ቀን እና ቀን ሲተላለፋ ግራጫማ #ዬግርዶሽ #ትዕይንት ሊፈጠር ይችላል። «ዜሌንስኪ ከዋይት ሃውስ እንዲወጡ የተደረገበት የዲፕሎማሲ ቀውስ ላይ እንዴት ተደረሰ?» BBC.

 

ቀን እና ቀን ሲተላለፋ ግራጫማ #ዬግርዶሽ #ትዕይንት ሊፈጠር ይችላል።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
ለእኔ ዓለማችን #ቀን ናት። ቀንም #ዓለማችን ነው። ቀን ሲከፋው ዓለማችን #ይከፋታል። ዓለማችን ጠቆርቆር ስትልም ቀንም መሰሉ ይደርስበታል። ትናንት #ከባድ ቀን ነበር። እንደ መቃብር የገዘፈ #ግራጫማ ከባድ ቀን ነበር ትናንትና 28/02/2025።
 
የዩክሬን እና የራሺያ ጦርነት የሁለቱ አገሮች ብቻ አይደለም። በእያንዳንዱ አውሮፓ በሚኖር ሰብዕ ሁሉ ቀጥታ ተደራሽ የሆነ የመኖር #መዛባትን አስከትሏል። ሁሉ ነገር ከአቅም በላይ ነው። ይህን ሁለቱ ተፋላሚወችም፦ ተዋጊወችም ዓለማችንም ያላስተዋሉት ሃቅ ነው።
ስለሆነም በነፍስ ወከፍ ለደረሰው የኢኮኖሚ ክራይስ ተከድኖ የሚንተከተክ ዘመን በቀል #የጓዳ ችግር ነው። #ባሊህም ባይም የለውም። መጀመሪያ ኮረና ከዛ #ራሺያወዩክሬን ጦርነት። አቅም ያሳጣል ሁኔታው። ስጋቱ ሳይታከል። በሁለቱ አገሮች የሰው እና የቁስ ውድመት ሳይጨምር ማለት ነው። 
 
በዚህ ጦርነት አሳዛኙ ትራጀዲ የአውሮፓ ትውልድ ሌላ ችግር ገጥሞታል። አውሮፓዊ ጉዳዮች ሁሉ አንዱን ያቀፈ ሌላውን #ያገለለ ነው። እስፖርት፥ ኪነጥበብ፦ መኖር …… ወዘተ። ጦርነቱ የመንግሥታቱ መከራው #የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ነው። መኖርም በኢኮኖሚ ድቀት ብዙ ፈተናን ተጋፍጧልም። ስለሆነምጦርነቱ ይቆም ዘንድ ተስፈኛ ከሆኑት ውስጥ አንዷ እኔ ነኝ። ጦርነት ምኑ ይናፍቃል። አጥፊ #ከይሲ አውዳሚ ክስተት። 
 
የሦስተኛው ዓለም ጦርነት ቢነሳ ደግሞ መጨካከኑ ከዚህም ይከፋ ነበር። ይህን ፍጥጫ ለማርገብ ይመስላል #ትራንፒዝም ትጋት ላይ የሚገኜው። ትትርናው በሁለቱ አገሮች መልካም ፈቃድ ካልተደገፈ፦ ግን ጥረቱ #አልቦሽ ሊሆን ይችላል። የሆነ ሆኖ ሰላም የሚያስከፍለው ዋጋ #ከጦርነት በላይ #ስለመክበዱ ሰሞናቱ ያመሳጥራሉ። 
 
ቀን አንገት ሲደፋ፤ ቀን ሲያነካክስ፤ ቀን አላውቅህም ሲል #ተስፋ አድራሻ ያጣል። በዚህ ሂደት የምናዬው እሰጣ ገባ ግሎባላይዜሽኑም ፍጥጫን #ለማቻቻል ያለውን የአቅም ክህሎት ነው። "ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው" ይላል የአገሬ ሰው። እኔ ይሄኛው፤ ያኛው ብዬ መበዬንም ሆነ ሃሳብ መስጠት ፈጽሞ አልሻም። ለቀኑ ቀኑ መሸከም #ከብዶት እንደነበረ ግን አስተውያለሁኝ። ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ደግሞ ቀን #ቀና ይላል እራሱ ቀኑ። ዓለማችንም #ውሽክ የማለት ዕድል ታገኛለች። ይህን ብሩህ ቀን ፈጣሪያችን ያምጣ። አሜን። 
 
