ልጥፎች
በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ደህና መጡልኝ በ መሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱“ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie 05.06.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። በ መሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። ውስጥህን እዬበወዘ ውስጥነት ሰጠሁኽ ምን አልባት ገና ፅንስ ላይ በእናታቸው ማህጸን ላሉት ላይገለጥ ይችል ይሆናል። ሰ ው ለሆነ ሁሉ ግን ይህ የአለመኖር ዕጣ ፈንታ ወይንም እያሉ ቀፎ ለመሆን መፍቀድ ከጽንስነት የማይሻል ተፈጥሮ ነው ላርባ ላይ ለላ ቢገልጹት መሃንዲሶቹ መልካም ነው። የ ሚገርመው እነሱ የሚያስቡት ኢትዮጵያዊ ዜጋን እንደ ፑፓ ነው። ድፍረት ነው ይህ በራሱ። በግርዶሽ ትዕይንት እያዛሉ የልባቸውን ይከውናሉ። ለ ሰው ልጅ አንገት ነው ወይንስ ሃብል ነው የሚያስፈልገው? ይህን ጥያቄ መመለስ ያለበት ሁሉም መሆን አለበት። 100ሚሊዮን ህዝን ላርባ ነህ ማቹሪቲ ይጎድልሃል የማለትም ያህል ነው ዴሞግራፊ ለእኔ። ዴሞግራፊ ፍልስፍና እያራመድክ በምርጫ ተወዳድረህ ታሸንፋለህ ብሎ ነገር ከቧልትም ያለፈ ሃጢያትም ነው። ዛ ሬ የማከብራትን ብዙም ፈተና የተቀበልኩባትን የክብርት ወ/ት ዳኛ ብርቱካን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ቃለ ምልልሱ ራሱ የተደረገበት ቦታ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ነው። የ ጠ/ሚሩ ቢሮ በሚሰጠው አመራር የሚሰጥ ሁለተኛ የከፍተኛ ዜጎች ቃለ ምልልስ መሆኑ ነው። ይህ የቤተመንግሥት ደረጃ ለOBN መሰጠቱንም በይበልጥ ያረጋገጥ...
ድምጽ አልባዋ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ደህና መጡልኝ ድምጽ አልባዋ የኢትዮጵያ እናት ለፖለቲካ አክተሮች የሊኳንዳ ቤት ማዘጋጀት አይታክታትም … ዛሬም። „ብልህ ሰው መጽሐፍን መስማት ይወዳል። የሚጠራጠር በመጽሐፉ የማያምን ሰው ግን በጥልቅ ነፋስ መካከል እንደምትጉላላ መርከብ ይሆናል።“ መጽሐፈ ሲራክ ምእራፍ ፴፮ ቁጥር ፪ የኢትዮጵያ አዬሩ ስትራፓ ያዘው። ጓጐለ። ውዶቼ እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? እስቲ ድብርታሙን ዛሬን እንዲህ አብረን እንቃኛው … ስክነት የት ይሆን የሚሸመተው? ውስጥሰ ከእርቃንነት መቼ ይሆን ለእራፊ የሚበቃው? ከቶ በቃን ህውሃት መባልን ትናንት በአኽትዮሽ መንፈስ በወል ማዕዶት የታለፈው ማዕደኝነትንም ጎበኘውን? የትውልዱ የሃሳብ ብክነትስ ማቆሚያ ለመቼ ተቀጠረ? መቼም አዘኔታ የለም ትውልዱን በዬዘመኑ ለቋያ ለመማገድ። ሥልጣኔ የለለን መሆኑን ሳስበው አይሆኑ ሆኖ ነገ ጠቆረብኝ። እንደዚህ ሰሞናት ባዶነት ተሰምቶኝ አያውቅም። እንዳሻኝ እምቀምረው ስፈለግ ግጥሙን፤ ስፈልግ ሀተታውን፤ ስፈልግ ልዩ ሪፖርቱን ስፈልግ ወጉን እንዳሻኝ በብራና ወክ እንዲህ ያላልኩበትን ያህል ሰሞናቱን ግን አልቻልኩም። ድብርት ቤቴ፤ ድብርት በብራናዬ ላይ ተዛናከተባቸው እንዳሻቸው … ክብረቶቼ የቀንበጥ ሚዲያ ታዳሚዎቼ እኔ መጻፍ ሥራ ሆኖብኝ አያውቅም። በህይወቴ ቀላሉ ሥራ መጻፍ ነው። ሰሞናቱን ግን በዬአቅጣጫው ያለውን እብለቱን፤ ፌኩን፤ ንደቱን፤ ቦክሱን፤ ውስጥን ከፍቶ እንዳሻህ መባሉን፤ ቁጥበንት መሸጥ መለወጡን፤ መታቀብ መቀበሩን ሳስተውለው ግን ያ ሁሉ ድካም ለምን ስለምን አስፈለ ገን ይሆን? ብዕሬም ብራናዬም ሱባኤ ላይ ነበሩ … ዛሬ የሙት ሙቴን ተሟግቼ...
ተስፋ {የወግ ገበታ}
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ወደ ቀንበጥ በሰላም መጡልኝ ተስፋ። „መዳህኒቴ እና ክብሬ በእግዚብሄር ነው። የረድኤቴ አምለክ ተስፋዬም እግዚአብሄር ነው።“ መዝሙር ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ v ተስፋ ጸጋ v ተስፋ ምህረት v ተስፋ መድህን ነው። ምን ያህል እንደተጓዝኩኝ አላውቀውም? ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም? አለማዋቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸልኝ። ተስፋን እጠብቃለሁኝ። እ.አ.አ 2010 ተስፋ መጸሐፌ ላይ የጀርባው ሽፋን ላይ ያልኩት ነበር አሁንም እምለው ይኸው ነው ... · እ ፍታ እንደ መግቢያ … የኢትዮጵያ ቅኔዎች የእኔም የኔታዎች የቀንበጥ ብሎግ ክቡር ታዳሚዎቼ እንደምን አላችሁልኝ? ዕለቱን ከተሰፋ ፈላጊና ተስፋ ፈጻሚ ጋር ያለው ድልድይ አስመልክቶ አንድ ወግ ቢጤ ለማቅረብ ተሰናዳሁኝ እንሆ … የተስፋ ጥገት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ በእጅጉ ያስፈልጋታል። ይህ ማለት የተሰፋ ጥገት ያለው ያው የፈረንጅ ላሞች ዝርያ ስለሆነ በገፍ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ እዮር ቢፈቅድላት ለእምዬዋ እንደማለት። የፈረንጅ ላሞች ወተተታም ናቸውና። ምኞት ... ግን እኛ ለማይነጥፍ ጥገት ግሬራውን ወይንም ቆሬውን በገፍ ማሰናዳት ይጠበቅብናል። ታዲያ ምርቃታችን ሳንረጋግጥ ጥንቃቄ ከኖረን ነው። በስተቀር ምርቃትን የፈጠረም የሰጠም ኤልሻዳይ አምላክ ከከፋው ያነሳዋል … ምርቃቱን። አምላካችን ሲከፋው ምርቃቱን ...