ገፋ አድርጎ ማሰብ ያስፈልጋል፤

ምኑን ይሆን ፍጥጫው?


"በእያሱም ጊዜ እነሳቸውን ያደነበት ቀን አለ። በገዴዎንም ጊዜ እነሳቸውን ያደነበት ቀን አለ። 
በሳምሶንም ጊዜ፤ በዲቦራም ጊዜ እነሳቸውን ያዳነበት ቀን አለ፤ በውንድና በሴትም ቢሆን አድሮ 
መከራ ከሚያጸኑባቸው ከጠላቶቻቸውም እጅ ያዳኗቸው ዘንድ መሳፍንትን ያስነሳላቸው ነበር።" 
                           መቃብያን ምዕራፍ ፬ ከቊጥር ፩ እስከ ፫ 

                 አቤቱ ልዑል እግዚአብሄር ሆይ! በዘመነ አብይም ኢትዮጵያን ከመፍረስ አድናት! 
                                 ለእኛም እንደ ቃልህ ይደረግልን፤ ይሁንልንም። 
                     ነፃነት ለአባ ቅንዬ! ነፃነት ለትንታጉ ብቁ፤ ሁገብ፤ ሁለመና ሙሴ!


 ከሥርጉተ©ሥላሴ 
19.08.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
  • ·     መነሻ።

Ethiopia: ጽዮን ግርማ አምባሳደር ካሳንአፋጠጠቻቸው“¡ ልዕልተይ ብቅ ያለችበት መሰረታዊ ምክንያት መፈንቅለ መንፈሱ ድልዳል መያዙ ስለተረጋገጠ ብቻ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ በማገገም ላይ ስላለ ይመስላል ... ከዶር ደብረጽዮን ልበ ሙሉ ቃለ ምልልስ ማግስት ... 

በተጨማሪም ምዕራባውያን ፊታቸውን ያዞሩበት አመክንዮ ዕድሜ ለዛ ቅን እንጂ እገታውን ስላስነሳላቸውም ነው … አድፍጠው የጠበቁትም አገር ሰላም ነው ብሎ በቃሉ  በአካል ተገኝቶ እንዲያረጋግጥ ነበር 100% ተሳክቶላቸዋል።
  • ·     ጠብታ።

የኔዎቹ ደህናን ናችሁን? ዛሬ ሁለት ተያያዥ ነገሮች ይነሳሉ። የሁለት ቀዳማይ ጋዜጠኞች ዕይታ፤ በመሰመር ሙያ እንጂ  የአቋም ጉዳይ ሃዲዱ እራሳቸው ይወቁት። እኔም ዘው ያልኩት ነገረ አብይ ትንፋሽ ስላለበት ብቻ ነው። መዘናጋቱ እና ውደቀቱን አስቀድሜ ስቸከችክ ከርሜያለሁኝ። 

አሁን ደግሞ የግራ ቀኙ የቤተ መንግሥት አንቶዎች አገር ሰላም ነው እያሉን ነው፤ ይሁናላቸው … እንደ አፋቸውም ያድርግልን“ ቸር ተመኝ ቸር ታገኝ“ በሚለው ብሂል …
የሆነ ሆኖ ትንሽ ቆይተን በልዕልት ጽዮን ጉዳይ የምለው ይኖረኛል። እንዲሁ በለብታ በቅንነት ዝም ብሎ ስለማይታለፍ ነገረ ጽዮን። 

ከዛ በፊት ግን አንድ ነገር ልበል። እንኳን ለዚህ አባቃህ ይባል አይደል ልጅ ጋዜጠኛ መሳዩ መኮነን /ሚሩ ምነው ጠፉብን? (መሳይ መኮንን) August 19, 2018 በዚህ ቀን በጣፈው ሃሳቡ ማለት ነው ይህን ያለው።

ያው እኔ የእሱን ጹሁፍ ሙሉውን አልሄድበትም፤ ጥቂቶች ነገር ነው የማነሳው፤ ሌላው ለመናጆ ነው ወግ ለማሰመር ስለሆነ የሚኮልማቸው።  

አሁንም እንደ ቀደመው ጥቂቶችን ብቻ ላንሳ ለዛሬ ከማሳረጊያው ልነሳ  አብያችን ሰላም ነው። አታስቡአብያችን“ ፐ! ፐ! ፐ! ዋው! ጋዜጠኛ ደረጀ የአመስተርዳሙ „የእኛ ወገን አብይ“ ብሎን ነበር አሁን ደግሞ ልጅ መሳዩ „የእኛ አብይ አብይ ኬኛ እያለን ነው።“

 እንኳን ባልንጀራ ሥርጉትሻ አገኜች ነው፤ እሰቡት የኔዎቹ ከቤተመንግሥት ወገን ሰው ሲገኝ ፍንጥዝ ያደርጋል አይደል¡
ለነገሩ እግዚኦ! ሲል የባጀው የሳተናው ብራና ሲወርድበት የነበረው መከራ፤ ሲያውከው ስለነበር በመንፈስ „እንኳን ለዚህ አበቃህ“ እንደሚለው ነው።

