ልጥፎች

ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ- ሕይወት! 31.12.2014ትን በምልሰት።

ምስል
ኢትዮጵያዊነት የደሜ ዕምነት ሥነ- ሕይወት! „ለፍጥረቱ ሁሉ ትራራለህ ይቅርም ትላለህ።“  መጽሐፈ ጥብብ ፲፩ ቁጥር ፳፯ ኢትዮጵያዊነት የፍጥረት ዓይነ - ህሊና ነው! እውነተኛ ሐሴትን የመፍጠር አቅሙ ሙሉዑ! ኪናዊ! ከሥርጉተ© ሥላሴ (Seregut© Selassie) ከጭምቷ፡ሲዊዘርላንድ። 31.12.2014 ለመነሻ። የኔዎቹ የፈተና ጥጉ ከ እሰከ የማይበልልት ኢትዮጵያዊነት በ2013 አዲስ ያገረሸ መከራ ነበረበት። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ወደ መድረክ ብቅ ያሉበት ጊዜ ነበር። የዛን ጊዜ ወጣት ጃዋርውያን በሁሉት ዙር ኢትዮጵያዊነትን ወጥረው የያዙበት ወቅት ነበር። በዓይነት ነበር ፓልቶኩ። ለመስማት ቀርቶ ሰምቶ ለመኖር ፈታኝ ጊዜ ነበር። እናም ይህን ጻፍኩኝ። ዘሀበሻም ፖስት አድርጎት ነበር። ዛሬ በምልሰት ሳስበው የዛን ጊዜው ጉግስ በተለያዬ ሁኔታ እዬታዬ ነው። ኢትዮጵያዊነት ጎላ ብሎ ሲወጣ ኦነግውያን እና ወያኔውያን ደማቸው ይፋላል፤ እሱን እንደ አንጡራ ባላንጣቸው ነው የሚዩት። ልብ ለልብ ሳይገናኙ እነሆ ዘመናት ነጎዱአ እነሱም አፈጁ። ትውልዱም አዲስ ዓራት ዓይናማ አብቅሎ ቀስ እያደረገ እያለበው ነው ጉድፋ ጉድፉን ጉንፋን ዕሳቤ። ተመስገን ነው። በታህሳስ 31 ቀን 2014 የተጠፈው በዛሬው ታህሳስ 11 ቀን 2018 ቤት ለእንግዳ ትለዋላች እትጌ ቀንበጥ። እትጌዋ አብራችሁ ትሆኑም ዘንድ በሞንሟናው ኢትዮጵያዊ አክብሮት ታከብራችሁለች። ማክብረን አትሰስትበትም እና። ·        ይህ ነበር መንፈሱ …  ዛሬ ላይ እትጌ ትግራይን ሳስባት እንደ እኔም እሰቧት በዚህ ውስጥ … የእነ ማህበረ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንታት የትጥቅ እና ስንቅ ጉዞ …...

