የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ #የፈረንሳይ ጉዞ እና ዕይታዬ።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ #የፈረንሳይ ጉዞ እና ዕይታዬ።
#እፍታ።
በጣም ረጅም ጊዜ ሆነኝ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ፎቶ ለጥፎ መሞገት ካቆምኩኝ። ምክንያቴ #አመክንዮዊ ነው። ዛሬም ግጥም የሆነ ቁምነገር ተገጣጥሞብኝ ነው እንጂ ፍላጎት የለኝም የሳቸውን ፎቶ ለጥፎ መሞገት። የሻሸመኔ ሰማዕትነት ሂደት ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፍላጎት ሞተሩ ተተከለ። ጥረታቸውም ድሉን ሀሌታ አለ። የአሜሪካ ጉዞ እና ስደተኛው ሲኖዶስን …?// የህክምና ባለሙያወች ለምግብ እጥረት መጋለጥ አቤቱታ እና የነነዌ ሱባኤ በኢትዮጵያ እና የጠቅላዩ የፈረንሳይ ጉዞ የዛንጊዜውም ሆነ የዛሬው …???
ዘመኑን እኔ #አሳቻ እለዋለሁኝ። መሪውንም ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊን አሳቻ መሪ እላቸዋለሁኝ። የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬም አሳቻ ነው እላለሁኝ። ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ሳትሆን አሳቻ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነው የሚገባኝ። መስቀለኛማ ወይ ስሜን፤ ወይ ደቡብ፤ ወይ ምስራቅ ወይ ምዕራብ ትንሽ ዘለግ ሲልም ስሜን ምስራቅ፤ ደቡብ ምዕራብ እያለ ይቀጥላል።
አሳቸነት ግን አቅጣጫውን ለመወሰን ይቸግራል። አቅጣጫውን ለመተንበይም #ጋዳ ነው። በጠቅላይ ሚኒስተሩ አውሮፕላን ስደተኛው ሲኖዶስ ወደ አገር ሲገባ ማን ይህ ይሆናል ብሎ ተነበዬ? ማንም። ሐሤታችን ከእልልታ በላይ ነበር። ይዘው የወሰዷቸውን አትገቧትም ብለው "አገር ናት ያሏትን" ሃይማኖት ቢዛ ሰጪም፥ ነሺም ሲሆኑ ማየት የሚተነበይ አልነበረም። አሳቻነትን ቢገልጽልኝ ብዬ ነው ይህን ለንጽጽር ያቀረብኩት። ደጋፊወቻቸውም፤ አክባሪወቻቸውም ሆኑ አጋዥወቻቸው ያወቋቸው ይምስሏቸው እንጂ አያውቋቸውም።
///
ከወፍ ዘር #የፒኮክ አማልክት ይቀርባቸዋል። ተቀምጦ ከመስራት በጉዞ አቅዶ በጉዞ ጉብኝት ላይ የአትኩሮት ሚዛናቸው ያደላል፤ ከብቻ ጉዙ ሙሉ አካል ይዞ መንቀሳቀስ ያዘወትራሉ፤ አደጋም ቢመጣ ተተኪ አልቦሽ ዓይነት። ዝቅ ካለው የኑሮ ዘርፍ ከሚኖረው ዜጋ ይልቅ የላይኛውን ድሎተኛ መራጭ ናቸው። ፖለቲካቸው - አቋማቸው - ንግግራቸው - ትልማቸው - ጉዟቸው- - ውሳኔያቸው #አሳቻ ነው። ይህን Sergute Selassie ሥርጉተ ሥላሴ ዩቱብ ቻናሌ ላይ በድምጽ ሠርቸዋለሁኝ። ሁለት ዩቱብ ቻናል ስላለኝ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሥሜ በተፃፈበት በተሠራው ዩቱቤ ላይ ነው ያለው።
ጉዟቸውም #ድንገቴ ነው። ዜና ሲፈጥሩም #ድንገቴ ነው። ሁልጊዜ ዜና የሚቀርጹት እሳቸው ናቸው። አቅጣጫው አሳቻ ነው። ገርበብ ያለ ነው። #ገርበብ ያለ ብቻ ሳይሆን #የተርገበገበ ነው። ባይብሬሽን ይበዛዋል። አንድ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ ሲከሰት አጀንዳውን ይዘው አወያይተው አያውቁም። አይተው እንዳላዩ ይሆናሉ።
