ልጥፎች

ሌላስ? ህም ተዚህ፤ ህም ተዚያ፤ ህም ተዚያ ማዶ!

ምስል
  ጭላጭ ሳይስቀሩ …  እም እንዳይሆን ስለ ጸዮን ዝም አልልም፤ ስለ እየሩሳሌም ጸጥ አልልም፤  ጽድቅዋ እንደ ጸዳል፤ መዳናዋም እንደሚያበራ  እስኪወጣ ድረስ።  ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የሚገርሙኝ ነገሮች የበረከተበት ወር ነበር ነሃሴ። ብዙ ብርካታ የሚባሉ ጉዳዮችን አስተውያለሁኝ። ዛሬም እንደ ትናቱ የሞገድ ጉጉሱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ትልቁ ጥያቄ ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው ለእኔ ለህሊናዬ ቅርብ የሆነው፤ ዕውን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ ትልቁ አምክንዮ ነው - ልንዘናጋበት የማይገባው። እርግጥ ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ አንድ ክንፉን ተመቷል ከሰሞናቱ። ችግሩን ከእርሱ ብዙ ማይልስ ርቆ መሬት ሲያስነጥስ፤ የራሱንም ህዝቤ የሚለውን ዕንቁውን ሳያስጨንቅ  በዕንባም ሳያሳጥብ "በሞኝ ክንድ" እንዲሉ መፈተኛው ሌላ ቦታ ነው፤ የምስራቅ ኢትዮጵያን ህዝብን ሲያስለቅስ የቆዬበት ሁኔታ የመፍትሄ አሰጣጥ ዘይቤን ብዙ ሰው አላስተዋለውም፤ ልብም አላለውም፤ አላደነቀውም፤ ዕውቅና ለመስጠት አልደፈረውም እንጂ የኢትዮ ሱማሌ ጉዳይን መስመር ለመሳያዝ የተሄደበት መንገድ እጅግ ዘመናዊ፤ ስልጡን ብቻ ሳይሆን እምነት የሚያስጥል ነው። ዶር አብይ አህመድ የመጨረሻውን የእውቀት ደረጃ ያዋዋሉበት ሙያ የሰላም እና የደህንነት ነው፤ ጥበብ መሬት ላይ በውን በዳግሚያ ትንሳኤነት እንዲታይ የተደረገበት፤ ከተከናወኑት ግዙፍ አገራዊ ጉዳዮች እንደ አንዱ ሊታይ የሚገባው ነው በሥርጉተ ዕድምታ። ልክ እንደ ኢትዮ ኤርትራ። እውነት ለመናገር በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን መሰል የመንፈስ ተረገጥ ...

ቅጣት እንዳያመጣ፤ ፈጣሪ የእውነት መስራች ነውና።

ምስል
በመገፋት ላይ የሰከነ 30 ኛ የ4ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መሪቆርዮስ በዓለ ሲመት አከባበር በአዲስ አባባ። „ደቀ መዛሙርቱም፤ --- የቤትህ ቅናት ይበላኛል   ተብሎ እንደተጻፈ አስቡ“   ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲፯   ከሥርጉተ©ሥላሴ 06.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። v       በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን! እንዴት ናችሁልኝ ደህና ናችሁ ወይ ውዶቼ? ዛሬ አንድ ዜና አዬሁኝ። ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን 4ኛው ፓትርያርከ  ዘኢትዮጵያ ባዕለ ስመትን በሚመለከት። ውስጤን ቀዘቀዘቀዘው። ብርድ ብርድ አለኝ።   ለብጹዕን አባቶቻችን ውጪ አገር እኮ ቁልምጫው ከ - እስከ አይባልም ነበር። እንዲያውም አንድ ጊዜ ይህ የበዕለ ሲመት ሲዘጋጅ የሊቢያ ሰምዕታት ጉዳይ ስለነበር አልሻም ማለታቸውን አውቃለሁኝ። ንዑዱ - ብጹዑው አቡነ መሪቀርዮስን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር መዘገበ ቃላት የለውም። ለኢትዮጵያ ልዩ ምርቃት ናቸው። ለ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክስተት ናቸው። እርጋታቸው የሰማይ እና የምድር ያህል ነው።    ዜናው ላይ ብጹዕ ወቅዱስ 6ኛው ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያን አቡነ ማትያስን አላዬሁኝም። ያዬኋቸው የቀድሞው ፕ/ ግርማ ወልደጊዮርጊስን አሳቸውን ነው።   እሳቸው መገኘታቸው ለይምሰል ወይንም ለላንቲካ አለመሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ። ቀድሞም ሲጥሩ ነበር ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ ለማድረግ፤ በጫና ብዛትም ቃላቸውን ሲያጥፉም አዳምጬ ነበር።   የሆነ ሆኖ መሰረታዊ ጉዳዩ ከልባቸው ስለመሆኑ ስለማምን የተባረከ ተግባር ከውነዋል። እንዲያውም...

ጥያቄው የብትን አፈር የነፍስ ጉዳይ ነው!

ምስል
ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም። ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንደምን አላችሁልኝ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ። በነገረ ጣይቱ ላይ ዛሬ ጥዋት እጅግ ከማከብረው ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት በላይ በግሉ ስለ ኢትዮጵያኒዝም የተጋ እና ያታገለ የአክቲቢስት አቶ መስፍን ፈይሳን ምልከታ አዳመጥኩኝ። ባለፈው ሳምንትም የርዕዮት ሚዲያን ምልከታ ተከታትያለሁኝ።  የወዳጄን የመስፍኔን ከቅንነት ስለሆነም በትርጉም ባቃናው፤ ትንሽ ዘለግ አድርጌ እንደ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ምልከታየን በሚል ነው እንዲህ ማለት ፈልግሁኝ።  እሱ ቅን ኢትዮጵያዊ ስለሆነ በሃሳብ ልዩነቱ ልናዝንበት የሚገባ አይሆንም። ምንግዜም በአንደኛው ሃሳብ ባንግባባ በሌላው ደግሞ እንስማማለን ወይንም በድምጽ ተዕቅቦ እንለያለን። ይህ የእውነተኛ ዴሞክራሲ ፈላጊው እውነት ነው። ግራው ዘመም መንፈስ ያደረበት ብቻ ነው ሞጋች ሃሳቦችን ወይንም ፈንጋጣ ሃሳቦችን የሚፈራው። ያው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አምላኩ ስለሆነ።  ·        የሆድ የሆድን።   ኢትዮጵያ የክት እና የዘወትር ልጅ የላትም። ኢትዮጵያ ስለ ልጆቿ ክፍልፋይ አሰናድታ አታውቅም። ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም ። ኢትዮጵያ ላይ ያለው ንጹህ አዬር ኦክስጅን አንተ / አንቺ የእኔ አይደለህም /ሽም ብሎ ገድቦ አይዋቅም፤ ለይቶም አያውቅም። አንድ ተራራ ላይ ያለው ነፋሻ አየር እኩል ነው ለሁሉ ፍቅሩን የሚያዳርሰው፤ ዝናቡም ሲመጣ እንዲሁም መቻቻልን በእግሩ አንዲሄድ ያደርገዋል፤ የኢትዮጵያ ጸሐይም ስትመጣ ለሁሉም ብርሃነኗን በሐሤት ትለግሳለች። ስታኮርፍም ስትስቅም እኩል ነው።  ...