ለዚህ ነው የዓለማችን ፖለቲካ፤ የዓለማችን ፖለቲከኞች ፕሬዚዳንት ዘለንስኪን #ሌሰናቸው ያደርጉ ዘንድ ሁልጊዜ እማሳስበው። #ተጽዕኖ ፈጣሪነት ወደ #አገር መሪነት ሲመጣ፦ ላለው ፋክት ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ራዲዮሎጂ ናቸው። እኔ የማስተውለው ከዩክሬንም በተጨማሪ የኔቶን ውስጥም የመሸከም ሁነትም አስተውል ነበር። ይህ ይቻላል ወይ? ለዛ የገዘፈ ተቋም አቅሙ እና ዘመኑ ይፈቅዳል ወይ??? የሆነ ሆኖ ይህን በእኛ አገር ፖለቲካም ውስጥ ስለማይም ነው፦ ሁልጊዜ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪን እማነሳ። በአወንታዊም ይሁን በአሉታዊ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ለዓለም ፖለቲካ #ካሪክለም ናቸው ባይ ነኝ። 
 
የሰው ልጅ እራሱን ለሆነ ቁልፍ ኃላፊነት እራሱን ሲያጭ ሆነ ዕድሉን ሲያገኝ፦ ከጥንካሬው ይልቅ በድክመቱ የደረሰውን ጉዳት አጉልቶ እራሱን ለማረም፤ እራሱን በጥሞና ውስጥ ሆኖ ለመመርመር ቢተጋ መልካም ነው። ጊዜ ለጥንካሬው #ከሚያጎርስ ይልቅ ሙሉ ጊዜውን በግድፈቶቹ ላይ ትኩረት ቢያደርግ የመኖር #ዩንቨርስቲ በእያንዳንዱ የመኖር ብሂል ባህል የመሆን ዕድሉን ይከፍትለታል። 
 
።በልኩ - ማቀድ። በልኩ እራስን መጥኖ መተርጎም። በልኩ ልኩን መቀበልም የሰው ልጅ ሊኖረው የሚገባ ሥነ - ምግባር ይመስለኛል። ሌላው ወጣትነትን ማሸነፍም ያስፈልጋል። ወጣትነት ስል የዕድሜ ብቻ ሳይሆን የመሻት - የልምድ - የተመክሮ - የተስፋ ወጣትነት ሁሉ በልካቸው ውስጥ ይንቀሳቀሱ ዘንድ ሚዛን መጠበቅ፤ ሚዛናቸውን ማስጠበቅም የካፒቴኑ ተግባር ይመስለኛል። የእኛ አገር ፖለቲከኞችም ከዚህ ታሪካዊ ክስተት ብዙ ሊማሩበት የሚገባ ቁምነገር ስለአለ ነው ጉዳዩን ያቀረብኩት። 
 
ሌላው ልብ ያልተባለው ጉዳይ ጦርነት ውስጥ ለሦስት ዓመታት #የባጄ ሰብዕና እና ከጦርነት ውጪ የቆዬ #ፖለቲከኛ፤ #አክቲቢስት፤ #ጋዜጠኛ፦ የቢሮ ሠራተኛ፦ በአንድ መድረክ ወጥ አትሞስፌር ለመፍጠር አስቻይ ሁኔታው ምን ያህል የገዘፈ ችግር እንደነበር ትናንት አሳይቶናል።
 
ጦርነት ብዙ ነገርን #ይቀማል። ያበሳጫል - ሆድ ያስብሳል - ዕንባ ዕንባ ያሰኛል፤ - ባር ባር ይላል፤ ብቸኝነት - ይሰማል፤ ብዙ ነገርን ይዘርፋል ጦርነት። ግዴለሽ የመሆን አጋጣሚ ሁሉ ይፈጥራል በአለባበስም ሆነ በአነጋገር፤ በውስጥ ያለ ቆስቋሽ #ጀብዱ እና #ወኔም ይታገላል ……… ይፈትናልም፦ ወዘተ …
 
በተረፈ የBBC የአማርኛው አጠቃላይ ውሎውን ሰብሰብ አድርጎ የዘገበውን አያይዤዋለሁኝ። ከሥር ያለው በሙሉ ባለ ንብረቱ BBC ነው። ለዚህም ነው በትምህርተ ጥቅስ ያስገባሁት። 
 
ቸር አስበን፦ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
መሸቢያ ምሽት። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/03/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
-------------------------------------------------------------------
• «ዜሌንስኪ ከዋይት ሃውስ እንዲወጡ የተደረገበት የዲፕሎማሲ ቀውስ ላይ እንዴት ተደረሰ?» BBC.
 