ሌላ ኢቤንት ፈጥረው በዛ #አስታከው - አቃለው - ደፋፍነው አለባብሰው ያነሱታል። ጭራሽ ከማይገናኝ ኢሹ ጋር ያጋቡና ወቅታዊ አገራዊው ሁነት አቅሙን #ያባክኑታል። ጦርነት - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ - የጀምላ እልቂት- ራህብ - ጠንከር ያለ የሃይማኖት ንቅናቄ - ወይንም የህዝብ የበቃን ንቅናቄ ሊሆን ይችላል። በገጠመኙ ይጠቀማሉ። ሲሰኛቸው #ድፍርስርስ አድርገው ያጎሹታል። ከዛ ማጣለያ፦ ማንዘርዘሪያ፤ ጠፈፍ ማድረጊያ ወይንም ማጥለያ እሳቸውን እራሳቸውን መፍትሄ አፍላቂ ፈላስፋ አድርገው #ዕድሜ ለአብይዝምን #አሰከነው ይቋጩታል።
የሚገርመኝ ተፎካካሪወቻቸው #በተለመደው መንገድ መጓዛቸው ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አሊን አቅመ ቢስ አድርገው አቃለው ማየታቸው ነው። ለትልማቸው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ትጉህ ናቸው። አያይዘው - አዋደው - አዋህደው ነው የሚፈጽሙት። ይህ ከስንፍና ወይንም አቅም ከማጣት ጋር ምንም ነገር አያዋድደውም።
አሁንም የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ስደተኛው ሲኖዶስን ወደ አገር ይዘው ሲገቡ የተሰጠው መንግሥታዊ ክብር እና ዛሬ ሞተራቸውን እንደምን እንደ ተከሉ አማሳጥሩት። ይህ ጅማሬ ነው። ገና ምን ታይቶ? ቂም - ቅሬታ - ቁጭት የፈጠረ መንፈስ በያንዳንዱ እርምጃቸው አስተውላለሁኝ። የተዘጋጁበትን ነው ሂደቱን እየመሩ ያለበት። የሆነ ሆኖ የመንበሩን ጉዳይ መጎርጎር ብቻ ሳይሆን የኮሪደር ልማት ብወዛ ሁሉ ይጎበኘዋል። የጎንደር ከተማን መንፈስ ተጫኝ እጅግ አስደንጋጭ #ግራጫ መንፈስ ሲያለብሱት ምክንያት አላቸው። የፋሲል ቤተ - መንግሥቱን ነጭ ጀሶ ሲያስታጥቁት በዕቅድ ነው። ይህ ዛሬ አይመሰክርም ሲመሽ ይታያል። ይህም ጅማሬ ነው።
የጎርጎራ ፕሮጀክት የሳቸው አልነበረም። አስበውትም አያውቁም ነበር። ቢሯቸው አማራ ክልል ሳለ ፋሲል ግንብም ጎርጎራም ሄደው አያውቁም። ይህ ዕውነት ነው። ቀደም ባለው ጊዜ በዘመነ ደርግ የመዝናኛ ማዕከልም ነበር። በአሁኑ ዘመን ደግሞ የጀግና ሻለቃ ኃይሌ ፕሮጀክት ነበር። ነጥቀው ወሰዱት። እንዲህም አለ። የሚቀድም መንፈስን አይሹም። እሳቸው የሚሠሯት ኢትዮጵያ በጀግና ኃይሌ ውስጥ ያለችውን አይደለምና። አይደለም ፕሮጀክት ያልተለመዱ ሙሽራ የአባባል ዘይቤ ካገኙም የሳቸው አድርገው ቀብ ያደርጉታል። እንዲህ የሚያደርጉ ጸሐፊወችም አሉ። እሳቸው ብቻ አይደሉም እንደማለት።
የሆነ ሆኖ የአማራ ክልል መሰተዳድር እንደዛ በደም አላባ ሲጥለቀለቅ፦ መሃል አዲስ አበባም የሠራዊቱ ቁንጮ ሰማዕትነትን ሲቀበሉ ዛሬ መዋቅሩ በዚህ መልክ ይበወዛል ብሎ ያሰበው አልነበረም። ከልብ ሆናችሁ ተከታተሉት።። የጎንደር ከተማ ከንቲባ ስንት ጊዜ ተቀየረ??? መደበኛ ሥራቸው ነው። ነገም ሌላ በጣም ሌላ ጉዳይ ይጠብቀዋል አማራ ክልል። ደቡብ ክልል ምን እና ምን እንደሆነ የ11/11 ጉዳይ ሲወጠን የገባው የለም። የካቢኔው አብዛኛው የደቡብ ሊቃ ያደረጉበት ሂደትም እራሱ ፍች ይሻል። አይተኙም። አያንቀላፋም። አይሰንፋም። ለፈለጉት ቅርጽ እና ይዘት ሌት ተቀን እየተጉ ነው። ይህን መንፈስ እንደ ትርፍ ሥራ የሚታየው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መመከት ቀርቶ መረዳት ይችል ይሆን????
