ልጥፎች
ክፋ ሃሳብ #ይጋባል። ያገባልም።ክፋ ሃሳብ #ተጓዥም ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ክፋ ሃሳብ #ይጋባል ። ያገባልም። ክፋ ሃሳብ #ተጓዥም ነው። "የቤትህ ቀናት በላኝ።" ክፋ ሃሳብ #ይዛመታል ። ሲንቀሳቀስ #ፈጣን ነው። እንደ እኔ ዕሳቤ ከብርሃን ፍጥነትም ይቀድማል የሚል ዕምነት ነው ያለኝ። ምንም እንኳን ጥናታዊ ሥራወችን ለመከወን ሁኔታው ባያመቸኝም። የሆነ ሆኖ ክፋ ሃሳብ የሰውን ልጅ ትዳሩ አድርጎ አግብቶ የመኖር አቅም አለው። ከአንዱ ክፋ አሳቢ ተነስቶ ሌላውን ለማጥቃትም ሲነቃነቅም፦ ማለትም ክፋቱን #ለማጋባት ቀላል ፎርሙላ ነው ያለው ነው። ያም መቻቻልን፤ ታጋሽነትን ነጥቆ እያጣደፈ ከሚቀቅለው የክፋ ሃሳብ ውቅያኖስ ወስዶ ይዶላል። ክፋ ሃሳብ ማስተዋል ላይ ጫና ፈጥሮ ወደ ድርጊት ተሎ የመንቀሳቀስ አቅም አለው ብዬም አምናለሁ። ለክፋ ሃሳብ #ህግ የተፈጥሮ፤ ሰው ሠራሽ #ድንጋጌወች ፤ #ባህላዊና #ትውፊታዊ ተለምዶወች ግድ አይሰጠውም። ይሉኝታ አያውቅም። ለነገሩ ይሉኝታ ያላት ብቸኛዋ አገር ኢትዮጵያ ናት። የሆነ ሆኖ ክፋ ሃሳብ ተጣዳፊ እና ሽሚያ ላይ ዘመኑን ሁሉ ስለሚሰዋ የማጥቃት አቅሙ ኃያል ነው። ክፋ ሃሳብ የሚንቀሳቀሰው #በቲምም ነው። የቲሙ አባላት መለያቸው #ተበቅለው የማይጠግቡ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፦ አዲስ አባላትን ለማፍራት ጥድፊያቸው ለጉድ ነው። ፤ #ጦርነት አነሳሹ፤ ማንኛውም ዐይነት ወንጀል፤ #ጥላቻ ፦ ዘረኝነት፤ አግላይነት፤ ተጫኝነት እኮ የክፋ ሃሳብ የቲም አባላት ናቸው። ክፋ ሃሳብ ቁንጥንጥ እና ስክነት የነሳው ነው። ምክንያቱም ማስተዋልን ተረግጦ ተልዕኮውን ስለሚያስፈጽም። ለምሳሌ አቶ "ሀ" አቶ "ለን" ሲገድለው #ገዳዩ #ክፋ #ሃሳብ ነው። አዝማቹ ክፋ ሃሳብ ነው። አቶ #ሐመርኋ አቶ ...
ሴቶች #ተገደው #ሲደፈሩ #በዓዋጅ ነውን??? (Vergewaltigung, Leiden, Sterben.)
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ሴቶች #ተገደው #ሲደፈሩ #በዓዋጅ ነውን???
