#የማይነጥፈው #ልሙጡ ህልመ - ግብጽ።
#የማይነጥፈው #ልሙጡ ህልመ - ግብጽ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፮ ክብረቶቼ እንዴት አደራችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ በጣም ደህና ነኝ። አቤቶ ግብጽ የራሱ የሆነ ጸጋ እና በረከት አለው። የአባይ ጉዞ ወደ ግብጽ ሲያቀና እራሱን የቻለ እዮራዊ ሚስጢር አለው። የግብጽ ሊሂቃን በዚህ እዮራዊ ሚስጢር ውስጥ ሆነው በቅንነት እና በዲስፕሊን የእግዘአብሄርን፤ የአላህን ስጦታ በማክበር ከክፋ ሃሳብ ጋር ሊፋቱ፤ ከቅናት ጋራ ሃራም ሊባባሉ በተገባ ነበር። እንደ እኔ የግብጽ ሊቃውንት ጸጋቸውን የማንበብ፤ የመተርጎም እና የማመሳጠር አቅም ቢኖራቸው ኖሮ ዘመናቸውን ሙሉ በስውር ሴራ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ከሚንቀሳቀሱ የየዘመኑ የክፋ ሃሳብ ባለሟሎች ጋር ባልተባበሩ ነበር። ለግብጾች ኢትዮጵያ #እስትንፋሳቸው ፤ የመኖራቸው ልሁቅ ሚስጢር ናት። ይህን ትንግርት በወጉ ዕውቅና ሰጥተው ልጆቻቸው፤ ትውልዶቻቸው ኢትዮጵያን የነፍስ አድን ህይወት መሆኗን በማስተማር፤ ስለ ኢትዮጵያ ሊጸልዩ፤ እሷን ሄዶ ለማየት ሊጓጉ በተገባ ነበር። ግብጽ እንደ አገር የመቀጠሉ ሚስጢር የአጤ አባይ የግዮን ሚስጢር ነው። የግብጽን መኖርን - ያኖረ፤ ማወቅን - ያተባ፤ ለግብፃውያን ትውልድ #ብራ የፈጠረ፤ የአገር ተስፋን ያለመለመ አጤ አባይ ነው። አጤ አባይ ልጆቹ በጨለማ እየማቀቁ፤ በምግብ እጥረት እየተሰለሰሉ ውሃ ብቻ ሳይሆን፤ የኢትዮጵያን እዮራዊ ቅን መንፈስ ይዞ እየነጎደ ግብጽን ድሯል፤ ኩሏል፦ ለወግ ለማዕረግም አብቅቷል። አባይ ሲጓጓዝ የኢትዮጵያ ንጹህ #ቅዱስ መንፈስንም ይዞ ነው። ይህ ረቂቅ ጉዳይ ነው። አጤ አባይ፤ ውሃ ብቻ እንጂ የኢትዮጵያን እዮራዊ ሁለመና ...