የሰባዊነት ልዩ #ዓርማ የነበሩት የሆኑትም የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር የዶር አንጌላ ሜርክል ፓርቲ (CDU+ CSU)ወደ ቁልፍ ሥልጣን ተመለሰ።
የሰባዊነት ልዩ #ዓርማ የነበሩት የሆኑትም የቀድሞዋ የጀርመን ካንስለር የዶር አንጌላ ሜርክል ፓርቲ (CDU+ CSU)ወደ ቁልፍ ሥልጣን ተመለሰ። "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄርግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) በእኔ ዘመን ከተከሰቱ ድንቅ #ክስተት መሪወች፤ #ዕንባን አድማጭ የዓለም ሊሊቀ - ሊቃናት፤ ለየትኛውም አገር የሰባዕዊነት፤ የየንግሥታት ችግር ልዩ #አትኩሮት እና #ቅድሚያ ከሰጡ መሪወች በቁጥር አንድ የእኔ ልዕልት ዶር አንጊላ ሜርክል ናቸው። ፍፁም ሰውኛ፤ ፍፁም ተፈጥሮኛ #በ100 ዓመት ፕላኔታችን ደግማ የማታገኛቸው ልዩ የዓለም #ሥጦታ ናቸው። እኔ ቀጣዩን #የተመድ #ቁልፍ ቦታም ቢሰጣቸው የዓለማችን ምስቅልቅል ፖለቲካ #ፈውስ ያገኛል ብዬ አምናለሁኝ። አድማጭነታቸው፤ የእናትነት ፀጋቸው የመሰጠታቸው አቅም ልዩ ነውና። እኔ በክብርትነታቸው ሁልጊዜም ለምንጊዜም አምላኬን መማኑኤልን አመሰግናለሁኝ። የሆነ ሆኖ በዚህ ዓመት የጀርመን የምርጫ ሂደት ልብ አንጠልጣይ ስለነበር፦ በተወሰነ ደረጃ ተከታትዬው ነበር። ትናንት ከምወደው የጀርመን ሚዲያ ውስጥ አንዱ በሆነው #በRTL ሂደቱን ተከታትዬው ነበር። ነፍሴ ተንጠልጥላ። ግሩንም እድገት ማሳዬቱን ተመልክቻለሁኝ። የሰብዓዊ መብትን ጥሰት፤ ድህነትን ሽሽት ወደ አውሮፓ የሚጎርፈው ስደተኛ ህይወት እንዴት ይሆን በማለት ነበር የተከታተልኩት። እርግጥ ነው ስደተኛ የየአገሮችን #ህግ በማክበር፤ በጨዋነት፤ በዲስፕሊን፥ #ዕድልን በማክበር፦ መኖር ሲገባ ጭራሽ በወንጀላዊ ድርጊት መሳተፍ፤ ያስጠጋን አገር ህዝብ ስለስጋት መዳረግ፤ ተጨማሪ ጫና መፍጠር፤ #ህይወትን #ያስቀጠ...