የኢዴፓ እጩነት /አዲስነት ትልሞሽ/
እንኳን ደህና መጡልኝ። የኢዴፓ እጩነት። የሚቀድመው የትኛው ይሆን? ግን ገነገነ ወይንስ ገነነ ልበል ከቶ! „የፃድቃን አፍ ጥበብን ያስተምራል፤ አንደበቱ ፍርድን ይናገራል።“ መዝሙር ምዕራፍ ፴፭ ቊጥር ፴ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 25.02.2018 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ትናንት በዋለው የአጋር ድርጅቶች ይሁን የአጋር ክልሎች ዓወደ ህዝባዊ ስብሰባ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ወጥ ፓርቲነት ድርጅታቸው እንደሚሸጋገር አብስረዋል። ጉደኛው ኢህአዴግ ወደ „ኢትዮጵያዊ ፓርቲነት“ ሊለወጥ ደስ ይላል። ኢትዮጵያዊ ፓርቲነቱን ሲያልም ግን የቋንቋ ፌድራሊዝምን ተሸክም ይሆን? ብቻ መሰናክሉን ማለፍ ከተቻለ ወሸኔ ነው ማለፊያ። መሰናክሉ የህሊና ለውጥን ነው የሚጠይቀው። የቅርቡን የወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ቃለ ምልልስ ብቻ በቂ ነው። ምን ያህል የዘለበ ገማና ኢትዮጵያ እንዳለባት። አሁን እንኳን በዬቦታው የራስን ሰው ለመሸጎጥ ማራቶኑ ተንጠራርቶ አገር እያመሰ ስጋት እያቀና መሆኑ ነው የሚደመጠው። የሳቸው ቸር ምኞት ግን ሁልጊዜም ይገርመኛል። እስኪ ያሳካላቸው … አሜን አሜን ይሁን ይሁን ብለናል። ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እኔ እንዲያውም ኦዴፓ አውራ ፓርቲ ሆኖ ለመውጣት ሥም ሲያድል ብአዴን ተቀብሎ አዴፓ ነኝ ከዛሬ ጀምሮ ሲል ምን አለ ኢዴፓ ብትባል ብዬም ነበር/ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ። / ማለቴ አማራ ክልል ነው እና ኢትዮጵያዊነትን ተሸከም የሚበላው በዬዘመኑ። እነ አቶ በረከት ስምዖን፤ እነ አቶ አዲሱ ለገሰ፤ እና አቶ ዮሴፍ ህላዊ፤ እነ አቶ ተፈራ ዋልዋ፤ እና አቶ አለምነህ መኮነን ...