ልጥፎች

ዘመነ ቤርሙዳ ትርያንግልን ለመመከት #ጥንቃቄ በአደብ ይጠጣ። ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነውና።

ምስል
  ዘመነ ቤርሙዳ ትርያንግልን ለመመከት #ጥንቃቄ በአደብ ይጠጣ። ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነውና።    "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       #እፍታ ።    ወጀቡ አዬለ። አቅጣጫውም ድብ አለበት እናም ዘለግ ያለ ሃሳቤን ማጋራት ፈለግሁኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ከመጡ ጉዳዬን በምዕራፍ ከፋፍዬ ስለምሰራ አስረአራተኛው ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። ለቅኖች ለማስታወስ።    ፁሁፋ ዘለግ ያለ ነው። ለፌቡ አይሆንም። ግን ብሎግም ስላለኝ ለዛም ጭምር ነው እምሰራው። ለወሳኝ ፖለቲካዊ አቅጣጫ በጭልፋ የልብ አያደርስም እና ተያያዥ ጉዳዬወችን አክዬ፦ ወይንም እያጣቀስኩ አብረን እንሁን ስል ትህትናዊ አክብሮቴ ይጠይቃችኋል - ክብረቶቼን።   #ውስጤ ።   እንዴት ነን? #አይዞን ። ሁለ የርሱ፤ ሁሉም በእርሱ የሆነ አምላክ አለን። አቅማችን #አምላካችን ፤ ተስፋችን #አላሃችን ነውና።   ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ከአንደበት ጀምሮ ማናቸውም ኩነታችን ጥንቃቄ ይመራቸው ዘንድ ከእያንዳንዳችን በግል፤ ከሁላችን በጋራ የሚፈለግ የወል መስመራችን ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ።    የትናንቱ የአዲስ አበባ የሽብር ክስተት አሳቻው ዘመን እና አሳቻው መሪ ዶር አብይ አህመድ አሊ ከመጡ ጀምሮ የተኖረበት የአዬር ፀባይ ነው። ባለመታደል። ትጋታችን መራራው የህዋህት ዘመን፤ በዘመናዊ የሽብር አገዛዝ እንዲሸጋገር አልነበረም። ቲም ገዱ ጥረታችን ለስልጣን አልታገልንም ብሎ በአፍጢሙ ከነበለው - እንጂ። አሁንም አዳኛችሁ ነኝ ሲል አዳምጣለሁኝ። የፊተኛውን በምን ቀበርከው በሻሽ፤ የኋለኛው እንዳይሸሽ"   ነገረ ኢትዮጵያ ከአንድ ጠቅላይ ሚር፦ ከአንድ ዩቱበር፤ ...

የሚገርም የሚያሳዝንም የታቀደ #ዝርክርክነት።

ምስል
 https://www.youtube.com/watch?v=9r-0BtrKD3U  ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ   የሚገርም የሚያሳዝንም የታቀደ #ዝርክርክነት ። እንኳንም ለዚህ በቃችሁ። "ሸኔ" ስትሉ ነበር የባጃችሁት። እኔ ግን ፈጽሞ ይህን መጠሬያ ተጠቅሜው አላውቅም ነበር። ዛሬ ደፍራችሁ የኦነግ ታጣቂወች አላችሁ።    የሆነ ሆኖ ጫካ የቆዩ የኦነግ የሰራዊት አባላት በጥንቃቄ ትጥቃቸውን ፈተው፤ ወደ ተመደበላቸው ጊዚያዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንዲሄዱ ሊደረግ ሲገባ #በአፍሪካ አንደኛ ርዕሰ መዲና፤ በዓለም #ከአራቱ የዲፕሎማሲ ከተሞች አንዷ በሆነችው፤ ለኢትዮጵያ #ርዕሰ መዲና በሆነችው #አዲስ አበባ ላይ እንዲህ አይነት ህዝብን የማስደንገጥ ተግባር፤ መንግስት ባለበት አገር #መፈፀም እና #ማስፈፀም እጅግ ያሳዝናል። ለምን፤ ስለምን ደግ፤ ቻይ፤ ቅን እና #ቀና ፦ የበዛ ጨዋን ማህበረሰብን እንዲህ ማስጨነቅ፤ እንዲህ ማራድ እንዳስፈለገ ለቀባሪው አረዱት ይሆናል። የራስን ፈቃድ የፈፀመ ቢሆን እንኳን ሥርዓቱ በዚህ መልክ ሊሆን አይገባም ነበር።    መልካሙ ነገር በፍጥነት የአብይዝም መንግሥት ይቅርታ መጠዬቁ ጥሩ እርምጃ ነው። ይህ ግን ቀድሞ ቢከወን መልካም ነበር። አንዲት እህት መጎዳታቸውን ሰምቻለሁኝ። በዬትም አገር የሚካሄዱ ስምምነቶች ለአፈፃፀማቸው ብርቱ ጥንቃቄ በቅድሚያ ይደረጋል። ጫካ የቆዬ ሰብእና ከብዙ አስጨናቂ፤ አድካሚ ጊዜ በኋላ ወደ ማህበረሰቡ በዘፈቀደ ተቀላቀል አይባልም። በፍፁም። በቂ የህሊና፤ በቂ የመንፈስ መሰናዶ ስምምነቱን በፈፀመው አካል ያስፈልግ ነበር። መንግሥት እኮ ናችሁ። ያው እሱ በእሱ ቢሆንም ሁለመናው። ጫካ በነበሩት የኦነግ የሠራዊት አባላት በእነሱ ቅንጣት ጥፋት የለም። ...