በየፈተናው ክስተት የሳቸው ድንገተኛ ጉዞ አለ፦ የአባይ ጉልላት የኢንጂር ስመኜው ህልፈት ጉዞው አሜሪካ ነበር። የጃዋሪዝም ተከበብኩኝ የኦሮምያ ላይ የነበረው የንጹኃን ዕንባ እሳቸው ራሽያ ነበሩ። የአማራ ክልል የሊቃውንት ግፋዊ ጭፍጨፋ በኋላ እሳቸው ምጽዋ ላይ ሽርሽሽር ነበሩ። የሻሸመኔው የሰማዕታት መከራ ጊዜ እሳቸው #ፈረንሳይ ነበሩ።
ዛሬም የቅድስት ተዋህዶ ኒዩክለስን መሠረቱን ካስጣሉ በኋላ እሳቸው #ፈረንሳይ። #አሸንፈው ማለት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ እሳቸው #ያላቀዱት ራህብ የቀሰቀሰው የጤና ባለሙያወች ንቅናቄ እንዳላዩ፤ እንዳልሰሙ ሆነው ጉዞ ወደ ፈረንሳይ አድርገዋል። በፈረንሳይ ሁለት ጊዜ ጉዟቸው ውስጥ ሲመለሱ ፈረንሳይ በህዝብ #ነውጥ ተንጣለች። ልብ ያለው አልነበረም። እኔ ግን ጽፌበታለሁኝ። አሁንስ እሳቸው ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ምን ይፈጠር ይሆን በፈረንሳይ?????
ይህ መንፈስ ምንድን ነው? በስሜት የሚመራው፤ ገጠመኝ ሥራ ማስኬጂያው የሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና አብሯቸው ያለውን መንፈሳቸውን ለመመርመር በሱባኤም ይሁን በድዋ፤ በኢነርጂ አምላክነት ይሁን በአይዲያሊዝም ፍልስፍና ቁጭ ብሎ ሊጠና፤ ሊመነዘር እና ሊዘረዘር አይገባም ወይ? አቅም ካልተመጣጠነ ልፋቱ ሽንፈት ስንቁ ይሆናል እና።
በአህጉሩም በእማማ አፍሪካ ይሁን በጎረቤት አገሮች በዚህ ፯ ዓመት ውስጥ ያሉ ውጥኖች - ቀውሶች- ጦርነቶች - ትርምሶች እና ተስፋወች፤ በግሎባል ደረጃ ይህ መንፈስ በማጥፋት ይሁን በማልማት እረገድ ያለው ድርሻ እንዴት ባጄ ወደፊትስ ብሎ መመርመር ይገባል?? የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከ፲ ጊዜ በላይ በኢትዮጵያ ጉዳይ መሰብሰብ እና የኖቤል ሽልማቱን ሂደት ሁሉ አደብ ገዝቶ ማጥናት፤ መመርመር ይገባል።
///ብልጽግና የማን ነው?
///ብልጽግና ለማን ነው?
///ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ማን ናቸው? የማንስ ናቸው?
ነገን መተንበይ በተተነበየው ልክ ከግብ ይደረሳል ወይ? ለመተንበይም ሆነ ለመፈጸም ከተለመዱ አሰልቺ ተደጋጋሚ ዲስኩር፤ ከለመድናቸው ገጾች እና ገጸባህሪ ውጪ አሳቻውን ስውር መንፈስ የሚመክት ምን አቅም? ምን ክህሎት ይኖር ይሆን???
