ጠንቃቃ መሆን ያተርፋል እንጂ አያከስርም።
ሞት የፖለቲካ አቋም የለውም። „እግርህንም ወደ ፍቅር አንድነት ጎዳና አቅና፣ የእግዚአብሔር ዓይኖች ወዳጆቹን ይመለከታሉና፤ ጆሮውም ልመናቸውን ይሰማልና ፍቅርን ፈልጋት ተከተላት።“ (መጽሐፈ መቃብያ ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ፰) ከሥርጉተ©ሥላሴ 26.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) በቃችሁ ቢለን ይህን የድንገተኛ ህውከት ቢያስታግስልን ምን አለ ፈጣሪ? ዛሬም አዲስ መርዶ አዬሁኝ። የአባይ ግድቡ የሙያው ማህንዲስ ከመኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኜ ይላል ክፉው ዜና። ዜናው ያገኘሁት ከአማራ ሚዲያ ነው። እኔ የአባይ ግድብን ጉዳይ በገለልተኝነት ነበር እምከታተለው። አልተቃውምኩትም አልደገፍኩትም። ምክንያቱም በማህል ያለው የፖለቲካ ጨዋታ ቀልቤን ሚዛናዊ አድርጎ አንዱን ሊያስወስነኝ ስላልቻል። ይህ ፕሮጀክት በጣም በዙ ኢትዮጵውያን ልባቸውን የሰጡት ብቻ ሳይሆን ህይወታቸውን ለመገበር የተሰለፉበት ነበር፤ ይህም ብቻ ሳይሆን በበዛ ተስፋ ፍንድቅድቅ የሚሉም ባለሙያዎችን አዳምጣለሁኝ። እኔ ደግሞ ሳይሞቀኝም ሳይቀዝቅዘኝም ነው የኖርኩት። የመንፈስ ነፃነት ነው ለእኔ ገዢዬ። ቁስ ብፈልግ ሲዊዝ ተቀብሬ አልቅመጠም ነበር። የተሻሉ ዕድሎች ስለነበሩኝ። ጉዳዬ ሰው በመንፈሱ ነፃ መሆን አለበት ነው። አሁንም ይህን አዲስ ለውጥ እምደግፈው የመንፈስ ነፃነት ያስፍናል የሚል ተስፋ ስላለኝ ነው። ጭንቅላት የተቆለፈበት ገነት ለእኔ ገሃነም ነው የፈለገ ዓይነት የኑሮ ደረጃ ይኑረው ...መንፈሴን ለመቆጣጠር ገና አንዲት ስንዝር እራመዳለሁ የሚል ማንኛውም ሰው ዕድል የለውም ከእኔ ጋር የመቀጠል። ምክንያቱም የራሱ መንፈስ አለውና ... መንፈስን በቅኝት ከመስጠት፤ ከመፍቀድ ሞት በስንት ጣዕሙ ... ...