ዬፀጋዬ ራዲዮ ከተመሠረተ እንሆ #መስከረም 18/2023 እኤአ #ሙሉ 15 (፲፭) ዓመት ዛሬ ሞላው።
ዬፀጋዬ ራዲዮ ከተመሠረተ እንሆ #መስከረም 18/2023 እኤአ #ሙሉ 15 (፲፭) ዓመት ዛሬ ሞላው። "ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፤ የወይራ ሥራ ቢጓደል፤ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፤ በጎች ከበረት ቢጠፋ፤ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ጌታ እግዚአብሄር ሃይሌ ነው።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ከቁጥር 17 -18 ) ይህ ቃለ ወንጌል የህይወቴ ማኒፌስቶ ነው። ቤተሰቦቼ የሰብሊ መንገድ ይሉታል። ለቅኖች ህሊና ላላቸው ወገኖቼ ብቻ እንዲያነቡት የተፃፈ ነው። ከዕውነት ጋር ለሚዘልቁት ወጀብ በመጣ ቁጥር ለማይወዛወዙት ጽኑ ዕውነቶች። ሼር አድርጉት ብዬ አላስቸግራችሁም። ታሪክ መሠረት መያዝ ስላለበት ለዛ የተፃፈ ነው። የፀጋዬ ራዲዮን መንፈስን የሚያግዙ ሁለት ዩቱብ ቻናሎች፤ እና አንድ ብሎግም ሊንኮችን አያይዣለሁ። አመሰግናለሁ። https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list= Matt Tsegaye https://www.youtube.com/channel/UCJEQXw86u_NG4A1FVC1j2qg https://www.youtube.com/channel/UCb4Maqp24liAGdbPE553WGA https://sergute.blogspot.com/2021/02/blog-post.html?spref=tw ልክ የዛሬ 15 ዓመት ይህ ቀን የፀጋዬ ራዲዮ ስጀምር ስደተኛ ካንፕ ውስጥ ነበርኩኝ። ቴሌቪዥን መስመር፤ የስልክ፤ የኔት ግንኙነት፤ የኮንፒተር አክሰስ በለለበት ሁኔታ በዙሪክ ክ/ አገር በአንደልፊንገን ዞን በክላይነአንደል ፊንገንባድ የስደተኛ ካንፕ ውስጥ ሆኜ የፀጋዬ ራዲዮን መሠረትኩኝ። ከዛ በፊት በዛ ሁኔታ ላይ ሆኜ ቀድሜ ለአንድ ዓ...