BBC "በሰሜን ጎጃም በድሮን ጥቃት ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ 50 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ" የምስሉ መግለጫ, ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉትን አካባቢ"
https://www.bbc.com/amharic "በሰሜን ጎጃም በድሮን ጥቃት ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ 50 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ" የምስሉ መግለጫ, ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉትን አካባቢ የሚያሳይ ካርታ 8 ህዳር 2024, 07:14 EAT በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። ጥቃቱ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ከወረዳው ዋና ከተማ ዱርቤቴ 40 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አርጌ (ዝብስት) በተባለች ታዳጊ ከተማ በተከታታይ ሦስት ጊዜ መፈጸሙን እማኞች እና ነዋሪዎች ገልጸዋል። ጠዋት 1፡10 አካባቢ በከተማዋ ገበያ አካባቢ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ጤና ጣቢያ ላይ ጥቃቱ እንደተፈጸመ እማኝነታቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ “ከልጅ እስከ አዋቂ ያለቀበት” ነው ብለውታል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው ጠቁሞ መረጃ እያሰባሰበ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል። በድሮን ጥቃቱ መረብ ኳስ ይጫወቱ የነበሩ ልጆች፣ ለሽምግል እና የተቀመጡ ሰዎች፣ ህክምና ላይ የነበሩ እናቶች፣ የጉልበት ሠራተኞች፣ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ እና እርሻ ቦታ ላይ የነበሩ ሰዎች ሰለባ እንደሆኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃት የደረሰባቸው ሦስቱም አካባቢዎች በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች የጠቆሙ ሲሆን፤ ቢቢሲ አካባቢዎቹ ከ300 ሜትር ራዲዬስ ባነሰ ርቀት እንደሚገኙ በካርታ እና በሳተላይት ምሥል አረጋግጧል። ከጥቃቱ አንድ ቀን አስቀድሞ የድሮን ቅኝት እንደነበረ ለማመልከት “አየሯ ስትዞር ነበር” ያሉት ነዋሪዎች ጥቃቱን “ከተ...