1 መጋቢት 2025, 11:53 EAT
«የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ አርብ፣ የካቲት 21/ 2017 ወደ ዋይት ሃውስ ሲያቀኑ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር መልካም ውይይት አደርጋለሁ በሚል መንፈስ ነበር።»
 
«ዩክሬን ብርቅዬ የሆነውን ማዕድኗን ለአሜሪካ በመስጠት በምላሹም የጸጥታ ዋስትና እንድታገኝ ቢያልሙም ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ያልታሰበ ሁኔታ ገጥሟቸዋል።»
 
«በዓለም መገናኛ ብዙኃን ፊት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ "ምስጋና ቢስ" የሚሉ ቃላትን ጨምሮ ተግሳጾች፣ በኃይለቃል የተሞላ ወቀሳ እንዲሁም ዘለፋዎችን ሰንዝረውባቸዋል።»
 
«ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ከአሜሪካ ባለስልጣናት ለቀረበላቸው ሃሳብ ዜሌንስኪ ጠንከር አድርገው ተቃውመዋል።»
 
«ይህንንም ተከትሎ ትራምፕ እና ምክትላቸው "አክብሮት የጎደለው" ሲሉ ዘልፈዋቸዋል።»
 
«ውይይቱ ሳይጠናቀቅ እንዲሁም በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከትራምፕ ጋር የዜና መግለጫ መስጠት ቢኖርባቸውም ዜሌንስኪ ከዋይት ሃውስ እንዲወጡ ተነግሯቸዋል።»
 
«ለሳምንት ያህል ሲሞገስ የነበረው የማዕድን ስምምነቱም ሳይፈረም ቀርቷል። "ለሰላም ዝግጁ ስትሆን ተመልሰህ ና" ሲሉም ትራምፕ የዜሌንስኪ መኪና ለቆ ከመውጣቱ በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስፍረዋል።»
 
«በዚህ ዘለፋ በተሞላበት ውይይት የተለያዩ ነጥቦች ቢሰሙም አራቱን አንጥረን አውጥተናል።»
 
«የዜሌንስኪ እና ቫንስ ኃይለ ቃል የተሞላበት ምልልስ»
 
«በዋይት ሃውስ የነበረው የመጀመሪያው ግማሽ ሰዓት ውይይት ሰላማዊ ነበር። ሆኖም ቫንስ "ለሰላም እንዲሁም ለብልጽግና መንገዱ በዲፕሎማሲ መፍታት ነው" ካሉ በኋላ "ፕሬዚዳንት ትራምፕ እያደረጉት ያሉት ይህንኑ ነው" ብለዋል።»
 
«ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ ጣልቃ በመግባት ሩሲያ ወረራ ከመፈጸሟ ከሶስት ዓመታት በፊት ያልተሳካ የተኩስ አቁም ስምምነትን በማጣቀስ "ማንም አላስቆመውም" ሲሉም የሩሲያ አቻቸውን ቭላድሚር ፑቲንን ወቅሰዋል።»
 
"ጄዲ ምን ዓይነት ዲፕሎማሲ ነው የምታወራው? ምን ማለትህ ነው?" ሲሉም ዘለንስኪ ጠየቁ።»
 
«የሁለቱ ባለስልጣናት ንግግር ውጥረት እንደተሞላበት ባሳየው በዚህ ቅጽበትም ቫንስ "የአገርህን ውድመት የሚያስቆመው ዲፕሎማሲ አይነት" የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል።»
 
«በመቀጠልም ቫይስ ፕሬዚዳንቱ "አክብሮት የጎደለው" በሚል ዜሌንስኪን ዘልፈዋቸዋል።»
 
«ቫንስ እየተናገሩ የነበሩት ትራምፕ ጦርነቱን ለማቆም ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑን ጋር የተናጠል ውይይት በማድረግ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረቡትን ሃሳብ በመደገፍ ነው።»
 
"ለወደፊቱ ምን ሊሰማን እንደሚችል አትነግረንም"
 
«ቫንስ ዩክሬን ወታደሮችን ለመመልመል እንዲሁም ለብሔራዊ ግዳጅ እያቀረበችው ያለው ጥሪ ችግር ገጥሟታል ሲሉ በዚህ ወቅትም የዩክሬኑን መሪ አፋጠዋቸዋል። ዜሌንስኪም "በጦርነት ወቅት ሁሉም አገራት ችግር ያጋጥማቸዋል፤ እናንተም ጭምር። በመካከላችን ጥሩ ውቅያኖሶች ስላሏችሁ ላይሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን ለወደፊት ይሰማችኋል" የሚል ምላሽ ሰጡ።»
 