የኛ ነገር ይሄው ነው የምንቃወምበትን፤ የምንደግፍበትም ፋክት ስላይደለ ወጀብ እንዳሻው ቀኝ እና ግራ ባሻው አቅጣጫ ይለጋናል፤ ለነገሩ እሱ የቤተ - መንግሥስት ሰው ስለሆነ „ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ“ 

ተብሎ ይታለፍ … ለነገሩ ስንት ሰንበት ነው ዶር አብይ አህመድ እረፍት ተሰጥቶት ያሳለፈው? አሁን በሽ ሆኗል እንደ እኛ ሰንበትን በ እገተ እያሳለፈ ነው ያ እርፈት አያስፈልገኝም ያለ ቅን ንጹህ ትሁት መንፈስ፤ ለነገሩ ካቢኔውም በዛብን ልንፈናዳ ነው ብለው ዲሞ ከመውጣቸው በፊት አቤቶ ሳጅን በረከት ስምዖን እና ሴረኞች የሆነውን አድርገዋል።

መረጃው ሁልጊዜ በእጄ ነው የሚለን ኢሳት አይደለም ፌድራል መንግሥት ላይ ክልሎችንም አውቃለሁ ሲል አታውቁም ብለው ብአዴኖች ወጥተው ሞግተዋቸው ነበር። ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ደግሞ እንውቃለን ተብሎ የተሰጠው መረጃ ሁሉ ውልቅልቁ ወጣ እና ከፎቅ ወጥቶ ሲፈጠፈጥ እንደ ባጀ ይታወቃል።

አሁንማ ፍርፋሪም አትገኘም፤ ብዙ ውስብስብ ገመና አለበት። የመረጃው መረብ ማዕላዊ ማዘዣ ጣቢያው ቤተ መንግሥት ነው፤ ለነገሩ ከቤተ መንግሥቱ ማን ነው ያለው? ግን የት ነው ጊዜያዊው የጠ/ ሚሩ አፐርትመንት? የትኛው ግቢ?  

እንኳንስ አሁን እጅግ በተከደነ ትንፋሽን በሰነገ ሰፊ የደህንነት ጉዳይ አንድም ብጣቂ መረጃ ትንበያ ለምልክት ፋይዳ ኖሯት አልታዬችም በ4ወራቱ የጠ/ ሚሩ ጉዞ። ከመጋቢት 24 እስከ ሐምሌ 19. 2010 በሙሉ ነፃነት የተከወኑ ተግባራት ሁሉ ከኢሳት እውቅና ውጪ ነበሩ። የፖለቲካው ማለቴ ነው። ኢኮኖሚ በሚመለከት ትንበያው ሳይሆን ትንተናው ከልብ ይገባል።

አሁን ደግሞ ጠ/ ሚሩ ምንም አልሆኑም የሥራ ብዛት ነው ለፌክ መረጃ አታረግርጉ ነው የሚሉን ባለ የውስጥ አዋቂው ምንጫችን። „አብያችን ደህና ነው ሥራ በዝቶበት ነው።“ እሱንማ ዶር አብይ አህመድ አቡነ መሪቀርዮስን ጠይቀው ሲመለሱ በተዘጋ በር ውስጥ ነገሩን ግለጸው ስለምን ሥራ እንደበዛባቸው እኮ ጸልዩ ብለው ነበር።


/ / አብይ አህመድ በአቡነ መርቆሪዮስ መኖሪያ ቤት ያደረጉት ሙሉ ቆይታ ተገልጧል። 


ስለዚህ አዲስ ነገር አልተነገረነም፤ ያው የታወቀ ነገር ነው። ለተባራሪው እና ለመላመቱ ደግሞ ሁሉም ቤተኛ ነው እንደ ተለመደው፤ ለማናቸውም መረጃ እነ ጋዜጠኛ መሳዩ መኮነን እና ድርጀቱ ሆን እኛ ተማላዎች ትቢያ ላይ ያለነው እኩል ለእኩል ነን። በፓትርያርኩ ጉብኝንት ላይም ETV Fana እራሱ በዚህ ጊዜ የተገኙት ሁለቱ ብቻ ናቸው። ስለምን? ይህንም የጠዬቀ የለም።  በር እንዴት እንደ ተዘጋ ሁሉ ማዬት ይቻላል፤ ቪዲዮው ላይ።  

 

እዬተከወነው ያለው ድርጊት በታላቅ ሚስጢር እጅግ ተከድኖ ነው በብርቱ ጥንቃቄ ነው። ስለምን? መሰረቱ የተንሸራተተው የታላቋ ትግራይ ህልም መልሶ ያገግም ዘንድ ጫናውን በአግባቡ ማስተንፈስ ስለሚያስፈለግ። እነሱ ይሄን ያክል ጠንካሮች ናቸው።

አፈንገጦ የወጣ አንጃ ነበር ብዬ አስባለሁኝ፤ ለዚህ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ በራሱ በአብይ ካቢኔ ደጋፊም፤ እሱን ሳይቀር እነ ሳጅን በረከት ስምዖን ያስተነፈሱት ይመስለኛል እንደ እኔ ዕይታ።

