ዕውነት አንቀላፋ በጃዋር ቀያፋ።
ውሎሽ? „ሁለት ዓይነት ሚዛን በእግዚአብሄር ዘንድ አጸያፊ ነው“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፳፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 20.29.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የስቃይ በረከት የዕንባ ዋናተኛ የፍትህ ውሏዋ የት ይሆን መገኛ? የጃዋር መ ጋ ኛ ለሽብር አይተኛ። ለጃዋር እርካታ የሚሊዮን ዋይታ፤ ለጃዋር ልቅና በመዲናዋ ላይ ንጹሃን ይሰዋ! ለጃዋር መታበይ አጀብ ነው ሁካታ ¡ ለጃዋር ጭካኔ የመንግሥት ትርክታ! ለጃዋር ግነቱ ሚዲያ ክርፋቱ፤ ለጆዋር ቅል...