«ይህ ዜሌንስኪ አስተያየት ትራምፕን ያበሳጨ ነበር። በዜሌንስኪ እና በምክትል ፕሬዚዳንቱ መካከል በነበረው የኃይለ ቃላት ልውውጥም ትራምፕ ገቡበት።»
 
«የዩክሬኑ መሪ ትራምፕ የጦርነቱን ጀማሪ ወይም ወራሪውን ማየት አልቻሉም የሚለውን የጠቆመ ነበር። እንዲሁም የትራምፕ አካሄድ የሩሲያን መገለል በማስቆም አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ መገፋፋት ፑቲንን ያደፋፍራል፤ በተጨማሪም አውሮፓን አዳክሞ ዩክሬንን የበለጠ ተጋላጭ ያደርጋታል የሚለውን እሳቤ አንጸባርቋል።»
 
«ዜሌንስኪ የጦርነቱ መዘዝ በዩክሬን ብቻ እንደማይወሰን እና ወደ አሜሪካም ሆነ ሌሎች አገራት እንደሚዳረስ በዚሁ ንግግራቸው ጠቆም አድርገዋል። ትራምፕ በዚህ የዜሌንስኪ ንግግር እሳት ሆነው "ለወደፊቱ ምን ሊሰማን እንደሚችል አንተ አትነግረንም። ይህንን መናገር የምትችልበት አቋም ላይ አይደለህም" ሲሉ በከፍተኛ ድምጽ ተናግረዋቸዋል።»
 
«አክለውም "በሚሊዮኖች ህይወት እየቆመርክ ነው" ሲሉ ገስጸዋቸዋል።»
 
"ብቻህን አልነበርክም"
 
«ዜሌንስኪ በንግራቸው መካከል "ከጦርነቱ ጅማሮ ጀምሮ ብቻችንን ነበር እናም እናመሰግናለን" ማለታቸው ትራምፕን በእጅጉ ያስቆጣ ነበር። ትራምፕ ከዚህ ቀደም ጦርነቱ የአሜሪካ ግብር ከፋዮች ሸክም ሆኗል በማለት በተደጋጋሚ ሲወቅሱ ቆይተዋል።»
 
"ብቻህን አልነበርክም። በዚህ ደደብ ፕሬዚዳንት [ባይደን] በኩል 350 ቢሊዮን ዶላር ሰጥተንሃል" አሉት"።
 
«ከዚያም ቫንስ በመቀጠል "በዚህ ሁሉ ወቅት አሜሪካን አመስግነሃል ወይ?" ሲል ዜሌንስኪን የጠያቃቸው ሲሆን በምርጫው ዘመቻ ወቅትም ተፎካካሪያቸውን ዲሞክራቶችን "ትደግፍ ነበር" ሲሉ ወቅሰውታል።»
 
«ዜሌንስኪ"ድምጽህን ከፍ አድርገህ ስለ ጦርነቱ ስላወራህ........" እያሉ በሚናገርበት ወቅት ትራምፕ አቋርጠው "ጮክ ብሎ አልተናገረም። አገርህ ችግር ውስጥ ናት" ሲሉ በብስጭት መለሱ።»
 
"እያሸነፍክ አይደለም። ከዚህ በጥሩ ሁኔታ ለመውጣት ያለንህ እድል እኛ ነን" ሲሉም በኃይለ ቃል መልሰዋል።
«የትራምፕ እና ምክትላቸው ተግሳጽ»
 
"በእንዲህ አይነት መንገድ ስምምነቶች ላይ ማድረግ ከባድ ነው። ባህርይህ መለወጥ አለበት" «ሲሉ ትራምፕ ዜሌንስኪን ለመገሰጽ ሞክረዋል።»
 
«በዜሌንስኪ "ባህርይ" የተናደዱ የመሰሉት ፕሬዚዳንቱ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለመዝለፍ፣ ለማሸማቀቅና ለመገሰጽ ሞክረዋል።»
«ቫንስ "አመሰግናለሁ ብቻ በል" ሲልም የዩክሬኑን መሪ አዘውታል።»
 
«ዜሌንስኪ አቋማቸውን ለማስረዳት እንዲሁም መረጃዎች እንዳይጣረሱ ለማስተካካል ሲሞክሩም ታይተዋል።
ከዋናው ካሜራ ውጭ በአሜሪካ የዩክሬን አምባሳደር ኦክሳና ማርካሮቫ በዚህ ውርጅብኝ ተደናግጠው ጭንቅላታቸውን በእጃቸው ይዘው ታይተዋል።»

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?