ልጥፎች

#የህወሃት #ጃርታዊ የፖለቲካ ፍልስፍና ለኢትዮጵያ #መቃብር እንጂ #ትፍስህት አይደለም።

ምስል
  #የህወሃት #ጃርታዊ የፖለቲካ ፍልስፍና ለኢትዮጵያ #መቃብር እንጂ #ትፍስህት አይደለም።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"     እሚታዬ ጽግሽ ተናግሮ ካናጋሪ ያድነኝ የዕለት ጸሎቷ ነበር። እኔ በህወሃት ዙሪያ ቅንጣት አቅም ማዋጣት አልሻም። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ቀበጥ ያሉ ዘመናይ ሃሳቦች ሲነሱ የተገባ መልስ መስጠት ያስፈልጋል።   ህወሃት በኢትዮጵያዊነት ላይ ቂም #የቋጠረ ድርጅት ነው። ቂምን እዬዘረዘረ ነው ኢትዮጵያን ሲበቀላት ነው የኖረው። እናት አገር ኢትዮጵያ #መተንፈሻ እንድታጣ ያደረገው እልል እያለ በፌስታ ነበር። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ተፈላጊነት #እንዲከሳ ያደረገው አቅዶ ነው። ህወሃት ትግሉን መሠረትም ሲጥል ቂም እና በቀልን #ከጥላቻ ጋር አጋብቶ ነው የጀመረው። ለዚህም ነው በሥልጣን ዘመኑ እንኳን "የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት" የሚለውን ሥያሜውን ያለወጠው። ህወሃት ጥንስሱም፤ ውልደቱም፤ እድገቱም፤ አስተምኽሮቱም፤ ፍልስፍናውም #በጸረ ኢትዮጵያዊነት የተጠቀለለ ነው።    በእያንዳንዱ የሥልጣን ዘመን ሂደቱ ነገ ኢትዮጵያ #ሊያሰቃይ ይችላል የሚለውን ክፋ ሃሳብ ሲያፈላ፤ ሲተክል፤ ሲኮተኩት፤ ሲያሳድግ እና ጨካኝ ሃሳብን ሲያሰብል ነው የኖረው። የውጭ ኃይሎች የነደፋትን ካርታ ተግባር ላይ ያዋለው ህውሃት ነው። ኢትዮጵያን ባህር በር እና ወደብ ያሳጣ ህወሃት ነው። የኤርትራ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ህብራዊነት #የጎረደው ህወሃት ነው።   ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ዒላማው ትምህርት ቤት፤ የህዝብ መገልገያ ክሊኒክ እና መንገድ ማውደም ነበር። ይህን እኔ በስማበለው ሳይሆን በዓይኔ በብሌኑ ያዬሁት ሃቅ ነውና #ቀለጤ ፕሮፖጋንዲስቶች አያስፈልጉኝም።  ...

የእቴጌ ጎንደር #ትናንት ይጠራ! ናልኝ አጤ ትናንት የእኔ ሸበላ - በመሸቢያ!

