ንጉሡ ድምጽ አልባ ተውኔት በቤተ - መንግሥትም አና አለብን።
ምጥ እና ማጥ!
„ዓይኖቹ የተገለጡ ናቸውና አያስቀርምና፣
ጆሮም የተከፈተ ነውና ቸል አይልምና፤
የተናገረውንም ቃለ ሐሰት አያደርግምና።“
መቃብያ ካልዕ ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፲
ከሥርጉተ©ሥላሴ
19.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
- · እንደ መግቢያ።
ዋዛ እና ቁምነገር ሳይሆን ቧልት እና ተረብ ነው
ይሄ የሰሞናቱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጨለማዊ ድራማ። ትራጄዲ ነው። ባለታወቀ መንገድ ላይ ሳንሆን ቁልጭ ያለው አብዮታዊ ዴሚክራሲ
ክንንቡን አውልቆ ዳግሚያ ትንሳኤውን ፈስኳል።
… ዛሬ ጠ/ ሚኒስተር አብይ አህመድ ባህርዳር ሄዱ
ይለናል ዋናው ዜና። ከዚህ ዜና ቀደም ብሎ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ያስተላለፉት መልዕክት ነበር። ያ መልዕከት ከጠ/ ሚር አዲሱ ቢሮ
የተሰጠ ቀጭን ትዕዛዝ ነበር። ተከትሎም ዶር ለማ መገርሳ መሰሉን ፈጽዋል። ከዛም ቀጥሎ አቶ አህመደ ሼዴ ያነውኑ ከልሰውታል።
ወ/ሮ ሙፊረያት ካሜል ደግሞ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር
ቁልጭ ቁልጭ እያሉ በሃዘን ተውጠው ታይተዋል። አቤት! ስንት ዓይነት ትውና ነው ያለው ሰሞኑን። አብሶ ድምጽ አልባ ትውና በታሪኩ
በኢትዮጵያ ምድር እንደዚህ ሰሞናት ነግሦ አያውቅም።
Ethiopia: አቶ ገዱ ህዝቡ የመጣውን ለውጥ በእርጋታ እንዲቀበለው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጡ!!
መንግስት የህግ የበላይነትን
የማስከበር ግዴታ
አለበት ለዚህም
ህብረተሰቡ ሊተባበር
ይገባል – አቶ ለማ
መገርሳ
August 17, 2018
https://www.youtube.com/watch?v=dDeOJRoVp24&t=124s
Ethiopia: [ሰበር ዜና] አቶ አህመድ ሽዴ በሶማሌ ክልል አምራሮች ሲሰሩ የከረሙትን ወንጀሎች ይፋ አወጡ
Aug 18, 2018
· የሰንበቱ ድምጽ አልባ ትውና።
ዛሬ የመጀመሪያውን ቀጭን ትእዛዝ መሬት ለማስረገጥ
በአዛዣቸው በህውሃት የበላይነት በሚመረው መፈንቅለ መራህይ መንግሥት ቃላቸውን ይሰጡ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ባህርዳር ተገኝተዋል።
የሚገረመው ክንፍ አውጥተው ይብረሩ ባባህር ይቀዘፉ በሰረገላ ይግቡ የተባለ ነገር የለም።
በስብሰባው ላይ ባህርዳር ላይ አለ የተበለ የብአዴን
አመራር ተገኝቷል። ነባሮቹ ፍንጋዮቹ ግን አልተገኙም። እነሱ አዛዦች ናቸው። አሻናፊም ናቸው። የ አብይ ካቢኔ
አለ ከነፍሱ ነው ጉዳዩ፤ ማላገጫው የድምጽ አልባው ትወናው ጭብጥ።
በዛ ሰሞን ሳጅን በረከት ስምኦን ታዩ ተብሎ መኪናቸው
ጎጃም ላይ ተቃጥሎ ነበር፤ ነገር ግን የሳቸው መኪና አልመሆኑ ማስተባበያ ተስጥቷል።
ብቻ ግን ድፍረቱ በማንነት ቀውስ ውስጥ ጭንቅላታቸው