እናት ስትታሰር የትውልድ ተስፋ ይጠነዝላል።

  እናት ስትታሰር የትውልድ ተስፋ ይጠነዝላል።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ጤና ይስጥልኝ ማህበረ ቅንነት። እንዴት ሰነበታችሁ? በብዙ ያልሰከኑ፤ ያልተገሩ፤ የሚወራጩ ሁነቶች ውስጥ ዝምታ የተሻለ በመሆኑ ዝምታ ቆምሶ ሰነበተ። ከውስጤ ሊወጣ ያልቻለውን የቤተሰብ ምስል በሚመለከት ትንሽ ልጽፍበት ወደድሁኝ።   ፎቶዋን ከፌስቡኬ  https://www.facebook.com/sergute.selassie/ #እናት ናት። #ትጉህ ፀሐፊ ናት። #ሞጋች ናት። #መምህርት ናት። ሚስትም ናት። #ፖለቲከኛም ናት። #ቁምነገርም ናት መስኪ። #ወጣቷ ፖለቲከኛ በሳልም ናት።    መስኪ እና ብዕሯን ከ2014 ጀምሮ እኔም እሷም የደጉ ዘሃበሻ፦ የደጉ ሳተናው #አምደኛ ሆነን አውቃታለሁኝ። እኔ እንዲያውም አገር ቤት ሆና እንዲህ ትሞግታለች ብዬ አላስብም ነበር። በውነቱ ውጪ የምትኖር ነበር የሚመስለኝ። አንድ ጊዜ አመስግኜ ኢሜል ፃፍኩላት። መልስም ሰጠችኝ።   መስኪ ባለትዳር እና የልጆች እናት መሆኗን ግን በጣም ዘግይቼ ነው የተረዳሁት። ምክንያቱም እኔ ከ2019 በፊት የፌቡ ተጠቃሚ ባለመሆኔ ለብዙ መረጃወች ቅርብ አልነበርኩምና። የሆነ ሆኖ መስኪ እንዲህ #ተደፍሮ ለካቴና ልትሰጥ የሚገባ ወጣት ፖለቲከኛ አልነበረችም። ልንሳሳላት የሚገባ ልዩ ወጣት ናት እና። እንዲሁም ለገዢውም ሆነ፤ ለተፎካካሪ፤ ለተጠማኝ፤ ለተደማሪ፤ ለተቀላች፤ ለተለጣፊ፤ ወይንም ለተደማሪ ለዬትኛውም ፖለቲከኛ የምትሰጠው ጉልበታም አስተያዬት ህዝብ ጠቀም በመሆኑ ይረዳዋል፤ የአቅጣጫ አመላካች ነውና። መስኪ ለግፋፎ ጭዳ ጭድ ክምር ግርግር አልተፈጠረችም። ለምታምንበት ቁም ነገር ጽኑ እና ዕውነት አፈላላጊ ናት።   ጹሁፎቿን በትጋት አነባለሁኝ። ...