? ጎንደር ተገበሪ - ሰለምን ትመሪ?!
ጎንደር ተገበሪ - ሰለምን ትመሪ? ሙተሽ ተወረሪ ደግመሽ ተመርመሪ? „የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፣--- እንሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል።“ (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፮) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 30.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ጎንደር ተገበሪ ስለምን ትመሪ? ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤ በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ... ደግመሽ ተመርምሪ። ጎንደር ምኞት ሁኚ ... የዕንባሽን አንገረብ ታቀፈሽውም፤ ተኚ። የዘመናት ማገዶ ስላንቺ መስታውት መንምኖ ሥምሽን ተዘካሪ ዋይታሽን አዝንቦ ኡኡታን አንግቦ! በቁልቁለት መንገድ ፈትልሽ ቢገመድም ዕንባሽ ዘመን በልቶት መብቀሉ አይቀርም። ጎንደር ተገበሪ ስለምን ትመሪ? ጆንያሽ አፈር ነው በእሱ ተሰፈሪ፤ በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ... ደግመሽ ተመርምሪ። መደመርሽማ ጥንትም የነበረ መቀነሰሽ ቢሆን ታሪክ ተረተረ። ተጋድሎሽ ብዙ ነው አንቺው አሳርኛ የመከራ እትብት የደመሯ ማኛ። ጎንደር ተገበሪ ስለምን ትመሪ? ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤ በምዕታት ቀመር ስትፈረፈሪ ... ደግመሽ ተመርመሪ። „ደመህም ደሜ ነው“ ብለሽ ሥትመሰከሪ „ድምፃችን ይሰማ“ ብለሽ ብትገሪ በሰኔል በቹቻ እንዲህ ትሰበሪ? ጎንደር ተገበሪ ስለምን ትመሪ? ጆንያሽ አፈር ነው በሱ ተሰፈሪ፤ በምዕታት ቀመር ስትወዳደሪ ... ደግመሽ ተመርመሪ። ሰንደቄ ይከበር የነብያት ሥራ ሉላዊት ይደነቅ የህብርነት ብራ ደንበሬ ይከበር የማንነት ዓውራ! ነበረ ነፃነት መከራ...