ለዞረው ሳጅን በረከት ስምዖን ከፍተኛ የጥቃት እርምጃ ነበር። ለአራት ወር ከሥራ ተገለው ቢቆይም የሳጀን በረከት ስምዖን የስለላ
መረብ ግን ሲደራጅ ባጅቶ አጋጣሚውን አገኘ እና ጠቅለል ብሎ ኦህዴድ ወደ ስሜን አሜሪካ መጭ ሲል የሚፈለግውን ነፍስ በአደባባይ
በተፈለገው ሁኔታ ፈጽሞ እዛው ለውጥ ውስጥ ፈንገጥ ብለው የቆዩትን ነፍሶች አስተባብሮ የልቡን ሠርቷል።
በማህል ከኦሮምያ አገራዊ ራዕይ ኢትዮጵያዊ ራዕይ
ይዞ ከች የላው የሳሙና አረፋ እና ቅጽበታዊ ትወናን ተሸክሞ ብአዴን ሲያረግርግ ከራርሞ ነበር፤ ይህም ብቻ ሳይሆን በራሱ በእግሩ
መጥቶ አዲስ አባባ ላይ እጅ የሰጠን የአማራ ዲሞክራሲ ሃይለ ተብዬውን
ወደ ኤርትራ ተመላሽ አድርጎ በድጋሚ በሦስተኛ ወገን ድርድሩ እንደ ገና እንዲካሄድ ተደርጓል። ይህ የላንቁሶን ጨዋታ እናኳን የእኛ
ሊሂቃን ልብ ብለው ሊያስቡት አልተቻላቸውም።
የሆነ ሆኖ አሁን አጀቡ ሽርጉድ ሲጠናቀቅ በሳጅን
በረከት ስምዖን ሥር ባላቸው ኢትዮጵያ የዛሬው የጠ/ ሚሩ ጉዞ በባሀርዳር ተከወነ። በእስር ላይ መሆናቸው እንዳይታወቅ ጉዞው እና
አፈጻጸሙ ያው በእገታ ውስጥ ነው የተከነው። ጠ/ ሚሩ ቁጭ ብለው ድምጽ አልባ በሆነ ሁነታ ባ ኢጅ እንቅስቃሴ ብቻ ታዳሚው ፈገግ
ሲል ሲስተዋል፤ ጋዜጠኛው ሃሳባቸውን እንዲገልጽ ተደርጓል።
ይህ እንግዲህ የሳጅን በረከት ስምዖን የመጀመሪያው
የድል ቀን ነው። አንበርክኮ የሚገዘብት አዲስ ትወና። ያው በጉዞው ላይ እንግዲህ ካቴናም አይቀሬ ይሆናል። አቀባበል ብሎ ነገር
የለም። ሹልክ ብሎ ግበቶ ሹልክ ብሎ መውጣት። ጫናው በማህበራዊ ድህረ ገጽ ከተበራከተ ያው ጮልቁ መባሉ አይቀሬ ነው … አዬ ወያኔ
ሃርነት ትግራይ ወንዱ ያስረግጠዋል ከሊቅ እስከ ደቂቅ …
Ethiopia: ዶ/ር አብይ ዛሬ በባህርዳር...
የበረከት ነፃነት ዕወጃ ቀዳመዊ ሥፍራ ነው።
ዛሬ ሰንበት ላይም መግለጫ ተሰጠ ተብሎ ደግሞ በንባብ
ቀርቧል። በንባብ መቅረቡ ግንቦት 20 ላይም መሰሉ ስለ ተፈጸመ ልዩነት የለውም፤ የግንቦት 20 የተሰጠው መመሪያ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ብጣቂ መንፈስ ያልነበረው እራሳቸው
ዶር አብይ አህመድ የፃፉት ነበር ለዛም ቃናም ስበትም ፍጥረትም ሰውኛም ነፍስኛም ነበር፤
የዛሬው መግለጫ ግን ሳጅን በረከት ስምዖን በሙሉ ሥልጣን የጠ/ ሚር ቢሮ ሃላፊ ስለሆነ ያው የተለመደው የተላመጠ አገዳ
የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መንፈስ ነው ያለው እጅ እጅ የሚል ውሃ ሲሄድበት የከረመ አለት ነው የሚመስለው።
በፍጹም የአብይ መንፈስ የተለመዱ ለዛዎች የለውም፤ የአብይ ቃናዎች ክው ብለው የሳጅን በረከት የድርቆሽ እንኩሮ ምናንቴ መንፈስ
ነው የተደመጠው።
እወጃው በስውር ለሦስተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ነው የተገለጠው።
ወደዚህ እንደሚኬድም ይታወቃል። አሁን ምልክቶቹን ነው እያዬን ያለነው። ነገ ደግሞ ሳንጃ ወድሩ ይቀጥላል፤ በ አብይ ጊዜ የለም