ገበር።

ምስል
ገበር። ይቺ ጥበብ ብቻዋን አስቀድሞ የተፈጠረ  አዳምን ጠበቀቸው። ከተፈጠረም በኋላ  እንደ አደራ ዕቃ ጠበቀቸው ከራሱ ኃጢያትም አዳነችው።“  መጽሐፈ ጥብብ ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute© Selassie) ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ 07.07.2010 እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ ባለለዛዎቹ፤ ባለአደቦቹ የቀንበጥሻ ታዳሚዎቼ። ይህን ጹሑፍ በሌላ አውደ ግንባር ሆኜ የኮልሙኩት ነበር። ተቀምጦ የኖረ ወግ ቢጤ ነው። ያው አእምሮ ያፍታታል። ቃል እና ቃሉን ስታሟግቱት፤ ተጠዬቅም ስትሉት። እና አደግድጌ ዛሬ እስኪ ቀንበጥዬ ቤት ለእንግዳ በይው ስላት „መሰናዶዋ ሙሉ ነው አምጪው“ አለችኝ ቀልጠፍ ብላ። ለዛውም ለአደብ የተፈጠረች እኮ ናት ቀንበጥሻ፤ ካለ ዕድሜዋ ምርቋን ዋጥ ያደረገች ናት። „ሁኖልኝ! ነውንም“ አከለችበት። ቀጠለችው  በረጅሙ … ትንፋሿን አስከንድታ …  „ይኸው አረቲው ቡክቡካው፤ ነጭ ራያኑ ጠጅ እሳሩን ቅይጡን … አለችና በልዩ አውድ አሰተናገደችልኝ። ስለምን እንደጻፍኩት እኔ እና ህሊናዬ ብቻ ነው የምናውቀው። ብቻ ለፍንጭ ታህል ያልታለመ እንግዳ ነገር ድንገት ከች ብሎ ስለነበረ … ·        የወግ ገበታ። እነዛ ደማም ፍኩ ርትዑ ቀናት ይዳስሱኛል። እነዛ ዓይነ ግቡ፤ ባለ ውሽክታ ሰዓታት ያጫውቱኛል። እነዛ የንጋት ኮከብ ሰከንዶች ያነጋግሩኛል። ሁሎችም ሰማያዊ ሥጦታዎቼ ናቸውና … እንደ ሰማይ ፕላኔቶች የራቁ መጥምቆች …. መጠመጡኝ በትዝታና ናፍቆት ….   ሽሽ ሽሽ ሽሽት አሰኘኝ ወዴት? አላውቀውም  …. ሽውታ … ግን እንዴት አለህ? … አነተ ሳትሆን እኔ ታስሬያለሁ። አንተ ሳ...

ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው፤ በ2014 ፖስት ተደርጎ የነበረ።

ምስል
ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው - ለእኔ! „ስለ ጽዮን ታላቅ ቅናት ቀንቻለሁ። በታላቅም ቁጣ ስለ እሷ ቀንቻለሁ።“ ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፪ ከሥርጉ ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 11.01.2014 ·        ማግባቢያ ለመቅደሙ እና ለዕለቱ ጡሑፍ። ውዶቼ ይህ ጹሑፍ በ2014 ነው የተፃፈው። ያን ጊዜ ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ በሳተመው "ጥቁር ሰው" ላይ ወጀብ የጠናበት ጊዜ ነበር። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት የመጡበት ያዙኝ ልቀቁኝ ይሉበት የነበረበት ዘመን ነው። ጠንከር ያሉ ፓኢልቶኮች ተከፍተው ኢትዮጵያዊነት ሲብጠለጥል የነበረበት ወቅት ነበር። በአንድ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ ኢትዮጵያ ተወክላ በእንሱ ዘመቻ እንዲቀር የተደረገበት ጊዜ ነበር ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ። እነሱም ደስታውን እያጣጠምን ነው ያሉበት ወቅት ነበር። ዛሬም ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዘመን ራሱን ደግሞ እንሆ ትግራይ ላይ ሌላ የጦርነት አዋጅ ነጋሪት አለ። ጦርነቱ በኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። እትዮጵያዊነት አሸናፊ ሆኖ ስለወጣ። ኢትዮጵያዊነትን በጥልቀት ማዬት ከተሳነን ለድጋሚ ሌላ ጦርነት እንጋለጣለን። የሃሳብ ጦርነቱ ይሁን፤ በሃሳብ ጦርነቱ ውስጥ የጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች እንደሚኖሩ ማሰብ ግን ይገባል። እነሱም ከጠራው መስመር ጋር ለመሆን ማሰብ እና መቁረጥ ይኖርባቸዋል። የትግራይ መሳፍንታት ህልም ቁሞ ቀር ከሆነ እንሆ ሦስት ዓመት ተቆጠረ።  የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ የተጀመረ እለተ አቡዬ ሐምሌ 5 ዕለት የታላቋ ትግራይ ኢትዮጵያዊነትን ጥሶ ለማለፍ የነበረው ህልም አፈር ድሜ ጋጠ ። ምክንያቱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የማህል አገር መዳራሻ፤ ...