ልጥፎች

????? #አገራዊ #የምክክር #ኮሚሽኑ #በኽረ #ተልዕኮ #ምን #ይሆን?????

ምስል
  ????? #አገራዊ #የምክክር #ኮሚሽኑ #በኽረ #ተልዕኮ #ምን #ይሆን ?????   #ዓለም #ዓቀፍ #ሰውኛ #ጉባኤ #ባለፈው #ሳምንት #ያስተናገደችው #ኢትዮጵያ #በገዢዋ #የብልጽግና #መንግሥት #በአማራ #ህዝብ #ላይ #የድሮን #ናዳ #ሲፈስ #መዋሏን #ዓለም #ዓቀፋ #ሚዲያ #ቢቢሲ #ዘገበ ።    "በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ትናንት ሐሙስ የካቲት 13/2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ አራት ቤቶች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 16 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።   ጥቃቱ በዞኑ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገሽ ቀበሌ (ሐሙስ ገበያ) በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሐሙስ ረፋድ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በሦስት ሱቆች እና ሻይ ቤት ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።   "[ድሮን] ስትዞረን ነበር" ያሉ አንድ የዓይን እማኝ ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ በግምት 100 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ የጥቃቱ ሰለባዎች መንገድ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህፃናት፣ ገበያተኞች እና ሻይ እየጠጡ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።   "ከፍተኛ ፍንዳታ" መፈጠሩን የሚናገሩት እማኙ፤ ወዲያው "አካባቢውን አቧራው፤ የቤቱ ፍርስራሽ በጭስ" እንዳፈነው እና ድንጋጤ እና ግርግር እንደተፈጠረ ገልፀዋል።   ሌላ የዓይን እማኝም በፍንዳታው አካባቢው በአቧራ ጭስ መሸፈኑን ጠቅሰው፤ በስፍራው ለመተያትም አስቸጋሪ እንደነበር ተናግረዋል። በደቂቃዎች ውስጥ ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው ቤቶች ደርሰው የቆሰሉ ሰዎችን እንዳወጡ እና አስከሬን እንዳነሱ የተናገሩት ሌላ የዓይን እማኝ "የሚጫወቱ ህፃናት እና ቆርቆሮ ሊገዙ የመጡ ሰ...

#በቁሙ #ቀብር #ላይ #የዋለ #ብትክትክ እንኮሸሽሌ #ዕሳቤ።

ምስል
  #በቁሙ #ቀብር #ላይ #የዋለ #ብትክትክ እንኮሸሽሌ #ዕሳቤ ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       Anchor Media ''ጦርነቱ ቢጀመር ደስ ይለኝ ነበር። ...ከዚያን በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ እፎይታን ያገኛል'' ፕ/ር መሀመድ ሀሰን» https://www.youtube.com/watch?v=XotdIljSVEA   ይህቺ አገር ኢትዮጵያ ስንቱን ዝክንትል ዕሳቤ፤ ስንቱን ድሪቶ ምልከታ፤ ስንቱን ስቃይ #ጠሪ ዕሳቤ እንደ ተሸከመች አመላካች ነው። እርእሱን በቁሙ ያለ ተርጓሚ ስታነቡት። ጥገኝነትን ተጠይፋችሁ አመሳጥሩት። የጦርነት ናፍቆት ለእኔ ጭካኔ ነው። በዚህ ጭካኔ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን እስቲ አፈላልጉ? ግን ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? ከሠራተኛ መሪነት፤ ከሊቃውንትም፤ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሥመጥሩነት፤ ከቀደምት የነፃነት ታጋይነት፤ ከመሪነትም ጎራ የሚመደቡት ባለሁለገብ የልምድ ባለቤቱ ፕሮፌሰር መሐመድ ሃሰን በጦርነት " #እፎይታ " ይገኛል ይሉናል። ማን በሚመራው ጦርነት ብላችሁ ጠይቁልኝ በትህትናም። ሎቱ ስብኃት።    ለእኔ ዝርግ ዕሳቤ ነው። ለእኔ ይህ አንካሳ ዕሳቤ ነው። ፍላጎቱ በግራ ቀኝ ቢኖር እንኳን ይህን ኩፍኝ መንገድ ማበረታት፤ ከጃርታዊው ጦርነትም ተስፋን መጠበቅ እርቃኑን የቆመ ምኞት ነው። እርግጥ ነው አጃቢ ይኖረዋል። ለእሳት ማገዶ እንደሚቀርበው። ግን ለትውልድ ፀር የሆነ አጥፊ ዕሳቤ ነው።   ፕሮፌሰር አንድ ጊዜ አንከር ሚዲያ ላይ "ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ #ባይስማማን ልንቀይረው ተነጋግረን እንችላለን" ሲሉ #እግዚኦ ብዬ ነበር። ጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነንም እናቱ ማንነቷን ሊገፍ የሚችል እጮኛ ግን ድውይ ሃሳብ ሲፈልቅ አልሞገተም። ዝም ብሎ አሳለፋቸው። እ...

እኔ መሬት ላይ ተቀምጬ አንተን ሶፋ ላይ አስቀምጬ አስተምርሀለሁ!! ልጆችን የሚያክም ሀኪም ልጆችን መስሎ ቢሰራ !...

ምስል

#ይቅናህ! #ይቅናህ! #ይቅናህ! #ኑርልን #ዋርካ አባቱ

ምስል
  #ይቅናህ ! #ይቅናህ ! #ይቅናህ !      #ዛሬን #ለአንተ #አላህ #ይመርቅልህ ! #ነገንም #አማኑኤል #ለአንተ #ይባርክልህ ! #ዓጤ #አማርኛ #ቋንቋ ፦ #የእማማ #አፍሪካ #ሁነኛ #ነህ ! #የበራህ ፦ #የምታበራ ፤ #የቀደምክ ፤ #የምታስቀድም #ቅኔ #ነህ !   በባዕትህ #ብትገፋም አቅም እና ብቃትህ በዝልቅ ልዕልና በዓለም ተናኝቷል ዛሬን በማግስት ያስጌጣል - ያስውባል- ያብባል።   #ኑርልን #ዋርካ አባቱ የጥንት #የጥዋቱ !   ሥርጉ2025/02/17 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።