ልጥፎች

የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የቀድሞውን የኢትዮጵያ  ፕሬዚዳንት  የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን! „ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ከሰሞናቱ ከተደመጡት ሃዘኖች አንዱ የዶር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈት ነው። አስደንጋጭ ነበር።  ድህነትን መውደዳቸውና መፍቀዳቸው፤ ክብር መጸዬፋቸው፤ ሥልጣን በቃኝ ማለታቸው፤ እንደማንኛው ተርታ ዜጋ ሆኖ መኖርን መውደዳቸው፤ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሄሮድስ መለስ ዜናዊን በድፍረት መሞገታቸው፤ ኢትዮጵያንም የሙጥኝ ብለው በቀዮዋ እስከ ህልፈታቸው መኖራቸው፤ ትዳራቸውን አክብረው መዝለቃቸው፤  „ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“ ይቅርታ የኢትዮጵያ ህዝብን ዝቅ ብለው መጠዬቃቸው የሚያስመሰግናቸው ጉዳይ ነው።  ልዩም መክሊት ነው የታደሉት ብቻ የሚያገኙት። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ የበቀል ፖለቲካ በመሆኑ በቀል እስኪበቃቸው የከተከታቸው፤ ግን ያነን ተቋቁመው ሁለተኛ ስደትን ሳይመኙ እዛው በአቋማቸው ጸንተው መዝለቃቸው ሌላው ጸጋቸው ነው።  ወላጅ አባታቸውም ይህን መሰል ጽናት እንደነበራቸው እና እስር ቤት ሆነው ግን ሃኪም ቤት ተኝተው ጃንሆይ ከእስር እንዳስፈቷቸው ሁሉ ከአንድ ሃይማኖታዊ ቃለ ምልልስ አዳምጬ ነበር። ጽናት የቤተሰብ ነው ለማለት። በተ...

በፈለገው መንገድ አዛውንትን ፍ/ቤት መከስስ የተገባ አይደለም፤ አላምንበትም።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  ከምርኩዝ ክስ ምን ሊተረፍ? „እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጎም የሚያውቅ ማን ነው?“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ·        መነ ሻ። https://www.satenaw.com/amharic/archives/67081 ዶ / ር አንማው አንተነህ፣ ድሮና ዘንድሮ አማራው አማራ መሆን የጀመረው አሁን ነው April 27, 2019 https://www.youtube.com/watch?v=XH6t4UhQbJ0 #Ethiopianews   #Ethiopia Ethiopia: ዘ - ሐበሻ የዕለቱ ዜና | Zehabesha Daily News April 27, 2019 Zehabesha Official Published on Apr 27, 2019 ·        እ ፍታ። እንዴት ቆያችሁ የኔወቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ከሰሞናቱ በተፈጠረ ቃለ ምልልስ አብን እከሳለሁ ብሎ መነሳቱ ተደምጧል። ይህ በጃዋርውያኑ የንግሥና ዘመን የሚፈለግ እና የሚመች ነው። ጊዜን ግጥም አድርጎ ይበላል፤ የፍርድ ውጤቱ ደግሞ በሸንፈት ሲጠናቀቅ ሞራል ድቅቅ ብሎ ደብቁኝ ይመጣል። ወይንም እልሁ ወደሌላ ነገር ይወስድና ያልታሰበ ቀውስ ያስከትላል። ·        ህ ግ እና አገር። ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ህግ አለን? ህግ አስከባሪ አለን? ተጠያቂ እንኳን የለም። ጎረምሳ ይምራት፤ ስውር መንግሥት ይምራት፤ ትጥቅ ይምራት፤ ጠ/ሚር ይም...

ኢትዮጵያ በዓለም የዜግነት ዕውቅና የሌለባት አገር ናት።

ምስል
የዜሮ ዜማ አገረ ገዢነት። ኢትዮጵያ በዓለም መቅድመ የዜግነት ዕውቅና የሌለባት   አገር ናት ። „ ሳቅን   እብድ   ነህ፤   ደስታንም፤ ---  ምን   ታደርጋለህ ?  አልኩት። “   መጽሐፈ   መክብብ   ፪   ቁጥር   ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.04.2019 ከእመ ብዙሃን ሲዊዘርላንድ ·        መ ቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ያለፈው ዓመት ፋሲካ ለመጀመሪያ ጊዜ በተስፋ ያከበርንበት ነበር። ዘንድሮ ደግሞ ዕንባው አገርሽቶ በጥልቅ ሀዘን። እኔ ከሀምሌ ጀምሮ ስጽፍ ነው የባጀሁት። ያ የፕ/ አለማርያም „ አክ ወሬ“ ይኽው አሁን ጉዱ እዬተዘረገፈ እዬታየ ነው። ሁሉም ትጥቁን ፈቶ፤ ሁሉም ተሰልቦ፤ ሁሉም ሰግዶ፤ ሁሉም ለሽ ብሎ እጁን ሰጥቶ፤ ሁሉም ምርኮኛ ሆኖ በዜሮ ዜማ ላይ ነው ። ምክንያት „አክ ወሬ“ ትርክት፤ ·        አ ይዋ ምንትሶ። ሲኖርህ ትከበራልህ ሳይኖርህ ደግሞ ትጣላለህ፤ ትጠቀጠቃለህ፤ ትወድቃለህ። የተሸከምከውን ገመና ተሸክምህ ባዶ እጅህን አብረኽ ጋሻ ጃግሬ መሆን ላይበቃ በተቻለው ሁሉ ሁልአቀፍ የሆነ ተጋድሎ በማድረግ ላይ የሚገኘውን የአማራ ተጋድሎ መርህ ደግሞ አደናቃፊ ሆነህ ታርፋለህ። አንተ አለመቻልህ አንድ ነገር ሆኖ፤ ሁሉም እንደ እኔ ትጥቁን ፈቶ ያረግርግ ደግሞ ወረርሽኝ ሆኗል። ባይሆን በእጅ የሚል አልተገኘም እንጂ። ውርዴትን አሽኮኮ አድርገህ ተሸክመህ አዝለህ እየዞርክ የባልዳራስን ንቅናቄ አውጋዥ ከሳሽ ሆ...