የምዕት ፈርጧን አርቲስት ኢፋ /ኢቢታ/ ፔሩን "በተባረከች አገር ለተባረከ ትወልድ" ተስፋ ውስጥ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።
ለውጡ እንደ ዝናሽ ንዑድ መንፈስ
የእኩልነት ማህደር ቢሆንልን።
„እግዚአብሄር ለሰው ልጆች ይደክሙበት
 ዘንድ የሰጣቸውን ጥረት አይቻለሁ።“
መጽሐፈ መክብብ ፫ ቁጥር ፲
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18.02.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።





ጥሞና መልካምነቱ ብዙ ነገርን ከውስጥ ለማዬት ይረዳል። ሳተናው ድህረ ገጽ ስገባ የማነባቸው፤ ዩቱብ ስከፍት የማደምጣቸው ነገሮች መከፋቴን አሳየሉበት። ስለምን ብትሉኝ በ2008 ላይ የነበረው ድቅድቅ ጨለማ እና „ሰከን በል“ የአርቲስት ይሁኔ በላይ የህሊና ተቋም እኔን ያልተለመዱ እርምጃዎች ያስወሰዱኝ የጭንቅ ወቅት ነበሩና።

እነዛ ያልተለመዱ እርምጃዎቼ ጥቋቁር ሰለነበሩ ያን መልክ ለማሳያዝ ደግሞ የግድ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ እጩ ጠ/ሚር ሲመጡ ማቃናት ነበረብኝ። እናም በድፍረት ያን ቁስለቴን የሚሸር ቀን ፊት ለፊት ዋዜማ ላይ ነው ብዬ የቀደመውን የጭንቀት መንፈስ የሚረገብ ጹሑፍ ጻፍኩኝ እና ለኩኝ። ኢህአዴግ ውስጥ የነበረው የለወጥ አዬር በጤናዳምነት በቅንነት ነው የተመለከትኩትና።

ያተስፋዬ በ ኢህዴግ ውስጥ ከተሳካ ያን የመሰለ ምሬት ከእንግዲህ ለመላክ አላማሰቤን ስስበው እራሱ ጤናዬን መለሰለኝ። የዛሬውም የቀድሞዎችም ኢህአዴግ ላይ የነበረው ጠባሳ መሻሪያው የተስፋ ዘመን መጣ በሚል በትልቁ ሰፋ አድርጌ መንፈሴን እርጋ አልኩት። በዛ የውስጥ ቁስለት ውስጥ የታደሙ መንፈሶች እንደ እኔው ተስፋ ያደርጉ ዘንድ ደግሜ መማጸን ስለነበረብኝ ነው የማቃኛ ሌላ ደብዳቤ የጻፍኩት ለሚያደምጡኝ።

አሁን የምሰማው የማዬው የማዳምጠው ደግሞ ለዬት እያለብኝ ነው። ዛሬ ጥዋት ከቀደመት አንጋፋ ጋዜጠኞች ውስጥ አቶ ኆኀተብርሃን ጌጡ /ቄሱ/ የጻፈውን አነበብኩኩት። ቅኔ ስላለከለበት ባለቅኔ ደምነት ትውፊቱ ነውና በግልጽ ቋንቋ ስለጻፈው ከልቤ ሆኜ አዳመጥኩት ሳይከብደኝ።

ለዉጡተስፋዎቹና ተግዳሮቶቹ (ኆኀተብርሃን ጌጡ)

በመሃከል ደግሞ ህብር ራዲዮም በዚኸው የስጋት ዙሪያ ያለውን ዕድምታ በጣምራ ቀርቦ አዳመጥኩኝ። „የድምፃችን ይሰማ እና የአዲስ አባባ ጉዳይ“

ከሰዓት ሳተናው ላይ በድጋሚ ስገባ ሌላ የስጋት ጹሑፍ ደግሞ ከጸሐፊ አቶ ምህረቱ ዘገዬ ተጽፏል። የቄሱ አውሮፓ ሆኖ ነው። ህብር አሜሪካ ሆኖ ነው። አቶ ምህረቱ ዘገዬ ግን ከመዲናዋ ሆነው ነው። አሁን ሦስቱንም በጣምራ ሳስባቸው የ2008 የ የአማራ ታገድሎና መስዋዕትነቱ የቅዳሜ ገብያ ቃጠሎን ጨምሮ፤ የሪቻ ጭፍጫፋ እና ሰቆቃ መጥቶ ድቅን አለበኝ። ለራሴ በራሴ አወራሁኝ። ምን ዋስትና አለን ብዬ።