ከመዳፍ የወጡትን ነገሮች ለማስመለስ እኮ ጥቂት ተግባራትን መሥራት ነበር፤ አብሶ አቅም ያላቸው ዲያስፖራ የሚገኙ እነ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና ፕ/ አለማርያም፤  ግን አልሆንም ሰላም ነው በዚህ፤ ሰላም ነው በዛ፤ ሰላም ነው? ሰላም አለመሆኑን ብዙ ምልክቶች አሉ። ልቡ ከኖረ። ይታወቃል እኮ ለ43 ዓመት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማለት። የ66ቱ ትውልድ ፖለቲካም እንዲሁ … 

እነዚያን እንደ ፖለቲካ ሰውነት አያይዞ ለእርምጃ መዘጋጀት ሲገባ እንተኛ ነው … ብቃታችን እስከዚህ ድረስ ነው … ወያኔ ሃርነት ትግራይን ስንበልጠው ይህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴራ ነው ብለን ወጀብ እንለቅበታለን ‚ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ሲመጣ‘ አሁን ደግሞ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመሸገበት ወጥቶ ድል ላይ ሲሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰራዊት የፈጠረው ፌካዊ ወጀብ ነው አርፋችሁ ተቀመጡ ነው የሚባለው … አቅጣጫ የጠፋብን ወይንም ቴርሞሜትር የሌለን ጉደኞች ነን … 

መረጃውን የሚሰጡ ሰዎች ቢሆን መረጃ ከማውጣታቸው በፊት እቀባ ተጥሎባቸዋል ብሎ ለማሰብ እንኳን አልተቻለም። … የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጹሁፍ ስለምን እንዲወጣ እንደ ተደረገ ሁሉ አናስበውም።

እሱ የሚያውቀውን ብቻ ይሆናል የጻፈው ግን የእሱ ብዕር ተፈላጊ ናት ለምስክረነት። ምክንያቱም አንድ የመረጃ ፍስት ምንጭ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ። ዕውቅናውም የዚያን ያህል ጉልበታም ነው። በጠ/ ሚር ቢሮም የተሰጠው አክብሮት እና ልቅና ከተለመደው በላይ ነበር። ስልክ እስከመያዝ እኮ ደርሶ ነበር። አንድ ንግግር ላይ እያሉ ስልክ ሲጮኽ እሱ ነው ያን ስልክ የተቀበለው። ስለዚህ ይህን ሰው ያዬኸውን ተናገር የሰማህውን መስክር መባሉ አይቀሬ ነው፤

እሱ ራሱ ከፌድራል ወርዶ አሁን አዲስ አባባ ላይ ባለው የባለሙያዎች ተሳትፎ ላይ ነው ያለው። በሸልማት አሰጣጥም ላይ። ድራሹን እንዳያጠፉት ቀኑ ገና ነው። ጊዜ ይጠብቃል ወያኔ ሃርነት ትግራይ። ማስበርገግ ተፈጥሮ አይደለም። „ሙያ በልብን“ ተክህኖበታል። እንዴት አድርጎ ቀድማ ደገፈቸውን አርቲስት አስቴር መዳኔን ከመድረክ እንዳወጣት አይታችሁዋል። በቀላል ቀመር ወያኔ ሃርነት ማንፌሰቶችን ሊቃናት መተርጎም አያቻልም። ቃልኪዳናቸው ከውስጥ ለውስጥ በዲስፕሊን ነው። 

በቀጠለው ሙቀት ቢሆን ግን ከውጭ ወደ አገር ስለሚገባው ሃይል አንድ ተቋም መገንባት ያስፈልግ ስለነበር በዛ ላይ ነበር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሊተጋ የሚገባው መድረክ ይከፈት ነበር።  … 

ምክንያቱም ሆድዕቃውን ስለሚያውቀው … በሌላ በኩል በቅዱስ ወብፁዕ አቡነ መሪቀሪዮስ ጥዬቃ ላይም የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አብሮ አለመሆን፤ ይመለሱ አይመለሱ ባላውቀውም የዶር ካሳ ከበደም አብሮ አለመገኘት ይህ ሁሉ የሚሰጠው ፍንጭ አለ። እንዲዳፈን የሚፈለግ መረጃ አለ። በዛ ላይ ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር የቀረበ ግንኙነት የነበራቸው ሁሉ ተቋርጠዋል። ይህን በጣም በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

ይህም ብቻ አይደለም እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ትእዛዝ ሲሰጡም ተናገር በተባለላቸው መንፈስ ብቻ ነው … ይህን ቅብ ጉዞ  የኤርትራ መንግሥት ሊመረመርው ከፈቀደ ይሳነዋል ብዬ አላስብም።

አሁን እኮ የአብይ መንፈስ ደመመን ውስጥ ነው። ሁሉም ይቀር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘውን ሞት እንዲህ በተዳፈነ ጉዞ ይቀጥላሉ ተብሎ አይታሰብም። ይህም ሌላ ፍንጭ ይሰጣል፤ በግድያው እንሱ አሉበት እንዲባልም ይፈለጋል፤ ለዚህ ነው ትግራይ ላይ የ ኢንጂነሩ ህልፈት አጀንዳ የነበረው፤ 

