ልጥፎች

የአቶ ዳውድ ኢብሳ "የእንትን" ፍልስፍና።

ምስል
ልብ። „አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ፤ በመ ዓትህ አትገስጸኝ።“ መዝሙር ፮ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 10.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·        መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=hwus5MSdFiA ሰበር መግለጫ ኦነግ ትጥቅ ፈቶ ለመግባት ነው የተስመማው https://www.youtube.com/watch?v=hwus5MSdFiA&t=3s ጤና ይስጥልኝ  እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ ክብረቶቼ። ዛሬ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦነግን በሚመለከት ግልጽ አቋሙን አሳውቋል። እጅግም ዘግይቷል። ቢሆንም ግን እኔ በገባኝ እና በጻፍኩት ልክ በሁሉም መስክ በተበራራ መልኩ በመንግሥትም ተገልጧል። ቆፍጠን ኮስተር ያለ መግለጫ ይመስላል መሬት ላይ ድፍረቱ ከኖረው። በዚህ እኔ ደስ ብሎኛል ደስ ያለኝ ግን እኔ የተረዳሁትን ያህል ስለገለጸው ነው። መግለጫውን የሰጡት አቶ ካሳሁን ጎፌ መ/ጉ/ኮ/ጽ/ቤት ም/ዴኤታ ናቸው። እኔ ብዙ ጊዜ በአዎንታዊነት ሥማቸውን አነሳዋለሁኝ። ለዬትኛውም ጥያቄ ግልጽና ጭብጥ ነክ ምላሽ ለመስጠት አቅማቸውን ያዬሁት አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦነግ መሪነት ኤርትራ ላይ እያሉ ፤ ዶር መራራ ጉዲና በኦፌኮ መሪነት፤ አቶ ካሳሁን ጎፌ ኦህዴድን ኦደፓን ወክለው በዶቼቨሌ ዲቤት ሲያደርጉ በተመስጦ ነበር የተከታተልኩት። ያን ጊዜ እጅግ ነው የተደነቅኩት።  ዲቤቱ ለእኔ 70% በአቶ ካሳሁን ጎፌ አሸናፊነት ነበር የተጠናቀቀው። ያን ጊዜም አቶ ዳውድ ኢብሳ 30 ሺህ እስረኛን መፈታትን በሚመለከት እምነታቸው ስስ ነበር ሰራን የምትሉትም በቂ አይደለም ብለው ነበር ያቃለሉት፤ ያበጨሉት። ያው ኦፌኮንም „ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አይጠፋጥም“ አቋ...

የመከራ ዚታ ተሸካሚዋ ስደተኛ እናት።

ምስል
አላዛሯ ኢትዮጵያ እና ልጆቿ። „ምህረት እና ዕውነት ከአንተ አይራቁ“ ከሥርጉተ© ሥላሴ 09.10.2018 ከጭምቷ ሰዊዊዘርላንድ። ·        መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=_JOWxawk32U Ethiopia:" ከስደት መልስ የምስኪኗ የመኪና ውስጥ ጎጆ " ፡ሁለት ልጆችዋን ይዛ በመኪና ዉስጥ ኑሮዋን ካደረገችዉ ከወ / ሮ ዘሪቱ ጋር የተደረገ ቆይታ ስልክ ቁጥር 011-893-2975 ወይንም 0920 -0196 -34 የመከራ ቁልል የዕለት ኑራቸው ቤተኛ የሆነባቸው ሁለት ህፃናት እናት ናቸው ወ/ሮ ዘሪቱ። ኡጋንዳም ሱዳንም በስደት ቆይተዋል። ስደት ለሁሉ አይደላም ለሁሉም አይከፋም። ዕድል ለቀናቸው ይቀናል ዕድል ፊቱን ለነፈገችው ደግሞ መከራ ይቆልላል። ስደት በልክ ያልተሰፋ ሽብሽቦ ወይንም እጀ ጠባብ ነው። ስደት እና ህይወቱ የፈተና ማሰልጠኛ ተቋም ነው። እርግጥ ነው በሰላ ሁኔታ የሰላ ገጠምኝ ባለቤቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ግን የሰላውም የሚባለው የማትቀበሉትን ዕድል መቀበል ከተቻለ ነው። ያ ካልሆነ ዘላቂ መከራ መሸከም አይቀሬ ነው።  ስደት ውስጥ ብዙ አቅጣጫ ያለው ተራራዊ ገጠመኞች ነው ያሉት። ይህን እንደ ተጠቀለለ ትቼ የእነዚህን ምንዱባን ህፃናት ዕጣ ፈንታ እና የነገ አገር ገንቢ ታሪካዊ ድርሻቸው በምን ሁኔታ ሊሰላ እንደሚችል ያለኝን ዕይታ መጥኜ ላንሳ። ለነገሩ በርዕሰ መዲናዋ በአዲስ አባባ ቀደም ባለው ጊዜ በሺሕ የሚቆጠሩ ወገኖች ኑሯቸውን ጎዳና ያደረጉ እንደ ነበሩ ይታዋቃል።  አሁን በብዙ እጥፍ አድጓል። ከዚህም አልፎ ከትግራይ በስተቀር ሁሉም ክልል በዬቀኑ ኗሪው ይፈናቀላል በ...

አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላት።

ምስል
የትውልዱ ብክነትን ለማስቆም ከቶ ለማን አቤት ይባል? „አቤቱ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ?“ መዝሙር ፲፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 08.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                  ከቶ የአማኑኤል አባታችን ሥጦታው እንዴት ይዞች ኋ ዋል? እኔ ፈጣሪ በቃቸሁ አለን የሚል ዕምነት ነበረኝ። ግን የሆነ አልመሰለኝም። ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል የሚስፈልገው የአዕምሮ ላውንደሪ ነው ። የ50 ዓመት የሴራ ፖለቲካ ባህል አሁንም አለ እንዳለ። ይህን እንለውጣለን ብለው የተነሱት የለውጥ ሐዋርያት ትግላቸው ከራሱ ከሊሂቃኑ ህሊና ጋርም ጭምር ነው። በምን ኦሞ አጥበው ከአዲሱ የአሰተሳሰብ መንፈስ ጋር ሊያዋድዱት እንሚቻላቸው ብርታቱን ይስጣቸው። እነኝህ የበቀልን ዓውደ ለመደምሰስ የተነሱ አዲስ ቡቃያዎች ያን  የቆዬውን የታቆረ የሴራ የሽምቅ ውጊያ አስወግደው የእነሱን ንጹህ ድንግል አሰተሳስብ እንዴት ማዋለድ እንደሚችሉ ፈተናው ውሃ ያዘለ ተራራ ሆኖ እዬታዬ ነው። ራሱ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ለመለወጥ ያላቸው ፈቃድ ምን ያህል ይሆን? ራሳቸውን ማሸነፍ ቢችሉ አባሎቻቸውን፤ ደጋፊዎቻቸውን በዚህ አዲስ  የአስተሳብ ባህል ለመቀረጽ እንዲህ አይችግርም ነው። የዬትኛውም የፖለተካ ድርጅት ይሁን ንቅናቄ ይሁን ግንባር መጀመሪያ ከራስ የመነሳትን ተጋድሎ መጀመር ያለበት ይመሰላል። ራስን ሳይለውጡ ተከታይን ሆነ አባልን መለወጥ ፈጽሞ የሚቻል አይመስልም። ለውጡ ወረቀት ላይ አይደለም። ለውጡ ከውስጥ መሆን አለበት። አንድ ሊሂቅ የዘመተበትን ሌላኛውን ሊሂቅ ራሱ...