በለማ መንፈስ እንደ እኔ ቆርጦ የገባ የለም። ለማሟያነት፤ አማራጭ በመጥፋቱ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ የመሆን ቁርጠኝነቱ ቢኖር ዘመን ተሻጋሪ አፋ ሞልቶ የሚያናግር እዮራዊ ስጦታ ነበር። አሁን እንዲህ ጠቃጠቆ የሆኑ እክሎች ሲገጥሙ ሳይ ከሚሰጉት ወገኖች ቤተኛ ለመሆን መገደዴ አይቀሬ ነው።

በሀምሌ 18 ለሀምሌ 19 አጥቢያ ወንበሩ ባዶ ሆኖ አዬሁት ብዬ ነበር። እስከ አሁንም ከወንበሩ ሰው ተቀምጦ መልሶ አላሳዬኝም። እንዲያውም ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍር ከሁለት የተሰነጠቀ ሰብዕና በሌላ ጎንም አይቼ ነበር። 

የወንበሩ ባዶነት ሲገርመኝ የተሰነጠቀው ትርትር ፊት ደግሞ አሁንም ሳስበው ፍች አላገኘሁለትም። ከሰሞናቱ የተፎካካሪ/ ተቃዋሚ እና ተቀናቃኝ ፓርቲዎች የመድክ ትዕይነት ደግሞ አብረው በ አካል አዬሁኝ። ብቻ ህልሜ እና ነገ መሳ ለመሳ ተፋጠው እንዳሉ አስባለሁኝ። ሸርተት ቢል … ተተኪነቱ ወደዜት ሊያደላ እንደሚችል …

ወደ ቀደመው ነገር ስመለስ የደልዳላዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው አያያዝ ግን የልቤ ሆኗል። የቀዳማዊ እምቤት ጽ/ቤት የእኩልነት ማህደርነት ኢትዮጵያዊነትን ያዘክርልኛል። ሁሉንም ተባደግ በሌለበት አኳሆን፤ ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ የእናትነት ተግባራቸውን እዬፈጸሙ ነው። እራሱ ትግራይ ሁለት ጊዜ ነው የሄዱት። ያ በእጅጉ አስደስቶኛል። ኢትዮጵያዊነት በዚህ ውስጥ ነውና የሚነጥረው።

ሃሳቡን አለመደገፍ፤ መቃወም፤ መሞገት፤ መተቸት መልካም ነው። በዛ በሚሞገተው፤ በሚተቸው፤ በማይደገፈው ሃሳብ ውስጥ ያለው ሰብዕና ውስጥ ግን ቂም መቋጠር የተገባ አይደለም። አብሶ አድሎ የተገባ አይደለም። 

እኔ ዬትኛውም ድርጅት ይሁን ግለሰብ ሃሳቡን ተቃውሜ ከፃፍኩት በሆዋላ ትዝ አይለኝም ያ ሰው ሆነ ድርጅት። በክፋት ይሁን በሌላም አሉታዊ ነገር። ቀጣይ አጀንዳዬ አይሆንም። ቂም ስቆፍር፤ ቋሳ ሳቦካ እና ስጋግር አልባጅም። የማይድን ከሆነ ባልዳነው ጉዳዩ ላይ ደጋግሜ ብንሸራሸረም ለሰከንድ ግን ከቂም ጋር ንክኪ በሌለበት ሁኔታ ነው። ለነገሩ የሚወቀሰው የሚነቀሰው የተቀረበው የእኔ ያሉትን ብቻ ነው። ካላቀረቡት፤ ካላስጠጉት ባዕድ ገላ ነውና አይወቀስም አይነቀሰም።

የሆነ ሆኖ እኔ የደልዳላዋ የቀዳማዊት እምቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው „ለተባረከች አገር፤ የተባረከ ትውልድ“ ውጥን፤ ሂደት፤ ክንውን ተስፋ ሰጪ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ተስፋነቱ ለዜግነት ፍትሃዊነት ማጫ ከመሆኑ ላይ ነው።