…. በሌላ በኩል መንግሥት የሌላት አገርም እንዲባልም ይፈለጋል … የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ሳይሆን ድፍን ተጋሩ እነሱ እንደ እኛ ዘርከራኮች አይደሉም። ሁሉም ነገር በመዳፋችን ሳለም አላወቅንበትም፤ ተጻራሪ ሆነን  የአብይን ትጋት ስናራክሰው ነው የባጀነው።

አሁንማ እነሱ በተገኘው የአብይ የሚሊዮኖች የድጋፍ ድምጽ የራሳቸውን የቤት ሥራ ሌት እና ቀን እንቅልፍ አጥተው በትጋት እና በተከታታይነት ኢንባሲዎቻቸው ሁሉ እዬሠሩ ነው።

ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ከዛው ካፍንጫውም ይሄው እዬተከወነ ስለመሆኑ የልዕልት ጽዮን ግርማ ቃለ ምልልስ ማዳመጥ ነው።

እሷም አገር ሰላም ነው ብላ ተረጋግታ፤ ደልደል ብላ ቃለ ምልልሱን እንዳደረገችው እንሱም በዚያው መንገድ መጪ ስለማለታቸው ይሄው ጹሁፍ ያመለከታል … ትንሽ እንኳን እዬተጋለብን ስለመሆኑ መጠርጠር የለም፤ ቢያንስ እንደ ጋዜጠኛ፤ ቢያንስ እንደ ድርጅት አባልነት…።

·     ሌላው የቅደስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕድምታ ነው።  
ቤተክርስትያን ወገንተኝነት ደግሞ አንስቷል ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ይህ ሆን ተብሎ የተቀናበረ ስለመሆኑ እንዴት እንዳላዬው አላውቅም። ቢያንስ መጠርጠር …
ቤተክርስቲያኗ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመርዳት ኢትዮጵያውያን እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበች።

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ልዩ የሆነ የፍጽምና እና የቅድስና ተግባር መከወናቸው ስኬታማ መሆናቸው ይታዋቃል። ድርሳንም፤ ታቦትም ሊያሰቀርጽ የሚችል ተጋድሎቻው እና ውጤታቸው የቀደመውን የደጋጎችን ዘመን በታሪክ የሰማነውን ደግመውታል።
አጤ እያሱ የደበረ ብርሃን ሥላሴን ታቦት ራሳቸው ዙፋናቸውን አውረደው እንደ ተሸከሙ ታሪከ ገድላቸው ይነገረናል። ያን ነው የደገሙት ቅኑ፤ ንጹሁ፤ ሰው አክባሪው ታታሪው ጠ/ ሚር እንግዲህ ከስንት ሺህ ዘመናት ወደ ኋዋላ ሂደው ትውፊቱን አያያዙት። 

