ልጥፎች

ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዛሬ ጀምሮ የሦስት ቀን የሱባኤ ዓዋጅ አወጀች።

ምስል
ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከዛሬ ጀምሮ የሦስት ቀን የሱባኤ ዓዋጅ አወጀች። "ዬሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱)   ፈተና ጥገቷ ዬሆነው ቅድስቷ እናታችን ማህበረ ምዕመኗ ሦስቱን ቀን፣ በፆም፣ በሱባኤ፣ በጥሞና፣ በስግደት ያሳልፋ ዘንድ ግሎባል ዓዋጅ አውጃለች። የዚህ ግራጫማ የሲቃ ዘመን የፈተናው ሁሉ ሸክም የተጋተችው ቅድስት እናታችን በተረጋጋ፣ በሰከነ፣ በተደሞ ሆና ዛሬ ሱባኤውን ብፁዑ ቅዱሳናት አቨው አህዱ ብላለች። ፈተና ሲጠፋ ፈተና እንበረታ፣ እንጠነክር፣ እንፀና ዘንድ ብለው ሱባኤ የሚገቡት የአቨው ይትበኃል ሕይወቷ ነውና፣ ዘመኑ ሰርክ የሚደቅንባትን ፈተና ትቋቋመው ዘንድ አምላኳን፣ ፈጣሪያዋን በአኃቲ ድምጽ ትለምናለች። ሐዋራያዊቷ ቅድስት እናት ቤተ ክርስትያን በተደሞ ልቅና፣ በዕድምታ ልዕልና በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ይህን ጭጎጎት ዘመን ትሻገረዋለች። ሰማዕቷ ፀጋዋ፣ ብርታቷ፣ መሰጠቷ ዬሚቀዳው ከሰማያዊ ኤዶም ነውና ዛሬም ስለ አገረ ኢትዮጵያ ሰላም፣ ስለ ሕዝቦቿ አንድነት እና ፍቅር ትሰብካላች፣ ታስተምራለች፣ ትለምናለች። በዘመናችን ይህን መሰል ንዑድነት ያሳዬን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን። ሁሉን የሰጠን አምላካችን ሁለንም አድርጎልናል። ሙሴ አለን። እረኛ አለን። ጠባቂ አለን። ስለሆነም ከትልልፍ ወጥተን አኃቲ ቤተክርስትያናችን በምትሰጠን መመሪያ መሠረት በአርምሞ፣ በጥሞና፣ በንጽህና ሦስቱን ቀን እናሳልፍ። ምንም ዓይነት የሥጋዊ ልቅምቃሚ ሰበር ዜና ወሬ ሳያስበረግገን፣ ለዛም አቅል ሳንመግብ፣ ለእሱም ደራሽ ሁነት ሳንሰግድ ዕዝነ ልቦናችን ከእናታችን ከቅድስት ቤተ ክርስትያን ውሎ እና አዳር ዜና ብቻ ይሆን ዘንድ በትህትና አሳልፋለሁ። ከተወረወረ ቀስት እንድን ዘ...

ፕትርክና አይገባኝም ስላሉ ብቻ መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በወታደር ይጠበቁ የነበረት ከወላይታ የተገኙት ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ

ምስል
ፕትርክና አይገባኝም ስላሉ ብቻ መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በወታደር ይጠበቁ የነበረት ከወላይታ የተገኙት ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ *** የቀደመው ስማቸው አባ መልአኩ ይባላሉ። ምንም እንኳን ውልደታቸው በጎንደር ጋዢን በምትባል ስፍራ ቢሆንም ረጅም ዕድሜያቸውን ያሳለፉት እና አብረው የኖሩት ማህበራዊ ስነልቦናቸው ያገኙት ወላይታ በሚባል ደቡባዊ ምድር ላይ ነው። ከሀገሬው በላይ ወላይተኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከውልደት ስፍራቸው በቀር አኗኗር እና አዋዋላቸው ሙሉ በሙሉ ከአንድ የወላይታ ገበሬ የተለየ አልነበረም። የመጽሐፍት ትርጓሜ በእዚሁ በወላይታ ምድር ባሉ ጉባኤ ቤቶች አጠኑ።ስርዓተ ገዳም ከተማሩ በኃላ በእዚያው ወላይታ በሚገኘው ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም መኖከሱ። የብህትህና ህይወታቸው በወላይታ ምድር ጀመሩ። ከ1926-1968 ለ42 ዓመታት ወላይታ ላይ በወላይተኛ ቋንቋ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመው ከ300,000 በላይ ኢ- አማንያንን እንዳስጠመቁ እና ከ65 በላይ አብያተክርስቲያናትን አሳንጸዋል። በእዛ ዘመን አስበኅዋል ወዳጄ? የደርግ መምጣትን ተከትሎ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን 2ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ የነበሩት ብጽኡ አቡነ ቴዎፍሎስን ተገደሉ። በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስቲያን 3ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ ለመምረጥ 909 አከባቢያቸውን የሚወክሉ አባቶች በአዋጅ ሰበሰበች። ከ565 ወረዳዎች ለማዕረገ ፕትርክና መንፈስ ቅዱስ የሚመርጠውን አባት ይገኝ ዘንድ ሁለት ሁለት ተወካይ ይላክ ዘንድ ታዘዘ። ገና ማዕረግ ጵጵስናን ያልተቀበሉት በቁምስና ያሉት መኖክሴው የወላይታው አባት የሆኑት አባ መላእኩ ከወላይታ "ተወካይ ሆኜ አልሄድም" ብሎ እንቢ ማለትን ከጅምሩ ቢያሳውቁም በገዳሙ አባቶች ትዕዛዝ እና ቃለ ውግዘት የወላይታ አው...

ሂደቱ ዬ5 ዓመታት መሰናዶ ነበር።

ሂደቱ ዬ5 ዓመታት መሰናዶ ነበር። ብጹዑ አቡነ ቀውስጦስ (ዶር) አገር ሲገቡ ቃለ ምልልስ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ተደርጎላቸው ነበር። ልዩ ሁኔታ ነበረው። ዛሬም ዬእሱን ዕይታ ሳደምጠው ያን ጊዜ እጠረጥር በነበረው ልክ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ዬገዘፈ መከራን ያዘለ ነው። ትናንት ሳዳምጠው «ከህግ ውጪ ዬወጣን ነገር በህግ ብቻ መፍታት አይቻልም» በማለት ማስፈራራት፤ መጫን፤ ትዕዛዝ መሰል ዕይታ ሲቃርብ ጨርሼ ማድመጥ ተስኖኝ አቋርጬ ወጣሁኝ። እሰሩ ሲል ሲታሰርለት። ፍቱ ሲል ሲፈታለት አፈ ካቢኔ ሆኖ ባጅቷል። አሁን ቀድሞ በሰራው እጅ ሥራ ደግሞ በድፍረት ሲናገር ሰማሁት። ቀደም ባለው ጊዜ ዬበዛ ክብር ስለነበረኝ ስሙን ብዕሬም ብራናዬም አንስተውት አያውቅም። ዬአሁኑ ግን ድፍረቱ እጅግ ገረመኝ። ለሰማይ ለምድር ዬገዘፈች አገር በእጇ ላበጀች ቤተ ክርስትያን ይህን ያህል መጫን ዬጤና አይመስለኝም። ሌላው ቀረቶ ዬዛሬ 5ዓመት ዬነበረ ትህትና ዛሬ አላዬሁም በብፁዑ አቡነ ቀውስጦስ (ዶር) በመታብይ ብትፈጽሙ ባትፈጽሙ ውርድ ከራሴ ሲሉ ገልጸዋል። ማህከነ። እግዚዖ ተሳህለነ። ። ጥበቃው ዬፈጣሪ ስለሆነ አንድዬ ይሁነን። አባታችን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛብዙውን ከድነው፤ አያሌውን ህፃፅ ወደ ራሳቸው ወስደውታል። እራሳቸውን ነው ዬወቀሱት ከእንግዲህ ዬሳቸውም ህይወት ጥበቃ ያስፈልገዋል። ብልሆች ቢያስቡበት ጥሩ ነው። እሳቸው እራሳቸው ክስተት ናቸው። ማድመጥ ለመሪነት ተሰጥዖ ነው። ይህ ግዴታም ነው። በጉልህ ዬተነሳው ዬማድመጥ ችግር ነው። ዬሆነ ሆኖ ጉዳዩ ይህ አይደለም። በአገር ላይ አገር ዬመገንባት ሂደት ነው። ዬወደቁ መላዕክት እንዳሉ ሁሉ እንደ መጸሐፈ ሲራክ ሚስጢራት ይህም ዘመኑን በምድራችን በምልሰት አሳይቷል። አሉታዊ ዴሞግራፊ በህጋዊ መልክ ዬተፈፀ...