ትካዜ ስንበቱ ነው ዛሬ የታወጀው። ይህም የሚጠበቅ ነው። ሰውዬው ሳጅን በረከት ነው።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ አይመረኝ ላልመራችሁ ነው ያለው።
ያው መሰሉ የ97 ቅልበሳ ድራማ ነው። እንግዲህ በዚህ ውስጥ እነ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ፈተናቸው በስፋት ያንዣበበ መሆኑ ማዬት ይቻላል።
ምርቃን በአግባቡ አለመያዝ ይኸው ነው ትርፉ።
Ethiopia: ከዶ/ር አብይ አህመድ የተሰጠ አስቸኳይ ማሳሰቢያ
ቀዳሚው ተግባር ስለተከወነ ቀጣዩ ደግሞ በመጪው ሰንበት ላይ ያው የተለመደው የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጉዞ ወደ አንዱ
ክልል ይሆናል ማለት ነው።
ነሃሴ ላይ የነበረው የብአዴን ጉባኤ ደግሞ ወደ መስከረም አጋማሽ መዛውሩ ተደምጧል ከወደ ብአዴን አዲስ ሰው ብቅ
ብለው መግለጫው ስጥተዋል። የጠ/ ሚሩ በኮንፈንሱ ላይ እንዲገኙ የተደረገበት ዋንኛው ምክያት በጥቅሻ በድምጽ አልባ ትውና
ሲካሄድ የብአዴኑ አዲስ ሹመኛ ደግሞ በቃል - በልሳን - በትናጋ ጎልቶ ቀርቧል። መቅደም የነበረበት ግን አዳማ ነበር።
የሰው ልጅ ተገድሎ የተንጠለጠለበት። የኦነግ አርማ በማህል አዲስ አባባ እወጃ የታከሄደበት፤ የኦነግ ሠራዊት
ትሪኢት በአደባባይ በሚያሳይበት …
እንዲያውም ከሁሉም በፊት በጠራራ ጸሐይ አብዮት አደባባይ ላይ የንጹሁ ቅዱስ ነፍስ ተገድሎ የተጣለበት፤ ቀባሪ
በግፍ እዛው ተደብድቦ ቀብሩ በእቀባ የተከወነበት፤ ዓለምን ጉድ ያስባለው ዜና እዛው ነበር። አዲስ አበባ ስለምን እንደተፈራ
አይታወቅም።
የሆነ ሆኖ የዛሬው ጉዞ ስለምን የኢሳት ሚስጢር አዋቂዎች እንዴት ሹክ እንዳላሉን ገርሞኛል፤ „ሥራ በዛባቸው“
የተባሉት ጠ/ ሚር አሁን ለቅሶ ለመድረስም ፋታ ስላገኙ።
ያው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የስብሰባ ሂደት ሰንበት ላይ እናድርገው ስላሉ ለማስመሰል ቀጣዩን ሰንበት ደግሞ ወይ
ኢትዮ ሱማሌ ወይ ደግሞ አዳማ ይሆናል ማለት ነው። ሦስቱ ክልሎች ናቸው አክቲብ ሆነው የሚታዩት።
ትግራይ ላይ ግን ወንዝ ወደ ታች
እንጂ ወደ ላይ እንዴት ተብሎ? የራሱ ንጉሥ አቤቶ ወያኔ ሃርነት ነው! አሁን ምርጡ የወያኔ ሃነርነት ትግራይ አካል ብቃቱን እያሳዬ ስለሆነ ኦህዴድ ከፍ ብሎ ሳይሆን ዝቅ ብሎ እንደ ለመደበት
ሰጥ ለበጥ ብሎ የሚሆነው ይሆናል።
ከልጅ ከሚስት እና ከራስ ምረጥ
ሚስጢሩ ይኸው ነው። ለዚህ ነው ፌክ ዜና እዬተባለ አፍዝ አደንዝዝ አዚም እዬተረጨ ያለው።
የሚስጢሩ ዕድምታ በአንተ
አንደበት በእኛ ትእዛዝ ሰጥ ለጥ ብለህ ግዛታችን አስቀጥል ነው በሳጅን
በረከት የቅርብ አማካሪነት መመሪያ ሥር። ይሄው ነው። እንግዲህ መደመሩ ይሄ ከሆነ ለሽ ብሎ መተኛት ነዋ „አብያችን ሰላም ነው፤ ሥራ በዝቶበት ነው“ ይሄው ነው የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ብልሁ ዕድምታው።
- · አንዲህ ወዲህ እንዲያ ወዲያ ... ተስተወዲያ ...