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ሴቶች #ተገደው #ሲደፈሩ #በዓዋጅ ነውን??? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በሕፃን ሔቨን ጉዳይ ጠንከር ያሉ ውይይቶች እዬተካሄደ ነው። በተለይም "የሴታ ሴት ፓወር" የሚባለው አዲስ ሃሳብ የያዙ ወጣት ሴቶች ሙግቱን በቲክቶክ ፎርማት ተጠቅመው ጠንክረው ይዘውታል። ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ቤተልሄም አካለወርቅ ወጣት ትንታግ ናቸው። ከሀሌታ ሚዲያ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ክፍል አንድን እና ሁለትን አዳምጫለሁኝ። በሚዲያው እና እሳቸው በሚመሩት ሃሳብ ዙሪያ የነበረውን ክፍተት ግራ ቀኙ ያስተካከሉት ይመስለኛል። የቅሬታቸውንም መሠረት አስቀድሜ አዳምጨው ስለነበር ውይይቱ ግልጽ ነበር ለእኔ። "የሴታ ሴት ፓወር" ሰብሳቢ ወ/ሮ ቤተልሄም አካለወርቅ በህፃን ሔቨን ጉዳይም ከእዮሃ እና ከአርተስ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አዳምጫለሁ። የእኔን የወጣትነት ጊዜ አስታውሶኛል። በዚህ ሃሳቤ እኔን በወጣትነት የሚያውቁኝ ወገኖቼ ይስማማሉ። በውነቱ እራሴን ነው ያዬሁባቸው። ማለፊያ ነው። የህግ ባለሙያወችም ቁጥብ በሆነ መልኩ ጉዳዩን የእኔ ብለው እዬተነጋገሩበት ይገኛል። ይህም ወሸኔ ነው። በሌላ በኩል ሚዲያ ላይ ያሉ ወገኖችም እንዲሁ ጠንከር ባለ ሁኔታ እዬተወያዩበት ነው። ይህም ይበል የሚያሰኝ ነው። በጠቅላላ ግሎባል ንቅናቄውና ግብረ መልሱ አበረታች ጅምር ነው። በሴቶች ጉዳይ ብዙ መጣጥፎችን ጽፌያለሁኝ። መዋለ ዕድሜያችን በፈተና ዘልቦ ስለሚጠናቀቅ። አደራጅም ስለነበርኩኝ ብዙ በጣም ብዙ አመክንዮወች የውስጤ ናቸው። ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ይህ ክስተት #አስፈሪም #ነውርም ስለሆነ መቆም ስላለበት በተከታታይነት ሊሠራበት እንደሚገባ ይሰማኛል። ሲጨልም መን...
«በጠለምት በናዳ የተቀበሩ የሁለት ሰዎችን አስክሬን ለማውጣት ሲሞክሩ ከነበሩት የ7ቱ ሕይወት አለፈ" bbc
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
https://www.bbc.com/amharic/articles/c0mnprenz00o «በጠለምት በናዳ የተቀበሩ የሁለት ሰዎችን አስክሬን ለማውጣት ሲሞክሩ ከነበሩት የ 7 ቱ ሕይወት አለፈ" 26 ነሐሴ 2024 "በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ በናዳ የተቀበሩ የሁለት ሰዎችን አስክሬን በመፈለግ ላይ ከነበሩት የ 7 ቱ ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። የወረዳው አስተዳዳሪ ጋሻው እንግዳው ለቢቢሲ እንደገለጹት የሰባቱ ግለሰቦች ሕይወት ያለፈው ባለፈው ዐርብ ነሐሴ 17/2016 ዓ . ም . አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በናዳ የተቀበሩ ሰዎችን በመፈለግ ላይ ሳሉ በድጋሚ በተከሰተ አደጋ ነው። በአደጋው እናትና ልጅን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጠቀሱት አቶ ጋሻው፣ ክስተቱ ባጋጠመበት ወቅት የልጁ አስክሬን ወዲያው ሲገኝ የሁለቱ የቤተሰብ አባላት አስክሬን ግን ሳይገኝ እንዳደረ ተናግረዋል። በማግስቱ ቅዳሜ ነሐሴ 18/2016 ዓ . ም ጠዋትም የሁለቱን ሰዎች አስክሬን ለማውጣት የተሰባሰቡ ከ 18 በላይ የሚሆኑ ዘመድ አዝማድና የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍለጋ በተሰማሩበት ወቅት ድጋሜ በተከሰተ ናዳ የሰባቱ ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል አስተዳዳሪው። በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪም በስምንት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል። በሁለቱም አደጋዎች ከሞቱት መካከል የአራት ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን የቀሪዎቹ አለመገኘቱንና ፍለጋውም መቋረጡን ...