አንድ ዩቱብ ላይ ሳዳምጥ እራሱ ህፃን ሚሊዮንን ሲረከቡ የትዳር አጋራቸውን ጠ/ሚር አብይ አህመድን አላመከሩም ነበር አሉ የሴቶች፤ የህጻናት ምኒስተሯ ወ/ሮ አለም ጸጋዬ እንደነገሩን ከሆነ። እንዲያውም ሚነስተሯ ሲገልጹ በቤታቸው ሰላም ስለመሆኑ  በትዝብታቸው ውስጥ በቅኔ አረጋግጠውልናል።

ይህን እኔም በህይወቴ ገጥሞኝ አይቸዋለሁኝ። ሚ/ሯ የተናገሩት ትክክል ነው እንደማለት። አንድ ወቅት እጅግ ፈተኝ ሁኔታ ላይ ነበርኩኝ። መቼም ፈተና እኔ የሰለጠንኩበት ነውና።  በአንድ ወቅት ለአንዲት የሃይማኖት ማተቤ እህቴ ደውዬ ያለሁበትን ሁኔታ ነገርኳት። "አሁኑኑ ጊዜ ሳታጠፊ ነይ" አለችኝ። ደግሞ አሞኛል አልኳት። "ነይ አልኩሽ ነይ" አለችኝ። ባለቤቷን አላማከረችም። እዛው እኔ አዬር ላይ እንዳለሁ ነው የወሰነችው። 

እኔ ሰው ቤት መሄድ ጭንቄ ነው። አይደለም ሰው ቤት ራሱ ወደ ደጅ መውጣት የግድ ሆኖ ነው። ቤቴ ነው ቤተመቅደሴ። ያን ጊዜ ግን ሰተት ብዬ ሄድኩኝ። ሁለት ወር አብርያቸው ተቀመጥኩኝ። ከባድ ጊዜ ነበር ታምሜ ስለነበር። እነሱ ግን በፍቅር እና በደስታ አሰተናገዱኝ። ባለቤቷ ሲመጣ ፊቱን ብቻ ነበር የተመለከትኩት። ባልተለመደ ሰዓት ባላተለመደ ሁኔታ ለዛውም እኔን ነበር ያገኜኝ። ተለምኜ ተፈልጌ እኮ አልሄድም። ይህን አገር ያውቀዋል። ወደ እኔ ሰው እንዲመጣ ነው እኔ የምሻው ... 

አብሶ ባለቤቷ ሲመጣ ፊቱን ለማዬት ጎጉቼ ነበር። አልነገረቸውም ነበረ። ግን ተዝቆ የማያልቅ ፍቅር ነበር የቀለበኝ። ያ የጋህዱ ዓለም ሊቀ ሊቃውንት ሳይንቲስት፤ ያ የመንፈሳዊው ዓለም ሊቀ ሊቃውንት ካህን ለእኔ ተጎንብሶ አልጋዬን ያነጥፍ ነበር። ምግብ ላይ እንብዛም ስለሆንኩኝ እኔን ሳያበላ ወደ ትምህርት አይሄድም ነበር። ያን ጊዜ የመጨረሻ ድግሪውን ይሰራም ነበር።

አሁን እሷ በአብይ የለውጥ መንፈስ ውስጥ ሆና በአንድ ስብሰባ ላይ አይቻታለሁኝ። ፍጹም ደግነቱ፤ ፍጹም ሰላሙን የቤታቸውን መግለጽ አልችለውም። በመጻህፍቴ ሁሉ በናሙናነት አንስቸዋለሁኝ። ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ልጃቸውን ሲረከቡም ያደረጉት ልክ እንደዛች ቅድስት ሴት ነበር። 

ደልዳለዋ ቀዳሚወት እመቤት ባለቤታቸውን ሳያማክሩ ልጅን ያህል ነገር ሲረከቡ ያን እንዲያደርጉ ያደረጋቸው የቤታቸው የሰላም እርግጠኝነት ነበር ክብርት ወ/ሮ ያለም ጸጋዬ እንዳሉት። እኔም ደርሶኝ መዝኘዋለሁ ... ሰላም ባለበት ሁሉ በመሆን ውስጥ አህታዊነት ቆምሶ ይገኛል። ለነገሩ አናውቅበት ብለን እንጅ አንድዬ እኮ የውስጡን ሰላም ነው ትቶልን የሄደው።፡