የግንቦት 7 መሪዎች እዛው ተቀምጠው አንድም ቀን እንደ ብሄራዊ አገራዊ መሪ እና አውራ ፓርቲነት ልያቸው አላሉም ነበር ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መሪቀርዮስን፤ እኒህ ቅዱስ ግን አደረጉት። ይህን በማድረጋቸውም የመስዕውትነት ገመዳቸው ጠብቋል፤ በሰማይ ግን በቀጥታ ገነት ያስገባቸዋል። ሰማዕትነቱን በቁማቸው እዬተቀበሉ ነው። ለዚህም ነው እኔ እንቅልፍም ያጣሁት፤ በዚህች ሰሞናት ሱባኤ ሁሉ ነፃነት ለ አብይ ነው። እንቅልፍም አልተኛም። ህልሜን አምነዋለሁኝ። ወንበሩ ባዶ ሆኖ አይቸዋለሁኝ።
በዚህ ሂደት የተናደው የተቃጠለው የተደረመስ አንድ አንኳር የፖለቲካ መስመር አለ።  አጥፍተናታል የተባለችው ቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶ ልዕልናዋ እንደ ገና በክብር መመለስ ብቻ ሳይሆን የህብር የሃይማኖታት ቀለማት አንድነት፤ ውህድት፤ መተሳሰብ፤ ስምረት የበለጸገበት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ መሆናችን ሰምተናል፤ አይተናል። ተመስገንም ብለናል! በዚህ ውስጥ አገረ ኢትዮጵያም፤ ኢትዮጵያዊነትም ባላውን አግኝቷል።
ግማሹ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ ተቀድዷል።  ይህ ቁርጥማት የሆነበት አካል ደግሞ ይህን ለማጠልሸት ኢትዮ ሱማሌ ላይ ምን አሰናድቶ እንደ ጠበቀ የአደባባይ ሚስጢር ነው። 
የሆነው ሁሉ ይታወቃል፤ ይህም ታቅዶ የተከወነ ነው፤ ያ ታቅዶ የተከወነ ነገር በዘመነ አብይ ተከወነ ለማለት ህጋዊ ጥበቃ ለቤተ ክርስትያናችን አልተደረገም ለማለት ነው ቅደስት ተዋህዶ ወጥታ አቤቱታ እንድታሰማ የተደረገችው፤ እሱ በእሱ ነው፤ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይሻለናል ነው፤ ሌላ ትርጉም የለውም። ፈራጁም፤ ዳኛወም፤ አቃቢ ህጉም፤ ደብዳቢውም መስካሪውም ያው እሱ በእሱ ነው፤ እንደተለመደው። በዛ ላይ ኦህዴድም ዕድሉን ሲዛበነን አሽሎኳል። ሌላ መፈንቅል ሲያል እሱም መዳፍ ውስጥ ነው አሁን።
እንዲሁም ሞጋቹ የቅኖኖ እስርን ባለቅብዕው መንፈስ የአብይ ቅድስና የዲያቢሎስን ቅስም ከሰባባረ እስሩን ከፈታ ስለምን ያስፈለጋታል የቅድስት ተዋህዶ መራህያን የአብይ መንፈስ ቀጣይነት? ፍጹም የተደራጀው ስደተኛው ኦርቶዶክ ተዋህዶ እኮ ለጊዜው መዳፍ ውስጥ ነው።
ይህን ነው እንግዲህ አድንቆ የጻፈው ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ቤተክርስቲያን እንኳን የመንግስት ትዕግስት አደጋ እያስከተለ ነውእስከ ማለት የደረሰችው ያለምክንያት አይደለም።“ ይሄ ደግሞ ከምን ጋር ተያዬዘ ስለምን ሆነ የሚለውን ጋዜጠኛ መሳይ ሊታዬው አልቻለም።
ነገም በዚህ ዙሪያ ይህ ለውጡ ከታገተ ሊመጣ የሚችለው ጫና ደግሞ አለ። ቀን አድብቶ የሚጠበቀው። የሃይማኖታችን አንድነቷን በቅንነት የምናዬውን ያህል የአባቶቻችን ደህንነት ደግሞ ያሳስበናል፤ ስለምን?
ልጃቸው ይስሃቅ እገታ ላይ ስላለ፤ ሙሉ ነፃነቱን ስለተነጠቀ። ብፁዑኑ አባቶቻችን እነሱ ይህን እንዳይጠረጥሩ ነው ያ የተደረገው … እርግጥ ነው የነፍሱን ያህል ይወዳቸዋል፤ አብይ ብጹዕኑን እሱን ባያምኑ ቅስቅስ አይሉም ነበር። ከፈቀዱላቸው አንድነቱን በማስቀጠል ግን ነፍሳቸው ስለሚያስፈልገን ዓይነ ገቦች ወደ ስደት ባዕታቸው ቢመለሱ ደስ ይለኛል። ለነገሩ በህልም ልዑል እግዚአብሄር ይነግራቸዋል ብዬም አምናለሁኝ። „ወንበሩ ባዶ መሆኑን“ እጅግ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ከሐምሌ 19 ጀምሮ ወንበሩ ባዶ መሆኑን ነው።  
·      ሌላም አለኝ …
ይህንን የሚያጠናክር አዲስ ሥር መዘዝ ያለችባትም ዛሬ ያገኘሁት የልዕልት ጽዮን ግርማ ከአንባሳደር ካሳ ተከለብርሃን ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ ያመለክታል … ያን አያይዞ መመርመር ነው። „የህግ የበላይነት፤ የዴሚክራሲ መስፈን“ ጉዳይ። ስለምን ያ እንደ ተፈለገ ሲመረመር፤ ከአሜሪካ መልስ ንጠት እንጂ እርጋታ የለም ነው። አብይን የማሳጣት ፖለቲካ ነው። ያው ሚዲያው ሁሉ የባጀበት ነው ይሄው ጉዳይ።

እነ ልጅ መሳይ መኮነን ተጥደውበት የባጁበት መንገድ ነው። ከሳተናው ብራና በስተቀር ሁሉም ሚዲያ በዚኸው በምሾ ዓውድ ላይ ነበሩ። ለዛውም በሰላሙ ጊዜ።
ይህ የቤተክርስትያን ህገ ቤተክርስትያን ሲደፈር መንግሥት የለም የማለት ያህል ነው፤ ጉዳይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የህግ የበላይነት ለማስከበር የተሻለ ነው፤ ሌላ ምንም ጣጣ የለውም።

የአብይ ሌጋሲው ደግሞ እገታ ውስጥ ነው ያለው። ማናቸውንም እርምጃ ወስዶ ማስተካከል እንዳይችል። የ አብይ ካቢኔ የ እርምጃ አወሳሰድ እና በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥር ወድቀን በአብይ ልሳን ተነግሮ እንዲወሰድ የሚፈለገው እርምጃ በማስተዋል ሊታይ ይገባል።

የ አብይ ካቤኒ ይህን የመቋቋም አቅሙን ለመስበር ብዙ ሳቦታጅ ነው የከረመበት። ራሱ የመንግሥት ሚዲያ ተብዬው እንዴት እዬቆራረጠ ሲዘንጥ እንደ ባጀ ይታወቃል።

ካቦኔውን የነፃነት ታጋይ ነኝ የሚለው ባንድ ወገን፤ ያኮረፈው በሌላ ወገን፤ ብሄርተኛው ፖለቲካም አጀንዳ ስለጣ በሌላ በኩል፤ የወያኔ ሃርነትት ትግራይ ደግሞ ጎድቦ ሰቅዞ ይዞ ሁሉም ያለ ርህራሄ ናዳውን ለቀበበት። 

