ልጥፎች

የኢትዮ አፍሪካኒዝም ህሊና ፕ/ ማሞ ሙጭ አትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች" ይላሉ ...

ምስል
„ኢትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች! ለዓለምም የመንፈስ ጸጋ የሰጠች አገር ናት!“ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፤ ተማመኑ አንተም አዳንህቸው። (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፩ ምዕራፍ ፬) ከሥርጉተ© ሥላሴ 2.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ኢትዮጵያ ካሏት ዓራት ዓይናማ ሊሂቀ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊነት ከሚንገበግባቸው ጥቂት የምርምር ሊሂቀ ሊሂቃን ቤተኛም ናቸው። ችግሩ አለተጠቀምንብትም። ድህነታችን ማን ታቅፎ ይኑርልን? እኒህ እውቅ ኢትዮ አፍሪካዊ ሐዋሪያ እኛ ጥበባቸውና እና ዐውቀታዊ ክህሎታቸውን ባንጠቀምበትም ሌሎች ብልሆች ግን ከልጅነት እስከ ዕውቅት በአህጉራዊ እና በሉላዊ ጉዳዮች ላይ ሁለገብ ትውልዳዊ ድርሻቸውን ተወጥተዋል። በዕውቀታዊ ብቃታቸውም ተጽዕኖ ማሳረፍ የቻሉ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ በማናቸውም አገራዊ ሆነ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎ የሚያደርጉ፤ ያደረጉም ቅን ሊቀ ትጉሃን ናቸው። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ህሊናችን እና መንፈሳቸውን ግን ዕውቅና ከመስጠት በታዕቆቦ የቆዬ ቢሆንም፤ ታሪክ ግን ምንግዜም ሲያስባቸው የሚኗሩ ባለውለታችን ናቸው። የሆነ ሆኖ እኛ ባናውቅበትም አፍሪካውያን እንደ ልዩ ዓርማቸው የሚዮዋቸው፤ ልክ እንደ የቅኔው ልዑል ብላቴው ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን፤ እንደ የእግር ኳስ እስፖርት ልዑል አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አፍካዊነትን አጉልቶ በማውጣት፤ ጉልበት እንዲያገኝ በማድረግ እረገድ ድርሳን የሆኑ የአፍሪካውያን የጸሎት መጸሐፍ ናቸው። እኒህ ታላቅ ኢትዮ አፍሪአካዊ የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍናንም በልዩ ክህሎት አቅሙ በልጽጎ፤ ጎልቶ እና ጎልበቶ እንዲታይ ሙሉ ጊዜያቸውን በመሰጠት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ጸጋቸው ዕውቀ...

ብርሃነ ትንሳኤ በወርሃ ክረምት!

ምስል
ባረኮተ ተመስገን። v        በስም አብ ወወልድ ወምፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤ አሜን! ከሥርጉተ©ሥላሴ 22.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) „የእግዚአብሄር ህግ ፍጹም ነው። ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሄር ምስክር የታመነ ነው፤ ህፃናትን ጠቢባን ያደርጋል። የእግዚአብሄር ሥርዓት ቅን ነው፣ ዓይንንም ያበራል። የእግዚአብሄር ፍርሃት ንጹህ ነው ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሄር ፍርድ እውነት እና ቅንነት ነው። ከወረቅ ከክቡር እንቁ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማር እና ከማር ወለላ ይጣፍጣል። ባርያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።“ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፰ ከቁጥር ፯ እስከ ፲፩ ቁጥር) v   መ ቅድመ ሃሳብ። እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው። እግዚአብሄር የፍቅር አምላክ ነው። እግዚአብሄር የመዳን አምላክ ነው። እግዚአብሄር የመቻቻል አምላክ ነው። እግዚአብሄር የመፍትሄ አምላክ ነው። እግዚአብሄር የሰላም አምላክ ነው። እግዚአብሄር የመተሳሰብ አምላክ ነው። እግዚአብሄር የእርቅ አምላክ ነው። እግዚአብሄር ለፍጡራን የሚያዝን ቸር እና ደግ አምላክ ነው። እግዚአብሄር የተበተኑትን ልጆቹን አይረሳም። እግዚአያብሄር በመከራችን ሁሉ መንገዳችን ቀያሽ ነው። ፈጣሪ የነባቢታቸን መንፈሳዊ መሃንዲሳችን ነው። v    የተ ስፋ ጵጵስና! እንሆ ቀኑ ደረሰ። እንሆ ብርሃን በራ። እንሆ ተስፋ ወደ እኛ መጣ። ባርኮ ሰጥቶን እና ግን ቆልፍን የያዝነውን ይቅርታን በልቦናችን ውስጥ እንጠቀምበት ዘንድ ፈቀደለን። ውስጣችን ጠረገልን። ተመስገን! እንሆ ቀድሞ የሰጠንን ማስተዋል ካለበት ፈትሸን እንቀርበው ዘንድ ፈቃዱ ሆነ። እሱ የሁሉ ጌታ፤...

"ሆድ ሲያውቅ ..."

ምስል
„ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ።“ „በውኑ ደንግል ረግረግ በሌለበት ቦታ ይበቅላልን?“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፲፩) ከሥርጉተ © ሥላሴ 21.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        በር። ዛሬን ደብሮታል። ደምኗል። እሜቴዋም ብቅ አልልም ብላ ጫጉላዋ ላይ ናት። እናም እኔም መውጣቱን አልፈለግሁትም። ስለዚህም ይህ ተኮለመ።፡ ·        የ ግራሞት ክራሞት! ከያንያን ምክንያት አይደሉም፤ ወይንም የአዲስ አባባ ከንቲባ ሹመት ምክንያት አይደለም። መሰረታዊ ጉዳይ የጠ/ ሚር አብይ የፍቅር ጉዞ እና ቀጣይ ተስፋው ነው መከራው። አጀንዳ ስለሚያሳጣ። ደጋፊ ስለሚያሳጣ።  ጸረ የአብይ ጸረ አብይ መንፈስን ከሳተናው ድህረ ገጽ በስተቀር፤ ብሎጎች፤ ታላላቅ ሚዲያዎች፤ የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ሁሉም የባጁበት ነው። ምክንያታዊ በሆኑ ጉዳዮች አይደለም ሲታመሱ የባጁት ሁሉም ሚዲያ። ለአገር ተቆርቋሪነት አልነበረም ሁሉም በጓዳው ደብቆ ያቆዬው የታቆረ ዓላማ እንጂ፤ ብጥብጡንም ሞከካረው መሬት ላይ እሱም ለግብ አላበቃም። ትንሽ ራፊ የ  ዕውቅና ከማሰገኘት በስተቀር ሞጋዳዊ ለውጡን፤ ሰላሙን በማወክ ያስገኘው ፋይዳ የለም። እንዲያውም እትጌ ኤርትራ የምሥራቹን ጀባ ብላ አቅልም ቀልብም በዚያ ላይ ሰከነ።    …. እራሱ  የአሜሪካ እና የጀርመን መንግሥት በጀት መድቦ የሚያሠራቸው ሚደያዎች ሳይቀሩ በምን ሁኔታ ላይ ሲታተሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ይህ የለውጥ መንፈስ በጥዋቱ ተሰብሮ እንዲቀር በዕድሜ ሁሉ ሲያላግጡ ነበር። እንዴት ዶር አብይ አህመድ 14 ዓመት ትግል ውስጥ ገባ የሚል ታሪ...