - አስባላት ልዩ ማዕዶት
የመሪነት የአገዛዝ አብነት የልሳነ ወርቅ
የተቋማት ድርጁ ተምሳሌያት፦ ዕንቁ።
የእኔ ዘንካታ ደርባባ የ፵፬ ዕንቁ ዘንጋት፦
ያን ሁሉ ዘመናት ትብትብ የፈተና ልቃቂት፦ የምጥ ሂደትን እንደምን - ተሻገርሽው?
 
እንደምንስ አገር መራሽ?
እንዴትስ ለዛ ሁሉ ዘመናት የፈላስፊት ኢትዮጵያ ባላ ወጋግራ - ሆንሽው?
እባክሽን እምዬዋ በምልሰት #ጥበብሽን እንደገና ሸምኚው ወይንም አበራይው?
ያነን በብቁነት የነገሽበትን፤ በክህሎት ያነገሽበትን ዘመን መልሰሽ ጥሪው
ናልኝ! ድረስልኝ! ልምድህን መግበኝ - በይው?
አንቺ እኮ፤ አንቺ ነሽ፤ ጥሩ የነጠርሽ
ቢፈሩሽ ሆነ በነጋ በጠባ ቢያነሱሽ ቢጥሉሽ ቢፎካከሩሽ፤
አይደንቀኝም - እናት ቀኑብሽ፤
በዬዘመኑ "እንዳያማ ጥራው፤ እንዳይበላም ግፋው" መባልሽ ነው ዕውቅ፥
ግን ከድምቀትሽ ሆነ ከድንቅነትሽ አላልሽ ፈቅ። 
 
……… #ብቻ ………
 
አከበርነሽ ሲሉም ከአንጀት ይሁን ከአንገት፤ አይሞቀኝ_____ም
ካለልክ በተሰፋ የፍላጎት ጥብቆ ሆነው ሲያጣጥሉሽም______ አይደንቀኝም፤
በምልዓት ያለሽ፤ በማይዳሰስ ፀጋ እና በረከት ሞልቶ የተረፈሽ፤
ለማግሥትም የሚኖረሽ ነሽና ዲታ #ቀኝ
እመ ቅንዬ - የበጌምድር ጥልፍ፦
የስሜን ቀለም ቀንዲል ንድፍ፦
የእርጋ ኪዳን መስታውት፦
የዕልፍ ልቅና በልዕልና የተሞሸርሽ ነሽና --- ራዲዮሎጂ
የመንፈስሽ የፀጥታ፥ ግርማ - ሞገስ አስራደ እንጂ።
ትናት_____ን በሐዋርያነት ~~~~~~~~~~~~የቀመርሽ
ዛሬን______ም እዬታዘብሽ ~~~~~~~~~~~የቀደሽ
ነገንም እዬባረከሽ ~~~~~~~የምታስጎበኝ
የጥርኝ አድባር #ህግ ነሽ።
 
…… #ግራሞቴ ……… በክራሞቴ ……
 
ንባብም -- ትርጉምም --- ፊደልም --- አናባቢ --- ተነባቢም --- በመሆንሽ
ውለው አድረው ሲያብጠለጥሉሽ ………
አግልለው /// አስገልለው ……… አዋርደውም___ ሲያጣጥሉሽ፦
ደግሞ ይፈልጉሻል፤ ካለአንቺ፦ ካለ መሠረት፦
ካለ ካስማ፦ ክብርም ማዕረግም የለምና።
ስታሳድጊኝ በቀልን - ቂምን ተጠዬፊ ብለሽኝ ነበር____________ና፥
ወደ ልቦናቸው ጌታዬ ይመልሳቸው ዘንድ ከንበል ብዬ ጠዬኩኝ______ና፤
ማገዶነትሽ ተፈልጎ፤
ሥራ ማስኪያጂያ ሆኖ፤
ግብርነትሽ ግን ተዳፍኖ> ተቀብሮ - ተከድኖ
ዕውነት - መኖ! መንምኖ መኖ!
አንቺ ለቸርነት- ለሁሉዬነት እንጂ መቼ ለልዩነት ተፈጠርሽ_____ና
አንቺ ለህብራዊነት፦ ለከበቡሽነት እንጂ መች ለህግ ተላላፊነት ተመረጥሽ____ና
ሚስጢርሽን በልኩ ያመሳጠርሽም፥ ነሽ_______ና
ና! ናና! በይው ቅዱስ ያሬድን በጠራሽበት ጹዑም - ቃናሽ
ና! ናና በይው አባ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን የሳብሽበትን- ዜማሽ
ና!ናና! በይው አጤ በካፋን ግዛኝ - ምራኝ ብለሽ የፈቀድሽበትን - ብልኃዊነትሽን፣
ነይልኝ እባክሽ በሞቴ ብለሽ አሳስቢያት፤ እቴጌ ማርያማዊትን ያጸደቅሽበትን ውልነትሽን።
 