ጥቂት ቅኖች ብቻ ናቸው ለዛውም ከመሼ ባለቅ  ሰዓት ሁሉን እንደሚሆን አድርጎ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ካደራጀ ኋዋላ ድጋፍ መስጠት የቻሉት።  አቅሙ በብዙ ፈተና በሽታሽቶሽ ፍዳውን ከከፈለ በኋዋላ። እኛ የምንታመሰው ለሚሊዮኖች የተስፋ አገር ሳይሆን በህሊናቸውን ውስጥ ለታነጸው የኢጎ እና የማንፌስቶ ጣዖት ነው።

አሁን የሚፈለገው ድንጊያ እስኪ ወረወርበት፤ ህዝብ ተስፋ አጥቶ ህዝብ አብይ ይነሳ የሚል መፈክር እስኪያስነሳ ድርስ ይጠበቃል … ጨዋታው ይሄው ነው።  ሥርዓት አልበኝነቱን እንደሆን አይተነዋል …ይህ ደግሞ መድረክ ላይ አለን የሚሉት ተጽዕኖ ፈጣሪ ነን የሚሉት የአብዛኞቹ ህልም ነው።  አብይ እና መንፈሱ ድርብ ንብርብር አቅሙ ያለስፈራው እንብዛም ነውና።

አዲሱ ሰላማዊ ሰልፍ „አንደመርም“ ነው። ልክ በአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎና በኦሮሞ ንቅናቄ ላይ ለታሰሩት 50 ሺህ ወገኖች „አይደገምም!“ ሳጅን በረከት ስምዖን ቲሸርት አሰርተው እንደ ቀለዱት ሁሉ። 

ይህን ደግሞ ለማንፌስቶ አምላኪዎች ላሜ ወለደች እንደሚሉት ልባቸው ያውቀዋል። እንተዋወቃለን። ምክንያቱም መልሶ ተመልሶ አገርሽቶ ደግሞ የዲያስፖራው ወጀብ ሽግግር መንግሥት፤ ተጽዕኖ ፈጣሪ መንግሥት ወዘተ ይጥላል …

ሌላ ልጅ መሳይ መኮነን ያነሳው ጉዳይ ወቅታዊ መረጃ በመንግሥት ይሰጥ ነው። በየዕለቱም ባይሆን በሳምንት ሁለት ቀናት ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ለህዝብ የማሳወቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል።“ ይህንማ እያደረጉት እኮ ነው።

 እሱ ማሳሰቢያ ሰጠ አልሰጠ የለበጣ የሽፋን የአብይ መንፈስ ሞገድን የሚያረሳሱ፤ የሚያዘናጉ፤ አፍዝ አደንዝዝ ጉዳዮችማ ልጅ መሳይ ባይልም ተግተው እዬከወኑት ነው። ሌላ አማራጭ እና መንገድ የላቸውም። 

ይህን እንዲደረግላቸው የሚፈልጉት የምዕራብውያን ጫና የተጣለው ማዕቅብ ሁሉ፤ ታግተው የኖሩ እድሎች ሁሉ እንዲከፈቱ፤ ይሄ የዲያስፖራው የሙያ እገዛ፤ የፋይናንስ እገዛ፤ ነፍስ አጥቶ የኖረውን ኢንባሲያቸው ከቦረዶነት ወደ ሞቃታማ ሞገድ፤ ከሥራ ፈትነት ወደ ትጋት እንዲቀዬር ይፈለጋል፤ ለዚህ ደግሞ  የግድ አብይን በፍሬም አስገብተው በግድግዳ ጌጥነት መጠቃማቸው አይቀሬ ነው።

ይህ ከደላው ብቻ ነው አቤቱ ግንቦት 7 አገር ቤት የሚገባው። በስተቀር ግን ምንም ዋስተና እንደ ሌለው እራሱም ያውቀዋል።

ግን የኡጋዴን ነጻ አውጪ ጋር ስምምነት ግንቦት 7 አድርጎ ነበር ፍራንክፈርት ላይ፤ አሁን አገር እንደ ገቡ ዜና አይቻለሁኝ፤ ከአገራዊ ንቅናቄም ዶር ኮንቴ ሙሳ የአፋሩ ማለት ነው አገር እንደ ገቡ አይቻለሁ እና ሁለቱም ያን ያህል ሚደያ ላይ የተደለቀላቸው የፖለቲካ ትርፍነታቸው በድርሳን የተዜመላቸው ውሎች የጭድ ክምር ሆኖ ቀረ ማለት ነውን? ፖለቲካ እንዲህ ነው ሞቅ ሲል መሰባሰብ ሚዛኑ ገለል ሲል ደግሞ እንዲህ ዘንበል ቀና …

„ከማያድሩበት ቤት አያመሻሹበት ነው“ በቁሙ ህብረቱ፤ ድርደሩ፤ ምክክሩ ሁሉ መናዱ አንድም ቀን ከኪሳራ አለመውጣችን ያሳያል … እንደገናም የፖለቲካ አቅማችን የአመራር ጥበባችን ጅራት እንጂ ቀንድ አለመሆኑን ያመሳክራል።