ሌላው ጉዳይ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸውን ቤተሰብ ሄደው እንዳጽናኑንም ይገልጻል
ዘገባው፤ ያው ነው ድምጽ አልባ ትውና። ወይ ዘንድሮ ድምጽ አላባ ትወና በጦቢያ ምድር እንዴት ቀን ወጣለት?
እንግዲህ ከዛ መሄድ ከተቻለ አዲስ አባባ ቤተሰብ አልባ ያሉት የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው ልጆቸስ ያው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በማዕቀቡ በአግታ ላይም ሆነው ቢሆን የተባለ ነገር የለም። መቼም የፈረደባቸው የኢቲቢ ጋዜጠኞች ናቸው። የእውነት ስንት ጊዜ ፈርሰው ይሰሩ? አጀብ ነው።
Ethiopia: ዶ/ር አብይ ባህርዳር አቶ ተስፋዬ መኖሪያ ቤት በመሄድ ቤተሰቦቻቸውን አፅናኑ!!
Published on
Aug 19, 2018 ይሄ ደግሞ ሌላው ትውና
ነው። ልክ ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መሪቀርዮስ እንደ ጠዬቁት መሆኑን ነው … በቃ በለበጣ ነው እያሸረገድን ያለነው እኛም
አብረን ከወያኔ ሃርነት ትግራይ የድምጽ አልባ ታዳሚነታችን ይሄው ነው።
ይህን አገናዝቦ መንገድን ማሰተካከል የአባት በሆነ ነበር
ያለው ግን ግልብጥ እና ዝንጉነት ነው … ድንዝዝ ብለናል፤ ግን ምኑ ተደገመብን? መረጃ መረጃ ይባላል ተዚህ በላይ መረጃ የት አለና?
በዛሬው የጉብኝት ዱብ
እዳ የውስጥ ምንጭ አዋቂው ሚዲያ እና ዕድምታው ደህንነታቸው ሲሰማ በሱማሌ ጉዳይ ባትለው ነው ሲባል እንዴት ዛሬ በብኤደን ኮንፈረንስ
ላይ ይገኛሉ ብሎ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ሹክ አላለነም?
ሌላው ግራሞቴ በዚህ በአብይ
ሌጋሲ 4ወራት ቆይታ ላይ በዙም ጎላ ብለው ያልታዩት አቶ ንጉሱ ጥላሁንም
ዛሬ በቢትልስ ጉብ ብለው ለማዬት ችያለሁኝ። ዶር አንባቸው መኮነን እንዲሁም አቶ ደመቀ መኮነን በገብርዲን ታይተዋል እነሱ እንኳን
ጉልህ ድርሻ ነበራቸው። እንዲያውም ዶር አንባቸው መኮነን ከደብረታቦር ወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ያረጋ ለውጥ ነው ብለው ነበር።
ስለዚህም ግቡና እርዱን ብለው ነበር።
ሁሎችም ግን መንፈሳቸው ነጻ ነው ብዬ ግን እኔ አላምንም። በፍጹም። መንፈሳቸው በራስ የመተማመን አቅማቸው ሁሉ አለ
ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም። በለወጡ ውስጥ ያሉ የቀደሙት ማለትም ከመጋቢት 24 ቀን 2010 በፊት የነበሩት የኦህዴድ እና የብአዴን
ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራው ጥንካሬ አብረው አንድ ላይ ቢቀመጡ ወጥ አቋም ይኖራቸዋል የሚልም ዕድምታ የለኝም። ያ ማስትሽ ላልቷል።
ብዙ ድራማዎች በውስጡ ተኮፍሰዋል። ይህን ስል ግን ድፈረት እና ነፃነት በ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ነፍስ የት ላይ እንዳለች ውል የለኝም።
የእሳቸው ልባቸውን ማወቅ ይከብዳል።
የእጩ ጠ/ ሚር አቶ ጃዋር