እንዲያውን እኔ አሁን አሁን ሳያቸው ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸውን የድሆችን እናት ኢቢታ ፔሩን / ኢፋ ፔሩን ወይንም ህይዋን በእኛ ትርጉሙ/ ይመስሉኛል። ስለ ኢቢታ ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁኝ። የ አንድ አገርን መላ ህዝብ ወይንም ማህበረሰብን በመልካምነት የለወጠች  የዓለማችን ብሩህ ድንቅ አርጀንቲናዊት ናት። ኢቢታ ፔሮን የመሆን ሳይንቲስት ነበረች፤ ሞት ቀደማት እንጂ። 

የኢትዮጵያ አዬር መንገድ የ2010 የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ሲያከብር ወደ አርንጀቲና ማቅናቱ የተገባ ነበር። የትም ቦታ የለም በማህበረሰብ ደረጃ የሴቶች የመብቃት ዕውቅና አርንጂቲና ላይ ያለውን ያህል --- ከሌላው ከሰለጠነው ዓለም ጋር ሲነፃጸር።

ኢትዮጵያዊነት የሚሰርጸው ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በያዙት መንገድ ብቻ ነው። በቂም፤ ከቁርሾ፤ ከሸር፤ ከሀሜት፤ ከአሉባልታ በፀዳ የእውነት ጉዞ ብቻ። በሌላ በኩልም ጊዜ አገኘሁ ተብሎ ከሚመጣ ማጋደል በዳነ መልኩ። ሚዛን ባልተጠበቀ ቁጥር ኢትዮጵያዊነት ይጎሳቆላል። የትናንቱ አልበቃ ብሎ ዛሬም እንደሚሰማው ከሆነ ያው ተመልሶ ጨለማ ነው። 

በነገራችን ላይ ኢቢታ ለእጩ አገር መሪነት ተወዳዳሪ ሆነ መውጣት ስትጀምር ነው በካንሰር በሸታ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዬችው። ባለቤቷም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ነበሩ። በዛ ዕድል ተጠቅማ ከታች ተነስታ ዓለምን ድንቅ ያሰኘ የድሆች እናትነቷን በፈርጥነት ያሰመሰከረችበት መድረክ የመጣው ከእውነት ህዝቧን በእኩልነት ስለምታፈቀር ብቻ ነበር። ይህን ፈተና ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ በውን በማስተዋል ሆነው ሊታደሙበት ይገባል። አገር መውደድ ማለት በራስ ላይ መወሰን ማለት ነውና።  

ኢፋ ፔሩን ተዋናይ፤ የራዲዮ ጋዜጠኛ፤ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች፤ ሙዚቀኛ፤ ፖለቲከኛ ነበረች። የኢፋ ፎቷዋ ቤቴ ውስጥ አለ። በድንገት አንዲት የህግ ባለሙያ አርንጅንቲናዊ ቤቴ ስትመጣ ፎቷውን ስታገኝ ደነገጠች። የእውነት ነው የደነገጠቸው። ፎቶው እንዳይመስለሽ ኢቢታ በውስጤም ነው ያለችው አልኳት።

ስኬት በስኬት ለማሳካት የተፈጠረ ነፍስ ነበራት ኢቢታ፤ እንዴት እንደተነሳች፤ በምን ህይወት እንዳደገች፤ ምን እንደገጠማት ታሪኳን ማነበብ ይቻላል። ጀርመኖች እንግሊዞች እንደ ታቦት ነው የሚያዮዋት። ለእኔም ታቦቴ ናት።

ዛሬ በወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እማዬው ነገር ያን ይመስልብኛል። በዚህም በዚያም ብሎ እኔ ባይሳካልኝም ግን መልካም ነፍሶች እኔ በሳብኩበት ጎዳና ሲጓዙልኝ ሐሴቴ የሰፋ ነው።
በክብርት ብርቱካን ሜዲቃስ ፈጣሪ እና እኔ የምናውቀው መስዋዕትነት ተገብሬበታለሁኝ። በቅኔው ልዑል በብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህንም መሰሉን የመከራ ግማድ ተሸክምቤታለሁኝ። ዛሬ ብርቴም ጥሩ ቦታ ላይ ናት። ትናንት ቀን ላይ ጎልጉል ድህረ ገጽ ላይ እንዳነበብኩትም የታቦቴ የብላቴው የምርምር ማዕከል በአንቦ ዩንቨርስቲ አጀንዳ ስለመሆነ አነበብኩኝ። እናም ሐሴት አደረግኩኝ።

