ቱማታበቱማታ።
እንኳን ደህና መጡልኝ
ቱማታበቱማታ።
„አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምህ?“
መዝሙር ፲ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Seregute©Selassie
12.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
የህቅ ታ ፍንዳታ
የትናጋ ቃታ
… አቤት ሲማታ!
በስንድድ ሲያምታታ
ሲያማታ ታ! ታ! ታ!
ግርታ… ለመባጃ
ስጋጃ … ይሆን እንጃ?
የቅቤው ንጠት ወዬው የብዛቱ የዛ እንትን በዳታ
የትናንቱ የናዳ አይዋ ከርታታ
የዕንባ ዘንካታ
ዘንከትካታ አባ ዝማታ …
የዬዘመኑ እእታእእታእእታእእታእእታ
አላባራም
…. ስቅዝታ።
ኡኡታ በኡኡታ የተዋጠው በድርቅታ
ክክክታ የመስቃ ሊኳንዳ እርካታ
የዛሬም እምታ፤ ከምንትሶ ያለልክ ተጋብታ
ግጥግጥ መልሱ አልቦሽ ውለታ ወና በሰርዴታ
ያ ባተሌ ነፍስ
በሁካታ ተፈታ - ታ! ታ! ታ!
ሳይፍታታ ተተብትቦ
በእፍታ ሳይሆን አንድአፍታ።
መታመኑ አንደተርታ ሆኖ እንሆ ተፋታ!
ሞት ሲል ሆ! ሆ! ሆ! በል ሲል ተራበተርታ
እንትኑ ተበራታ
ላከ ማገዶ ለጭስታ ዝርጋታ።
ህምታ----- በግርምታ!
የክህደት ገመድ
ሰርታታ!
የማታማታ ዘመነኛ
ባለተርታ
የፈረደበት አሳረኛው ያ ከርታታ …
ዳግሚያ ተንሳዩ
የሞት ሆታ!
የምሾ ሾህ አክሊል
ገበታ።
ተደገሰለት ለባተሌው
በክትክታ
ታ! ታ! ታ! ስንድድ ዝንጋታ
ሲተለትል ሲምግ የጭካኔ ፍካታ፤
አባ - ጋሼ
- አቶ የቦኮሃራም ትርታ
የለውም ይቅርታ…………ለእሱ አንተ ተርታ… .
እንሆ እንደዋዛ!
አዎን! እንደዋዛ አገር ፈታ ….
ለባተሌው ለሊጋባው ሞት ሸለመው ለባለውለታ
ለከልታሜ ዝም
ብሎ ነዳው በሀተታ።
ባለነጋሪት
… አለሁብሎ በኩራት በእንዴታ!
ዘውድ ሲደፋለት ማን አለበት ከቶ ጌታ?!
አንድታ
ሁለታ
ሦስታ
አራታ
አምስታ
ስድስታ
ሰባታ ተረታ ወይስ ረታ?
ህቅታ ---
ብንታ ----
ስርቅርቅታ
ስንግታ ---
በባለተራ ጫንተደል ቻለውበል ለባለተርታ
በዝቅታ በለጥታ።
ታ! ታ! ታ!
ቄንጠኛ ዘመነኛ ትርታ …
የሽብር ሠርገኛ --- የስጋት እልልታ።
ሆታ! ተናኛ
ብቻ „በቃል ወለምታ“
ቃል ተዝልዝሎ
ተጠብሶ በድቁስታ
ደግሞ ደግሞ
ተቁ = ላልቶ ታወጀ በግርርታ
የግራኝ ዘመን
በምልሰታ
ሂደታ በፍልሰታ
…።
-------
አቤት ተበልታ … .
እሺ! ተበልታ እንደ ጥንስስ ተንተክትካ ተብላልታ
ሩኽ ሆይ? ሩኽ
ሆይ!ሩኽ ሆይ …!
ወይኔ! በል
በሆታ
….እሩቁን በምልካታ
አስኪደው በቁስለታ በሁካታ ትርታ …
የድንኳኑ
--- ፍግምታ …
በፈረስ ጉግስ
እምታ ….
በሻምሎ ኩልልታ …
እንዲያ ነው
የማታማታ የነቱማታ …
· 12.04.2019
ሲዊዘርላንድ ቪንቲ። 19.14
· መታሰቢያነቱ ለኢትዮጵያዊው ሩህ …
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