ለተዋህዶ እጮኛነት ማን ታጬ? ደቡብ ወይንስ ---------? ያልተለመዱ - ያልተደጋገሙ ወይንስ ገጠመኝነቱ ሰበርነቱ ለእኛ እንጂ ለጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ትልሙ፦ ታቅዶ መከወኑ የጠቅላዩ ነው። ባየሁት ፯ ዓመታት ሂደት አንድ አብይዝም ሳይሆን ወዘተረፈ የአብይዝም ትወናው በተሟላ ባንድ ሲከወን ነው እማዬው።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ንግግራቸው ሁልጊዜ #ሽፍን ነው። ለትርጉም አሻሚ ነው። ለእኔ ሃይማኖታቸውም እንዲሁ አሳቻ ይመስለኛል። እንዲያውም የሚያደላው ዕሳቤየ ኢነርጂ ይሆን እላለሁኝ። ማንም ሊቅ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይን አወቅኳቸው ሊል የሚችል አይመስለኝም። አሳቻ ክስተትን የማንበብ - የመተርጎም - የማመሳጠር ልከኛ አቅም ይጠይቃልና።
ብዙ ነገሮች ከሆኑ በኋላ ነው ትችቱም፤ ወቀሳውም የሚመጣው። ከመሆኑ በፊት ቀድሞ መሰናዳት የተፎካካሪው ድርሻ ነበር። በራሱ አቅም መፍጠርም የሚታሰብ አይደለም ተቃዋሚው። ይልቁንም አቅም ባለበት ሄዶ ይዳበላል ከዛ የኮፒ ራይት ፍልሚያ ይገናል፦ በማህል የተጀመረው ሂደት ትርምስ ገዢው ይሆናል። ድካሙም ……… መስዋዕትነቱም ………
ለዚህም ነው እኔ ዘለግ ላለ ጊዜ በዝምታ የቆየሁት። የሰባዊ መብት ጥሰቱን እና ጉዳቱን ብቻ እየዘገብኩኝ። ሚዲያወቼን ዩቱብ ቻናሌን፤ #የጸጋዬ ራዲዮን፤ እና በቅርብ የጀመርኩት ቲክቶኬ ሁሉንም ከዛሬ 15 ዓመት በፊት ተመድን እና አውሮፓ ህብረትን በትህትና በጠየቅኩበት የፍቅር ተፈጥሮ እና ህግ የዜጎች መደበኛ ትምህርትም ሙያም ይሆኑ ዘንድ ይወሰን ባልኩት ላይ ይተጋሉ።
ከመዋለ ህፃናት ጀምሮ ትውልድ የፍቅር ተፈጥሮ ካሪክለም ተነድፎለት ይማረው። ህግ የባለሙያወች ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ ይሁን በሚለው ሚዲያወቼ ሁሉ እንዲያተኩሩ አድርጌያለሁኝ። ድምጼ ድምጽ ካወጣ፤ ከማይክ ጋር ከተገናኜ ሰውነትን፤ ተፈጥሯዊነትን፤ መርህን በማክበር ላይ ብቻ ሊሆን ይገባል ብዬ ከወሰንኩ ቆየሁኝ። የፖለቲካ ሙግት ሲኖረኝ ፌስቡኬ እና ብሎጌ በቂ ናቸው። በጥሁፍ ብቻ እንደማለት።
አቅም ሊያብክን የሚገባው ብክነትን በቅጡ መተርጎም ሲቻል ብቻ ነው። አቅም የለውጥ ስኬት ሊያመጣ ካልቻለ ማባከን ተገቢ አይደለም። አቅምን በቅጡ ማኔጅ ማድረግ ብልህነት ነው። ራዕይን ፕሮፖጋንዳ አይሠራውም። ራዕይ በአቅም ልክ ተመኝቶ ድርጊት ላይ ለማዋል ብልህነት ያለው ትጋት ይጠይቃል። ሳይጠላሉ - ሳይከፋፉ - ሳይደፋፈሩ መርኽን - ዕውነትን - አደራን ማስከበር ይቻላል። ለፍላጎትም ስኬት መትጋት ይቻላል። ተከባብሮ መሞገት ለትውልድ ቀረፃ ካሪክለም ነው ብዬ አምናለሁኝ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ግን አዱኛወቼ ደህና አደራችሁልኝ? ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/05/2025
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