ምስል
  የእቴጌ ጎንደር #ትናንት ይጠራ! ናልኝ አጤ ትናንት የእኔ ሸበላ - በመሸቢያ!   "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።"       ሽው አለኝ - ሽው፤ የተሰራሽበት ቀመር ------በምልሰት ትዝ አለኝ ትዝ፤ የተመሰጠርሽበት የልቅና - ፍጥረት አንቺ ወይዘሮ እሜቴ፤ የሺ ዘመናት #የላቂያ ምህረቴ እንዴት አለሽልኝ - የእኔ ውዴ? የእኔ - ህሊናዊነቴ! ህላዊነቴ!   እሙ የእኔ ልዕልቴ፤ ሥህነ - እመቤት - ፍቅርቴ የናፍቆት የስስት ሃብል ትፍስህቴ፦ የጽናት #ጽላቴ ፤ የትርታዬ - እትብቴ ብቃቴ፦ እንዴት አለሽልኝ የመኖር ዘይቤ አውራ የእናቴ የማንነቴ ምስባክ ጥበበ - ትንግርቴ። አንች የዘመን #ኮንፓስ ፤ አንቺ የሜትሮፖል አናት - ህብስቴ አንቺ የህብራዊነት ካንፓስ፦ የመኖር ግብረ ሰብ - ግርምቴ፦ የጀግንነት፤ የአንድነት፦ የህብረት መለዮ አሻራ - ጉልላቴ እኮ እንደምን አለሽልኝ የእኔ ቀለበቴ፤ የውስጥነት - ብርክቴ?   … ሳማትርሽ ግን #ሳልመትርሽ ……   የተበጀሽበት ዘሃ ግራው፥ - ጥልቀቱ የተቀመርሽበት የልቅናው፦ - ባዕቱ የተዋህድሽበት የዊዝደም፥ - ጉልላቱ የዕድምታ፦ የተደሞ፤ የቅኔ፦ የድጓ፥ የዝማሬ የተክሌ አቋቋም ህብስቱ የንባብ፤ የመፃህፍት፦ የትርጉም ሃውልተ - የሚስጢራት - ቁልፍ መፍቻ ሟተቱ የት ሄዶ ይሆን እንዲህ ዛሬ የአንቺ ውሎ እና አዳር የናዳ መገማሸሪያ ሆኖ የተገኜውየሞገድ መቅዘፊያ፦ መዳረሻ _______ የቻለውም /// ያልቻለውም የሆነው የአፍ መፍቻ ማሟሻ????   … #እ ………   እኮ! ሆድዬ የእኔይቱ - የጣይቱ - የምንቴወቹ - ምነው - ምነው ምነው? …… እንዲህ ወጀቡ በግራ ቀኝ ተበራከተ - የኛይቱ? የድፍረቱ - የፍጥረቱ፦ የእላፊው፤ የጥድፊያው -------ው...

ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?

  ማህበረ ነፃነት እንዴት ሰነበታችሁ? እንዴት ናችሁ?   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የተከበረው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን "አህያውን ፈርቶ መደላድሉን" እንዲሉ ብሄራዊ ሆኖ ግን የእስረኛ ፍቺን አስመልክቶ፤ የአማራ ክልል ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከሩ ግርም አለኝ። #አዝኛለሁም ። በእድሜ ዘመኑ የ365 ቀናት በራሱ አቅም የመንቀሳቀስ ምንም አቅም የሌለውን አልቦሽ ክልል ላይ ሃሳቡን ማቅረብ በራሱ ኮሚሽኑን ግምት ውስጥ ይጥላል።    የሆነ ሆኖ አጠቃላይ የፖለቲካ እስረኞች የእስር ፍቺ #በብሄራዊ ደረጃ ቅድሚያ ተሰጥቶት፦ በበኽረ ጉዳይ አጀንዳነት ተይዞ ሊሠራበት ሲገባ እንደ ተራ #ተለጣፊ ጉዳይ፦ የአማራ ክልል እስረኞች ብቻ እንዲፈቱ መጠዬቁ ኮሚክ እሳቤ ሆኖ ነው ያገኜሁት። ቀድሞ ነገር የህወሃትን መንበረ ሥልጣን እንዲለቅ ምዕራብውያንን ያሳመነው መሠረታዊ አንኳር ጉዳይ የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ ነበር። ያንጊዜ ተደማሪ፤ #ተጠማኝ ፤ ተዋህጂ ስስ ስለነበር በዬትም ሁኔታ የሚደመጠው ድምጽ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ነበር የትግሉ ሞቶ። እናም አሳካን።    የሆነ ሆኖ የአማራ ጉዳይ ብሄራዊ እንጂ ክልላዊ አይደለም። በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የአብይዝም መንግሥት በቆራጥነት ሊወስዳቸው ከሚገቡ መቅድመ እርምጃወች ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የፖለቲካ እስረኞችን #ያለምንም #ቅድመ ሁኔታ መፍታት ለቀጣዩ የፖለቲካ ንግግር ይሁን ስምምነት በር ከፋች ይሆናል።   እንደ እኔ ምኞት እና ተስፋ በኢትዮጵያ ምድር ማንም በአስተሳሰቡ፤ በምልከታው፤ በፖለቲካ #አቅሙ እና #አቋሙ አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊታሰር፤ ሊንገላታ፤ #ቤተሰቡ #ሊጉላላ አይገባም። በእስር ምክንያት የመኖር ተስፋው ሊዘረፍ፤ ወጣትነቱን ሆነ የ...