ነገ ደግሞ ከማን ጋር ይሆን ድርደሩ? ለዛ ደግሞ እስተ ምርጫ ማግስት ድረስ በስንት ወቄት አቅም ይባክን ይሆን? አቅም የሌለው ቢያንስ ኢትዮጵያን የሚታደግ አቅም ያለው ሲመጣ ተቀናቃኝ ሆኖ መውጣት የለበትም ስል የነበርኩትም ለዚህ ነው።

አሁንማ ሁሉም እንዳልሆነ ሆኗል። የአባቶቻችን አምላክ ጸሎት ደግፎን የሚሆን ነገር ከመጣ ተስፋ ይጠበቅ ከዛው ከግንባሩ …

ቀሬው ነገር ዶር አብይ አህመድ ጤና አጥቻለሁኝ በቃኝ፤ ወይንም ብቁ አይደለሁም ብለው ራሳቸው ከሥልጣን እንዲያገሉ እስከ ማድረግ ሊደርስ እንደሚችል ሁሉ ገፋ አድርጎ መጠበቅ ይገባል።

ይህም ብቻ አይደለም አጥፍቻለሁ፤ የግንባሬን፤ የህገ መንግሥቱን ህግ ተላልፌያለሁ፤ ለቀውሱ ሁሉ ተጠያቂ እኔው ነኝ ብለው ይቅርታ ያቺ የተለመደችው ድርድርም ሊመጣ እንደሚችል ማሰቡ አያቀሬ ነው … ሲደርስ እንዴት ብለን ከምንደነገጥ፤ አጋጣሚው ከተፈጠረ ደግሞ ለቃል ብርቱው መሪ …

ዶር ደብረጽዮን እንደሚነግሩን ሁሉ ነገን ተቀርፆል ነው። እኛን የሚችል እንደ እኛ አቅም ያለው ማንም የፖለቲካ ድርጅት ከግንባራችን ውስጥ የለም ነው የሚሉት።
ለዚህ ነው እኔ ሌቦች ተፈቱ ብቻ ሳይሆን ለውጡ ሊቀለበስ ይችላል ብላችሁ እሰቡ ሁሉ ብዬ የጻፍኩት። እንዴት ነው ያ የዘመናይነቱ ኬክ ቆረሳ ተጠናቀቀ ወይስ …?

በብቃት በዬሰከንዱ ያን ያህል ዕውቀት፤ ያለ ክፍያ ሲያፈልቅ፤ ሰብዕና ሲታነጽ፤ በተሟላ ትህትና ስንጠመቅ፤ ምንም ነበር ለእኛ። ያው የለመድነው ኮኮብ ቆጠረ እና የረጋ እውሃ ሽታ ነበር የናፈቅን … 

አሁን ተንቀሳቀስን ተብ ተብ የሚታዬው ከኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወደ ፖለቲካዊ ትራንስፎርሜሽን ምጥቀቱ በገድላት አጋዢነት፤ እኮ ዕድሜ ለአብይ ወርክ ሾፕ፤ ሰሚናር፤ ተቋማዊ የኦን ላይን የነፃ የእውቀት አውደ ምህረት  ….
  • ·     አሜን ብለናል ልጅ መሳዩ … „ግን“ አትቀርም አብራ ትደምር ዘመኑ መደመር አይደለምን?  

„እግዚአብሄር ሀገራችንን ከክፉ ነገሮች ይጠብቃት!!!“ ይህ የመጨረሻው ድርሳን ነው የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን። አሜን! ልባል እና እውን እኛ ግን የኢትዮጵያን ደህነንት ወይንስ የኛ ማንፈሴቶ ደህንነት የቱ ይሆን የሚያሳስበን፤ የሚልቅብንስ? ዳኝነቱን ለንጹሃን ለቅኖች ልተዎች እንደ ዳኛ ሼክስፐር ላሉ ብርቱዎች የዕውነት ደፋሮች ።
  • ·     ምልስት ወደ ልዕልተይ …

የልዕለት ጽዮን ውይይት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አዳመጥኩት። እርስ ሰጥተው ፖስት ያደርጉላት ወገኖቼ „አፈጠጠች“ ነው የሚሉት? ምኑን ነው ያፋጠጠችው? ያው ያዬነውን የሰማናውን ነው የጠዬቀችው?

እርግጥ አንድ ትልቅ ዕውነት ወጥቷል። የዲሰ መታመስ መሰረቱ የአብይን የጉዞ መርሃ ግብር እኛ እንመራው ስለመሆኑ። ይህንም „እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምስናል“ ስለመሆኑ ቀደም ብለን እኔ እና ብዕሬ ተናግረነዋል።
እንደዛ ባይሆን ደግሞ ማዕከላዊ አቋም የነበራቸውን ወደ ማህል አያመጣቸውም ነበር። የተወሰደው እርምጃ ትክክል ነበር። እኔ ከዚህ ሆኜ የማይታወቅ ሰው ስለምን ጉባኤትን አይመራውም ስል ሁሉ ነበር።

