አላልቅአለኝ ህምታ!
እንኳን ደህና መጡልኝ
አላልቅአለኝ ህምታ!
„ለሁሉም ዘመን አለው። ከሰማይ በታችም ለሆነው ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።
ለመወለድም ጊዜ አለው። ለመሞትም ጊዜ አለው፤ የተተከለውንም
ለመንቀል ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤
ለማፈረስም ጊዜ አለው፤ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስም ጊዜ አለው“
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ እስከ ፫
"እኔም ተመለስኩ ከፀሐይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዬሁ፤
እንሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር የሚያጽናናቸውም አልነበረም
በሚገፏቸው እጅ ሃይል ነበር፤ እንርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
እኔም እስከዛሬ ድረስ በሕይውት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን
አመሰገንሁ ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው ከጸሐይም
በታች የሚደረገውን ግፍ ያላዬው ይሻላል።" መክብብ ፬ ከቁ ፩ -፫
አላልቅአለኝ ጥምልምሉ
አላልቅአለኝ ጥምንምኑ
አላልቅአለኝ ጥልፍልፉ
አላልቅአለኝ ጥምዝምዙ
አላልቅአለኝ ንጥፍጥፉ
አላልቅአለኝ ስግስጉ
አላልቅአለኝ ምንድግድጉ
አላልቅአለኝ ትልልፉ
አላልቅአለኝ ጉርድርዱ
አላልቅአለኝ ድርዳሩ
አላልቅአለኝ ልጥፍጥፉ
አላልቅአለኝ ውትፍትፉ
አላልቅአለኝ ንድልድሉ
አላልቅአለኝ ምንጥልጣሉ
አላልቅአለኝ ውትፍትፉ
አላልቅአለኝ ግንዝንዙ
አላልቅአለኝ ስንብትብቱ
አላልቅአለኝ ንዝንዙ
አላልቅአለኝ ውጥንቅጡ
አላልቅአለኝ ግርድፍድፉ
አላልቅአለኝ ዝንቅንቁ
አላልቅአለኝ ፍርጥርጡ
አላልቅአለኝ ፍጥምጥሙ
አላልቅአለኝ ዝብርቅርቁ
አላልቅአለኝ ግጥምጥሙ
አላልቅአለኝ የጥምጣሙ… ዝርዝሩ.
የመሄድ /////// የመጪታ /////// የግጭታ///////
--- የፍንጭታ ዝምታ ህምታ!።
· ሚያዚያ
11.04.2019 ሲዊዘርላንድ ቪንቲ።
· የአላዛሯ
ኢትዮጵያ ለህልውና ህምታ መታሰቢያ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእመ ዝምታ ከሲዊዘርላንድ
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