ልጥፎች

የአትሌት ሲሳይ ለማ #አብነትነት ትውልዱ፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ምን ይማሩበታል?

ምስል
  የአትሌት ሲሳይ ለማ #አብነትነት ትውልዱ፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ምን ይማሩበታል?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     ግን እንዴት ሰነበታችሁልኝ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁን? ሰሞኑን ተጠፋፋን። የዘንድሮን ኦሎንፒክ ብዙም አልተከታተልኩትም። ምክንያቴ ውዝግቡ አውሎማ ስለነበር ብቻ ሳይሆን መክፈቻው ላይ የነበረው ሁነትም ብዙ በትጋት እንድከታተለው አልገፋፋኝም። የሆነ ሆኖ የሴቶቼ 10 ሺን፤ የወንዶች ማራቶን እና የሴቶች ማራቶን ተከታትያለሁኝ።   በውድድር ማሸነፍ እና መሸነፍ እኩል ዕውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ። ድካሙ #እኩል ስለሆነ። በልፋት፤ በጥረት የሚገኝ መሸነፍም ቢመጣ ከባለ መዳሊያው ጋር እኩል ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። አሰልጣኞችም ቲሙም እንደሚያስገኙት ውጤት ሊመዘኑ ይገባል ባይም ነኝ።    አራቱ ኮከብ አትሌቶች መዳሊያ ያስገኙት በዛ ውዝግብ ላይ ሆነው ነው። ይገርማል። እንደምን ተረጋግተው ለድል እንደበቁ ሚራክል ነው - ለእኔ። የውስጥ ሰላም ከሌለ የጎረስከውን እህል እንኳን በቅጡ አጣጥሞ መዋጥ ያቅታል። በአፍህ ውስጥ ከርታታ ስደተኛ ይሆናል። ይተናነቅኃልም። አትሌቶች ተሰናድተው ሄደው ግን የውድድር ዕድል ተነፍጓቸው ሲመለሱ፤ የተፈቀደላቸውም አሰልጣኛቸውም ግዳጃቸውን ሳያጠናቅቁ #ተመላሽ ሲሆን፤ በቀጥታም ይሁን በተጠባባቂነት የተመረጡትም ተመላሽ ሲሆኑ በራሱ በቀሪ ተወዳዳሪወች ላይ ሊያመጣ የሚችለው #ተጽዕኖ ከባድ ነው። ተስፋቸው ይኮማተራል።    አትሌቲክ ብቻ ሳይሆን ስፖርት የአንድ አገር #የውጭ #ጉዳይ ሚር ማለት ነው። ኢኮኖሚካሊም የሚክስ፤ ለተሳታፊወች የመኖር ዕድላቸውን ቧ አድርጎ የሚከፍት፦ ታሪክን በዓለም አደባባይ የሚያበጅ ልዩ አርት ነ...

ስለ አሜሪካ እና ስለ 100 ዶላር በማውራቴ የመጣብኝ ጉድ... ፡ ጭራሽ Appleን ለቆ መጣ!! #apple #ame...

