ልጥፎች

ልቅና በልዕልና፨ ቢስ አይይብን፨ አሜን፨ #ማህበረ #ቅንነት እንዴት አደራችሁልኝ። ኑሩልኝ ክብረቶቼ።

ምስል
#ማህበረ #ቅንነት እንዴት አደራችሁልኝ። ኑሩልኝ ክብረቶቼ። ዛሬ እማመሰግናቸው ወጣቶች አሉኝ። የፀጋዬ ራዲዮም ለ16 ዓመት የተጋበት፤ የከበቡሽ ልሳንወርቅ ሚዲያም ከውስጡ፤ ከህሊናው ዝቀሽ ተስፋን ሰንቆ ያመሰግናቸዋል። ትናንት ሙሉው ቀን እስከ ማምሻ ድረስ ስለነሱ ነበርኩኝ። ይገባቸዋል። አዋርዳቸው ምስግና ነው። ሽልማታቸው ምርቃት፤ ፀሎት እና ድዋ። አልጠግባቸውም። እነ ማህበረ #ማንጠግቦህን ።   1) #ሩህሩሁ ኮሚዲያን እሸቱ መለሰ፤ 2) የሙያ #ህግ አክባሪው ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ። ምን የቀረው አለና በፍቅር እኮ እያስተዳደረን አይደል? " ልጅ ግዛቸው" 3) #የሳቁ አጤ አቶ ማንያዘዋል እሸቱ፤ 4) ቡናዬን #ዝምን ያደረጋት ሊቀ - ትጉኃኑ አቶ ከናዕን አሰፋን፦ 5) #የእሽታ አውታሩ አቶ ጥጋቡ ኃይሌ፦ የአወንታዊነት አርበኛዬ። 6) መሳጩ #ልዩ አቶ ኢዘዲን ካሜል።    በተለይ ሚዲያ ላይ የሚሠሩት ለሚዲያ #ትርታ ናቸው። ሁሎችም ትህትናን ዕውቅና የሰጡ ወጣቶች ናቸው። ርህርህናን የተቀበሉ ወጣቶች ናቸው፨ ፈርኃ እግዚአብሄር፤ ፈርኃ አላህም ያላቸው፤ አምላካቸውንም ያስቀደሙ፤ #ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የተስፋ #ብራወች ናቸው። #እስፔኖችን #ቢስ #አይይብኝ ። አሜን።   ·         https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye ·         https://sergute.blogspot.com/2021/02/. https://www.facebook.com/sergute.selassie/    https://www.youtube.com/channel/UCJEQX...

የሰውን ልጅ መኖር በግፍ መቀማት #ስርቆት አይደለምን?

