ቀን እና ቀን ሲተላለፋ ግራጫማ #ዬግርዶሽ #ትዕይንት ሊፈጠር ይችላል። «ዜሌንስኪ ከዋይት ሃውስ እንዲወጡ የተደረገበት የዲፕሎማሲ ቀውስ ላይ እንዴት ተደረሰ?» BBC.
ቀን እና ቀን ሲተላለፋ ግራጫማ #ዬግርዶሽ #ትዕይንት ሊፈጠር ይችላል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ለእኔ ዓለማችን #ቀን ናት። ቀንም #ዓለማችን ነው። ቀን ሲከፋው ዓለማችን #ይከፋታል ። ዓለማችን ጠቆርቆር ስትልም ቀንም መሰሉ ይደርስበታል። ትናንት #ከባድ ቀን ነበር። እንደ መቃብር የገዘፈ #ግራጫማ ከባድ ቀን ነበር ትናንትና 28/02/2025። የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት የሁለቱ አገሮች ብቻ አይደለም። በእያንዳንዱ አውሮፓ በሚኖር ሰብዕ ሁሉ ቀጥታ ተደራሽ የሆነ የመኖር #መዛባትን አስከትሏል። ሁሉ ነገር ከአቅም በላይ ነው። ይህን ሁለቱ ተፋላሚወችም፦ ተዋጊወችም ዓለማችንም ያላስተዋሉት ሃቅ ነው። ስለሆነም በነፍስ ወከፍ ለደረሰው የኢኮኖሚ ክራይስ ተከድኖ የሚንተከተክ ዘመን በቀል #የጓዳ ችግር ነው። #ባሊህም ባይም የለውም። መጀመሪያ ኮረና ከዛ #ራሺያወዩክሬን ጦርነት። አቅም ያሳጣል ሁኔታው። ስጋቱ ሳይታከል። በሁለቱ አገሮች የሰው እና የቁስ ውድመት ሳይጨምር ማለት ነው። በዚህ ጦርነት አሳዛኙ ትራጀዲ የአውሮፓ ትውልድ ሌላ ችግር ገጥሞታል። አውሮፓዊ ጉዳዮች ሁሉ አንዱን ያቀፈ ሌላውን #ያገለለ ነው። እስፖርት፥ ኪነጥበብ፦ መኖር …… ወዘተ። ጦርነቱ የመንግሥታቱ መከራው #የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ነው። መኖርም በኢኮኖሚ ድቀት ብዙ ፈተናን ተጋፍጧልም። ስለሆነምጦርነቱ ይቆም ዘንድ ተስፈኛ ከሆኑት ውስጥ አንዷ እኔ ነኝ። ጦርነት ምኑ ይናፍቃል። አጥፊ #ከይሲ አውዳሚ ክስተት። የሦስተኛው ዓለም ጦርነት ቢነሳ ደግሞ መጨካከኑ ከዚህም ይከፋ ነበር። ይህን ፍጥጫ ለማርገብ ይመስላል #ትራንፒዝም ትጋት ላይ የሚገኜው። ትትርናው በሁለቱ አገሮች መልካም ፈቃድ...