ይህም ማለት እንደ ባለቤት አልባዋ ዜጋ ሥርጉተ ሥላሴ ያሉ ነፍሶች እጅግ በጣም ደስተኛ ሆነዋል ይህን መሰል ውሳኔ በመወሰኑ። ሰልችቶናል። አዲስ ዓይን፤ አዲስ መንፈስ ነው አሁን የሚናፍቀን። በሌላ በኩል አዲስ ቃል ማድመጥ ነው የምንሻው፤ በረጋ ነገር እኮ የተገኘው መሳሳት ብቻ ነው፤ እያነሱ መሄድ … 

የሄው ነው እንግዲህ የእኛ የትግል የነፃነት ረጅሙ እሩቁ ራዕይ … አንደ ሰው ሲታሰብ ላይ ያንጠለጠልናቸው ሰዎች ወርደው እንደ ህዝብ ለመኖር አቅመ ቢሶች መሆናቸውን አይተናል። ከ እኛ ጋር ወንበር ይዘው መቀመጡ ያርዳቸዋል። ሰነፎች ናቸው ዝቅ ብለው ለመመራት። መሪ ለመሆን እንጂ ለመመራትም አልመፈቅዳቸውን በትክክል ተመልከተናል። መሪ ማለት ለመመራትም መፍቀድም ነው።

በሌላ በኩል ግን እያንስን … እያነስን … እየሟሟን የመጣንበት ዘመን ተቀይሮ በአንድ ንጹህ ቅን ሰው ቃለ ምህዳን ሚሊዮን ወደ አንድነት ሲመጣ ያ ነበር ቁም ነገሩ ነፃነት ለሚፈለግ አባ ወራ ሆነ እማ ወራ እንጂ ኢህአዴግ በሚያዘጋጀው ስበሰባ ቆሜ አጋፋሪ ልሁን ማለት? በውነቱ ያስፍራል? እውነት ያሳፍራል? ያ ሁሉ ጉጉስ ለዚህ ነበርን?


የሆነ ሆኖ ልዕልተይ ዋናውን ጥያቄ አላነሳችም፤ እሷ ምዕራቡ ዓለም ወያኔ ሃርነት ትግራይ አጋጣሚውን ተጠቅሞ የተጣለበትን እቀባ እና የተዞረበት ፊትን ለማስመለስ ምን እዬተሠራ ነው ዋሰኙ ጉዳዮዋ? የልባሞች ቤሰብ ናታ።

ፍዳውን ከፍሎ በዬሰከንዱ ባትሎ ዶር አብይ አህመድ ባለማው እና በተደላደለው ማሳ ላይ ህሊናን ቀይሮ በዞረ ድምር ልዕልና የተጋሩ መንግሥት ለማስቀጠል እንዴት እዬተጠቀማችሁበት ነው ወይ ነው ዋና  ጉዳዮዋ። እንደ አውሮፓዋ ጸሐይ በጋ ላይ ብቅ ያደረጋትም ይሄው ነው። ጉሙ ተገፈፈ ... 

ያው የወያኔ ሃርነት ትግራይም ከማገገም አልፎ ማዕቀብ ጥሎ እያመሰ ስለሆነ እቀባው በድል መጠናቀቁን ፍቺና ቁልፍ ሰጥታናለች ልባሟ ወጣት ቃለ ምልልስ አድራጊዋ። በዚህ ዙሪያ አንዲትም ቃል ስለ ጠ/ ሚር የስኬት፤ የብቃት ልክ ማንሳት አልፈለገችም እና ስለምን ጠፉ አልተነሳም? ሥማቸውንም ለማንሳት አልደፈረችም?

እነዚህን ነገሮች ስናያይዛቸው ቤተ መንግሥት አካባቢ ላይ ያለው ዕውነት ገዢው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት እና ፌዙ የአብይ መንፈስ ጎርባጣውን በደለደለው ልክ እንዴት ልብ ተመልሶ የነጮቹ መንፈስን ገዝቶ ንግሥናው በሰላው መስመር ይቀጥላል ነው … ጨዋታው ይሄው ነው … እያዘናጉ ማደናበር … እያዘጉ ማዳዳጥ…

ከሰሞናቱም የአሜሪካ ኢንባሲ በኢትዮጵያ ቃለ አቀባይ የሰጡትም የተረገጥ እድምታም አለ። አቶ አህመድ ሽዴም እንዲሁ እነሱ እቴ ጠላትን ማጥቃትም፤ ማንበርከኩንም በሥርዓት ያውቁበታል።
  • ·      የሚገርመው።

 የነፃነት ፈላጊው የትናንት አውራዎች የአብይ ተቆርቋሪ ነን ቢሉም አያምርባቸውም፤ የተባጀውን እናውቀዋለን እና። አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ ደግሞ እኛ እንምራ ነው ግብግቡ፤ መከራ ሲመጣ ደግሞ ምንም ችግር የለም ዝም በሉ፤ አገር ሰላም ነው ይህ የቹፌው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህሪ ነው።

ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳቅ እና ተስፋ አይደለም ትግሉ፤ ድካሙ አቅም ሲባከን የተኖረው። እራሱ ላነገሠው የወረቀት ጣዖት እንጂ …

ነፃነት ለአብይ መንፈስ እና ለቤተሰቡ!
አብይ እገታ ውስጥ ነው ልንጮኽለት ይገባል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።