ምስል

ክብርህ እየሸሸህ ሲሄድ የመሪነት ወንበርህ መሸርሸሩን አስበህ ከታበይክበት መንበር ወርደህ ሱባኤ ግባ። 09.08.2019

 በቀይ የደም ሴል አፈጣጠር ግጭት እንደሌለው ሁሉ በኢትዮጵያዊነት ማንነት እና አማራነት ግጭት የለም።  ተፈጥሮዋዊ ነውና።    አማራ መሆኔን እወደዋለሁ፣ ሐሤትም አገኝበታለሁ።  የዕድምታው ቅኔ ቃና በሱባኤ፣  በድዋ የተቃኘው ሚስጢር ሽልማቱ ወደርየለሽ ማንጠግቦህ ስለሆነ።    በዘመን የኢትዮጵያዊነት ፈተና ላይ ከጠሚሩ ጀምሮ ቁንጮዎቹ ጅራት ሆነዋል።  አማራ ሰው አይደለም ከማለት ጀምሮ ብዙ መንጠራራትን አዩን፣ እነሱ ዘጭ እኛ ከፍ። ተመስገን።    በኢትዮጵያዊነት ሚስጢር የቆሞሱ አማራ ቤተሰባቸው እንጂ ጠላታቸው አለመሆኑን አመሳጥረውታል።  ብዙዎች ሲንጠባጠቡ ጥቂቶች ነጥረው ወጥተዋል። ተመስገን።    አማራና ኢትዮጵያን መነጣጠል የማይቻልበት ሚስጢር መግቦቱ ነው።    በዘመን መፈራረቅ፣ መደበላለቅ አማራና ኢትዮጵያዊነት ተቀላቅለው  ሳይሆን ተዋህደው ይገኛሉ። ስለምን? አማራ አቅሙን መግቦ አበጅቶዋታልና።    ለዚህ ዘመን ቀለበት ይታሰርለት የ፷ዓመታት የዜግነት ቁማር ግባዕቱ ስለተፈፀመ።    ያላበለ ኢትዮጵያዊነት ጤና ነው። ያበሉት የድዌ ሽልማተኛ ናቸው።  እጭጌው ሂደት ያንዘረዝራቸዋል።    ኢትዮጵያዊነት ፈውስ ነው።    አማራ ከኢትዮጵያ ጠረን ለሰከንድ መኖር አይችልም። እስትንፋሱ ናት። ንጹህ አየሩ።    አማራ እና ኢትዮጵያ የተፈጣጠሩ ናቸው።     አማራ ግቡ ኢትዮጵያ ናት።    ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።     #አላዛሯዋ ኢትዮጵያ ክህደትን በእዮራ...

ተሰብራለች ግን ታምራለች! ሐዋርያዊት።

ምስል

ካናዳ በስኮላርሺፕ መውሰድ የሚችለው ብቸኛው ጥቁር ፕሮፌሰር! ከካናዳ ጠ/ሚ ልዩ ሽልማት ተቀብሏል!#canada#pr...

ምስል

በ14 ዓመቷ ጠለፋት! ያለቤተሰቧ ፈቃድ አስጠመቃት!|| እንተንፍስ #26

ምስል

ይቅርታ! | 4 ሺህ 6 መቶ ሠራተኞቹ እና ዶፉ የዶላር ምንዛሪ | የፍትሕ ተማጽኖ ለኦሎምፒክ ኮሚቴ | ክፍል 2

ምስል

ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???

ምስል
  ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)          ለትውልድ የሆነ #መሰጠት ። ለአደራ ያበቃ #አጽናኝነት ። ባለ አሻራ #አይዟችሁባይነት ። ድንቅ - የሚያስቀና - የሚመስጥ ሰብዕና። ዕጣ ነፍስ #በይቻላል መንፈስ ችግርን የመጋፈጥ ልዩ ተጋድሎ። አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። የፕለይ ፀሐፊወች ይህን የዕውነተኛ ታሪክ ጭብጥ ትዘሉት ይሆን???   የእዮር #መሰጠት ። ዓለም ዓቀፍ ሸላሚ ድርጅቶች አሜሪካ እና ካናዳ ያሉትም የኢትዮጵውያን ተቋማትም ይህን ብቃት #ባሊህ ይሉት ይሆን ወይንስ #ያገሉት ??? እምናዬው ይሆናል።   አብነትትነት ይህ ነው። #አሻራ ይህ ነው። የአገር #ካስማነት ይህ ነው። #የትውልድ መሆን ይህ ነው። #ሰዋዊነት ይህ ነው። #ተፈጥሯዊነት ይህ ነው።     እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል እላለሁ። መፃህፍቶቼ ላይም አበክሬ እገልፀዋለሁ። ይህ ጥሪ፤ ይህ ለደግነት ፖስተኝነት፤ ይህ ችግርን ተቋቁሞ ለመፍትሄው የመምራት የማስተዳደር ብቃት እንዳይሰወር ስለምሰጋ ነበር እንደዛ እምተጋው።    እንዲህ በጥሪ ልክ ሆኖ መገኜት #መታደልም - #መመረቅም - #መሰጠትም ነው። አንድ ሰው ይህን ያህል ችግርን የመቋቋም አቅም ከዬት አገኜ? #ከእዮር #አደባባይ ። #ቅንነት የሰራው #ደግነት ነው።    ሁሉም ለአንዱ ፦...