ልጥፎች

ነገረ አዲስ አበባ "በእልህ ተነሳስተው አዲስ አበባን አስጨነቁ አንዳንድ አመራሮች" ምስጣዊ ጉዞ ………

ምስል
  ነገረ አዲስ አበባ "በእልህ ተነሳስተው አዲስ አበባን አስጨነቁ አንዳንድ አመራሮች" ምስጣዊ ጉዞ ……… እልህ ሊባል የሚገባው የወይብላ ማርያም ቀራኒዮ ዕለት ነበር። እኔ ከሥሩ ሳጠናው።   አዲስ አበባን መዋጥ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሚመራው ዬስውሩ መንግሥት ፕሮጀክት ነው። ግልጥ መንግሥታቸው ኢትዮጵያ እያለ ያነሆልልኃል። ስውሩ ደግሞ ከሥርህ ይነቅልኃል። ያመካኛሉ "ሸኔ" እያሉ።   በ15/11/2022 በነበረው የፓርላማ ውሎ ይልቅ አንድ ሚስጢር አውጥተዋል #ምክትል ከንቲባ ሆኜ እዬሠራሁ ነው ብለውናል። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"       ዬቧልተኛው፤ ዬአሳቸው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቲም ነው ይህን ዬሚለን። በአዲስ አበባ እዬሆነ ያለው ጥቂት አመራሮች በእልህ ዬሚያደርጉት እንጂ የታቀደ አይደለም ይላሉ እነ ዘመን አይፈሬ ማህበረ ኦነጋዊው አመራር። ይህን መረጃ ዬገለፀው ዋዜማ ራዲዮ ሲሆን ምንጩን ገልፆ በዘገባ ያቀረበው ለስላሳው ሚዲያ ኢትዮ ኒውስ ነው።   1) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በ100 ቀን ትጋታቸው ስለምን በሚሊዮን ወጥቶ ዬደገፋቸውን ህዝብ ከሁሉም ክልሎች ለይተው ተውት? 2) ስለምን ከሱማሌ ክልል ግማሽ ሚሊዮን ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ በአዲስ አበባ እና በዙሪያው አሰፈሩ? 3) ስለምን ቡራዩ፤ ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ሰበታ ያ ሁሉ ግፍ በጥዋቱ ተከወነ? 4) ስለምን ኦነግከነትጥቁ እንዲገባ ተደረገ? 5) ስለምን 600 ሺህ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች ከተለያዩ የኦሮምያ ክልሎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደረገ? ዶር ለማ መገርሳ እራሳቸው ዬተናገሩት ነው። 6) አዲስ አበባ በአንድ መኖሪያ ቤት ከመቶ በላይ ለሆኑ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች መታወቂያ በህገ ወጥ እንዲሰጥ ተደረገ? የባልደራስ የመነሻ ምንጩ...

በንቅንቁ መበላት እንዳይኖር ……

ምስል
  በንቅንቁ መበላት እንዳይኖር …… " ዬቤትህ ቅናት በላኝ። "   ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የጎሹ ነገሮች ጥራት አግኝተዋል። የኃይል አሰላለፋ ጥርት ብሎ ወጥቷል። 1) አብይዝምን ተስፋ ያደረጉ ሌላ ፈሰስ ቀይሰዋል፤ 2) ህወሃትን የደገፋ በተንጠልጠል ላይ ናቸው፤ 3) ዬኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችን መደገፍ የቴራፒ ያህል ዬሚያዩት መተርተር ጀማምሯቸዋል፤ 5) በነፃነት ትግሉ በአውራ ፓርቲደጋፊ ዬነበሩት ሙሉ አቅማቸውን ለአብይዝም አራግፈው ኤሉሄ ላይ ናቸው። 6) ተረስቶ የባጀው የአንድነት ኃይል ማፏሸኩን አስታግሶ በጉቶ ላይ እንደሚያጨበጭብ ቀንበጥ ምልስ ቅልስ ማለትን ታቱ እያለ ነው። 7) ፍንካቹ እና ጉራጁ ኢህአዴግ በጀሶ ተጠጋግኖ እዩኝ እዩኝ እያለ ነው። ••••••• ጠቅላዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለአቅመ አዳም አልደረሳችሁም ሁሉ በእጄ ነው፤ ከአምስት ዓመት በፊት ዬነበረችው ኢትዮጵያ ዬለችም፤ ቆባ ላይ ናችሁ፤ ወይንም እጭ ላይ ናችሁ በስላችሁ ብቅ በሉ ሲሉ መራራ ስንብትን አዋሳ ላይ አስታጥቀዋቸዋል። ነገረ ኤርትራ ተከድኖ ይንተክተክ፤ ግን አቅም አላት የእኔ የምትለው የፖለቲካ ድርጅት አላት። በነገራችን ላይ የፓርቲን የአደረጃጀት መርህ ሳያዛባ መንግሥትም፤ ፓርቲም ሆኖ የተደራጀው የግንቦቱ ኢዜማ ነው። ነባር ሥ / አ / አልበተነም ብዬ ነው በጽኑ እማምነው። በጉልህ በአማካሪነት፤ በሎጅስቲክስ ይደግፋታል። ፖሊሲ በማመንጨትም የሊቃናት ስብስብ ነው። በአካሄድ ሆነ በአደረጃጀት እስከ አሁን አ...