አህመድ „ኢህአዴግ በምርጫ አሸንፋለሁ“ ብሎ አያስብ ተረብ ሆኖ ስለመቀረቱ ከሂደቱ መገመት ይቻላል።
ተረብ ነው ያልኩት አሁን
ሙሉ ለሙሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው አገር ምድሩን እዬመራ ያለው። ይህም ማለት ቀጣዩም
ምርጫ ጠብንጃ እና ሳንጃ ይሆናል ማለት ነው።
እርግጥ ነው በነፃነት
የአብይ መንፈሱ እንደ አሳ እንዲ- ቀዝፍ ቢለቀቀ እንዲያውም በአደባባይ ኢህአዴግ ተወዳደሮ የማሸነፍ ዕጣው በጉልበት ሳይሆን ባብላጫ
ድምጽ በቀጥተኛ ምርጫ ይሆን ነበር። ዓለምም ጉድ ይል ነበር። ግን ሁሉም ትእግስት አልቦሽ ሆነ።
አንጃውም በለውጡ ውስጥ
የነበረው፤ ወያኔ ሃርነትም ሁሎችም ትእግስት ነሳቸው እንጂ መኢሶንን ያህል ተመክሮ ዘለቅ የፖለቲካ ድርጅት፤ አቶ አበራ የማነ አብን
የመሰለ የሰከኑ ፖለቲከኛ፤ ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያን የመሰለ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች ምርጫችን አብይን ነው ብለው ነበር።
ይህም ማለት እንመርጣለን
ሲሉ ኢህአዴግ እንዲቀጥል እንፈቅዳለን ግን የምርጫ ህጉ ዴሚክራሲ ከሆነ ነበር ያሉት። ያ ሎተሪ ነበር። የሰማይ ታምር
ነበር። በስሜን አሜሪካ ሆነ በኢትዮጵያ የታዩ የህዝብ ድጋፍም ትዕይንቶችም ሰፊ የሆኑ የመንፈስ ሃብቶች ነበሩ።
ህዝብ ራሱ ቆሞ ዘብ ሆኖ
ያስፈጽመው ነበር፤ ግን ሁሉም ቸኮሉ። አብሶ ኦህዴድ እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅል ነሳቸው፤ የወሰዱት እርምጃ ሁሉ የህጻናት
ጨዋታ ነበር።
አሁን ባለው የግልበጣ
የኩዴታ መንፈስ ግን ያ በቀጣዩ ምርጫ በኩዴታ በተለመደው ጉልበታዊ ሁኔታ ይከወናል ማለት ነው።
አብይን አንደበቱን ዘግቶ
አንዲትም ቀንጣ ነፍስ ኢህዴግን አይመርጥም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስን መርዝ ቀስ እያለ እያወጣ የነበረው አብያዊ መንፈስ
እገታ ሆነ የግድያ ሙከራ ለራሱም ለወያኔ
ሃርነት ትግራይ መጪ ዘመን መከራ ውስጥ ነው የሚጨምረው፤ ኢትዮጵያም በባሳ ሁኔታ ከሚጠፉት አገሮች ተርታነቷ ይዘልቃታል።
በዚህ አያያዝ ተፎካካሪዎች
ያ ቅን መንፈስ አለልን ብለው ባያስቡ መልካም ነው ህልም እልም ሆኗል። አሁን ያለው ነገር ሁሉ ዴኮሬሽን ነው። ቅብ ነው። ለነገሩ ተፎካካሪ የሚባሉት እኮ ራሳቸው ሲያጣጥሉት ነበር የከረሙት የአብይን ሌጋሲ …
ቅልብ ሆነው ያሉት ከውጪ
የገቡት ደግሞ ሌላው የተውኔት አድማስ ናቸው ልክ እንደ ኤርትራው የ አቶ ሞላ ስገዶም ታጠቂ ሃይል … ሆድ እና ምርጫ?
እርግጥ ነው ሁኔታውን
ወደ ነበረበት ለማስመለስ አቅሙ ያለው ዴያስፖራው ነበር፤ ግን ማዘናጋያዎቹ አሁንም ለወያኔ ሃርነት አብዮታዊ ዴሚክራሲ፤ ለሄሮድስ
መለስ ዜናው ሌጋሲ ቅጥልጥል መከራ አጃቢ ሆነው እዬታዬ ነው … ጤነኛ ልብ ጠፋ። ኡኡኡ ጤነኛ ልባም ልብ ሆይ! የት ይሆን የምትሸመተው?
ነፃነት ለአብይ እና ለቤተሰቡ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