…… #ጥሪው ……
 
የአጤወቹ #ማግኔትሽን
የ፬ቱ አቅጣጫ ሊቀ - ሊቃውንቱ - መሳቢያሽን
የአላማጅነትሽ ወረብሽ ይጠራ ዛሬ ______
ተጣሪ! አንቺ የተግባር ትንታግ --- ገበሬ!
ትጋትሽ --- ይናገር - ይመስክር - ይወጅ - ሃቁን ይዘርዝር ……
የዘመናት ማዕዶተ የተግባር ዓውደ ምህረትሽ - ይመንዝር
አንቺ የዕውነት ጓል፤ አንቺ የሃቅ ፍልቅ፦ እባክሽን ከቅጽበታውያን ተለይ፦
ከስሜታውያን ማህበር ተለይ ……
ከሚያንጓጥጡሽ፤ ከሚዘልፋሽም ተለይ ………
አንቺ ለግለሰብ ሰብዕና ማሟሻ ሥራ ማስኬጂያ አልተፈጠርሽምና --------።
አንቺ ዛሬ ተመስርቶ ነገ በሚናድ የሰውኛ ዕለታዊ እንክብል አልተበጀሽም____ና
የአንቺ ጥሪ ሌላ፤ ፍጹም ሌላ ነው፤ የአህጉር ፓላስ
የአገር ምስባህክ ስዋሰው፦ የትሩፋት ቅጽ መስተዋድድ
የድንጋጌ ዶግማ ብርቱ ክንድ ………
ልቅናሽ - ሊቅነትሽ፤ ዝክረ - ተመክሮሽ
ለግርግር ወከባ --- ጥብቆ ነውና
ካለተፈጥሮሽ በዬዘመናቱ መገበርሽን ደግመሽ፤ ደጋግመሽ መርምሪው፦
የቀደምት ምግባረ - ሰናይ ሰነዶችሽን ቅርስ ውርስሽን ፈትሺው ……
ሁለመናሽን በጥልቅት መርምሪው፦
ሳያውቁሽ_________________|______ #ላጩሽ
ሳያጠኑሽ______________ #ለወጠኑሽ
ተሰርተሽ ማደርሽን፦ የዘመናት የልቅና ሊቅነት መሪነትሽን
……… መዝገቡን ግለጪ! አሳምረሽ - አስምሪ! አትሚም።
 
…… በውሽክታ የሳቄ #ምጣት
 
በምን --- አቅም?
በምን --- አደብ?
በምን---- አቅል?
በምን --- ክህሎት?
በምን ---- ልቅና???? ______ አንቺን ሊመሩ እንጎቻ አነጎቱ?
ጠይቂያቸው --- ይዠሻለሁ በሰለስቱ ……
ፈትኛቸው ካሰኜሽም በማስተዋልሽ ፍተያቸው ---- አዳዲስ እጮኛወችሽን?
ስኬታቸውን ያቀርቡ ዘንድ አስታውሻቸው፦
በትነው - ሊበትኑሽ ከሆነም ሃግ! በያቸው፦
ጠቀሜታውን ለኪው፦ መሪ አልቦሽነቱን በልኩ ለኪው፤
እረኛ አልቦሽ ስትሆኚ፤ በምንጣሮ እስከ መቼ ልዝለቅ ብለሽ _____አፋጥጫቸው?
ባክነው _______አባካኑሽ፤
ርጉ መንፈስሽ፤ ተፈሪ ፀጋሽ ደፈረሰ፦
ውርስሽ ተሳሳ።
 
ከመቼ ወዲህ አንቺ ታውቂና ከዘለለው ጋር - ተዛለሽ?
ካጎፈረው ጋር አጎፍረሽ ታውቂና አንቺ - የተከበርሽ?
ባለ ጽዑም ለዛ ልስሉስ መንበርሽ
ርጋ ነው ስክነት ወግሽ
ክሱትነትሽ።
 
* እና --- * እናማ ---
 
በልቅናሽ ልኬታ አዳዲስ እጮኛወችሽን በልካቸው አወያያቸው፦
ወይንም ሙያ በልብን መስጥረሽ እሱ እራሱን አዋውይው።
የቀደመው ነብይነትሽ እንሆ ይጠራ ---
አጤ ትናት ውዱ ክብሩ ይጎምራ
ብራን ያብራ!
 
ሥጦታ ዘመን ለማያፋድስታ፤ ወቅት ለማያውይባት፤ ሁነት ለማይበውዝታ፦ ለጽኑዋ የጽናት ንግስቴ ለልዕልት ጎንደር ተፈጥሮ ይሁንልኝ።
01/05/2025 ሲዊዘርላንድ፤ ዙሪክ፤ ቪንተርቱር።13.306ሰዓት።
 
ውዶቼ እንዴት ናችሁ?
ደህና ናችሁ ወይ?
መቻሉ በዛ እና መረማመጃነቱ አና አለ።
የሆነ ሆኖ ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
እንከባበር!
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?