በአብይ ኬኛ ጹሑፌ አረጋዊው ስለሚራዳው ቅዱስ ስለ ሜቅዶንያ ተራድኦ ድርጅት መጸሐፌን ለመስጠት ዝግጁ መሆኔን ጽፌ ነበር። ዛሬ ቀዳማዊት እመቤት ቤተኛ ናቸው። በእኔ እጅ ባይሆንም በሌላ ቅዱስ መንፈስ ፍላጎቴ እዬተሳካ ነው። ስለዚህም በአንዱ ጥንዝል ቢልም፤ በሌላው ጥውልግ ቢልም „ላይከስ አይበድል“ እንደሚሉት ጎንደሬዎቹ  በደልዳላው እምቤት ተግባር መጽናናትን አግኝቻለሁኝ። 

ሁሉንም በ እኩል ዓይን ማዬት። ለሁሉም እኩል ፍቅር መስጠት። ለሁሉም እኩል አትኩሮት መለገስ። መጨረሻውን ያሳምርላቸው እንጂ እኔ ከጠበቅኩት በላይ መንፈሴ እዬተጽናና በሌላው የማዝንበትን ሚዛኑን እያስጠበቀልኝ ነው። በመሪነት ውስጥ ተባደግ ጉዞ ያማል ... አብሶ ተስፋ ያደረጉት በተስፋው ውስጥ መሆን ከተሳነው ወደ ተለመደው የዕንባ ዘመን ምልሰት ይሆናል። 

ክብርት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ከሰሞናቱ በደቡብ ክልል፤ በጋንቤላና በቤንሻንጉል፤ ዛሬ በጅጅጋ የሚያድርጉት መልካምነት ይህ በወጀብ የሚናጠውን የተባደግ ጉዞ ይገራዋል የሚል ሙሉ እምነት አለኝ።

እማሳርገው በአንድ ብልህ የማስተዋል ስንኝ ይሆናል። የራሴንም አክዬ …
በነዶ/ አቢይ የገባው መንፈስ የሌላ ሣይሆን የእግዚአብሔር ይሁንልን፡፡ ይሉናል ጸሐፊ አቶ ምህረቱ ዘገዬ።ሁሉን እዩ፣ የሚበጀውንም ያዙ ባሉት“ በዛሬው ጹሑፋቸው። ለጥቆ ለማንበብ ሊንኩ ይኸው ነው …


እኔ ደግሞ በዝናሽ ያለው ንዑድ የእኩልነት ማህደረ - መንፈስ ለለውጡ ያድርግልን ነው የምለው። እንደ ቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤትም የጠ/ሚር አብይ ጽ/ቤት ወጣገባውን ዕይታ ገርቶ „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ“ ነው የግድግዳ ማሳመሪያ ሆኖ እንዳይቀር ይታጋ ነው እማልመው። 

ገና ከዛሬው ይሕ ከሆነ ነገማ ምን ሊሆን እንደሚችል አንድዬ ይወቀው። ህዝብ እዬተሸበረ ነው። በተስፋው ልክ "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን" ማግኘት ይሻል። በፈለገው የፈተና ውስጥ ማለፍ የሚቻለውም ያሉት ሆነው መገኘት ሲቻል ብቻ ነው … 

በተረፈ የቀዳማዊት እምቤት ጽ/ቤት ለሚያደርገው ትጋት እና እና ትትርና ያለኝን ጽኑ አክብሮት ስገልጽ ቢስ አይይብን በማለት። በተጨማሪ በፓን አፈሪካኒዝም በቀዳሚውት እመቤቶች ጉባኤ ላይም የፍቅራዊነት የተስፋ መንገድም ሽልማቴ ነው። ስለሆነም አቅሜ ጸሎት ነውና የአቅሜን በጸሎት እረዳለሁኝ።

ሴቶች ጥበበቦች ናቸው!
ሴቶች የተግባር እምቤቶች ናቸው!

የኔዎቹ ማለፊያ ጊዜ ይሁንላችሁ። ኑሩልኝ። 








አስተያየቶች

አስተያየት ይለጥፉ

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።