ምስል

#ማን ተጫወተው? ለእንግሊዞች ለዋንጫ ውድድር እግዚአብሄር ነው የፈፀመላቸው ማለት ይቻላል።

  #ማን ተጫወተው? ለእንግሊዞች ለዋንጫ ውድድር እግዚአብሄር ነው የፈፀመላቸው ማለት ይቻላል።   #ማን ተጫወተው? ለእንግሊዞች ለዋንጫ ውድድር እግዚአብሄር ነው የፈፀመላቸው ማለት ይቻላል። ያን አሰልቺ ላንግባይሊክ፤ እጅግም አድካሚ ለተጫዋች ብቻ ሳይሆን ለተመልካች የአጨዋወት ዘይቤያቸውን ይዘው በፔናሊቲ ሎተሪ ዛሬም ሆላንድን ሁለት ለአንድ ረተው ለዋንጫ ተፋላሚ ሆነዋል። ግርም ነው ያለኝ። በግል ያላቸውን ብቃት ሳያቀናጁ ለዋንጫ መብቃት የእግዚአብሄር ሥራ ነው ማለት እችላለሁኝ። በግል በጣም ቀልጣፋ ኮከቦች እንዳሏቸው አስተውያለሁ።    ዛሬን በጎል እልልታ አህዱ ያሉት መጀመሪያ ለግብ የበቁት ሆላንዶች ነበሩ። እንደ ጀርመኑ Das Erst ትንታኔ ሆላንዶች ለዚህ ዕድል ለመብቃት 20 ዓመት ጠብቀዋል ብሎ ነበር። ዛሬ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እንግሊዞች ተስለው ነበር የቀረቡት። ባይቀጥሉበትም። አቻ ያበቃቻቸውን ግብ ያስቆጠሩት በለመዱት ፔናሊቲያዊ ዕድል ቀንቷቸው ነው።ከእረፍት መልስ ሁለተኛውን ግብ አክለው እንሆ ሆላንድን ረተው ለዋንጫ ደረሱ። ይገርማል።    ትናንት ብቃታቸው በግል እና በቡድን በቋሚነት እያሳዩ የመጡት ስፔኖች በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ፈረንሳይን ሁለት ለአንድ በሆነ ጎል ብቻ ሳይሆን በጨዋታ ብልጫ በአቅም፦ ብቃት ፈረንሳይን ሸኝተው እነሱ ለዋንጫ አልፈዋል። #ይገባቸዋልም ። ዬፈረንሳይ ቡድን ካታር ላይ ለዓለም ዋንጫ ያበቃው ያ ታይቶ የማይጠገብ ቅልጥፍናው እና አርቱ ብቃቱ ሸሽቶት ከዚህ ግባ የሚባል ጨዋታዊ ትዕይንት ሳያሳይ ነው ከዚህ የደረሰው።   #ኦስትርያ ፤ #እምዬ ሲዊዝ፤ #ቱርኪ ፤ የክርስቲያ ሮናልዶ እና የፔፔ ፖርቹጋል፦ እንዲሁም ቀደም ብሎም #ኮራ ተሰናብተው #የእንግሊዝ ...

የሰውን ልጅ መኖር በግፍ መቀማት #ስርቆት አይደለምን?

ምስል
  የ ሰውን ልጅ መኖር በግፍ መቀማት # ስርቆት አይደለምን ? " የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፦ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። " ( ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ )    # መቅድም ። እ ንዴት አላችሁልኝ ክቡራት እና ክቡራን የልቦቼ። ደህና ናችሁ ወይ ? ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጠሩ አገዛዞች የሚቆሙት ባላ እና ወጋግራወች ኢትዮጵውያን በሚከፍሉት መስዋዕትነት ነው። የኢትዮጵውያን አብራክ እና ማህፀን ቄራ ነው ዘመን ከዘመን። እግዚኦ። በተለይ አማራ። እኔ ከተፈጠርኩ፤ ነፍስ ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ በተፈጥሮ አደጋ ከምናጣቸው ቤተሰቦቻችን በላይ በድህነት፤ በአስተዳደር ብልሹነት፤ በጦርነት የምናጣቸው ወገኖቻችን ይበልጣሉ። በተፈጥሮ ሞት የምናጣቸውም ቢሆን በድህነት የሚሞቱ ወገኖች አሉን። ድህነት እኮ የበሽታ ምንጭ ነው። ጭንቀት ይፈጥራል። ለበርካታ በሽታወችም ያጋልጣል ድህነት። በተስተካከለ የህክምና እጦት ምክንያት የምናጣቸው ወገኖች አሉን። በእስራት፤ በአፈና የምናጣቸው ወገኖች አሉን። ይህ ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በሰው ልጅ መኖር ላይ የፈፀመው ስርቆት አይደለምን ? የቀደሙትም ቢሆን ሊጠዬቁበት የሚገባ ነው። ሚሊዮን ተረጂ አልበቃ ብሎ ማደህዬትም ታቅዶ እዬተሰራበት ነው። ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ሰባዕዊ ጉዳዮች እያሉ ሚሊዮኖች ከጎርፍ ጋር እያደሩ አንድ አይሉ ሁለት # እዮቤል ቤተ - መንግሥት እና በዛ ዙሪያ ለሚሰባሰቡ ድሎተኞች ሽሙንሙን ቢሮ መገንባት የዜጎችን የመኖር ተስፋ መቀማት አይደለም...