ክፍል አራት ርትህ።
ርትህ። ክፍል አራት። ከሥርጉተ © ሥላሴ 01.06.2018 (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።) „የሚምሩ ብብፁዓን ናቸው ይማራሉ እና“ (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯) · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_WVc5bXyb5c ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ከአፋር ህዝብ ጋር ያደረጉት ሙሉ ውይይት PM Dr Abiy Ahmed discusses with the people of Afar · የወግ ገበታ። ውዶቼ ቀደም ሲል የነሳ ኋ ዋቸው ከክፍል አንድ እስከ ሦስት ድረስ ለመነሻ መዳረሻ የሚሆኑትን ብቻ ስለነበር ሊንኩ አለጠፍኩትም ነበር። አሁን በዚህ በክፍል አራት የምናዬው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሠመራ በነበረው ጉባኤ ላይ የሰጡትን መልስ አስኳል ጉዳዮችን ማዬት ስለሚያስፈልግ ነው። በዚህ ክፍል እስከ መግቢያዋ ላይ ያለችውን ጥላቻን ብቻን ማዬት ብንችል ብያለሁኝ አሁን። እንዳይበዛ እንዲሁም አሰልቺም እንዳይሆን። „ሰው ጠልተህ መተኛት አትችልም። ሌሊቱን ሰውዬው በሌለበት ስትቃጠል ነው የምታድረው። እሱ አያይህም። ያለህበትን ሁኔታ አያውቅም። አንተ ግን ስትቃጠል ታድራለህ። ከዚህ ውጪ መወጣት አለበት። ሰውን ለመጥላት መሮጥ ነገርን ለማሰብ አዕምሮአችን ማበላሸት የለብንም! ጊዜያችን ማጥፋት የለብንም! እኛ ምን እንደርጋለን? ሰው እንወዳለን! ሰው እናቀርባለን! እስከተቻለን ድረስ ሰውን እንረዳለን። ነገር ግን የሚጠሉን ሰዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን። ዓለም እንዲህ ስለሆነች። ሰዎች ሲጠሉህ አንተም ቁልቁ...