የሚገርም የሚያሳዝንም የታቀደ #ዝርክርክነት።
https://www.youtube.com/watch?v=9r-0BtrKD3U
ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተሰጠ መግለጫ
የሚገርም የሚያሳዝንም የታቀደ #ዝርክርክነት።
እንኳንም ለዚህ በቃችሁ። "ሸኔ" ስትሉ ነበር የባጃችሁት። እኔ ግን ፈጽሞ ይህን መጠሬያ ተጠቅሜው አላውቅም ነበር። ዛሬ ደፍራችሁ የኦነግ ታጣቂወች አላችሁ።
የሆነ ሆኖ ጫካ የቆዩ የኦነግ የሰራዊት አባላት በጥንቃቄ ትጥቃቸውን ፈተው፤ ወደ ተመደበላቸው ጊዚያዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ እንዲሄዱ ሊደረግ ሲገባ #በአፍሪካ አንደኛ ርዕሰ መዲና፤ በዓለም #ከአራቱ የዲፕሎማሲ ከተሞች አንዷ በሆነችው፤ ለኢትዮጵያ #ርዕሰ መዲና በሆነችው #አዲስ አበባ ላይ እንዲህ አይነት ህዝብን የማስደንገጥ ተግባር፤ መንግስት ባለበት አገር #መፈፀም እና #ማስፈፀም እጅግ ያሳዝናል። ለምን፤ ስለምን ደግ፤ ቻይ፤ ቅን እና #ቀና፦ የበዛ ጨዋን ማህበረሰብን እንዲህ ማስጨነቅ፤ እንዲህ ማራድ እንዳስፈለገ ለቀባሪው አረዱት ይሆናል። የራስን ፈቃድ የፈፀመ ቢሆን እንኳን ሥርዓቱ በዚህ መልክ ሊሆን አይገባም ነበር።
መልካሙ ነገር በፍጥነት የአብይዝም መንግሥት ይቅርታ መጠዬቁ ጥሩ እርምጃ ነው። ይህ ግን ቀድሞ ቢከወን መልካም ነበር። አንዲት እህት መጎዳታቸውን ሰምቻለሁኝ። በዬትም አገር የሚካሄዱ ስምምነቶች ለአፈፃፀማቸው ብርቱ ጥንቃቄ በቅድሚያ ይደረጋል። ጫካ የቆዬ ሰብእና ከብዙ አስጨናቂ፤ አድካሚ ጊዜ በኋላ ወደ ማህበረሰቡ በዘፈቀደ ተቀላቀል አይባልም። በፍፁም። በቂ የህሊና፤ በቂ የመንፈስ መሰናዶ ስምምነቱን በፈፀመው አካል ያስፈልግ ነበር። መንግሥት እኮ ናችሁ። ያው እሱ በእሱ ቢሆንም ሁለመናው። ጫካ በነበሩት የኦነግ የሠራዊት አባላት በእነሱ ቅንጣት ጥፋት የለም። በአብይዝም መንግስት ረገድ ወግ ያለው ግድፈት ለመፈፀም እንኳን ይህን ያህል ስስነት ያሳዝናል።
ምጥ ላይ ያሉ ሴቶች፤ ኦፕራሲዮን ላይ ያሉ የህክምና ባለሙያወች፤ ውጭ ሲጫወቱ የነበሩ ልጆች፤ ከቤታቸው ውጭ ለነበሩ ነዋሪወች ሁሉ ይህን መሰል የተፈቀደ የስጋት ድባብ አቅዶ መከወን #ነውር ነው። መጥኔ ለዛች ላልታደለችው እናት አገር ለኢትዮጵያ። ሳቋ ዘልቆ ለማያውቀው የጭንቀት በዓት።
በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ህዝብ በተለይ ወጣቱ የኦነግ ታጣቂ አባላት በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ እራስን በጥንቃቄ ውስጥ አድርጎ መቀመጥ ይገባል። የያዙት የኦነግ አርማ ነው። የኦነግ ሰራዊት አባላት #የታገሉበት፤ #የታገሉለትም ስለሆነ የአዲስ አበባ ወጣቶች ይህን ታግሶ የማለፍ ልዩ #ጥበብን ሊቀዳጁ ይገባል። ጉዳዩ መልክ እስኪይዝም ተረጋግቶ በጣም #በቁጥብነት ወጀቡን ማሳለፍ ይገባል። ጫካ የቆዬ መንፈስ ተሎ ተሎ የሚቀያዬር ባህሬ ሊኖረው ይችላል።
በተረፈ ውዶቼ ደንግጬ ነው የገባሁት። እንደ ከተማ ውጊያ የሚጨንቀኝም፤ የሚከብደኝም ጉዳይ የለም። ያ የምርጫ ፍጥጫ መጥቶ እስጢናቀቅ ድረስ ይህን መሰሉ የስጋት መአበል ተጠባቂ ነው ለእኔ። አዲስ አበባም በእኔ ግምገማ ከየስከረም 5/2011 ዓም ጀምሮ ወደ ኦሮምያ እንደተጠቃለች ነው እማምንበት። የኦሮምያ ህግም እንደሚገዛት ነው የሚገባኝ። ይህንኑ ስጽፍ ነው የባጀሁት። ቀድሞ ማወቅ ለአቅም አወጣጥ መሃንዲሱ ነበር ሰሚ ቢኖር።
ቸር አስበን፦ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08/12/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