ፀረ ኢትዮጵያው አቶ ሌንጮ ይምሩኝ ስትል ኮንቬንሽናል ሴንተር …… አርባጉጉን እርሳው አዲስ #አበባ አራባ ጉጉ ሆኖልኃል ……ብቻ ተውበህ ተገኝለት ለሞነር ዬቁም ተዝካር።

ምስል
    ፀረ ኢትዮጵያው አቶ ሌንጮ ይምሩኝ ስትል ኮንቬንሽናል ሴንተር …… አርባጉጉን እርሳው አዲስ # አበባ አራባ ጉጉ ሆኖልኃል …… ብቻ ተውበህ ተገኝለት ለሞነር ዬቁም ተዝካር።   ይህ ሠርግና መልስህ ከሆነ በዕለተ ሃሙስ ኮንቬንሽናል ሴንተር ቤተኛ መሆን ነው። ኮንቬንሽናል ሴንተር ሃሙስ ቀጠሮ ተይዟል አገር አልባ ላደረገህ መቅሰፍታዊ ዘመን ወረፋ ይዘህ ተሰልፈህ ተገኝ እና ስለሞትህ ማረጋገጫ ፊርማ ስጥበት ¡¡¡¿¿¿¿ ማህበረ ጲላጦስ ጋር ማህበርተኛም ሁን። ያምርብኃልና ¡¡¡¡ " ዬቤትህ ቅናት በላኝ " አትገኙ ዬሚል ቅስቀሳ አለ ተብሏል። አቶ ወንድም አቤ ቱኩቻው ነው ይህን ሲል ዬሰማሁት። ይህ ዬተገባ አይደለም። የሚቃወም እንደአለ ሁሉ ዬሚደግፍ መኖሩ ተፈጥሯዊ ነው። ለዴሞክራሲ እንታገላለን ከሆነ ዬማይማቹትን ሃሳብ ሁሉ ማስተናገድ ይገባል። ሌላውን መጫን ዲስክርምኔሽን ነው። ሞልቶ የፈሰሰ ሃቅ ስላለን እሱን አቅርበን እንሞግታለን። ዬሚሞገተው ሰውኛ ለሆነ ተፈጥሮ ብቻ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ማን እንደተገኜ ማወቅም ይጠቅማል። ዬተወሰነ ኃይል ተገኝቶ ለታሪክ በሚያመች መልኩ ሂደቱን ዘግቦ መያዝ ለሰባዕዊነት፤ ለተፈጥሯዊነት፤ ለፓን አፍሪካ ሙቭመት እጅግ ጠቃሚ ነው። ለዚህ ግብረ ኃይል አደራጅቶ መሰነድ ይገባል። በተለይ # ዬአማራ ማህበር በአሜሪካ ታሪኩን መያዝ ይገበዋል። አሁን ዬሚሰጠው ፊርማ 360 ቀናት አሜሪካ ነጩ ቤተ መንግሥት አስፓልት ላይ ካለ እህል ውኃ ቢቀመጡ ከቶውንም ...