መከራው የዕለት ደራሽ አይደለም። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ= ዘ ቬርሙዳ ትርያንግል።

መከራው የዕለት ደራሽ አይደለም። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ= ዘ ቬርሙዳ ትርያንግል። ዬግራጫማው ዬሲቃ ዘመን ፍልሚያው ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያዊነት ጋር ነው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" በቅንነት፤ አማራጭ የለም በማለት፤ የፈለገው ይሁን በማለት፤ ሃይማኖት ነክ ነው በማለት፤ ወይንም ፖለቲካ ቀመስ ነው በማለት፤ ወይንም በገዘፈው የህወሃት ችግር ምክንያት እሱ ከሚመለስ በሚል፤ በከበደ መልኩ የሶሻሊስት ርዕዮት መጤ ሃሳብ ተፈጥሯዊ ከሆነው ከኢትዮጵያ አመሰራረት ጋር ባለመመጣጠን ብዙ አቅም የዴሞክራሲ ፍላጎቱን ጥረት አሰልቺ አድርጎታል። ከዚህም ዬተነሳ አቅምን መጥኖ፤ አቅምን አዋህዶ፤ አቅምን አዋዶ ቢያንስ እንደ ኩርድሽ ብትን አፈር ለማኝ እንዳንሆን በሚያደርጉን መሠረታዊ ብሄራዊ አመክንዮ ስክነት ነሳን። የእኛ የምንላቸው አቅሞች ዛሬ የሌላ ናቸው። ተሳስተውም ይሁን ተዘናግተው፤ ተዘናግተውም ይሁን አማራጭ የለም ከሚል ድፍን እሳቤ በቅንጥብጣቢ ጉዳዮች ብቻ ሲደመሙ የገዘፈው መሠረት ንደት ቁብ ሳይሰጡት አያለሁኝ። ይህም ብቻ ሳይሆን መለያ ክብራችን ንፁሁ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅን ጥንት የህወሃት አመጣሽ ብለው የተጠዬፋትን ዛሬ ህጋዊ ሲሉ አዳምጫለሁኝ። ጋዜጠኛ አቶ ሲሳይ አጌና በብዙ ሁነት በአብነት ትምህርት ቤት ስንጠቅሰው ኑረናል። አብሶ እኔ። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አድናቆት ቃሉ እራሱ ምንጩ ዬእኛ ምስክርነት ነበር። ለረጅም ጊዜ እዬሰማሁ፤ እንዳልሰማሁ፤ እያዬሁ እንዳላዬሁ ተጨማሪም ተቃውሞም ሳልሰጥ ቆዬሁኝ። ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ብዕሬ አነሳችው። ሌሊቱን ሁሉ ሳስበው አደርኩኝ። እኔ ዬማላውቀው እሱ ዬሚያውቀው አገራዊ ችግር ምንድን ይሆን ብዬ። ከውድቀቱ አካሄድ ጋር እራሱን አስማምቶ ይህን አትዩት፤ ይህን አትስሙት፤ አዋጪው መንገድ ይህ ነው እያለ ...

ዬአማራ ክልል መሪ ድርጅት ዬብአዴን ደረጃ በዘመነ ገዳወዖዳ ሥርዕወ ……

ምስል
·         ደቡብ ክልል ጣጣው አላለቀም ደረጃውን ማውጣት አልቻልኩም። ይቅርታ።

ሸክም ዬሙጃ። 05.01.2023

ምስል

ሱባዔዋ ትዕይንት።

ምስል
·        ሱባዔዋትዕይንት። ( ዬፊደላት - ቃና።) ·        ኢትዮዽያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ ዬተፈጠረ ሚስጢር ነው። ·        ኢትዮዽያዊነት ፍልስፍና ነው። ·        ኢትዮዽያዊነት ሳይንስ ነው። ·          ኢትዮዽያዊነት ዩንቨርስ ነው። ·          ዬኔወቹ እንዴት አመሻችሁ? ቸር እደሩልኝ። አሜን። ሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 03.01.2023 ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር ከተማ።