የነገው አስኳባ የከንቱ ውዳሴ ካባ።
እንኳን ደህና መጡልኝ የነገው ብሄራዊ የ አስኳባ ሠርግ የከንቱ ውዳሴ ካባ። „አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን።“ መዝሙር ፴፱ ቁጥር ፲፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 13.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ነገ የአስኮባ ብሄራዊ የሠርግ ቀን ነው። ጠ/ሚር አብይ አህመድ አስኮባቸውን ይዘው መንገድ ሲያጸዱ እናያለን። የነቀምቱ እግር ኳስ ቲምም እንዲሁ በተመደበለት ቦታ ሆኖ የአስኮባ ቀነኑን የፊሽካ ድምጹን ይጠብቃል - ለዛውም በጉጉት። ወይንም በታምራነት ትዕይነቱ ይከናዳል። የካሜራ ርችት ይተኮሳል፤ እልልታ በስላቅ ትንግሩትን ይዘጋግባል፤ የመዲናዋ ንጉሰ ነገሥታት አብረው ይታደማሉ … ሚዲያው ሁሉ ፎቶ ቀጭ ለማድረግ ይሰለፋል። ለዛውም በሽሚያ ... https://www.youtube.com/watch?v=q6TE5zEYp-w እሁድ በሚካሄደው የጽዳት ዘመቻ ዙሪያ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር መግለጫ Fana Television Published on Apr 11, 2019 ካቢኔውም እንዲሁ። ከኪጋሌ መልስ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላማዊ የተረጋጋች፤ የህግ የበላይነት የሚከበርባት፤ የመኖር ዋስትና ያለባት፤ መኖር ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የተፈቀደበት፤ ተስፋ ያበባት ሚሊዮን ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉበት፤ ሚሊዮኖች ሜዳ ላይ የወደቁበት፤ ነፍስ የትም ቦታ እንደተርታ ጉዳይ የታዬበት፤ ርዕሰ መዲናዋን ልታጣ ሞት አፋፋ ላይ ያለች የመከራው ሲሳይ ከአፍ እስከገደፉ ስለሞላ ነገ አስኮባ ዲል ባለ ሠርግ ይዳራል ፤ ይኳላል በመላ ኢትዮጵያ። ቅልቅሉ፤ ግጥግጡ ደግሞ መቼ ስለመሆኑ ቀን ተቆጥሮ...